Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የሰርጥ አድራሻ: @zephilosophy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.78K
የሰርጥ መግለጫ

"Strong minds discuss ideas, average minds discuss events, weak minds discuss people."
Rinu Ruzvelt

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-02 12:27:55 የፖለቲካ ጠቅላላ ደስታ «ጠላት» ውስጥ የተደበቀ ነው

በመሬት ላይ ሳይሆን በካርታ ላይ ብቻ የሚገኙትን የወሰን መስመሮች ካጠፋናቸው ስለ ፖለቲካ የሚጨነቅ ማን ይኖራል? አዎ' አንድ የዓለም መንግስት ይኖራል። ይህ መንግስት ግን አገልጋይ ብቻ ነው የሚሆነው:: ከማንም ጋር ስለማይፎካከር የተለየ ክብር አይሰጠውም፡፡ የዓለም መንግስት ፕሬዝዳንት ሆናችሁ ታዲያ ምን ይጠበስ? መንግስት ብትሆኑም ከማንም አትበልጡም፡፡ . .. .

የሃገራት ኢጎ መጥፋት አለበት፡፡ የሃገራት ኢጎ ሲጠፉ ፖለቲካም ይጠፋል፤ ራስን በራሱ ያጠፋል። እንክብካቤ የሚያደርግ አንድ የስራ (ተግባር) ድርጅት ብቻ ይቀራል። ልክ እንደ ሮታሪ ክለብ ስለሚሆን መሪው አንዳንድ ጊዜ ጥቁር ይሆናል፤ አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ይሆናሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ቻይናዊ ይሆናል፣ አንዳንድ ጊዜ ሩሲያዊ ይሆናል፤ አንዳንድ ጊዜ አሜሪካዊ ይሆናል - ልክ እንደጕማ ይሽከረከራል።

አንድ ሰው ከአንድ ጊዜ በላይ ባይመራ መልካም ነው፡፡ ከዚያ በላይ ሲሆን አደገኛ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው እንደ ፕሪዝዳት ከሆነ በኋላ ተመልሶ አይሾምም፡፡ አንድ ሰው ደጋግሞ ከተመረጠ የብልህነት ድህነት ይመጣል፡፡ ለናንተስ እንደ የብልህነት ድህነት ሆኖ አይታያችሁም?

ሰውን አሁን ባለው ደረጃ ስንመለከተው መንግስት እንደሚያስፈልግ እንገነዘባለን፤ ፖሊስ እንደሚያስፈልግ እንገነዘባለን፡፡ አለበለዚያ ይህን ተከትሎ ነፍስ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ዘረፋ ይስፋፋል. . . ህይወት ሁከት የበዛባት ትሆናለች፡፡ ቁጥጥር ሲጠፋ ሁካታ ይነግሳል፡፡ ሰዎች በቡድን ተደራጅተው ደካሞችን ይበዘብዙና ህይወት የተሻለች በመሆን ፈንታ አስከፊ ትሆናለች::

መለወጥ ከቻልን፣ ብዙ ሰዎችን ወደ ተመስጥኦ ካመጣን፤ ብዙ ሰዎችን እውነተኛ ና ተፈጥሯዊ ኑሮ እንዲኖሩ ፣ ፍቅር እንዲጋሩ፣ ህያው ለሆነ ነገር ሁሉ ትልቅ ርህራሄ እንዲኖራቸው፣ ለህይወት ከበሬታ እንዲኖራቸው ማድረግ ከቻልን. ..

እነዚህ ግለሰብ አብዮተኞች፣ እነዚህ ግለሰብ አማፅያን (የፖለቲካ አማፅያን) ብቻ አይሆኑም ፤ ተቃውሟቸው ባለፈ ልምዳቸው ላይ በሙሉ ይሆናል። የማንነታቸውን ማዕከል የሚያገኙ ይሆናሉ. . . አዎን፣ ደስተኛ የሆኑና ምድርን የማይክዱ ግለሰቦች እየመጡ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በሁሉም ሰዎች ተፈጥሯዊ ያልሆነ ስነልቦና የህይወት መንገድ የማይደግፉ ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች በመላው ዓለም እንደ ሰደድ እሳት ቢበተኑ የቁጥጥር አለመኖር ፍልስፍና ግብ መሆኑ ቀርቶ ተረፈ ምርት ይሆናል።

መንግስታት የሰዎችን ግለሰባዊነት ክፉኛ ጎድተውታል። ሁሉንም ህጎች፣ ፍርድ ቤቶችና ዳኞች ይቃወማል - ምክንያቱም እነዚህ ሁሉ ፍትህን የሚያስጠብቁ፣ ለደካሞች የቆሙ፣ ለተበዳዮች የሚከራከሩ አይደሉም - እነሱ የቆሙት ስልጣን ላላቸው፣ ለተቋማትና ለሃብታሞች ነው። ከፍትሃዊነት በስተጀርባ በሰው ልጅ ላይ ታላቅ ደባ ይፈፅማሉ፡፡

መጪው ጊዜ እንደ ባኩኒን፣ ባክሃሪን፣ ቶልስቶይ፣ ለመሳሰሉ ሰዎች ታላቅ ከበሬታ ይሰጣል - ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ሳይንሳዊ አሳቢያን ባይሆኑም ቢያንስ ሃሳቡን ፈጥረዋል፡፡ መሰረቱን ሳይጥሉ ስለ ቤተ - መቅደሱ ማውራት ጀምረዋል፡፡

የእኔ ጥረት በሙሉ በቤተ - መቅደሱ ላይ ሳይሆን መሰረት በመገንባቱ ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ ከዚያ በኋላ መቅደሱን መስራት አስቸጋሪ አይሆንም:: ቁጥጥር አያስፈልግም የሚለው ፍልስፍና በስነ - ልቦና ረገድ ጤናማ የሆነ፣ ጫና የሌለበት ፣ መንፈሳዊ ጤና ያለው፣ የውጫዊውን ዓለም ውበትም ሆነ ውስጣዊውን የንቃት ሃብት የሚያውቅ ማህበረሰብ ተረፈ - ምርት ይሆናል፡፡ በቅድሚያ እንዲህ አይነት ሰዎች ካልኖሩ በቀር ፍልስፍናው እውን ሊሆን አይችልም! እንደ ተረፈ ምርት ብቻ ነው መምጣት የሚችለው::

አንድ ነገር ልትገነዘቡ ይገባል። ዓለም ነፃነትን እንድታገኝ ከተፈለገ ፖለቲካ ያን ያህል አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ከዙፋኑ ሊወርድ፣ ስልጣኑ ሊቀንስ ይገባል - ሰልጣን ሊኖረው የሚገባበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ መንግስት እንደ ፖስታ ቤት ሰራተኛ ሊሆን ይገባዋል። የፖስታ ቤት ሃላፊው ማን እንደሆነ የሚያውቅ ማንም አይኖርም፡፡ ስለፖለቲከኞች ጥሩ እና ትልቅ ስም ሰጧቸው፣ ነገር ግን ያን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እነዚህን ለዘመናት የሰውን ልጅ ሲያሰቃዩ የኖሩ ሰዎች በየጋዜጣው የፊት ለፊት ገፅ ላይ ማስፈሩ አላስፈላጊ ነው፡፡

ከፖለቲካ ጋር ምንም የማያገናኛቸውን የተለዩ የገለፃ እና የፈጠራ መንገዶችን ተጠቀሙ:: ከፖለቲካ ግንኙነት የሌላቸውን፣ የስልጣን ፍላጎት የሌላቸውን፣ ህይወትን በምሉዕነት የሚኖሩትን ሰዓሊያን፣ ገጣሚያን፣ ቀራፂያን እና ዳንሰኞች ያቀፉ ትናንሽ ማህበራትንና መንደሮችን መስረቱ፡፡

መላው ህብረተሰብ ቀስ በቀስ የፈጠራ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው መንደሮች ይከፋፈል፡፡ በዓለም ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አያስፈልግም። እያንዳንዱ ፖለሰብ በራሱ መቆም መቻል አለበት፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ የሚኖረው ለምንድነው? ምንም ምክንያት የለም። አንድ የገንዘብ ሚኒስትር ካስፈለጋችሁ ሁሉም የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ባለሙያዎች ተወዳድረው አንዱ ሊመረጥ ይችላል፡፡ ሌላ ፓርቲ አያስፈልግም። ከፓርቲ ፖለቲካ ወጥተን ወደ ንፁህ ግለሰባዊነት - ከዲሞክራሲ፣ ከአምባገነናዊነት ወደ ሜሪቶክራሲ መሸጋገር አለብን።

ወሳኙ ነጥብ ችሎታ መሆን አለበት፡፡ ትላልቅ ችሎታ ያላቸው ብዙ ሰዎች አሉን - ነገር ግን የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን የለባቸውም፤ ራሳቸውን ዝቅ ማድረግም የለባቸውም። የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን ለእነሱ ዝቅ ያለ ነገር ነው- ድምፅ እንዲሰጣቸው መለመን፣ ማሟላት የማይችሉትን ሃሰተኛ ነገር ቃል መግባት ዝቅ ያለ ነገር ነው፡፡ ስለዚህም የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሚሆኑት በሶስተኛ ደረጃ የሚኖሩ፣ ተራ ሰዎች እንጂ ምርጥ የሚባሉት አይደሉም፡፡

ምርጦቹ ማህበረሰቡን መምራት የሚችሉት መሆን አለባቸው። በየመስኩ ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች አሉን፣ ነገር ግን እነዚያን የተሰጥኦ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም ፕሬዝዳንት ሆነው እናገኛቸው:: የፖለቲካ ፓርቲዎች የማይኖሩ ከሆነ ፕሬዝዳንቶች ና ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ተስጥኦዎቻቸው በቂ ስለሆነ ከእነሱ ጋር የሚወዳደር አይኖርም:: የእናንተን ድምፅ መለመን አይኖርባቸውም፣ በሙሉ ድምፅ ይመረጣሉና::

ጨለምተኛ መሆን፣ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም፡፡ በታሪክ ያየነውን የማያቋርጥ ውድቀት በመገንዘብ ተፈጥሯዊ ነው ልንል እንችላለን፡፡ ይህን ግን ለማንም አይጠቅምም፡፡ አንድ መንገድ ማግኘት አለብን. .. አሮጌዎቹ ሙከራዎች ለምን እንዳልተሳኩ ማወቅና አዳዲስ ዘዴዎችንና ስትራቴጂዎችን መተለም አለብን፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ ወጣቶች በአንድ አይነት ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ከመሆናቸው በተጨማሪ አሮጌዎቹን መዋቅሮች በሙሉ ለውጠው የሰውን ልጅ ነፃ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው፡፡

ነፃነት የሰው ልጅ ሰውነቱን የሚያገኝበት መንፈሳዊ ነገር ነው። ከሞቱ የማይረቡ አስተሳሰቦች፣ ርዕዮተ- ዓለሞች፣ ቀኖናዎች ነፃ መዉጣት አስፈላጊ ነው። ከእነዚህ ነገሮች ነፃ ስትሆኑ ክንፍ አውጥታችሁ በስማይ ላይ የምትበሩ ያህል ይሰማችኋል፡፡

ምንጭ ፦ ህያዉነት፫ (ኦሾ)
ተርጎሚ ፦ ሀብታሙ ተስፉዬ
               ተስፋሁን ምትኩ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.3K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 21:24:38 መመሰጥ-ግስታልት ቴራፒ

የብዙዎቻችን ሕይወት በተግባራት የተጨናነቀ እና ፋታ አልባ ነው፡፡ ጸጥ ማሰኘት የማንችለው ብዙ ጫጫታ አለ፤ መተንፈስ እስከሚያዳግተን ድረስ እንጨነቃለን፡፡ እንቅልፍ ርቆናል፡፡ ሕይወታችን አሁንም ድፍርስ ነው፤ መስከን አንችልም፡፡ ለብቻችን የምንሆንበት ጸጥ ያለ ቦታ ያስፈልገናል።ይህ ነው የግስታልት ቴራፒ ተብሎ የሚጠራው።

ግስታልት ቴራፒ መነሻውን ያደረገው “አሁንን ብቻ ኑር” ከሚል የህላዊነት እሳቤ ነው፡፡ ዓለምን ያለምንም ጣልቃ ገብ ሃሳብ ቅመሳት። ያለፈ ታሪክ፣ የነገ ስጋትህን ሁሉ ለአፍታ ዘንጋቸው፡፡ ሸክምህን ሁሉ አራግፍ᎓᎓ አሁንን ብቻ በጸጥታ ውስጥ ሆነህ ኑረው፡፡ አሁን ላይ ብቻ አተኩር። ይህ ሳይኮሎጂስቶች የሚጠቀሙበት ቴራፒ (ህክምና) ነው ለጥቂት ደቂቃዎች ራስህን ከዓለም ለይተህ ጸጥ ባለ ስፍራ ሁን ምንም አታስብ ... ምንም አትስራ፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረህ ማንነትህ አሁንህን ይጫነዋልና እርሳው᎓᎓ ሆነ ጭምትነትህ ያለፉ ድህነትህ፣ ኃብትህ... ተጫዋችነትህም ማንነቶች ናቸው፡፡ ወደ ኋላ መመለስ የለብህም። እኔ እንዲህ ነኝ ብለህ የምታስበውን ሁሉ እርሳ።

ይህ የባዶነት ስፍራ Fertile void ይሰኛል። ልክ ዘርን እንደሚሰጥ እርሻ ያልታረሰ ባዶ ስፍራ፡፡ በዚህ ስፍራ ያለኸው እንዲደብርህ ወይም ከራስህ ጋር እንድታወራ አይደለም። ልክ እንደማብሪያ ማጥፊያ መብራት እንደሚያጠፋ፣ ልክ በር ከውጪኛው ዓለም እንደሚለይህ ወይም ሰው ሲረብሽህ “እሽሽ” እንደምትልበት አይነት ... ይህም የጨለማ እና የባዶነት ስፍራ ነው። ሁሉንም ነገር ታጠፋለህ፣ ትዘጋለህ።

ሃሳቦችህ ባንተ ታዘው ሳይሆን በራሳቸው ይፈሳሉ፡፡ ላንተ ማሰብ አልተፈቀደምና የሃሳብ ወንዙን ዳር ሆኖ ከመመልከት ውጪ መሟገት አልያም ከወንዙ ጋር ትግል መግጠም አትችልም።

ይህ የባዶነት ስፍራ አዳዲስ እና ያላስተዋልካቸው ሃሳቦች ከህቡዕ ህሊናህ ወደ ውጭ የሚፈሱበት ስፍራ ነው፡፡ ይህ ስፍራ ልክ እንደ ለም መሬት ፍሬን ያፈራል፡፡
በባዶነት ስፍራ ውስጥ መሆን በእጅጉ ይከብዳል፡፡ ልክ አለቃ ስራ ሲያዝህ አልሰራም የማለትን ያህል ይከብዳል፡፡ ከዚህ ቀደም አልለመድከውምና አዙሪትህን መስበር ቀላል አይሆንልህም:: ሆኖም ራስህን በባዶነት ስፍራ መሆንን አላምደው፡፡ ምንም አለማሰብ፣ ምንም
አለማድረግ፣ ከማንም ጋር አለመሆን... ባዶነት

ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
7.5K viewsedited  18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 11:43:49 ውስጣዊ ምሕንድስና (Inner Engineering)
Sadhuguru

ለመሆኑ አብዛኛው የሰው ልጅ ምንድነው የሚሰራው? ይበላል፣ ይተኛል፣ ይዋለድና ይሞታል፡፡ ብዙ ነገሮች ልትሰራ እንደምትችል ታምን ይሆናል፤ ግን የመሞቻህ ቅጽበት ሲደርስ ወደ ኋላ መለስ ብለህ ትመለከትና ስትሰራ የነበርካቸው ነገሮች በሙሉ የመኖር ሂደትህን ማወሳሰብ እንደነበረ ትረዳለህ፡፡ የሰው ልጅ እያንዳንዱ ትል፣ ነፍሳት፣ ውሻ፣ ድመትና ወፍ ሊያደርጉት የቻሉትን ቀላል የሕይወት ሂደት ማድረግ አልቻለም፡፡ የሰው ልጅ በሕይወቱ መጨረሻ በዙሪያው ባሉት ነገሮች ሁሉ የተጎዳ ይሆናል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ፣ ብዙ ሰዎች እድሜያቸው ሲገፋ ጥበበኛ አይሆኑም- የቆሰሉ እንጂ፡፡

እኛ በለውጥ ሂደት ውስጥ ነን፡፡ ምክንያቱም ይህ የሕይወት ተፈጥሮ ነው። ሁሉም ነገር ቀጣይነት ያለው የለውጥ ሂደት ነው፤ · እኛስ? በፕላኔታችን ላይ ያለ ነገር ሁሉ በለውጥ ሂደት ውስጥ ነው፡፡ አንተስ የለውጥ ሂደት ነህ? ይህ ትልቅ ጥያቄ ነው፤ ለዚህ ጥያቄ መልስህ አዎን የሚል ከሆነ፣ ምንም ችግር የለም፡፡ ከዚህም ከዚያም ጋር የምትቀላቅልና በየቀኑ ለምን እንደተቀላቀልክ አሳማኝ ምክንያት እየፈለግክ  ያለህ በራሱ የማይንቀሳቀስ ውሃ ከሆንክ፣ ተስፋ የለህም፡፡ በዚህች ፕላኔት ላይ ጊዜ የምታባክን ነህ፡፡ ጊዜ ማባከን ሲባል ሕይወትን ማባከን ማለት ነው፣ ምክንያቱም ሕይወትህ ጊዜ ነው፡፡ ሌላ ፍጥረት፣ ቅን ካልሆነ ሰው ይልቅ በደስታ ሊዘል ይችላል፡፡ አንተ ከሌሎች ፍጥረታት በበለጠ የተሻለ ነገር መስራት የማትችል ከሆነ፣ እጅግ ውድ ሕይወት መሆንህ ምንም ጥቅም የለውም፡፡ በጫካ ውስጥ ምንም አይነት ወጥ ቤት የለም፣ በውስጡ የሚኖሩት ግን በሚገባ ይመገባሉ። ዝሆንም ጫማ አድርጎ ሲራመድ አትመለከትም፤ እኛ ግን ለመብላት፣ ለመተኛት ለመራመድ፣ ከጫማ እስከ ልብሶች እንዲሁም እስከ ቤቶች ድረስ በሁሉም መንገድ እጅግ ብዙ ዝግጅቶች የሚያስፈልጉን እጅግ ውድ የሆንን ሕይወት ነን፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁሉ ወጪ፣ ሌሎች ፍጥረታት ሊሰሩት ከሚችሉት የተሻለ ነገር መስራት ይገባናል።የመኖራችን ትርጉም በልቶ ከማደር የተሻለ ምክንያት ሊኖረው ይገባል።

በእውነት ደህንነት ተሰምቶህ የሚያውቀው የተደሰትክ ጊዜ ነው፡፡ በአካልህ ላይ ህመም ቢኖር እንኳን ደስተኛ ከሆንክ ደህና እንደሆንክ ይሰማሃል። ደህንነት ማለት በመሰረታዊነት በሕይወት ውስጥ የተወሰነ ደረጃ ደስተኛ መሆን፣ ሐሴት ማድረግ ማለት ነው፡፡ ደስተኛ ሆነህ መኖር የምትፈልግ ከሆነ፣ በውስጥም ይሁን በውጪ አኗኗርህን፣ አካባቢህንና ራስህን በምታስተዳድርበት መጠን የተወሰነ ይሆናል፡፡

በመሰረታዊነት ሕይወት አስተዳደር ነው፡፡ አካልህን፣ አእምሮህን፣ ስሜትህንና ሁኔታዎችህን እንዴት መጠበቅ እንዳለብህ የማታውቅ ከሆነ፤ ሕይወትህ፣ ቤትህ፣ አካባቢህ፣ በዓለም ላይ  ያለ ህዝብ አጠቃላይ የሕይወትህ ጥራት የሚወሰነው ነገሮችን በራስህ ማስተዳደር በምትችልበት መጠን ነው፡፡ በአጠቃላይ ስለ አስተዳደር ስንነጋገር የምናስበው በአጠቃላይ ስለ ሕይወት ሳይሆን፣ ከኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች አንጻር ሆኗል

ዛሬ በብዙ መንገዶች ሌሎቹ የሕይወት ገጽታዎች ወደ ጥግ ተገፍተው ፕላኔቷ ያለችበት ህግ ኢኮኖሚክስ መሆኑ የሚያሳዝን ነው፡፡ የሚገዛው ኢኮኖሚክስ ሲሆን፣ የምናስበው ኢኮኖሚክስ ብቻ ሲሆን፣ በብዙ መንገዶች ያልታረምንና ደስታ የራቀን እንሆናለን፡፡ በሕይወታቸው ያልተሳካላቸው ሰዎች በውድቀታቸው እየተሰቃዩ ሲሆን፣ በሕይወታቸው ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ደግሞ በስኬታቸው እየተሰቃዩ ነው፡፡ ውድቀት በቀላሉ የሚመጣ በመሆኑ በውድቀትህ መሰቃየት ምንም አይደለም፡፡ እየተሰቃየህ ያለኸው በስኬትህ ከሆነ ግን፣ ስኬት በቀላሉ የሚመጣ ነገር ባለመሆኑ ያ አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ ስትሰራው _ የነበረው ነገር፣ ስትናፍቀው የነበረ ነገር፣ በሕይወትህ ውስጥ ልትፈጥረው ትፈልገው የነበረ ነገር፣ በተከሰተ ጊዜ፤ በዚያ መሰቃየት ከጀመርክ፣ ያ በሕይወት ውስጥ እውነተኛው አሳዛኝ ነገር ነው። በምድር ላይ ያሉ በጣም ብዙ ስኬታማ ሰዎች በስኬቶቻቸው እየተሰቃዩ ነው። በስኬታቸው እየተሰቃዩ ነው ሲባል፣ የአምስት አመት ልጅ ሳለህ ምን ያህል ደስተኛ ነበርክ፣ ዛሬስ ምን ያህል ደስተኛ ነህ? በሀያ አራት ሰዓታት ጊዜ ውስጥስ ለምን ያህል ጊዜ ደስተኛ ሆነሃል? በሕይወትህ ውስጥ ደስተኛ ካልሆንክና የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ደስታን ማሳደድ ከሆነ መጥፎ አስተዳዳሪ ነህ ማለት ነው፡፡

በሕይወትህ ውስጥ የምታደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ፣ የምታደርገው ያ ነገር ደስታህ እንደሆነ ስለምታምን ነው፡፡ ራስህን ታስተምራለህ፣ ሙያህን ታሻሽላለህ፣ ቤተሰብ ትገነባለህ፣ ምኞቶችህን ትከተላለህ፣ ብዙ ነገሮችን ትሰራለህ... ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ማሳካት ደስታ እንደሚያመጣልህ ስለምታምን ነው፡፡ ያንን ሁሉ ካደረግክ በኋላ ደስታህ ከመብዛት ይልቅ ከቀነሰ አንተ የራስህ መጥፎ አስተዳዳሪ ነህ ማለት ነው፡፡

የራሱን አካል፣ የራሱን አእምሮ፣ የራሱን ስሜት፣የራሱን ኃያል እንዴት ማስተዳደር እንዳለበት የማያውቅ ሰው፣ ውጪያዊ ነገሮችን በሚያስተዳድርበት ጊዜ የሚያስተዳድረው በአጋጣሚ እንጂ እርሱ እንደሚፈልገው ሆነ ብሎ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አእምሮህን፣ ኃያልህን፣ ውስጣዊ ነገሮችህን እንዴት ማስተዳደር እንደምትችል ካላወቅክ፣ ውጪያዊ ነገሮችን ማስተዳደርህ በአጋጣሚ መሆኑ አይቀርም፡፡ ነገሮችን በአጋጣሚ በምታስተዳድርበት የምትኖረውም በአጋጣሚ ይሆናል፡፡ በአጋጣሚ ስትኖር ደግሞ ድንገት ሊከሰት እንደሚችል አደጋ ነህ ማለት ነው፡፡ ሊሆን እንደሚችል አደጋ ከተከሰትክ ደግሞ፣ሁልጊዜ ጭንቀት ውስጥ መሆን የተለመደ የሕይወትህ ክፍል ይሆናል፡፡ ከዚያ ሰዎች በዓለም ላይ ምንም ነገር ብታገኝ ጭንቀታም መሆንህ የማይቀር ይሆናል፡፡

መንገድ ውጣና ምን ያህል ደስተኛ ፊቶች እንደምታገኝ ተመልከት፡፡ በጣም ጥቂት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ውጪያዊ እንጂ ውስጣዊ አስተዳደር ስለሌለን ነው፡፡ የምንፈልገውን በመፍጠር ሂደት ውስጥ የሕይወታችን ምንጭ የሆነችውን ይህቺን ፕላኔት እያጠፋናት ነው፡፡ ደስታችንን በማሳደድ ውስጥ ይህቺን ፕላኔት እንደ ደመራ እያጋየናት ነው፡፡ ግን አሁንም አልረካንም፤ ሰዎች ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ከብዙ መቶ አመታት በፊት ከነበርነው የበለጠ ደስተኛም አልሆንንም፡፡ ስለዚህ የሆነ ቦታ ላይ ውስጣዊ ነገሮቻችንን ችላ ብለናል፡፡

ታዲያ ወደ ውስጣችን ለመመለስ ምን ያስፈልገናል?
ይቀጥላል...

@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.2K viewsedited  08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 17:32:04 የበታችነት ስሜት (Inferior complex)

ሰው በሁለት ነገሮች ተጠምዶ ህይወቱን ያባክናል። ወይ በበታችነት ስሜት ወይ ደግሞ በበላይነት ስሜት ይሰቃያል።

አንድ ሰው በበታችነት ስሜት ከተያዘ ውስጡ በጥልቀት ይታመማል፡፡ ከንቱ እንደሆነ እያሰበ ከኖረ በህይወት የመቆየቱ ጉዳይ አስቸጋሪ ይሆናል። በህይወት እየኖረ ቢሆንም ሙት ነው፡፡ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በህይወት የሚቆዩ በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ። አብዛኞቹ ግን ከመሞታቸው በፊት የሚሞቱ ናቸው። በሰባ አመታቸው ቢቀበሩም የሞቱት ግን ቀደም ብለው ነው። በሞታቸውና በቀብራቸው መሀል የሰላሳ፣ የአርባ ወይም የሃምሳ ዓመታት ክፍተት ሊኖር ይችላል፡፡

በዙሪያችሁ የተንሰራፋውን ግዝፈተ ተፈጥሮ ስትመለከቱ የበታችነት ሊሰማችሁ ይችላል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ሰው ምንም ነው። በውቅያኖስ ሞገዶች ላይ እንደተንሳፈፈ ገለባ ነው። ምንም አይነት ሃይልም ሆነ አቅጣጫ የለውም፡፡ እንደዚህ አይነት የበታችነት ስሜት አይምሮን ጨምድዶ ከያዘ የሰው ህይወት በመከፋት የተሞላ ይሆናል። በህይወት የሚኖር ሙት ይሆናል፡፡ ህይወቱ አመድና ትቢያ ይሆናል። የህይወታችሁ ነበልባል ከውስጣችሁ ከጠፋ፣ የፋኖሳችሁ ነበልባል ከጠፋ፣ በፀሃይ ብርሃንም ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡ ለናንተ ፀሃይ ምንም ጥቅም አይኖራትም፡፡

በሰው ውስጥ መላው ግዝፈተ ተፈጥሮ እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በሰው ውስጥ መለኮት እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ሰው የበታች አይሆንም፡፡ በጣም የሚገርመው ሰው የበታችነት ስሜቱን ለማውደም አስቦ በበላይነት ስሜት መጃጃሉ ነው። የበታችነት ስሜቱን ለማፈን የተለያዩ መንገዶችን መፈለግ ይጀምራል። ውስጡን የበታችነት ስሜት ሲሰማው ሃብት በማከማቸት ለአለም ህዝብ ከንቱ አለመሆኑን ሊያሳይና ከሌላው የበላይ የመሆን ስሜት ሊሰማው ይችላል። ከበታችነት ስሜቱ የተነሳ ጭንቅላቱ ላይ ዘውድ ደፍቶ ከንቱ አለመሆኑን ለማሳየት ይሞክራል። የበላይነት ፉክክር ውስጥ የሚከተው የበታችነት ስሜት ነው። እናም የበላይ ለመሆን በሚደረግ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ያሉ ሰዎች ያለጥርጥር ውስጣቸው በበታችነት ስሜት እየተሰቃየ ነው።

ከዚህ አንፃር አድለር ብዙ አስገራሚ ነገሮችን ተናግሯል። ገለፃዎቹ አስፈላጊ ናቸው። እንደ አድለር ገለፃ ከሆነ በሩጫ ውድድር አንደኛ የሚወጡ ሰዎች በልጅነታቸው በትክክል መራመድ የማይችሉ ነበሩ። ልዩ የሙዚቃ ክህሎት ያላቸው በልጅነታቸው መጠነኛ የመስማት ችግር የነበረባቸው ናቸው፡፡ ርዕሰ ብሔር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት ደግሞ በትምህርት ቤት ህይወታቸው ኋላ ወንበር ላይ የሚቀመጡ የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በልጅነት በደረሰባቸው የበታችነት ስሜት ጉዳት ሳቢያ ከንቱ አለመሆናቸውን ለዓለም ለማሳየትና ለማረጋገጥ ይፈልጋሉ። አንድ ፖለቲከኛ በበታችነት ስሜት ቢሰቃይ አያስገርምም፡፡ ከንቱ ነኝ የሚል የበታችነት ስሜት ውስጡን እንደ ትል ይበላዋል፡፡ በዚህም አይምሮው ተጐድቶ ችግር ውስጥ ይከተውና የበላይ መሆኑን ለማሳየት ወደ ውድድር እንዲገባ ያነሳሳዋል።

ሌኒን ወንበር ላይ ሲቀመጥ እግሮቹ ወደ ወለሉ አይደርሱም ነበር፡፡ ከወገቡ በላይ ያለው የሰውነቱ ክፍል ከወገቡ በታች ካለው ይረዝም ነበር። እናም ወንበር ላይ ሲቀመጥ እግሮቹ ወደ ወለሉ መድረስ አይችሉም፡፡

ሂትለር ደግሞ ተራ ንቃተ ህሊና የነበረው ወታደር ነበር። በዚህም የጦር ሰራዊቱ አባል ለመሆን አትመጥንም ተብሎ ተባሮ ነበር። ስታሊንና ሊንከንም የጫማ አዳሽ ልጆች ነበሩ፡፡

የአለማችንን ፖለቲከኞች የኋላ ታሪክ ብንመለከት እንገረማለን። የእሽቅድምድማቸው መንስኤ በልጅነታቸው የገጠማቸው የበታችነት ስሜት ጉዳት ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ እንደ እብድ መሽቀዳደም የጀመሩ ናቸው፡፡ ወደ አንድ የከፍታ ጫፍ ላይ መውጣት ካልቻሉ አይረኩም፡፡ እዛ የከፍታ ጫፍ ላይ በመውጣት ከንቱ አለመሆናቸውን ለአለም አሳይተዋል። በውስጣቸው ግን ምንም ነበሩ። ከዚህ አንፃር ሁሉም ስልጣን፣ ሃብት፣ ወይም ዝና ለባለቤታቸው ትርጉም አልባ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ግለሰቡ የፈለገውን በእጁ ቢያስገባም ውስጡን ግን ያው እንደ በፊቱ ሆኖ ያገኘዋል። የበታችነት ስሜቱ አሁንም እንደ ትል ይበላዋል። ትልቁ የስልጣን እርከን እንኳ እርካታን አያመጣም፡፡ እናም ቀድሞ መገኘት ያለው እሽቅድምድም አይጠፋም፡፡ አንድ ሰው አሌክሳንደርን፡- “አለምን ለመቆጣጠር እንደምትፈልግ ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን አለምን ከተቆጣጠርክ በኋላ ምን እንደምታደርግ አስበህበት ታውቃለህ?ምክንያቱም ያለው አንድ አለም ብቻ ነው።” ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ እሌክሳንደር በጣም ተከፍቶ፡- “በዚያ መልኩ አስቤ አላውቅም፤ ትክክል ነህ፡፡ መላውን አለም ከተቆጣጠርኩ በኋላ ምን አደርጋለሁ? ሌላ አለም ያለው የት ነው?” በማለት መልሷል። አለምን ከተቆጣጠረ በኋላ እንኳ አይምሮውን ጠፍሮ ከያዘው የበታችነት ስሜት ማምለጫ አይኖረውም፡፡ ሌላ አለም ቢኖርና ቢቆጣጠረው እንኳ ማምለጫ አይኖረውም፡፡ የበላይነት ስሜት የበታችነት ስሜት ነፀብራቅ ነው።

በኩራት የሚኮፈስና ሌሎች እንዲታዘዙት ሃይል የሚጠቀም ስው ሊታዘንለት ይገባል፤ ምክንያቱም በበታችነት ስሜት እየተሰቃየ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ የአይምሮ ጭንቀት ሳቢያም የበላይ ለመሆን በሚደረጉ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ተካፋይ ይሆናል።

የበታችነት ስሜት በሽታ ነው፤ ይህን የበታችነት ስሜት ለመደበቅ የሚመጣው የበላይነት ስሜት ደግሞ የባስ በሽታ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ መድሃኒቱ ከበሽታው ይልቅ አደገኛ ነው።

ምንጭ ፦ የንቃት ፀሀይ (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ መርሻ በነበሩ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
3.5K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 11:54:27 የሰው ልጅ ሶሻል ሚዲያን ፈጠረ፥ በሰው የተፈጠረው ሶሻል ሚዲያም ሰውን አፍርሶ እንደ አዲስ መስራት ጀመረ !

ፌስቡክ በአንድ ወቅት ስሜት የሚሰጥ ጥናት አደረገ። በጥናቱ መሰረት በፌስቡክ አጠቃቀም የሰዎችን ስነልቦና መረዳት ይቻላል። ያውም ሪአክት ብቻ በማጥናት ከቅርቦቻችን ሰዎች በላይ ፌስቡክ ያውቀናል!

እንዲህ ነው፤ አስር ፖስት ላይ ያለንን ሪአክሽን በመተንተን ከስራ ባልደረባ በላይ ስለእኛ ፌስቡክ ይናገራል። በ150 ፖስቶች ላይ የሰጠናቸው ላይኮችን በማየት ደግሞ የቅርብ የሚባሉ ጓደኞቻችን ስለኛ ከሚያውቁት በላይ ፌስቡክ ስለኛ ያውቃል። እጅግ የጠበቀ ግኑኝነት ያላቸው ባለትዳሮች ስለ ትዳር አጣማሪያቸው መናገር ከሚችሉት በላይ ፌስቡክ ስለ እነሱ ይናገራል። ይህን ለማድረግ 350 ፖስቶች ላይ የተሰጡ ላይኮች ብቻ ለፌስቡክ በቂ ነው።
እጅግ ጥቂት በሚባሉ ላይኮች ብቻ ከቅርብ ጓደኛ እና ቤተሰብ በላይ ፌስቡክ  ግለሰቦችን የሚረዳበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

ተወዳጁ ፀሐፊ ዮቭል ኖሃ ሃራሬ 'Homo deus' በሚል መፅሐፉ አይን ገላጭ ሃሳቦችን አስፍሯል። የአሜሪካ ምርጫ ከመደረጉ በፊት ፌስቡክ ማን እንደሚመርጥ፥ እያንዳንዱ ሰው ማን ፕሬዝዳንት እንዲሆን እንደሚፈልግ በዝርዝር ያውቅ ነበር። ይህን ያወቀው የሰዎችን ሚስጥራዊ መረጃ በመበርበር አይደለም። ይልቅ ሰዎች ለፖስቶች የሚሰጡትን ላይክ በማየት እንጂ! ሰዎች ላይክ የሚያደርጉትን በማወቅ የፖለቲካ ዝንባሌያቸው፥ ርዕዮተ አለማዊ ምርጫቸው ወዘተ ታውቋል። ይህ ብቻ ሳይሆን ምን አይነት አካሄድ ምርጫቸውን እንደሚያስለውጣቸው ጭምር!

ጎግል በ2012 ላይ በእንግሊዝ ምድር የተፈጠረውን እንፍልዌንዛ ከ እንግሊዝ ጤና ሚኒስቴር ቀድሞ አውቋል።
ዛሬ ላይ አብዮት ከመፈንዳቱ በፊት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ይታወቃል። 'እንዴት?' ከተባለ ደግሞ ሰዎች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው  ስነልቦናቸውን ፥ ፖለቲካዊ አስተሳሰባቸው ፥ ህልማቸውን እና ስጋታቸውን የመግለፅ አቅም አለው።

እኔ እንዲህ አምናለሁ። ዝርዝር ድርጊቶቻችን ከዋናው ስነልቦናዊ ስሪታችን ይቀዳል። እያንዳንዷ ነጠላ ድርጊታቸን ማንነታችንን የመግለፅ ጉልህ አቅም አላት። እለታዊ ውሳኔያችን የህይወት ፍልስፍናችንን ያሳያል።
የፌስቡክ አጠቃቀማችን ማንነታችንን ይገልፃል። አየሩን የሞላው ወሬ አስተሳሰባችንን ያሰጠዋል።

የታሪክ ተመራማሪ ፀሐፊ እና ፈላስፋው ሃራሬ ማህበራዊ ትስስር ገፆች የሰዎችን ማንነት ከመግለፅ አልፎ ሰዎችን ወደ መግራት እና ወደ አንድ አቅጣጫ ወደ መምራት አድገዋል ይላል። ቲክቶክ ላይ በሚጫን የድመት ቪዲዮ ፥ ፌስቡክ ላይ በሚፖሰት አጭር ፅሁፍ፥ በዩትዩብ በሚጫን አዝናኝ ምስል ፥ ማንነታችን ገሃድ ይወጣል። ፈገግ እያልን ሚስጥራችንን እንገብራለን።

ይህ ብቻ አይደምለም! ቴክኖሎጂ ሁለት አስፈላጊ ነገሮችን እየነጠቀን ነው። "አሁን" እና "እዚህ" በቴክኖሎጂ ተፅዕኖ የተነጠቅናቸው ናቸው።

የፌስቡክ ማህበረሰብ የተገነባው ከፌስቡክ ውጭ ያለውን ህይወት ዋጋ በማስከፈል ነው!

ሰዎች አካል አለን። ባለፈው ክፍለዘመን ግን ቴክኖሎጂ ከገዛ አካላችን እያፋታን ነው። ለምንቀምሰው እና ለምናሸተው ነገር ትኩረት መስጠት ካቆምን ቆይተናል። ይልቅ በስማርት ስልኮች እና በኮምፒውተር ተውጠናል። ጎረቤታችን ከሚደረገው ነገር ይልቅ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለሚሆነው እንጨነቃለን።...

#ግራ_አጋቢው_ዘመን


@Tfanos
@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.2K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 15:59:31 ኢጎ የዘመናችን የሰዎች ማንነት


ኢጎ ማለት ከሀሳባዊ ፣ አካላዊ እና ስሜታዊ ቅርፆች ጋር የሚደረግ ቁርኝት ነው። በዘወትር አጠቃቀማችን "እኔ" ቀዳሚ ስህተትን ፣ ስለ ራስ የተሳሳተ አረዳድንና ሐሳዊ ማንነትን ያነገበ ነው። ይሄ ታዲያ ኢጎ ይባላል።

ኢጎ ሁልጊዜ ከቅርፅ ጋር ቁርኝት ሲሆን ፣ እራስን በሆነ ቅርፅ መፈለግ ፣ ፈልጎም ማጣት ነው። ብዙዎች አሁን ድረስ ከማያቋርጥ ፣ ተደጋጋሚና እርባና ቢስ የሀሳብ ጅረት ጋር ሙሉ በሙሉ የተቆራኙ ናቸው። ከሀሳባቸዉና ተከትሎ ከሚመጣዉ ስሜት ዉጪ እኔ የሚባል ነገር የላቸዉም። በመንፈሳዊነት አለመንቃት ትርጉሙም ይኸዉ ነው። በአእምሮአቸው ውስጥ የማያቋርጥ ድምፅ እንደሚመላለስ ስትነግራቸው ፣ ላለመቀበል ብስጭት ብለው "የምን ድምፅ?" ይሉሀል። በርግጥ ድምፁ የማይመለከቱትና የሚያስበው አእምሮአቸው ነው ፤ ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠራቸው አንድ አካል አድርገህ  ልትወስደው ትችላለህ።

❖ የኢጎ ይዘትና መዋቅር ፦ የኢጎ መነሻ አእምሮአችን ሲሆን ኢጎአዊ አእምሮአችን ሙሉ በሙሉ በትናንትናችን የተቃኘ ነው። ቅኝቱም በሁለት የተገመደ ሲሆን ይዘትንና መዋቅርን ያጠቃልላል። መጫወቻው ስለተወሰደበት በጥልቅ ስቃይ የሚያለቅሰውን ህፃን ጉዳይ ብንመለከት ፣ መጫወቻው ይዘትን ያመለክታል። በሌላ ይዘት ፣ በሌላ መጫወቻ ወይም እቃ ሊተካ ይችላል። የምትቆራኝበት ይዘት ፣ በአካባቢህ ፣ በአስተዳደግህ እና በዙሪያህ ባለው ባህል የተቃኘ ነው። የአንድን ሰው ማንነት ለማጠናከር ሲባል ከነገሮች ጋር የሚደረግ ያልተስተዋለ ቁርኝት ፣ በኢጎአዊ አእምሮአችን መዋቅር ላይ የተመሰረተ ነው። 

ኢጎን ህያው የሚያደርገው መሰረታዊ የአእምሮአችን መዋቅር  'መቆራኘት'  ነው። ለምሳሌ

ከቁሶች ጋር ቁርኝት ፦ በዚህ ቁሳዊ አለም አካላዊ ማንነታችን ይኖራልና እቃዎች አስፈላጊና ሊተዉ የማይችሉ የሕይወታችን ክፍሎች ናቸው። ነገር ግን ቁሶችን ለማንነታችን ማጠናከሪያ አልያም እራሳችንን በእነርሱ ውስጥ ለማግኘት ከሞከርን በእርግጥ ልናወድሳቸው አይቻለንም። የዘመናችን አንዱ በሽታ ንብረትን ማባዛት የሆነው ለዚህ ነው። የሆንከውን ህይወት ማጣጣም ሳትችል ስትቀር ፣ ህይወትህን በነገሮች ለመሙላት ትባክናለህ። የተወሰኑ የያዝካቸው ንብረቶችህ የተፈላጊነት ወይም የታላቅነት ስሜትን  በጥቂቱም ቢሆን ይጭሩብሀል? እነዚያን ነገሮች ስታጣ ነገሮቹ ካላቸው ሰዎች አንፃር ትንሽነት ይሰማሀል? ለማንነትህ ያለህን ዋጋ ለመጨመር ስትል ያሉህን ንብረቶች በየአጋጣሚው አውጥተህ ለማሳየት ትሞክራለህ?

ከአካልህ ጋር ቁርኝት ፦ ከቁሶች ውጭ ያለው ሌላው መሰረታዊ ቁርኝት ከ "የእኔ "አካል ጋር የምታደርገው ቁርኝት ነው። አካል ወንድ ወይም ሴት ነው። ስለዚህ ወንድ ወይም ሴት መሆን የብዙዎችን የማንነት ስሜት ለመፍጠር ጉልህ ድርሻ ይወስዳል።
በምዕራቡ አለም ደግሞ ማንነቴ ነው ብለህ ለምታስበው ስሜት ጉልህ ድርሻ የሚወስደው የአካልህ ሁኔታ ነው። ጥንካሬው ወይም ደካማነቱ ፣ ከሌሎች አንፃር ያለው ውበት ወይም አስቀያሚነት ነው። ለብዙዎች ለማንነታቸው ዋጋ ያለው ስሜት ፣ ካላቸው አካላዊ ጥንካሬ ፣ መልካም ገፅታ እና ውጫዊ ገፅታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው። ብዙዎች አካላቸው አስቀያሚ ወይም ጎዶሎ መስሎ ስለሚታያቸው የኮሰሰ የማንነት ስሜት ይሰማቸዋል።

ምንጭ ፦ አዲስ ምድር (ኤክሀርት ቶሌ)
ተርጓሚ ፦ ኦስማን መሐመድ
                 
                   ይቀጥላል

@Zephilosophy
@Zephilosophy
5.7K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 21:52:56 መቼ ነው ማመፅ ያለብህ-ሆብስ

ራስህን በዋሻ የሚኖር የጥንት ሰው አድርገህ አስበው፡፡ በየለቱ ሚዳቋ በማደንህም ፊትህ በደስታ ተሞልቶ ወደ ልጆችህ እና ወደ ሚስትህ ትመለሳለህ። ሕይወትህን በእንዲህ አይነት ሁኔታ እየመራህ ሳለ፣ አንድ ቀን በመንገድህ ላይ ካንተ የገዘፈ ሰው ያጋጥምሃል፡፡

“ርቦኛል፤ ካደንካት ሚዳቋ ጥቂት አምጣ ይልሃል... ትደነግጣለህ፤ ፍዳህን አይተህ ነው ይህቺን ሚዳቋ ያደንካት፡፡
“ለምን?” አልከው፡፡
“አንተን እና ቤተሰቦችህን ከሌላ ጉልበተኞች እጠብቃለሁ፤ አንተም ምግብ ትሰጠኛለህ”

ሆብስ ይህን የማህበረሰብ #ኮንትራት ሲል ይጠራዋል፡፡ አሁን ላይም መንግስት ብለን የምንጠራው ተቋም የተወለደው በዚህ መንገድ ነው።

መንግስታት ከመመስረታቸው - በፊት ያለው የሰው ልጆች ሕይወት እጅግ አስፈሪ እና አዳጋች ነበር። ሰውም ከመጥፎነት የሚጋርደው ኃይል ከሌለው እና ያሻውን እንዲያደርግ ከተለቀቀ፣ ለፍቶ ከመብላት መስረቅን ያስቀድማል፡

ደህንነቱ ባልተጠበቀ ቦታ ላይ መኖር አስቸጋሪ ነውና፣ ሰዎች እንደ ማህበር የሚጠብቃቸውን እና ከግለሰቦች በላይ ኃይል ያለውን አካል ከመሃላቸው ይሾማሉ፡፡ አዎን መንግስት ካለ፣ ልክ እንደ ሌሎች እንስሳዎች ሁሉ ደስ እንዳለን የመስረቅም ሆነ የመገዳደል ነጻነት አይኖረንም፤ ሆኖም ንብረታችን እና ደህንነታችን እንዲጠበቅ ያደርግልናል። ሆብስ ይህ ነጻነት እና ምቾትን ይሰጠናል ይለናል - ለምሳሌ ስራ መስራት  ስንፈልግ ቤታችንን ዘግተን መውጣት እንችላለን፤ ለሰራነው ስራም በእርግጠኝነት ደሞዝ እንደምንቀበል እናውቃለን፡፡ ይህም እንድናድግ ይረዳናል፡፡

የማህበረሰብ ኮንትራት በማህበሩ አካል በሆኑ ሰዎች መሃል የሚፈረም ስምምነት ነው:: በፊርማችንም #ከነጻነታችን ቀንሰን እንደምንሰጥ ቃል እንገባለን፤ በሰጠነውም ነጻነት ልክ ደህንነትን እና ምቾትን እናገኛለን፡፡ የብዙሃን ድምጽም ከግለሰቦች ድምጽ በላይ ይሰማል።

ሆብስ መንግስት ቢያስከፋንም ትዕዛዙን አልቀበልም ብለን ማመጽ አንችልም ይለናል። ምክንያቱም ለእኛ ባይመቸን እንኳ ለብዙዎች ልክ ነውና፤ ይህንን ኮንትራት መቅደድ የለብንም፡፡ በአንጻሩ ጆን ሎክ እና ዣን ዣክ ሩሶ ይህን የማህበረሰብ ኮንትራት ቀድሞውኑ መንግስት ካፈረሰው፣ ህዝቦች አመጻን ማስነሳት አለባቸው ይሉናል፡

አንተ እና መንግስትህ ስለምን ነገሮች ተፈራርማችኋል? መቼ ነው መንግስትህ ቃሉን የሚያፈርሰው? መቼስ ነው ማመጽ ያለብህ?


ምንጭ-ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
5.9K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 09:46:55 የባህል ጦርነት -አዶርኖ

የምትስማው መዚቃ፣ የምታያቸው ፊልሞች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እና ሌሎች የትርፍ ጊዜ መዝናኛዎች ይዘታቸው ተመሳስሎብህ አያውቅም? ገና ፊልሙን ሳትጀምረው መጨረሻውን ገምተህ አታውቅም? ይህ ለምን ሆነ? የፊልሞቻችን፣ የመዚቃዎቻችን መመሳሰል ከየት ተጀመረ?

ቴውዶር አዶርኖ የሚባል አንድ ፈላስፋ ነበር በዘመናዊው ዓለም የካፒታሊዝም ስርዓት ውስጥ ያለውን የስነ-ልቦና ችግርን አጥንቷል። ካፒታሊዝም ከኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ድርሻው በተጨማሪ የራሱ የሆነ ባህልም እየፈጠረ እንደሆነ ይገልፃል። አዶርኖ ካፒታሊዝም ባህልን ይመርዛል ሲል ያስረዳናል - ካፒታሊዝም ባህልን ለመመረዝ የሚጠቀመው መንገድ የትርፍ ጊዜያት መዝናኛዎችን ነው ይለናል፡፡ እነዚህን መዝናኛዎች በአንድ ጠቅልሎ የባህል ኢንዱስትሪ (The culture Industry) ብሎ ይጠራቸዋል፡፡

ዝቅተኛው ማህበረሰብ ትርፍ ጊዜውን ምን ላይ እያዋለው ነው? መጠጥ እየጠጣ ወይስ አስቂኝ ፊልሞችን እየተመለከተ?

- አዶርኖ ትርፍ ጊዜያችንን ሃብታሞች ምን ሲሰሩ እና ሲበሉ እንደሚውሉ በቴሌቪዥን እያዩ በመዋል አልያም እንቶ ፈንቶ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያዎች ወሬዎችን እየሰሙ የሚታለፍበት የፈንጠዝያ ጊዜ አይደለም ይለናል፡፡ ይልቁኑ ትርፍ ጊዜያችንን የአእምሯችንን አስተሳሰብ እና የሕይወት ደረጃ ሊቀይሩልን የሚችሉ ተግባራትን በመፈጸም ማሳለፍ ይኖርብናል። መጽሐፍትን ማንበብ፣ ለመነቃቃት የሚጠቅሙንን ሙዚቃዎች መስማት፣ አዲስ አስተሳሰብ ሊያስገኙልን የሚችሉ ፊልሞችን በመመልከት ማሳለፍ እንችላለን።

ሆኖም በዘመናዊው ዓለም ላይ ይለናል አዶርኖ፤ ትርፍ ጊዜያችን በካፒታሊስቶች እጅ ወድቋል። አዲስ የሆነ ባህልም ተፈጥሯል። ዘመናዊ ፊልሞች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ ዘፈኖች፤ ማህበራዊ ሚዲያዎች(ፌስቡክ ፣ቲክቶክ)  ሁሉም ዓለምን ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ እየሳቧት ነው፡፡ ሃብታሞች ደሃውን በማይጨበጥ የውሸት ዓለም ውስጥ እየዘፈቁት ነው:: ፊልሞች በውብ ህንጻዎች ውስጥ ይቀረጻሉ፤ ሙዚቃዎች ስለ ሴት ፍቅር ብቻ ሆነዋል... ደስታንም የወሲብ ሌላኛው ስም አድርገውታል፤ ብዙ ሰዓቶቻችንን በማይመለከቱን የዓለም ዜናዎች ላይ እናሳልፋለን፤ የሕይወት ጥያቄዎቻችንን በራሳችን ጥበብ ለመመለስ ከመሞከር ይልቅ “አነቃቂ ንግግሮችን” መመልከት ይቀናናል፡፡ ዘመናዊው ዓለም ፋታ አሳጥቶ በራሳችን እንዳንወስን አድርጎናል፡፡

አዶርኖ ከዚህም ሲብስ የህጻናት ፊልም አምራች የሆነውን ታዋቂውን ዋልት ዲዝኒ እጅግ አደገኛ አሸባሪ ይለዋል፡፡ -አፍሪካውያንም የራሳቸውን ባህል ጥለው ሁለ ነገራቸው ነጮችን እየመሰለ መጥቷል፤ ራሳቸውም አውሮፓውያኑ የነበራቸውን ባህል እና ወግ ጥለው ወደ አንድ ወጥ ማህበረሰብነት እየተቀየሩ ነው፡፡
ቀስ በቀስ ሳይታወቀን እየገደሉን ነው። የባህል ኢንዱስትሪው በራስ ወዳድ እና ስግብግብ ነጋዴዎች እጅ ወድቋል። በራሱ የሚያስብ እና አመጸኛ የነበረውን ትውልድ አልፈስፍሰውታል፡፡ ጠልቆ ከመመራመር ይልቅ መፍትሄን ከሌሎች የሚጠብቅ ለማኝ ትውልድን ፈጥረዋል:: ይህ በባህል ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው፡፡ ጥበብ ሊቃወማቸው ይገባል ፤ ጥበብ ካፒታሊስቶች እንደፈለጉ የሚዘውሩት ሜዳ መሆን የለበትም ይለናል አዶርኖ፡፡

ምንጭ-ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.9K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 15:16:32 ገንዘብ እና ፍቅር
======
ኦሾ

ሰውን ለማፍቀር ያልቻሉ ሰዎች የሚያፈቅሩት ገንዘብን ነው። ምክንያቱም ገንዘብ ነገሮችን የራስ የማድረጊያ መንገድ ነው።ገንዘብ ለነገሮች(ለቁሶች) ያላችሁ ፍቅር ነው።ገንዘብ ሞትን ለማራቅ የምትጠቀምበት መከላከያችሁ ነው።ሕይወትን ለመቆጣጠር የምትሞክሩበት መሳሪያችሁ ነው።

ማፍቀር ሲሳንህ ገንዘብ ትሰበስባለህ ታከማቻለህ ሰውን ማፍቀር ትፈራለህ። ስለዚህም ከብር ወይም ከዶላር ፍቅር ይይዘሀል። ንፋግ ሰው አይተህ አታውቅምን? ገንዘብ ሲያይ ከዓይኖቹ የሚንፀባረቀውን ብርሃን ልብ ብለሀል ልክ ቆንጆ ሴት እንዳየ ያህል እሰከሚመስል ዓይኖቹ ቦግ ብለው ያበራሉ።ብሮቹን ፍቅረኛውን ያገኘ ያህል ይዳስሰችዋለህ ፤ገንዘብ አምላኩ ጣዖቱ ሆኗል።

በርግጥ ገንዘብ ሀይል ነው።በገንዘብህ ብዙ ነገሮችን መግዛትና የራስህ ማድረግ ትችላለህ ነገር ግን ፍቅርን ለመግዛት አያስችልህም ፤ ወሲብ መሸመት አያዳግትህም ይሆናል።ወሲብ የሸቀጥ እቃ ልታደርገው ትችላለህ፤ ፍቅርን የሸቀጥ እቃ ልታደርገው አትችልም። ምቾት ሊሰጡህ የሚችሉ አካላዊ ፍላጎቶችህን ልታሟላበት ትችላላችህ ፤ ነገር ግን ፀሎትን መግዛት አትችልም። አምላክህ ጋር በአለህ ገንዘብ ልትገናኝ አትችልም።

ስለሆነም ገንዘብ ሊገዛ የሚችለው ነገር ሁሉ ተራ (የተለመደ) ነው። ሀይማኖትን ሊገዛ አይችልም ሀይማኖት  ከቁሶች ባሻገር በአይን የማይታይ ጥልቅ እና ረቂቅ የሆነ ነገረ ነው።በገንዘብ ብቻ ሊገዙ የሚችሉን ነገሮች ብቻ የምታውቅ ከሆነ ሕይወትህ ባዶ ሆኖ ይቀራል። የምታውቀው የሚሸጡ ነገሮችን ብቻ ከሆነ ሕይወትህ እርባና ቢስ እና ከንቱ ይሆናል። ግንኙነትህ ከሸቀጥ ዕቃዎች ብቻ ይሆንና ይቀራል። በገንዘብ ከማይገዙ ነገር (ፍቅር ፣መልካምነት...) ጋር መጎዳኘትህን ታቆማለህ።

ገንዘብን የህይወት የመጨረሻ ግብ አታድርገው። የዚች አለም ማለቂያ የሌለው ሀብት የሚገኘው ከፍቅር እና ከአምላክ  ነው። ገንዘብን ተጠቀምበት በራሱ መልካም ነው ነገር ግን ፍቅርን ከገንዘብ ለማግኘት አትሞክር።ም/ቱም ፍቅር የውስጣችሁ ህልውና ነው።እ/ርን ከገንዘብ ዘንድ አትፈልገው እርሱ ከአለማትም በላይ የላቀና ያለፈ ነው።

ለአንተ ፍቅር ብቻ ነው ነፃነትን ሊያቀዳጅህ የሚችለው። ፍቅርን ደግሞ ነፃነትን የሚያጎናጽፍህ ለማፍቅር ዝጉጁ ስትሆን ብቻ ነው።ካፈቀርክና አንተም በምላሹ መፈቀርን ካገኘህ ፍቅር ዘውድህ ይሆናል።የገዛ ራስህም ንጉሰ ነገስት ያደርግሃል።
በአንተ ላይ ፍቅር  ካልሰፈረብህ ፤ ፍቅርን በውስጥትህ ካላበበ ፤ እንደምን የተዋብክ ትሆናለህ አስቀያሚ ነው የምትሆነው።ዝግ የሆነ ነገር ትሆናለህ።   ስስታም ሰዎች ፈሪ ናቸው።ም/ቱም ሁሉም ብሩን የሚጋራቸው መስሎ ስለሚታያቸው ከሰዎች ጋር መቀራረብ አይፈልጉም ።ቁሳቁሶችን የሚያፈቅሩ ሰዎች ራሳቸው ቁሳቁሶች ይሆናሉ።ሙት ዝግ በውስጣቸው ምንም የሚነዝር ፤ ደስ የሚያሰኝ እርካታ የላቸውም።ልብ ምቶቻቸውን አጥተዋል።የሚኖሩት ኑሮ መካኒካዊ ይሆናል።ፍቅርን እንደ ጦር የሚፈሩት ሰዎች ፤ ገንዘብን የተመለከተ ራስ ወዳድ(ሁሉም ነገር የኔ ነው ባይነት )  ስሜት ያድርባቸዋል።

ገንዘብ መንገድ እንጂ ፍፁም ግብ አይደለም። ገንዘብን የሚያነፈንፉ ሰዎች ግን ግባቸው ገንዘብ ነው።የሚፀልዩትም ፀሎት እንኳን ስለገንዘብ ነው።ፀሎትም ለነሱ ወደ ገንዘብ መዳረሻ መንገድ ነው።

እኔ የገንዘብ ተቃዋሚ አይደለሁም። ገንዘብ መልካም መገልገያ ነው። ገንዘብህ ካለህ ከድሀው በተሻለ ለራስህ የሚሆን በቂ ጊዜ ይኖርሃል። ስለምትበላው እና ስለምጠጣው ነገር አትጨነቅም። በቤትህ የራስህ የሆነ አነስተኛ የፀሎት ቦታ ይኖርሃል ወይም የአትክልት ስፍራ ይኖርሃል።ገንዘብ ካለህ ሌሎችን ልትረዳ የምትችልበት አቅም ይኖርሃል።
ገንዘብን እንደ ሀጥያት እና ሴጣን የሚቆጥሩ ሀይማኖቶች አሉ፤ ገንዘብ ላይ ምንም ስህተት የለም።ገንዘብ ፍቅርን እና አምላክን እንዲሰጣችሁ  መጠበቃችሁ ነው ችግሩ ። ችግራችሁ ገንዘብን የምታዩበት ምልከታ ነው።
እያንዳንዱ ነገር በእናንተ የህልም መጠን ሳይሆን በገዛ ራሱ አቅም ተጠቀሙበት። በዚህም ጊዜ ጤናማ እና የተረጋጋ ተፈጥሮአዊ ትሆናላችሁ።


@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.9K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 15:15:10 ፈጣሪ ወዴት አለ?
በሩሚ

በክርስቲያን መስቀል ላይ እሱን ለማግኘት ሞከርሁ ፣ ግን እርሱ እዚያ አልነበረም ፡፡ ወደ ሂንዱዎች ቤተመቅደስ እና ወደ ድሮው ፓጋዳ ሄድኩ ፣ ነገር ግን የትም የት ዱካ ማግኘት አልቻልኩም ፡፡

ተራሮችን እና ሸለቆዎቹን ፈልጌ ነበር ነገር ግን በከፍታዎቹም ሆነ በጥልቁ ውስጥ እሱን ማግኘት አልቻልኩም ፡፡
በመካ ወደ ካባ ሄድኩ ፣ እሱ ግን እዚያ አልነበረም ፡፡

ምሁራኖቹን እና ፈላስፋዎቹን ጠየቅኳቸው ፣ ግን እሱ ከሚረዱት በላይ ነበር።

ከዛ ወደ ልቤ ተመለከትኩ እና እሱን አገኘሁት እዚያ ነበር ፡፡ ሌላ የትም ቦታ ሊገኝ አልቻለም ፡፡

በምንም እመን በምን ፈጣሪክን የምታገኘው ልብክ ውስጥ ነው።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.0K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ