Get Mystery Box with random crypto!

የሚያስፈልገው ምን ያህል ነው? Repost ከዘመን ዘመን ሳይንስ እየተራቀቀ ተክኖሎጂ እየመጠቀ ለ | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የሚያስፈልገው ምን ያህል ነው?
Repost

ከዘመን ዘመን ሳይንስ እየተራቀቀ ተክኖሎጂ እየመጠቀ ለሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎትን የሚያቀል ፈጠራ እየተበራከተ መጥቷል። ሩጫን እና ሸክምን የሚቀንሱ እልፍ ግኝቶች በገፍ ቢቀርቡም ሩጫ አልቀለለም ሸኽም አልቀነሰም።

የየእለት ኑሯችሁን ተመልከቱ። ለቅንጦት ተብለው የሚጀመሩ ነገሮች ሳይቆዩ መሰረታዊ ፍላጎት ይሆናሉ። ለትርፍ ጊዜ ታስበው የተጀመሩቱ በመደበኛ ጊዜ የሚከወኑ ይሆናሉ። ጊዜን ይቆጥባሉ ተብለው የተጀመሩቱ ጊዜን የሚሻሙ ሆነው ይገኛሉ።

ምንድነው እየሆነ ያለው?
ፌስቡክ የቅንጦት አልነበር? አሁን መሰረታዊ ፍላጎት ወደ መሆን ራሱን አሸጋግሯል።

በፊት ሰዎች ከተረፋቸው ገንዘብ ላይ በመቀነስ የሚሸምቱት ቁስ ዛሬ ላይ መሰረታዊ ፍጆታ ከመሆን አልፎ መወዳደሪያ ሆኗል።

የሚያስፈልገን ምን ያህል ነው? በየትኛው ፍላጎትስ መዳኘት አለብን? የማይሞላ ፍላጎትን ለማስታገስ የምንሮጠው እስከየት (እስከመች) ነው?

ህይወትን ያቀላል ተብሎ የተጀመረው በሂደት ህይወትን የሚያከብድ ይሆናል። ጊዜን ለመቆጠብ የተጀመረው መንገድ ጊዜን ይበላል። ለቅንጦት ያህል እንከውነው የነበረው መሰረታዊ ፍላጎት ወደ መሆን ይሻጋገራል።

የሚያስፈልገን ጥቂት ብቻ ሆኖ አላስፈላጊ የሆነውን ለማግበስበስ ታትረን ይሆን?  ወይስ የሚያስፈልገንን ሁሉ ለማከማቸት ተጋን?

@Tfanos
@Zephilosophy