Get Mystery Box with random crypto!

#በዓለ_ጰራቅሊጦስ ከዕርገተ ክርስቶስ በኋላ ደቀመዛሙርቱ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰብስበው | ዝክረ ብሒለ አበው

#በዓለ_ጰራቅሊጦስ
ከዕርገተ ክርስቶስ በኋላ
ደቀመዛሙርቱ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰብስበው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ በዓለ ሃምሳ
የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዐውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፡፡
ተቀምጠው የነበሩበትን ቤት ሞላው እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡
በሁሉም መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው ፡፡መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር፡፡
በዓሉን ለማክበር የተሰበሰቡ አይሁድ ተደነቁ፡፡ በየቋንቋቸው ሲናገሩ ሰሙ፡፡ “እነዚህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? የገዛ
ቋንቋችንን እንዴት ሊያውቁና ሊናገሩ ቻሉ?” በማለት ተጠያየቁ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ያስገኘውን ጥቅም፤
የእግዚአብሔር መንፈስ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ማደሩን፤ የትንሣኤውን ወንጌል፤ የማዳኑን ዜና፤ የምሥራቹን ድምፅ ሰበከላቸው፡፡
እነርሱም “ምን እናድርግ?” በማለት ከልባቸው ተመለሱ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም “ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ
እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ” አላቸው፡፡
ሦስት ሺሕ ሰዎች በአንድ ስብከት ተመለሱ ተጠመቁም፡፡ ያም ዕለት የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ይባላል፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት አጽናኝ፤ በመንገድ ደጋፊ፤ ረዳት ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ለማጽናናት ወደ ዓለም ስለመጣ
ጰራቅሊጦስ ተብሏል፡፡ የአገልጋዮች ሩጫ፣ የምእመናን ጉዞ የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አፈጻጸም ያለ መንፈስ ቅዱስ አይከናወንም፡፡
መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው መንፈስ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያን መሪ እና የመምህራን መምህር ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሰጪና ምስጢር ገላጭ ነው፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት አጽናኝ (ረዳት) ማለት ነው፡፡ እርሱም መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስ
አማኞችን ለማጽናናት ወደ ዓለም መጣ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያንን የልደት በዓል በእሳት ላንቃና በዓለም ቋንቋ አከበረ፡፡
መንፈስ ቅዱስ የሊቃውንት ምስጢር ገላጭ የፍጥረታት ሕይወት ሰጭ ነው፡፡