Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የሰርጥ አድራሻ: @zephilosophy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.78K
የሰርጥ መግለጫ

"Strong minds discuss ideas, average minds discuss events, weak minds discuss people."
Rinu Ruzvelt

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-03 22:43:38 ክቡር ሰው - ካንት

ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም

ከጓደኞችህ ጋር እራት እየበላህ፣ አንዱ ተስተናጋጅ ከመጠን በላይ እያጨበጨበ አስተናባሪውን ይጣራል “እዚህ ጋር አንድ ምግብ፡፡” አንዳንድ ሰውም በሰላም ላደረሰው ሾፌር “እንዴት ነህ፣ ቻው ወይም አመሰግናለሁ” ሳይል ከታክሲ ወርዶ ወደ ጉዳዩ ያቀናል፡፡ ወንጀለኞች ህጻናትን ሰርቀው እንደ እቃ ይሸጣሉ፡፡ መንግስትም አገሩን ከዳ ብሎ ያስበውን ግለሰብ ያስገድላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች በጋራ የያዙት ነገር ምን አለ?

ኢማኑኤል ካንት አስተናጋጁን የሚያመናጭቀው ጓደኛህም፣ ለሾፌሩ ግድ የሌለው ተሳፋሪም፣ ልጆች የሚጠልፉ ወንጀለኞችም፣ አስገዳዩ መንግስትም... ሁሉም የሰውን ልጅ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ አስተናግደዋል ይለናል።

ካንት በምክንያታዊነት ላይ ባለው የጸና አቋም በእጅጉ ይታወቃል። ለእርሱ ምክንያታዊነት ከሁሉ የላቀ ንብረታችን እንደሆነ ነው የሚነግረን። ከዚህም በላይ ምክንያታዊነት ምን ልክ ምን ስህተት ምን ኃጢአት ምን ጽድቅ እንደሆነ ይለይልናል፡፡

ካንት የሞራል ህግጋት አይለወጤ እና የጸኑ ናቸው ብሎ ያስባል። የሚደረስባቸውም በምክንያት እና ምክንያታዊነት ብቻ ነው። ይህንንም ምክንያታዊ ግብረገብነትንም ለማስረዳት ካንት ባለ ብዙ ገፅ መጽሐፎችን አሳትሟል።

ካንት ሁሉም ሰው ሊነካ የማይገባው
ክብር አለው ይለናል። እናም የሁላችንም ድርጊቶች ይህን ክብር የጠበቁ ሊሆኑ ይገባል። በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም የሰውን ክብር መንካት የለብንም፡፡ ሰዎች የምንገለገልባቸው ቁሳዊ መሳሪያዎች አይደሉም፡፡ ሁሉም የራሳቸው ዋጋ አላቸው። ለሁሉም ሰው ግድ ሊኖረን ይገባል።

ሁላችንም እንደ ግለሰብ ዋጋ እንዳለን እናስባለን፡፡ ዓለም የግለሰቦች ጥርቅም ናትና ለራሳችን የምንሰጠውን ዋጋ ለሁሉም ሰው መስጠት የተገባ ነው፡፡ እኛ ምንም አይነት ጥያቄ እና ምክንያት ሳንደረድር፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለራሳችን ከፍ ያለ ዋጋን ከሰጠን፣ እንደ ማህበርም ለሌሎች ሰዎች ዋጋ ሊኖረን ይገባል።

አዎ በማህበረሰብ ውስጥ አንደኛው ተገልጋይ፣ ሌላኛው አገልጋይ ሊሆን የተገባ ነው፤ ሆኖም በዚህ ሂደት ውስጥ ሰዎችን እንደ ሰውነታቸው ልናከብራቸው የተገባ ነው፡፡ አስተናጋጁም፣ የታክሲ ሹፌሩም ሆነ ሀገር ከዳተኛው ሰው ናቸው። ሁሉም ለራሳቸው ዋጋን ይሰጣሉ፡፡ ካንት ከእርሱ በኑሮ ደረጃ ዝቅ ያሉትን አገልጋዮቹን በታላቅ ክብር ይመለከታቸው ነበር፡፡

በቀጣይም ሰውን እንዴት ማዋራት እንዳለብህ ስታስብ ይህን “እንደ ሰው እያከበርኳቸው ነው ወይንስ እንደ መሳሪያ እየተጠቀምኩባቸው?” ይህም ቀላል እና ሊተገበር የሚገባው ግብረገባዊ ህግ ነው፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy
23.8K views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-17 20:44:51 ማራኪ የዜን ትረካዎች
በግሩም ተበጀ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
12.8K viewsedited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 22:24:28 መሳጭ የኦሾ ትረካዎች
በግሩም ተበጀ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
16.0K viewsedited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-02 09:59:28 አድዋ፦ ሶስተኛው ፍልስፍናዊ  አብዮት !!!!!
**

<<
አድዋ ሶስተኛውን ፍልስፍናዊ አብዮት ትወክላለች፡፡ በጥቂቱ ርእሰነገሩን ለማስረዳት ያህል፣ በአለም ላይ ሶስት ፍልስፍናዊ አብዮቶች አሉ፡፡ ስለመልካም ግብ ግህደት (እውንነት) የነበረውን ሁሉ እንዳልነበረ ያደረጉ፣ በእግሩ የቆመውን በሙሉ በጭንቅላቱ የተከሉ፣ የውስጡን ወደውጪ የገለበጡ፣ተደብቆ የነበረውን ሁለንተና ሀቅ ነጻ ያወጡ እሳቤያዊ አብዮቶች ናቸው፡፡
‹‹የመጀመሪያው አብዮት ኮፐርኒከን ሬቮሉሽን፣ ሁለተኛው አብዮት ካንሺየን ሬቮሉሽን እና ሶስተኛው አብዮት ምኒሊከን ሬቮሉሽን በመባል ይታወቃሉ፡፡

"ኮፐርኒከስ በቶለሚ ተነጽሮ የነበረውንና ምድርን ማእከሉ (ጂኦሴንትሪክ ቪው) ያደረገውን ፍልስፍና ዘ ሳይንስ ወስነፈለክ ከውስጥ ወደውጪ በመገልበጥ ጸሀያዊው ስርአት (ሶላር ሲስተም) በምድር ዙሪያ የሚሽከረከር ሳይሆን ምድር ራሷ ናት በጸሀይ ዙሪያ የምትሽከረከረው፤ በማለት አዲስና ፋና ወጊ የሂልዮሴንትሪክ (ጸሀይን ያማከለ) አብዮትን በስነ ፈለክ አወጀ፡፡

‹‹ካንት በበኩሉ በስነእወቀት የፍልስፍና መስክ አዲስ አብዮትን ነፍስ ዘራበት፡፡ ነገሩ፣ ቀለል ባለ አገላለጽ እንዲህ ነው፡፡ በህሊናችን ውስጥ ያለውን ይዘት ልምድ አይወስነውም፡፡ ይልቅዬ ልምድን እራሱን የሚወስነው ህሊናችን ነው፡፡ እናም የምንዳስሰው አለም በራሱ ሆኖ የሚገኝ ሳይሆን የአእምሮአችን የተለያዩ ፈርጆች በወቀሩት፣ በሰሩት፣ ባበጃጁት፣ ፈር ባስያዙት፣ ልክ ባገቡት እና በጫኑበት ቅርጽና በለገሱት ስርአት መሰረት የሆነ ነው፡፡ እናም እውነታ ለእኛ ህሊናችን አቡክቶ በጋገረው መሰረት የሚታየው፣ የሚለበበው እና የሚቀርበው ሲሆን፣ እውነታ በራሱ ግን ምን እንደሆነ አይታወቅም፤ በማለት አዲስ የእሳቦት ፈር በስነ እውቀት ቀደደ፡፡

‹‹ሶስተኛው አብዮት በፖለቲካዊ ፍለስፍና ዘርፍ በምኒሊክ መሪነት አድዋ ላይ እውን የሆነው አብዮት ነው፡፡ እስከአድዋ ድል ድረስ ከኢትዮጵያ በስተቀር አለም በሙሉ በነጮች ገዢነት፣ በነጮች ፍጹም የበላይነት፣ በነጮች ወሮ ድልአድራጊነት፣ በነጮች ሉላዊ መሪነት፣ በነጮች ብቸኛ ተሰሚነት፣ ፍጹማዊ ፈላጭ ቆራጭነት ስር ስትፍገመገም ኖረች፡፡ ከአድዋ ድል በሁዋላ ግን ይህ ታሪክ በጭንቅላቱ ተተከለ፣ ከፍጹምነት አምድ ወደአንጻራዊነት ወታቦ ተሸኳለለ፤ ከአለማቀፋዊ ገዢ እውነታነት ወደወራዳ ፖለቲካዊ ድስትፊያነት ተንደባለለ፡፡

" ይህ የነጮችን የበላይነት በፍትህ የበላይነት፣ የዘርና የቀለም ልዩነትን መራሄነት በሰው ልጆች ሁሉ ልእልና ገዢ አስተምህሮነት፣ የጥቁሮችን መናቅና ውርደት በሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት የተካ ሁለንተናዊ ፖለቲካዊ አብዮት ምንሊክ ሬቮሉሽን ወይም ሶስተኛው ፍልስፍናዊ አብዮት ተብሎ ይጠራል፡፡ "


ሰው ናሰው፣ ምእራፍ 1
ምንዳርአለው ዘውዴ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
18.8K viewsedited  06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-27 17:08:08 "በእርሻ ማሳዎቻችሁ ላይ የሚፈራረቁትን ወቅቶች ሁልጊዜ በፀጋ እንደምትቀበሉዋቸው ሁሉ የልቦቻችሁን የሀዘን ወቅቶችም  በፀጋ መቀበል ይኖርባችኋል።"
ካህሊል ጂብራን

"ሰዎች ፍቅር እውር ነው ይላሉ። እንዲህም የሚሉት የፍቅርን ትርጓሜ ስላላወቁ ነው። እኔ ግን እላችኋለሁ ፍቅር ብቻ ነው አይን ያለው። ከፍቅር ውጪ ሌላው በሙሉ እውር ነው። "
ኦሾ

"የእኛ ህይወት ግማሹን የምንወዳቸውን ሰዎች ለማግኘት እየጠበቅን፤ ግማሹ ደግሞ የምንወዳቸውን ስንሰናበት እናሳልፋለን።”
ቪክቶር-ሁጎ

"ሰዎች ብርቱዎችን ይጠላሉ ግን ይታዘዛላቸዋል ፤ ደካሞችንም ይወዳሉ ግን ይንቋቸዋልም! "
ዶስቶቭስኪ

"በብርሃን ስትሆን ሁሉ ነገር ይከተልሃል:: ጨለማ ውስጥ ከሆንክ ግን ጥላህ እንኳን አይከተልህም።"
  ሂትለር

‹‹ ቁንጅና ያለው ፊት ላይ አይደለም፡፡ ቁንጅና በውስጣችን የሚገኝ የልብ ብርሃን ነው፡፡ ››
ካህሊል ጂብራን

"የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ። ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።"
-ዊሊያም ሼክስፒር

"አዋቂ ሆኖ ለመታየት የምናደርገው ጥረትና ከንቱ ድካም አላዋቂ አድርጎ ያስቀረናል"
         ሶቅራጥስ

"ሌሎችን የሚያሸብር ሁሉ እርሱ ራሱ በማያቋርጥ ፍርሃት የተዋጠ ነው።"
ክላውሲያ

"የሰው ልጅ የሚሰቃየው ራሱ ባጠረው አጥር ራሱ በገነባው ቅጥር ራሱ በሸበበው ውትርትር ነው። የዘር፣ የሃይማኖት፣ የርዕዮተ አለም ፣... የፍልስፍና አጥር። የብቸኝነት፣ የአውሬነት፣ የወፈፌነት ፣ ... አስማት የሚመስል አጥር።" ...
 ይስማዐከ ወርቁ

"ቤትህን ፅዱ አድርግ ልክ እንግዳ ትጠብቅ
ይመስል፣ ልብህን ፅዱ አድርግ ልክ ሞትህን ትጠብቅ ይመሰል"
አረቦች

“ሰው የሚማረው አንድም በፊደል፣ አንድም በመከራ ነው፣ አንድም በሳር “ሀ” ብሎ፣ አንድም በኣሳር “ዋ” ብሎ።”
ፀጋዬ ገ/መድህን

@zephilosophy
@zephilosophy
16.4K viewsedited  14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 08:51:42 ከፍቅር ወደ አፍቃሪነት.......2

ምንጭ ፦ ነፃነት (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ ዘላለም ንጉሴ

መፈለግ (መውደድ) ከሰዎች ታላላቅ ፍላጎቶች አንዱ ነው:: ስለዚህ ፍቅር ህልውናን ይዞ ይኖራል። የሰው ልጆች እስካሉ ድረስ የፍቅርን ያህል ትልቅ ነገር አያገኙም፡፡ በምድር ላይ የሚገኝ ግን የምድር ያልሆነ ነገር ነው:: በፀሐይ ፊት እንደንስር የምትበሩበት ክንፍ ይሰጣችኋል።

ያለ ፍቅር አክናፋት አይኖሯችሁም፡፡ እጅጉን አስፈላጊ የመንፈስ ምግብና ተፈላጊ ነገር ከመሆኑ የተነሳ በዙሪያው ችግሮች ይከቡታል፡፡ ፍቅረኛህ ወይንም ፍቅረኛሽን ነገር የራስህ /ሽ/ ማድረግ ትፈልጋላችሁ ዛሬ ውብ ነገር አሳልፋችኋል፣ ለነገ ደግሞ ትጨነቃላችሁ፡፡ ስለዚህ ትዳር ይመጣል። ፍቅረኛችን ነገ እንዳትከዳን ስለምንፈራ በማህበረሰብና በሕግ ፊት ውል እንፈርማለን። ፍፁም አስቀያሚና ዘግናኝ ነገር ነው:: ፍቅርን ወደ ውል መለወጥ፣ ህግን ከፍቅር ማስቀደም ማለት፣ ማህበረሰብን ከራስህ ህልውና ማስቀደም ማለት ነው፡፡ የፍርድ ቤቶችን የጦር ሠራዊቱን፣ የፖሊሲንና የዳኞችን ከለላ በመሻት ጥምረታችሁን የተረጋገጠ ለማድረግ መጣር ማለት ነው:: ነገ ጠዋት ማንም አያውቅም፡፡ ፍቅር እንደነፋስ ሽውታ ሆኖ ይመጣል። ድጋሚ ታገኘው ይሆናል፣ ፈጽሞ ላይመጣም ይችላል። ሳይመጣ ከቀረ በህግና በትዳር የተነሳ ብቻ፣ በማህበረሰብ ክብር ከመጨነቅ የተነሳ ብቻ፣ በዓለም ዙሪያ ያሉት ጥንዶች ሕይወት ሁሉ ማለት ይቻላል፣ ወደ ወሲብ ንግድ ይለወጣል።

ከፍቅር በስተቀር በሌላ በማንኛውም ምክንያት፣ ለደህንነት ወይንም የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ተብሎ ከማትወዳት ሴት ጋር መኖር፣ ከማታውቂው ወንድ ጋር መኖር ኑሯችሁን የወሲብ ንግድ ያደርገዋል፡ የወሲብ ንግድ ከዓለም ሙሉ ለሙሉ እንዲጠፋ እፈልጋለሁ፡፡ ኃይማኖቶች ሁሉ የወሲብ ንግድ መኖር የለበትም ይላሉ፡፡ የሰው ልጅ አይረቤነት የሚታየው ይህን በመሳሰሉ ሁኔታዎች ላይ ነው።

ከእምነት ማጣት ውስጥ ፍቅርን የሚያበለጽግና የሚያሳድግ ምንም ነገር የለም፡፡ ከነአካቴው ያጠፋዋል። አፍቅር ግን ሁለተኛ አታጥፋው፡፡ ፍቅር ትክክለኛ የሚሆነው ነፃነትን ሲያጎናፅፍ ብቻ ነው::

ቅድመ ሁኔታው ይህ ይሁን። እውነተኛ ፍቅር የሚባለው የሌላውን ሰው ነፃነት የማይጋፋ ከሆነ ነው:: የሌላውን ሰው የግል ኑሮና ማንነቱን ያከብራል፡፡ ዳሩ ግን በዓለም ዙሪያ የምናያቸው ፍቅረኞች ጥረት ግን ምንም ነገር የግል መሆን የለበትም የሚል ነው፣ ሁሉም ምስጢሮች ሊነገራቸው ይገባል። ግላዊነትን ይጠላሉ፣ ይፈራሉ፡፡ አንዳቸው የሌላቸውን ማንነት ያጠፋሉ፣ ይህን በማድረጋቸውም ሕይወታቸው ርካታና ደስታ የተሞላበት አንደሚሆን ያስባሉ፡፡ ሰቀቀናቸው እለት እለት እየጨመረ ይመጣል::

አፍቃሪ ሁን፤ እውነተኛ ሆነ ማንኛውም ነገርም ዘወትር እንደሚለዋወጥ አስታውስ፡፡ ትክክለኛ ፍቅር ዘለዓለም ይኖራል የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ተቀብለህ ሊሆን ይችላል። ትክክለኛ ጽጌሬዳ አበባ ዘለዓለም አትኖርም፡፡ ህያው ፍጥረት እንኳን አንድ ቀን መሞት ይኖርበታል። ሕልውና የማያቋርጥ ለውጥ ነው፡፡ ፍቅር ዘለዓለም ይኖራል የሚለው ሀሳብ እውነት ቢሆን ኖሮ  ፍቅር አንድ ቀን ቢጠፋ የምንደርስበት ምክንያታዊ ድምዳሜ፣ እውነተኛ ፍቅር አልነበረም የሚል ይሆናል፡፡

እውነተኛ ፍቅር በድንገት የሚይዝህ አንተ ስለጣርክ አይደለም:: በቃ ተፈጥሮ ስጦታ ነች:: ሲመጣ ግን አንድ ቀን እንዳመጣጡ ይሄዳል ብለህ ብትጨነቅ ኖሮ ከነአካቴው ባልተቀበልከው ነበር፡፡ ግን የሚያስጨንቅ ነገር የለም:: ምክንያቱም አንድ አበባ ሲከስም ሌላ አበባ ይፈነዳል።

ካልሆነ ግን ብዙም ሳትቆይ የሞተና የረገፈ አበባ ላይ ሙጥኝ ብለህ ትቀራለህ፡፡ እውነታውም ይኸው ነው። ሰዎች በአንድ ወቅት ህያው የነበረ የሞት ፍቅርን የሙጥኝ ብለው ይታያሉ:: አሁን ወደ ትዝታና ስቃይ ተለውጧል፡፡ ለክብርና ለህግ ካለህ ጭንቀት የተነሳም ታስረህ ትቀራለህ።

ካርል ማርክስ ለዚህ ትክክለኛውን ሀሳብ አቅርቧል፣ ይህም በኮሚኒውዝም ስርዓት ውስጥ ምንም አይነት ትዳር አይኖርም፡፡ ሩሲያ ውስጥ አብዮቱ ከፈነዳ በኋላም፣ በመጀመሪያዎቹ አራት አምስት ዓመታት ውስጥ ፍቅርን ነፃነት ለማድረግ ሞክረዋል። ግን የካርል ማርክስ ጽንሰ ሀሳብ ወደ ተግባር ሲለወጥ ችግር ተፈጠረ ምክንያቱም ትዳር ከሌለ ቤተሰብ ይጠፋል፡፡ ቤተስብ ከጠፋ ደግሞ የማህበረሰቡና የህዝቡ /ሀገር/ የጀርባ አጥንትና መሠረት ነው፡፡ ቤተሰብ ከጠፋ ሀገርም መጥፋቱ አይቀርም፡፡
ከአብዮቱ እውን መሆን ከአምስት ዓመታት በኋላ የሩሲያ ኮሚውኒስት ፓርቲ ይህን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ለወጠው። ትዳር ዳግመኛ ድጋፍን አገኘ፡፡ ፍቺ ተፈቅዶ ግን መፋታት እጅግ ከባድ ሆነ፡፡ ምክንያቱም ቤተሰቡ እንዳለ መቆየት ይችላል የሀገሪቱን አንድነት ለማጠናከርም ይረዳል:: ያለ ሀገር ፖለቲከኞችም ሆኑ መንግሥት ሊኖር አይችልም። ትዳር የመጣው የግል ንብረት ከሚለው ሀሳብ ጋር ተያየዞ ነው የሚለውን የማርክስን ሀሳብ አላነሱም፡፡ ምክንያቱም የግል ንብረት ሲጠፋ ትዳርም አንድ ላይ ይጠፋል:: ከዚያ በኋላ አልተነጋገሩበትም፡፡

ዓለም ወደ ብዙ አካላት እንድትከፋፈል አልፈልግም። ነፃ ግለሰቦች በራሱ ጊዜ በሚቀጣጠል ፍቅር ውስጥ፣ በፀጥታና በደስታ የሚኖሩባት አንድ ዓለም እንድትፈጠር እፈልጋለሁ፡፡ ገነትን እዚሁ መፍጠር እንችላለን፡፡ ገነትን ለመፍጠር የሚያስፈልገን እምቅ ሀይል ሁሉ ቢኖረንም እየተጠቀምንበት አይደለም፡፡ በተቃራኒው ግን ብዙ እንቅፋቶችን እየፈጠርን እንገኛለን።

እኔ የፍቅር ተፃራሪ አይደለሁም፡፡ ፍቅርን እጅግ እደግፈዋለሁ፡፡ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን ሙሉ አብረው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ መለያየት አለባችሁ ማለት ሳይሆን፣ ይህን አብሮ መኖር የሚመሠረተው ፍቅር ላይ ብቻ መሆንና የሌላውን ግላዊ ሕይወትና ነፍስ በማይነካ ነፃነቱን በሚጠብቅ ሁኔታ መሆን አለበት፡፡ ይህ የሌላው ሰው ክብር ነው።

አፍቃሪ መሆን ትችላለህ፣ ፍቅር መሆን ትችላለህ:: አፍቃሪ ብቻ ከሆንክ ፍቅርን ራሱን ብቻ ከሆንክ፣ ፍቅር ወደ ጥላቻ የሚለወጥበትን ምንም ዓይነት እድል አትሰጠውም፡፡ ተስፋ የምትጥልበት ነገር ስለማይኖር ድንገተኛ ነገር ሊረብሽህ አይችልም፡፡ ስለፍቅር የምንናገረው ግን በመንፈሳዊ ክስተትነቱ እንጂ ከስነ-ተፈጥሮ አንፃር አይደለም፡፡ ስነ ፍጥረት ሴሰኝነትን እንጂ ፍቅር አይደለም፡፡ የስነ-ፍጥረት ዓላማ ዘርን መተካት ሲሆን፣ የፍቅር ሀሳብ ስነ-ተፈጥሯዊ ብቻ ነው፡፡ ሰው ተራክቦ ከፈፀመ በኋላ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓታት ፍቅረኛው እንደማትፈልገው ይሰማዋል፡፡ ይህ ደግሞ ከእድሜ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እድሜህ እየገፋ ሲሄድ ጊዜው አርባ ስምንት ሰአት፣ ወደ ሰባ ሁለት ሰአት... እያለ ይቀጥላል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
2.5K viewsedited  05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 08:51:09 ከፍቅር ወደ አፍቃሪነት...........1

ምንጭ ፦ ነፃነት (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ ዘላለም ንጉሴ

ፍቅር  ሁለት ፍፁም የተለያዩ እንደውም ሙሉ ለሙሉ ተቃራኒ ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ አንዱ ትርጉም ፍቅር በፍቅር ግንኙነት መልኩ ሲገለጽ እና ሌላው ደግም ፍቅር በራሱ ህልውና ይዞ ሲገኝ ነው:: ፍቅር ወደ ፍቅር ግንኙነት በሚለወጥበት ወቅት ባርነት ይሆናል:: ምክንያቱም የምንጠብቃቸውና የሚጠበቁብን ነገሮች እንዲሁም መረበሽ እና ፍርሀትን ይፈጥሩብናል፡፡ ከሁለቱም ወገንም እኔ እበልጥ ስሜት ይመጣል፡፡ የኃይል እሽቅድምድም ይሆናል:: የፍቅር ግንኙነት ትክክል አይደለም:: ፍቅር ህልውና ይዞ ሲገኝ ግን ሙሉ በሙሉ የተለየ ነገር ይሆናል፣ ስታፈቅር ከፍቅር ሌላ የፍቅር ግንኙነት እየፈጠርክ አይደለም ማለት ነው:: ፍቅርህ እንደ አበቦች ጥዑም መዓዛ ይሆናል። የፍቅር ግንኙነት አይፈጠር፣ ይህን አድርግ፣ ባህሪህ እንዲህ ይሁን አይልህም:: ከአንተ ምንም አይፈልግም። ያካፍላል። በማካፈሉም ምንም ሽልማት አይፈልግም፡፡ ማካፈሉ በራሱ ሽልማት ነው፡፡

ፍቅር ለአንተ እንደ አበቦች መዓዛ በሚሆንበት ጊዜ ታላቅ ውበት ይኖረዋል ከሰብዓዊነት በላይ የመጠቀ መለኮታዊ ነገር ይኖረዋል፡፡

ፍቅር ብቻውን ከመጣብህ ምንም ልታደርገው አትችልም፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ አሳርን አያመጣም አንተም በማንኛውም ሰው እንድትታሰር አይፈቅድም፡፡

ግን ከልጅነት አንስቶ የፍቅር ግንኙነቶችን የመፍጠር ልምድ አለህ፡፡ ከማታውቀው ወንድ ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ትፈጥራለህ:: አባትህ መሆኑን በፍፁም ርግጠኛ ልትሆን አትችልም፡፡

አንድ የሰዎችን መዳፎች በመመልከት ዕጣ ፈንታቸውን ስለሚተነብይ ሰው የሰማሁት ታሪክ አለ። በእጅ መዳፍ ንባብና በአስትሮሎጂ በመሳሰሉት እንዲሁም በእግዚአብሔርም የማያምን አንድ ወጣት ወደዚሁ ሰው ይሄድና፣ ሳይንስህ ትክክል ከሆነ እጄን አንብብና አባቴ የት እንደሚገኝ ንገረኝ አለው።»

አዋቂውም መዳፉን ተመልክቶ እንዲህ አለው «አባትህ አሳ እያጠመደ ነው፡፡» ወጣቱ ኢአማኒ ሳቀ፡፡ «እኔ የምለው ይህንኑ ነው፣ የማይረባ ሥራ ነው:: አባቴ ከሞተ ሶስት ዓመት ሆኖታል፤ ዛሬ እንዴት አሳ ለማጥመድ ይሄዳል።>>

አዋቂውም ሲመልስ፣ «ይህ እኔን አያገባኝም፤ እውነቱ ግን ያ የሞተው ሰው አባትህ ያለመሆኑ ነው፡፡ ትክክለኛ አባትህ አሳ እያጠመደ ነው፡፡ ወደ እናትህ ሂድና ጠይቃት፡፡ ታማኝና እውነተኛ ከሆነች የሞተው ሰው አባትህ እንዳልሆነ ትነግርሀለች። አንተ ግን አባትህ ነው ስለተባልክ ከእሱ ጋር የአባትና የልጅ ፍቅር ግንኙነት ፈጥረሀል፡፡

ሕይወታችሁ በሙሉ በብዙ ዓይነት ግንኙነቶች የተሞላ ነው:: ይህ መሰል ግንኙነቶች ደግሞ እውነትም ይሁን ሀሰተኛ፣ እጅግ ውስብስብ የሆነ ስነልቦናዊ ባርነትን ይፈጥራል። ወይ ሌላውን ባርያ ታደርጋለህ፡፡ ወይንም ራስህ ባርያ ትሆናለህ::

ሌላው መታወስ ያለበት ነጥብ ደግም ራስህን ባርያ ሳታደርግ ሌላውን ሰው ባርያ ማድረግ አትችልም፡፡ ባርነት ባለሁለት ሶስት ሰይፍ ነው፡፡ አንደኛው የበለጠ ጠንካራ፣ ሌላው የበለጠ ደካማ ሊሆን ይችላል፤ ግን በሁሉም የፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ አንደኛው አሳሪ ሌላው ታሳሪ ይሆናል። ከእሱ አንፃር ሲመለከተው እሱ አሳሪው አንተ ደግሞ ታሳሪ ትሆናለህ። የሰው ልጅ ይህን በመሰለ ሀዘንና ሰቆቃ የመኖሩ ዋነኛ ሀቅና ምክንያት መካከል አንዱ ይኸው ነው፡፡

ጥላቻ ደግሞ ከፍቅርህ የጠነከረ ግንኙነት ይፈጥራል ምክንያቱም ፍቅርህ ከአንገት በላይ ነው:: ጥላቻህ እጅግ ጥልቅ ነው:: ጥላቻህን የወረስከው ከእነስሳዊነት ባህሪህ ነው:: ፍቅርህ ለመጪው ሕይወትህ ያለህ ብቸኛ እምቅ ኃይልህ ነው:: እውን የሆነ ክስተት ሳይሆን ወደፊት ፍሬ የሚያፈራ ዘር ነው:: ጥላቻህ ግን ሙሉ በሙሉ በተግባር ላይ የሚገኝ፣ እጅግ የጎለመሰ፣ ያለፈው የብዙ ሺህ ዓመት ታሪክህ ህያው ቅርፅ ነው፡፡ የሚያድግበት ጊዜና ቦታ የነበረው:: ለውጡ መከሰት የሚጀምረው ግን በሰው ልጆች ላይ ነው::

ግን ማንንም እኔን ከመጥላት ማገድ አልችልም ስለዚህ ማንም ሰው እንዲያፈቅረኝ ማድረግ አልችልም:: ልገልፀው የምችለው ነገር ቢኖር ጥላቻም ሆነ ፍቅር የግንኙነት መልክ በሚይዝበት ጊዜ ንፅሕናውን እንደሚያጣ ብቻ
ነው፡፡

ፍቅርህን ህልውናህ አድርገው፡፡ ፍቅር
እንዲይዝህ ሳይሆን አፍቃሪ እንድትሆን ጣር፡ ፍቅር ባሪያህ ነው። ለአንተ ፍቅር የህልውናህ ጥፁም መዓዛ ነው:: ብቻህን ብትሆን እንኳን በአፍቃሪ ኃይል ትክበባለህ፡፡ የሞተ ነገርን ለምሳሌ ግዑዝ ወንበርን ብትዳስስ እንኳን ከእጅህ ፍቅር ይፈልቃል:: ፍቅርህን የምትሰጠው ለምንም ወይንም ለማንም ሊሆን ይችላል፡፡

በፍቅር ስሜት ውስጥ መሆን የለብክም እያልኩ አይደለም፡፡ ዳሩ ግን በፍቅር ስሜት ውስጥ መኖር የምትችለው ቀድሞውን የፍቅር ግንኙነት አስተሳሰብህን በምትተውበት ጊዜ ነው:: ፍቅር በሰዎች መሀል የሚመሰረት ግንኙነት ዓይደለም።

ሁለት ሰዎች አንድ ላይ እጅግ አፍቃሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አፍቃሪነታቸው በጨመረ ቁጥር በመካከላቸው የሚፈጠረው የፍቅር ግንኙነት ይጠፋል። አፍቃሪነታቸው በጨመረ መጠን፣ አንዳቸው ከሌላቸው የሚፈልጉትንና አንዳቸው በሌላቸው የሚጥሉት ተስፋ ይቀንሳል፡፡ ውስጥም ይገባሉ፡፡

በውል ሳይተዋወቁ ፍቅርን ብቻ እያሰቡ ሲወዳደሱ በመጨረሻ መወቃቀስ ይጀምራሉ፡፡ ለዚህም ነው ምንም ዓይነት ተስፋ ማድረግ እንደማያስፈልግ ልታስታውስ የምፈልገው፡፡ ፍቅር የራስህ ውስጣዊ እድገት መሆኑን አውቀህ አፍቅር። ፍቅርህ ወደላቀ ብርሀን፣ ወደላቀ እውነትና ነፃነት ከፍ ያደርግሀል፡፡ ግን የፍቅር ግንኙነት አትፍጠር፡፡

አንድ ነገር ብቻ አስታውስ፣ ፍቅር ማንኛውንም ዓይነት መጥፎ ነገር የማጥፋት አቅም አለው፣ ፍቅርን ወደ ፍቅር ግንኙነት እንዲለወጥ ከፈቀድክለት ግን፣ ፍቅር ይጠፋና የጓደኝነት ስሜት በውስጥህ ያለው ውብ ባህሪ ሲሆን ጓደኝነት ግን ወደ ትስስር ያመራል፡፡

ስለዚህ ፍቅር መልካም ነገር ነው:: እንደውም ፍቅር የሌለበት ነገር
ሁሉ ስህተት ነው:: ግን ፍቅር ከፍተኛ ዋጋ በመሆኑ ከማንኛቸውም ዓይነት በካይ መርዘኛ ነገሮች መጠበቅ አለበት፡፡ ትስስር ይበክለዋል። ዓለም በግለሰቦች የተሞላች እንድትሆን እፈልጋለሁ:: «ጥንድ» የሚለው ቃል እንኳን ይጎዳኛል፡፡ የሁለት ግለሰቦችን ህልውና አጠፋችሁ ማለት ነው፡፡ ጥንድ በራሱ ውበት የለውም፡፡

ዓለም በግለሰቦች ብቻ የተሞላች ትሁን፡፡ ፍቅር በራሱ ጊዜ ጎምርቶ ሲፈነዳ ፍቅርን ዘምሩት ፣ ጨፍሩት፣ ኑሩት፣ ግን ፍቅርን ወደ ሰንሰለት አትለውጡት፡፡ ሰውን በባርነት ለመያዝ አትሞክሩ፣ ሌላም ሰው በባርነት እንዲይዛችሁ አትፍቀዱ፡፡

ነፃ ግለሰቦችን የያዘች ዓለም በትክክል ነፃ አለም ትሆናለች።

ይቀጥላል

@Zephilosophy
@Zephilosophy
2.4K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 19:51:24 የሚያስፈልገው ምን ያህል ነው?
Repost

ከዘመን ዘመን ሳይንስ እየተራቀቀ ተክኖሎጂ እየመጠቀ ለሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎትን የሚያቀል ፈጠራ እየተበራከተ መጥቷል። ሩጫን እና ሸክምን የሚቀንሱ እልፍ ግኝቶች በገፍ ቢቀርቡም ሩጫ አልቀለለም ሸኽም አልቀነሰም።

የየእለት ኑሯችሁን ተመልከቱ። ለቅንጦት ተብለው የሚጀመሩ ነገሮች ሳይቆዩ መሰረታዊ ፍላጎት ይሆናሉ። ለትርፍ ጊዜ ታስበው የተጀመሩቱ በመደበኛ ጊዜ የሚከወኑ ይሆናሉ። ጊዜን ይቆጥባሉ ተብለው የተጀመሩቱ ጊዜን የሚሻሙ ሆነው ይገኛሉ።

ምንድነው እየሆነ ያለው?
ፌስቡክ የቅንጦት አልነበር? አሁን መሰረታዊ ፍላጎት ወደ መሆን ራሱን አሸጋግሯል።

በፊት ሰዎች ከተረፋቸው ገንዘብ ላይ በመቀነስ የሚሸምቱት ቁስ ዛሬ ላይ መሰረታዊ ፍጆታ ከመሆን አልፎ መወዳደሪያ ሆኗል።

የሚያስፈልገን ምን ያህል ነው? በየትኛው ፍላጎትስ መዳኘት አለብን? የማይሞላ ፍላጎትን ለማስታገስ የምንሮጠው እስከየት (እስከመች) ነው?

ህይወትን ያቀላል ተብሎ የተጀመረው በሂደት ህይወትን የሚያከብድ ይሆናል። ጊዜን ለመቆጠብ የተጀመረው መንገድ ጊዜን ይበላል። ለቅንጦት ያህል እንከውነው የነበረው መሰረታዊ ፍላጎት ወደ መሆን ይሻጋገራል።

የሚያስፈልገን ጥቂት ብቻ ሆኖ አላስፈላጊ የሆነውን ለማግበስበስ ታትረን ይሆን?  ወይስ የሚያስፈልገንን ሁሉ ለማከማቸት ተጋን?

@Tfanos
@Zephilosophy
5.0K viewsedited  16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 11:14:00 ሕይወት በሚታይና በማይታይ ማዕበል የተከበበች ናት!

ሰው ሃሳቡ በግንባሩ ላይ ቢጻፍ ማን ማንን ቀና ብሎ ያያል? ደግነቱ በውስጣችን ያለውን ማንም አያውቅብንም። የምናስበውን አስበን፤ የፈለግነውን አሳውቀን የምንደብቀውን ደብቀን የመኖር ጥበቡ ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ ጥበብ ነው። ልብ በሃዘን ደምቶ ፊት በፈገግታ ሲፈካ ፤ ግንባር ኮስተር ብሎ ልብ በሃሴት ሲሞላ ፤ ጉልበት ተንበርክኮ ልብ በትዕቢት ሲቆም ፤ አፍ እንደ ማር ጣፍጦ ልብ እንደ እሬት ሲመር ፤ ማን ማንን ያውቃል ያሰኛል?!

የሰው ልጅ በሚታየውና እና በማይታየው ማዕበል ውስጥ ያልፋል፤ የሚታየው ማዕበል ሌሎች የሚረዱት እና የሚያዩት ችግራችን ሲሆን፤ የማይታየው ማዕበል ደግሞ ከሌሎች ደብቀን ለብቻችን የምንጋፈጠው ችግር ነው”።

ሌሎች የማውቁት ምን አይነት ጭንቀት ይሆን እያንዳንዳችን በውስጣችን ያለው? ምን አይነት የማይታይ ማዕበል እየተጋፈጥን ይሆን?

አዎ በሰው ፊት እንስቃለን ለብቻችን ግን እንባችንን በገዛ መዳፋችን ያለማቋረጥ እናብሳለን። ከሰው መሃል ደምቀን ለብቻችን ስንሆን መግቢያ እናጣለን። ከህዝብ ፊት ከብረን በቤታችን ግን የሰው ያህል የሚቆጥረን የለም። ጠንካራ መስለን፤ ልባችንን ግን በክህደት ስብርብሩ ወጥቷል። ከላይ ሰላም የሰፈነብን እንመስላለን፤ ውስጣችን ግን በተስፋ መቁረጥ ማዕበል ይተራመሳል። ከውጪ ሲታይ ቤታችን የደመቀ ቢመስልም ውስጡ ግን እንደ ዋሻ ቀዝቅዟል። ተለቀም አነሰም ሁላችንም ለሌሎች የማይታይ ለብቻችን የምንጋፈጠው ማዕበል አለን።

እናም በየመንገዳችን ስንተላለፍ ልብ እንበል፤ ሌላው ከኛ ያነሰ ትግል የሚታገል እየመሰለን ፊት አንንሳው፤ እየረገጥን አንለፈው። የኔ ችግር እና ጭንቀት ከሌላው ይበልጣል የሚል አስተሳሰብ ሲኖረን ለሌሎች የምንዘረጋው እጅ ያጥረናል። ትኩረታችን ሁሉ የራሳችን ችግር ላይ ሲሆን ይበልጥ እናማርራለን፤ ሌሎች ለብቻቸው የሚገፈጡትን ማዕበል ስለማናይ “ምነው እኔን ብቻ” እያለን የሃዘናችንን ጉድጓድ ይበልጥ ወደታች እንቆፍረዋለን።

ከትዳር አጋራችን ጋር ክንድ ተንተርሰን እያደርን፤ እርስ በርሳችን የምንፋለመውን ትግል አናውቅም። ለዚህ ነው ጭቅጭቅ ሲነሳ መሸናነፍ እና እርቅ ማውረድ የሚከብደን፤ ማን የማንን ማዕበል ያያልና? እናም በየመንገዳችን የሚያጋጥሙን ሰዎች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ታሪክ አላቸው፤ በጫማቸው ሳንቆም አንፍረድ። በደቂቃ ውስጥ ያየነውን ምግባራቸውን ተንተርሰን አንፍረድ።

ሌላውም እንደኔ ስሜት አለው የሚል አስተሳስብ መያዝ ስንጀምር፤ የሌላው ህመም ይሰማናል እናም ብዙ ስህተቶችን ከመፈጸም እንድናለን። ምናልባት ለብቻሽ/ ለብቻህ የምትጋፈጠው ማዕበል ካለህ በርታ… አጋዥ የለኝም ብለህ አትስጋ ፈጣሪ የማትችለውን ችግር አይሰጥህም። አንተ/አንቺ ብቻ ከሰው የተለየ መከራ አልተሰጠሽም/አልተሰጠህም እንደየአቅማችን ለሁላችንም የታደለን ነው እንጂ……ከምንም በላይ ግን እርስ በርሳችን እንተጋገዝ፤ እየተገፈታተርን መተላለፉን እናቆም ምክንያቱም ሁላችንም ለየብቻችን በምንጋፈጠው ማዕበል ደክመናልና።

                       ሚስጢረ አደራው

            ውብ አሁን

@zephilosophy
4.6K viewsedited  08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 22:19:24 «የድሀ ፊት የአምባገናኖች ግፍ በየእለቱ የሚጻፍበት የማስታወሻ ደብተር ነው፡፡ እናም ድሃ ምን ፊት አለው? አምባገነንት የክፋቱን ገድል በየቀኑ በግፍ ቀለማት የሚስልበት የስቃይ ሰሌዳ ነው፡፡ ተስፋውን በቁም ሲገድሉበት ተመልሶ ላይወዛ የገረጣ ቆዳ፣ ቤቱን በጠራራ ጸሀይ ሲያፈርሱበት አሮ የከሰለ ፊት፣ ሲያስሩትና ሲገርፉት በሰንበር ሞዛይክ የተሳለ ገላ፣ ልጆቹን ሲያስሩበትና ሲገድሉበት ባነባው እንባ የታረሰ ፊትና ደም የለበሰ አይን የተሳለበት ሰሌዳ ነው፤ የድሃ ፊት፡፡ እናም ድሀ የኔ የሚለው ፊት የለውም፡፡ የሌለውን ፊት ደሞ ሊሸፍን አይጥርም፡፡››

ምንዳርአለው ዘውዴ
አፍን ዘግቶ ፉጨት

@Zephilosophy
4.5K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ