Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የሰርጥ አድራሻ: @zephilosophy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.78K
የሰርጥ መግለጫ

"Strong minds discuss ideas, average minds discuss events, weak minds discuss people."
Rinu Ruzvelt

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-01-04 22:26:59 ፍልስፍና ምንድነው?

ምንጭ ፦ የፍልስፍና አፅናፍ
ፀሀፊ ፦ አለማየሁ ገላጋይ

ለፍልስፍና ቁርጥ ያለ ፍቺ ለመስጠት አዳጋች የሚያደርገው ተገለባባጭ ርዕሰ-ጉዳይና ዓላማ ላይ መቆየቱ ነው፡፡ በአንድ በኩል ነገሮች ተፈጥሯዊ
ባህርይ ላይ መሰረታዊ እውቀት የማስጨበጥ ዘርፍ ተደርጐ ይታሰብ እንዳልነበር ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ መልካም ኑሮ መመሪያም ይታይ ነበር፡፡ በመካከለኛው ዘመን ፍልስፍና እንደ ሃይማኖታዊ መቀሰቻ ድጋፍ ተደርጐ ተወስዶ ነበር። አሁን ደግሞ ብዙዎች እንደተፈጥሯዊና ማህበራዊ ሳይንስ ተራዳ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡

«ፍልስፍና» ቃሉ ‹‹የጥበብ ፍቅር»  (love of wisdom) ማለት ነው። ከዚህ ስንነሳ ፍልስፍና የጥሬ እውቀት ማካበቻም ሆነ ማስተላለፊያ ዘርፍ ሳይሆን በጥበብ ስለጥበብ የሚደረግ ከፍተኛ መነሳሳት እና መጠየቅ ነው:: ሶቅራጥስ እንዳመላከተው ፈላስፋ ጥበብን ለማፍቀር እንጂ የራሱ
ለማድረግ መጠየቅ የለበትም።

ሶቅራጥስ፣ ምርመራችን የትም ያድርሰን የትም፣ ያልተመረመረ ህይወት እርባና የለውም በማለቱ የፈላስፎችን መንገድ እንደጠረገና እንደደለደለ ተደርጐ ተቆጥሮለታል፡፡ አባባሉ ለፍልስፍና የመመርመር ግንዛቤና የመጠየቅ ባህርይ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ በተጨማሪም የመልካም ህይወት ስነ-ምግባራዊ ግንዛቤን መልሶ መላልሶ በፍልስፍና የመመርመር ትኩረትን እንደሚያሻ ይጠቁማል፡፡

አርስቶትል ታላላቅ የሚባሉ ስራዎችን በማጥናት የፍልስፍናን ጭብጦች ከፋፍሎ ለማስቀመጥ ሞክሯል፡፡ ከዚህ ተነስቶ ፍልስፍናን በብዙ ዘርፎች ከፋፍሏል፡፡ አርስቶትል <‹ቀደምቱ ፍልስፍና›› ለሚለው «ዲበአካል» (Metaphysics) የመጀመሪያውን ስፍራ ይሰጣል፡፡ ዲበ አካላዊነት የመሰረታዊ መርህ እና ምንጭም እውቀት ስለሆነ ነው ቅድሚያውን የሰጠው። ለዲበ አካል ትኩረት መስጠቱ በፍልስፍናው ዘርፍ የሚጫወተው ከፍተኛ ሚናም ይኖረዋል።

ወደ ዘመናዊነቱ ስንመጣ ሙሉ ትኩረት የሚያገኘው የእውቀት ምንነትና እውቀትን ስለሚያውቀው አእምሮ መዋቅር ነው᎓᎓ ኢማኑኤል ካንት የዚህ ዝንባሌ በር ከፋች ነበር፡፡ ካንት ለተፈጥሮ ሳይንስ ግልጋሎት በሚውለው በ«ዳሰሳዊ እውቀት» (empirical knowledge) እና በምክንያታዊ እውቀት» (Rational knowledge) መካከል ያለውን ልዩነት የሚያሳይ ፍልስፍና በማስተዋወቅ የዘመናዊውን አዲስ አቅጣጫ በር ከፈተ፡፡ በዚህም አሁን ድረስ ስለፍልስፍና እና ሳይንስ አንፃራዊ ሚና የጦፈ ክርክሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ በግልፅ መመልከት እንደምንችለው የዘመናችን ሰዎች መሰረታዊ እውቀትን የሚሹት ከፍልስፍና ሳይሆን ከሳይንስ እየሆነ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ በጊዜያችን ጠንካራ አስተሳሰብ እየሆኑ ከመጡት ዘመናዊ ፍልስፍናዎች ውስጥ «ተጨባጫዊነት» (Positivism) አንዱ ነው፡፡ በዚህ ፍልስፍና መሰረት «ዳሰሳዊ ሳይንስ» (empirical science) ብቻ የትክክለኛ እውቀት ምንጭ ተደርጐ ሲወስድ የፍልስፍና አስተዋፅኦ ይሄንኑ ሳይንስ መተንተንና መሔስ ብቻ እንደሆነ ተደምድሟል።

በእኔ አመለካከት ፍልስፍና የጥበብን ልዕልና የሚያስመሰክሩ የነጠሩ እውቀቶች የሚገኙበት ዘርፍ ነው፡፡ ስለሰው ልጅ፣ ስለአለምና ስለፈጣሪ ተፈጥሮ የሚያትቱ ጥበቦች ከፍልስፍና ይቀርብልናል:: ስለ መልካም ህይወትና ጥሩ ማህበረሰብ የሚተነትን ጥበብም የሚገኘው ከፍልስፍና እንደሆነ መዘንጋት አይገባም፡፡ የነገሮችን ተፈጥሮና የህይወትን ፍፃሜ በተመለከተ መሰረታዊ ጥያቄዎች ተነስተው ይስተናገዳሉ፡፡ ስለዚህ ከተውጠንጣኝነትም ሆነ ከተተግባሪነት አንፃር ሲመዘን እጅግም ከሚያስፈልገውና ሰው ሰራሽ ከሆነው ሳይንስ ይልቅ ፍልስፍና እጅግ የላቀ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ከዚህ አመለካከት አንፃር ካየነው ፍልስፍና የሰው ልጆች ሁሉ ግድ ነው፡፡ የልሂቃን ጉዳይ አይደለም፡፡ ውስብስብ አሰራርን ግድ አይልም፡፡ የከፍተኛ ስሌት ወይም የውስብስብ መሳሪያ ጥገኛም አይደለም፡፡ ፈላስፋ ብርቅዬ የሚሆነው በሌላ ሳይሆን የሐሰሳ ጥበቡ ሙያ ሙሉ ቀልብና ተከታታይ ጥረት ፈላጊ በመሆኑ ብቻ ነው፡፡ ለፈላስፋነት ጥሪ ማንኛውም ሰው ምላሽ መስጠት ይችላል፡፡ ምላሽ ሰጪው የሚያስፈልጉት እግዚአብሔር የሰጠው አእምሮና ፍፁማዊ እውነትን ለማወቅ መሻት ብቻ ናቸው፡፡

ፍልስፍና እንደ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የቤተ ሙከራ ተረጋጋጭ ሳይንስ አይደለም፡፡ ተውጠንጣኝ ምክንያታዊ ሳይንስ ነው ብንል ያስኬዳል። ልክ እንደ ሂሳብ ደርዝ-ደርዝ ባለው እሳቦት ውስጥ በትንተና እየበለፀገ ይመጣል፡፡ የሂሳብ ሊቅም ሆነ ፈላስፋ ከተለምዷዊ እውቀቱ ውጭ የተጨባጭ ማስረጃ ጥገኛ አይደለም፡፡ ሁለቱም ሐሰሳ እውቀታቸውን ከወንበራቸው ላይ ሳይነሱ ያከናውኑታል፡፡ በዚህም ሁለቱም የወንበር ላይ አሳቢዎች (Thinkers) ናቸው::

ፍልስፍና፤ ስነ-ፅሁፍ፣ ስነ ጥበብ ወይም ኪነጥበብ የሚወክለው ቱባ ጥበብ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከቱባ ጥበብ ይልቅ ነፃውን ጥበብ በተለይም የክርክር ጥበብን ይጠቀማል፡፡ ይህ ግን መንፈሳዊ መዛግብትን እያጣቀስ ክርክር ከሚገጥመው ሃይማኖታዊነት ፈፅሞ የተለየ ነውና ፍልስፍና መነሻው ሃይማኖታዊ መዛግብቶች ሳይሆኑ ተለምዷዊዎቹ ግንዛቤዎች ናቸው፣ በተለምዷዊነት ስር ፈዘውና ደብዝዘው ያሉትን እውነታዎች በሙላት እንዲያንፀባርቁ ማድረግ አንዱ የፍልስፍና ተልዕኮ ነው:: የዓለምን ግንዛቤ በማጥራትና ጠልቆ በመጓዝ ተለምዷዊነት ቀብሮ ያስቀራቸውን እውቀቶች ለአደባባይ ያበቃል፡፡

ፍልስፍና ከቅድመ ሳይንሳዊነት እጅግ የተለየ እንደውም ድህረ- ሳይንሳዊነት የሚንፀባረቅበት ዘርፍ ነው፡፡ ይህም ማለት አብዛኞቹ ፍልስፍናን በጭፍን እንደሚተገብር የቅድመ ሳይንስ መላምት መመልከታቸው ተገቢ አለመሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡ ፍልስፍና እንደታሪካዊ እውነታዎች ጠንካራ ከመሆኑም በላይ ከሳይንሳዊ ምርምሮች በፊት የተጀመረ ጥንታዊ ዘርፍ ነው፡፡ ከጥንታዊነት ባሻገርም ዘመን ሳይሽረው እስካሁን የቀጠለና ወደፊትም ምርምር ከሚያረጋግጠው ሳይንስ በላይ ለሆኑ ርዕሶቻችን ለመድረሻነት በማገልገል የሚታደገን እውቀታችን ነው፡፡ «ዳሰሳዊ ሳይንስ›> ያበቃበት ዘመን ላይ ደርሷል፡፡ ይህም የሚያመላክተው መጓዝ የሚቻለውን ያህል እንደተጓዘ ነው፡፡ ነገር ግን ፍልስፍና አሁንም በአፍላነት እድሜ ላይ የሚገኝ ባለተስፋ ነው፡፡ እድገቱን ለማጠናቀቅም በሺህ የሚቆጠሩ አመታት ከፊቱ ተነጥፈውለታል፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy
121 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 20:04:52 ጥያቄ፦ኦሾ ፣የምትነግረን ነገር በሙሉ እውነት ሆኖ ሳለ ስለምን ብዙኃኑ ይቃወሙሃል?

መልስ፦ትክክለኛ ምክንያት -የምናገረው እውነት መሆኑ ነው።እውነት አደገኛ ናት።በተለይ ሐሰተኛ የሆነ ተምኔታዊ ሕይወታቸውን በተዋቡ ሕልሞች ሐሰቶች እና አስደሳች በሆኑ ሀሳባዊ ሕልሞች በመኖር ላይ ለምገኙ በሙሉ እዉነት በርግጥም አደገኛ ናት።
እነዚህን መሰል ሰዎች እውነትን በጠላትነት ይመለከቷታል።ምክንያታቸው ደግሞ ዕድሜያቸውን በሙሉ ያመኑበትን ፣የኖሩበትን ሐሰተኛ አመለካከቶች ስለሚያፈርስባቸው ነው።
እውነት ማለት የሐሰቶች ሁሉ ሞት ናት።በተዋቡ ቃላት የተናገሩትን ሐሰቶች ጨምሮ የምትገድል ናት።
ብዙኃኑ ለምን ነበር ሶቅራጠስ ላይ የተነሡበት? ሃይማኖተኞችስ ለምን ነበር ኢየሱስን የተቃወሙት? የሁለቱም ጥፋት የብዙኃኑን እንቅልፍ እና ያማረ ሕልም መረበሻቸው ነበር።ማንም ቢሆን ከምቹ እንቅልፉ መቀስቀስ አይወድም።
              osho

@Zephilosophy
1.1K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 17:23:43 በዘመነ ሳይንስ የፍልስፍና እጣ ፋንታ ምንድነው?

ምንጭ ፦ የፍልስፍና አፅናፍ
ፀሀፊ ፦ አለማየሁ ገላጋይ

እስኪ መጀመሪያ ሳይንስ ሊያደርግና ላያደርግ የሚችላቸውን ነገሮች ለይተን እናውጣ፡፡ የሳይንስ ማዕከላዊ ትኩረቱና ነጠላ ግቡ የማያወላዳ መረጃ ማግኘት ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ በቁስ አካላዊና በማህበራዊ ጥናታቸው የሚታዩ ክስተቶችንና ለውጦችን ይመዘግባሉ ጠባያትን በትኩረት ይከታተላሉ፡፡ ህዋ ውስጥ ያለውን የፕላኔቶች እንቅስቃሴ በትክክል ለመረዳት ሙሉ ኃይላቸውን ይጠቀማሉ፣ የቁስ አካልን ውስጣዊ ሁናቴ የሰውነታችንን አሰራርና ማህበራዊ እንቅስቃሴን ሆነ ሰዋዊ ባህሪን በመመርመር እንዲህ ነው እንዲያ ነው ይላሉ።

የሳይንስ ዕውቀት አስፈላጊነቱ ምንድነው? እንግሊዛዊው ፈላስፋና ቀደምት ሳይንቲስት ፍራንሲስ ቤከን ይሄን ጥያቄ የሚመልሰው «ኃይል ይሰጠናል» በማለት ነው፡፡ ምን አይነት ኃይል? ሳይንስ በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ያሉ አንዳንድ ቁስ አካላዊና ማህበራዊ ምስጢራትን መርምረን እንድናውቅ ማስቻሉን ነው «ኃይል» ሲል ቤከን የሚገልፀው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንዳንድ መጠቀሚያ ቁሳቁሶች በሳይንስ አማካኝነት መፈብረካቸው የሰው ልጅ ህይወትን አቅልለው ፍጥነት ጨምረውለታልና ቤከን «ኃይል» ቢለው ተገቢነት ይኖረዋል፡፡ በምህንድስናው ሆነ በህክምናው ዘርፍ የተገኙ ዕውቀቶች ለጤናና ለኑሮ መሻሻል እንደ ዋነኛ መሸጋገሪያ ድልድይ ጠቅመዋል።

እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚያሻው ከሳይንስ የሚገኘው «ኃይል» ለኑሮ ማሻሻያና ለህይወት ማቅለያ ብቻ እንደማይውል ነው፡፡ ሰው ሰውን መግደያና አካባቢውን ማጥፊያ፣ ሰላማዊ ህይወቱን ማደፍረሻ... አድርጐ ከሳይንስ ያገኘውን «ኃይል» ስራ ላይ ያውለዋል፡ በሌላ አገላለፅ እኛ ሰዎች ሳይንስ የሚሰጠንን «ኃይል» ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ ነገር እንጠቀምበታለን ማለት ነው፡፡ የጥፋት ይሁን የመልካም ነገር ፍላጐታችንን እውን እናደረግ ዘንድ ሳይንስ ነገሮችን ያመቻችልናል፣ ሳይንስ በራሱ ምንም አይነት የስነ ምግባር ልኬት የሌለበት ልቅ ዘርፍ ነው ማለት ነው፡፡ ሰው በሳይንስ የሚያስፈልገውን ብቻ ሳይሆን የማያስፈልገውና መጥፊያውንም ነገር
ያገኛል፡፡

እንግዲህ አስተያየትህ ትክክል ሆኖ ሳይንስ ፍልስፍናን ሊተካ ይችል የነበረው ከሳይንስ የምናገኘውን ኃይል ለጥሩ ነገር ብቻ የምናውለው ቢሆን ነበር። በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች ፍልስፍናን ከሳይንስ ጋር እያወዳደሩ ፍልስፍና አስፈላጊ እንደሆነ ያስባሉ፤ ምክንያታቸው ግልፅ ነው:: በፍልስፍና የዕለት ተዕለት መጠቀሚያ ቁሳቁስ ማምረት ስለማይቻል ነው:: በእኔ አስተያየት ፍልስፍና ከሳይንስ በተሻለ ለሰው ልጅ አስፈላጊ ዘርፍ ነው፡፡ ምክንያቱም ሙሉ ትኩረቱን ትክክለኛ የህይወት አቅጣጫን ማፈላለግና መጠቆም ላይ በመጣሉ እንደ ሳይንስ ላይ ላዩን በማጫፈር ለመሸንገል አይሞክርምና ነው᎓᎓ ፍልስፍና ለህይወታችን አስፈላጊና የማይተካ ሚና አለው፡፡ ይሄንን ማሰሪያ ድምዳሜ እንዳብራራው ይፈቀድልኝ፡፡

ደስታ ምንድነው? የደስታ መገኛውስ? በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ያለን ኃላፊነት ምንድነው? እንዴት ያለ መንግስት ቢቋቋም ፍትህና ርትዕ ይሰፍናል? ምን አይነት ህገ መንግስት የህብረተሰቡን የጋራ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል? ነፃነት ምንድነው? የሰው ልጅ ነፃነት ውስጥ ምን አለው?... ለእነዚህና መሰል ጥያቄዎች በምንስጠው ምላሽ ማህበራዊ ደህንነታችንና የህይወት መስመራችን ይወሰናል፡፡ እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች ደግሞ ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉት በሳይንስ ሊሆን አይችልም:: አሁንም ሆነ ወደፊት ሳይንስ በእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ ተሳትፎ እንደማይኖረው የተረጋገጠ ነው:: ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ የፍልስፍና ብቻ ይሆናል፡፡ ጥያቄዎቹ በፍልስፍና ካልተነሱና ምላሽ ካልተሰጠባቸው ህይወታችን ዓለም ላይ ያለ አቅጣጫ መጠቆሚያ እንደሚንከላወስ መርከብ ይሆናል፡፡ ንፋስ በራሱ ወደፈለገበት የሚነዳው ኃይል አልባ መርከብ፡፡

የፍልስፍና ቅሪት ካለንና መርከባዊ ግዛቲቷ ጥቂት ኃይል ካመነጩች በፍፁም ከፍተኛ አደጋ ላይ ልንወድቅ አንችልም፡፡ ነገር ግን አንተም እንዳልከው በዚህ በአቶሚክ ዘመን በከፍተኛ ፍጥነትና ኃይል በሳይንስ የምንፈተለክ ከሆነ ትክክለኛውን  ከሐሰተኛው የህይወት መታጠፊያ በፍልስፍና ልንፈትሽ ይገባል፡፡ ያ ካልሆነ ምን ጊዜም አደጋው ፊት ለፊታችን የተጋረጠ ነው::

በእውነትና በሐሰት መካከል ያለውን ልዩነት የምንፈትሸው በፍልስፍና እንጂ በሳይንስ አይደለም፡፡ ከተፈጥሯችን ጋር የተስማማውን የኑሮ አቅጣጫን አብላልተን የምንደርስበት አሁንም በፍልስፍና እንጂ በሳይንስ አይደለም፡፡ ሳይንስ በቁስ አካል ላይ የሚያሳየውን ትጋት ፍልስፍና በህይወት አቅጣጫና በስነ ምግባር ላይ ያከናውነዋል:: እያንዳንዱ የእውቀት ዘርፍ ሌሎቹ የእውቀት ዘርፎች የማይደርሱበት የራሱ ጥያቄና ምላሽ አለው:: ለዚህ ነው በተለያየ መንገድ ሁሉም አይነት የእውቀት ዘርፍ ለሰው ልጅ አስፈላጊ ሆኖ የሚገኘው፡፡

በእኔ ምልከታ በየትኛውም ባህል ሆነ ስልጣኔ ውስጥ እጅግ አስፈላጊውን የሰው ልጅ ጥያቄ በመመለስ የተካነው ፍልስፍና እንጂ ሳይንስ አይደለም፡፡ በእርግጠኝነት ለሳይንስ ከፍተኛ ትኩረት በሰጠን ቁጥር የዚያኑ ያህል ፍልስፍና በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያስፈልገን ግልፅ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም በሳይንስ የበለጠ «ኃይል» ባገኘን ቁጥር በፍልስፍና የበለጠ አቅጣጫ ጠቋሚ ያሻናልና ነው፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.6K viewsedited  14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 14:52:51 ከፍቅር ወደ አፍቃሪነት

ምንጭ ፦ ነፃነት (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዘላለም ንጉሴ

ፍቅር ሁለት ፍፁም የተለያዩ እንደውም ሙሉ ለሙሉ ተቃራኒ ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ አንዱ ትርጉም ፍቅር በኢጎ በተሞላ ፍቅር ግንኙነት መልኩ ሲገለጽ እና ሌላው ደግም ፍቅር በራሱ ህልውና ይዞ ሲገኝ ነው:: ፍቅር ወደ ኢጎአዊ ፍቅር ግንኙነት በሚለወጥበት ወቅት ባርነት ይሆናል፡፡ ምክንያቱም የምንጠብቃቸውና የሚጠበቁብን ነገሮች እንዲሁም መረበሽ እና ፍርሀትን ይፈጥሩብናል:: ከሁለቱም ወገንም እኔ እበልጥ ስሜት ይመጣል፡፡ የኃይል እሽቅድምድም ይሆናል:: ኢጎአዊ የፍቅር ግንኙነት ትክክል አይደለም፡፡ ፍቅር ህልውና ይዞ ሲገኝ ግን ሙሉ በሙሉ የተለየ ነገር ይሆናል፣ ስታፈቅር ከፍቅር ሌላ የፍቅር ግንኙነት እየፈጠርክ አይደለም ማለት ነው:: ፍቅርህ እንደ አበቦች ጥዑም መዓዛ ይሆናል። ኢጎአዊ የፍቅር ግንኙነት አይፈጠርም፣ ይህን አድርግ፣ ባህሪህ እንዲህ ይሁን አይልህም፡፡ ከአንተ ምንም አይፈልግም። ያካፍላል። በማካፈሉም ምንም ሽልማት አይፈልግም፡፡ ማካፈሉ በራሱ ሽልማት ነው፡፡

ፍቅር ለአንተ እንደ አበቦች መዓዛ በሚሆንበት ጊዜ ታላቅ ውበት ይኖረዋል ከሰብዓዊነት በላይ የመጠቀ መለኮታዊ ነገር ይኖረዋል።

ፍቅር ብቻውን ከመጣብህ ምንም ልታደርገው አትችልም፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ አሳርን አያመጣም አንተም በማንኛውም ሰው እንድትታሰር አይፈቅድም።

ግን ከልጅነት አንስቶ ኢጎአዊ የፍቅር ግንኙነቶችን የመፍጠር ልምድ አለህ፡፡ ከማታውቀው ወንድ ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ትፈጥራለህ። አባትህ መሆኑን በፍፁም ርግጠኛ ልትሆን አትችልም፡፡

አንድ የሰዎችን መዳፎች በመመልከት ዕጣ ፈንታቸውን ስለሚተነብይ ሰው የሰማሁት ታሪክ አለ፡፡ በእጅ መዳፍ ንባብና በአስትሮሎጂ በመሳሰሉት እንዲሁም በእግዚአብሔርም የማያምን አንድ ወጣት ወደዚሁ ሰው ይሄድና፣ «ሳይንስህ ትክክል ከሆነ እጄን አንብብና አባቴ የት እንደሚገኝ ንገረኝ አለው፡፡»

አዋቂውም መዳፉን ተመልክቶ እንዲህ አለው «አባትህ አሳ እያጠመደ ነው::» ወጣቱ ኢአማኒ ሳቀ፡፡ «እኔ የምለው ይህንኑ ነው፤ የማይረባ ሥራ ነው:: አባቴ ከሞተ ሶስት ዓመት ሆኖታል፤ ዛሬ እንዴት አሣ ለማጥመድ ይሔዳል?

አዋቂውም ሲመልስ፣ «ይህ እኔን አያገባኝም፣ እውነቱ ግን ያ የሞተው ሰው አባትህ ያለመሆኑ ነው፡፡ ትክክለኛ አባትህ አሳ እያጠመደ ነው:: ወደ እናትህ ሂድና ጠይቃት፡፡ ታማኝና እውነተኛ ከሆነች የሞተው ሰው አባትህ እንዳልሆነ ትነግርሀለች:: አንተ ግን አባትህ ነው ስለተባልክ ከእሱ ጋር የአባትና የልጅ ፍቅር ግንኙነት ፈጥረሀል።

ሕይወታችሁ በሙሉ በብዙ ዓይነት ኢጎአዊ ግንኙነቶች የተሞላ ነው:: ይህ መሰል ግንኙነቶች ደግሞ እውነትም ይሁን ሀሰተኛ፣ እጅግ ውስብስብ የሆነ ስነ-ልቦናዊ ባርነትን ይፈጥራል። ወይ ሌላውን ባርያ ታደርጋለህ፡፡ ወይንም ራስህ ባርያ ትሆናለህ፡፡

ሌላው መታወስ ያለበት ነጥብ ደግም ራስህን ባርያ ሳታደርግ ሌላውን ሰው ባርያ ማድረግ አትችልም። ባርነት ባለሁለት ስለት ሰይፍ ነው:: አንደኛው የበለጠ ጠንካራ፣ ሌላው የበለጠ ደካማ ሊሆን ይችላል፣ ግን በሁሉም የፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ አንደኛው አሳሪ ሌላው ታሳሪ ይሆናል። ከእሱ አንፃር ሲመለከተው እሱ አሳሪው አንተ ደግሞ ታሳሪ ትሆናለህ:: የሰው ልጅ ይህን በመሰለ ሀዘንና ሰቆቃ የመኖሩ ዋነኛ ሀቅና ምክንያት መካከል አንዱ ይኸው ነው፡፡

ጥላቻ ደግሞ ከፍቅርህ የጠነከረ ግንኙነት ይፈጥራል ምክንያቱም ፍቅርህ ከአንገት በላይ ነው፡፡ ጥላቻህ እጅግ ጥልቅ ነው:: ጥላቻህን የወረስከው ከእነስሳዊነት ባህሪህ ነው:: ፍቅርህ ለመጪው ሕይወትህ ያለህ ብቸኛ እምቅ ኃይልህ ነው፡፡ እውን የሆነ ክስተት ሳይሆን ወደፊት ፍሬ የሚያፈራ ዘር ነው:: ጥላቻህ ግን ሙሉ በሙሉ በተግባር ላይ የሚገኝ፣ እጅግ የጎለመሰ ያለፈው የብዙ ሺህ ዓመት ታሪክህ ህያው ቅርፅ ነው:: የሚያድግበት ጊዜና ቦታ የነበረው። ለውጡ መከሰት የሚጀምረው ግን በሰው ልጆች ላይ ነው፡፡

ግን ማንንም እኔን ከመጥላት ማገድ አልችልም ስለዚህ ማንም ሰው እንዲያፈቅረኝ ማድረግ አልችልም፡፡ ልገልፀው የምችለው ነገር ቢኖር ጥላቻም ሆነ ፍቅር የግንኙነት መልክ በሚይዝበት ጊዜ ንፅሕናውን እንደሚያጣ ብቻ
ነው፡፡

ፍቅርህን ህልውናህ አድርገው፡፡ ፍቅር እንዲይዝህ ሳይሆን አፍቃሪ እንድትሆን ጣር፤ ፍቅር ባሪያህ ነው፡፡ ለአንተ ፍቅር የህልውናህ ጥፁም መዓዛ ነው፡፡ ብቻህን ብትሆን እንኳን በአፍቃሪ ኃይል ትከበባለህ፡፡ የሞተ ነገርን ለምሳሌ ግዑዝ ወንበርን ብትዳስስ እንኳን ከእጅህ ፍቅር ይፈልቃል፡፡ ፍቅርህን የምትሰጠው ለምንም ወይንም ለማንም ሊሆን ይችላል::

በፍቅር ስሜት ውስጥ መሆን የለም እያልኩ አይደለም፡፡ ዳሩ ግን በፍቅር ስሜት ውስጥ መኖር የምትችለው የቀድሞውን ኢጎአዊ የፍቅር ግንኙነት አስተሳሰብህን በምትተውበት ጊዜ ነው:: ፍቅር ኢጎን መሰረት ያደረገ በሰዎች መሀል የሚመሰረት ግንኙነት ዓይደለም።

ሁለት ሰዎች አንድ ላይ እጅግ አፍቃሪ ሊሆኑ ይችላሉ:: አፍቃሪነታቸው በጨመረ ቁጥር በመካከላቸው የሚፈጠረው የፍቅር ግንኙነት ይጠፋል። አፍቃሪነታቸው በጨመረ መጠን፣ አንዳቸው ከሌላቸው የሚፈልጉትንና አንዳቸው በሌላቸው የሚጥሉት ተስፋ ይቀንሳል፡፡ ፍቅር ውስጥም ይገባሉ፡፡

በውል ሳይተዋወቁ ፍቅርን ብቻ እያሰቡ ሲወዳደሱ በመጨረሻ መወቃቀስ ይጀምራሉ፡፡ ለዚህም ነው ምንም ዓይነት ተስፋ ማድረግ እንደማያስፈልግ ልታስታውስ የምፈልገው:: ፍቅር የራስህ ውስጣዊ እድገት መሆኑን አውቀህ አፍቅር። ፍቅርህ ወደላቀ ብርሀን፣ ወደላቀ እውነትና ነፃነት ከፍ ያደርግሀል፡፡ ግን በኢጎ ላይ የተመሰረተ የፍቅር ግንኙነት አትፍጠር::

አንድ ነገር ብቻ አስታውስ፣ ፍቅር ማንኛውንም ዓይነት መጥፎ ነገር የማጥፋት አቅም አለው፣ ፍቅርን ወደ ኢጎአዊ ፍቅር ግንኙነት እንዲለወጥ ከፈቀድክለት ግን፣ ፍቅር ይጠፋና የጓደኝነት ስሜት በውስጥህ ያለው ውብ ባህሪ ሲሆን ጓደኝነት ግን ወደ ትስስር ያመራል።

ስለዚህ ፍቅር መልካም ነገር ነው፡፡ እንደውም ፍቅር የሌለበት ነገር ሁሉ ስህተት ነው፡፡ ግን ፍቅር ከፍተኛ ዋጋ በመሆኑ ከማንኛቸውም ዓይነት በካይ መርዘኛ ነገሮች መጠበቅ አለበት፡፡ ትስስር ይበክለዋል። ዓለም በግለሰቦች የተሞላች እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ «ጥንድ» የሚለው ቃል እንኳን ይዳዳኛል፡፡ የሁለት ግለሰቦችን ህልውና አጠፋችሁ ማለት ነው:: ጥንድ በራሱ ውበት የለውም፡፡

ዓለም በግለሰቦች ብቻ የተሞላች ትሁን፡፡ ፍቅር በራሱ ጊዜ ጎምርቶ ሲፈነዳ ፍቅርን ዘምሩት ፣ ጨፍሩት፣ ኑሩት፣ ግን ፍቅርን ወደ ሰንሰለት አትለውጡት፡፡ ሰውን በባርነት ለመያዝ አትሞክሩ፣ ሌላም ሰው በባርነት እንዲይዛችሁ አትፍቀዱ። ነፃ ግለሰቦችን የያዘች ዓለም በትክክል ነፃ አለም ትሆናለች።

መፈለግ (መውደድ/ ከሰዎች ታላላቅ ፍላጎቶች አንዱ ነው። ስለዚህ ፍቅር ህልውናን ይዞ ይኖራል። የሰው ልጆች እስካሉ ድረስ የፍቅርን ያህል ትልቅ ነገር አያገኙም። በምድር ላይ የሚገኝ ግን የምድር ያልሆነ ነገር ነው:: በፀሐይ ፊት እንደንስር የምትበሩበት ክንፍ ይሰጣችኋል።

ያለ ፍቅር አክናፋት አይኖሯችሁም። እጅጉን አስፈላጊ የመንፈስ ምግብና ተፈላጊ ነገር ከመሆኑ የተነሳ በዙሪያው ችግሮች ይከቡታል። ፍቅረኛህ ወይንም ፍቅረኛሽን ነገ የራስህ /ሸ/ ማድረግ ትፈልጋላችሁ ውብ ነገር አሳልፋችኋል፣ ለነገ ደግሞ ትጨነቃላችሁ::

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.3K viewsedited  11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 20:46:44 #Moral_Philosophy
በዚህ ዓለም ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥሩ የሆነ ነገር ምንድን ነው?
___
በሥነ
ምግባር የፍልስፍና ታሪክ ውስጥ እንደ አብሪ ኮኮብ ሆነው ከሚታዩ ፈላስፋዎች መካከል አንዱ ጀርመናዊው ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት ነው። በዚህ የፍልስፍና ዘውግ ውስጥ "ደስታ" እና "ጥቅም" ለረጅም ጊዜ የህልዮቱ ማንፀሪያዎች ሆነው አገልግለዋል።

ካንት ግን በ18ኛው ክ/ዘ መጨረሻ ላይ አዲስ የሥነ ምግባር ማንፀሪያ ይዞ መጣ። ይሄንንም ማንፀሪያ ለማሳየት በቅድሚያ አንድ ወሳኝ የሥነ ምግባር ጥያቄ ያነሳል፤ እንዲህ የሚል፦

"በዚህ ምድር ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ (ያለምንም Qualification) ጥሩ የሆነ ነገር ምንድን ነው?"

እስቲ እንገምት መልሱ ምን ሊሆን ይችላል?

#ገንዘብ!? አይደለም፤ ገንዘብ ጥሩ የሚሆነው ለጥሩ ነገር ስናውለው እንጂ ገንዘብ በራሱ በተፈጥሮው ጥሩነት የለውም፡፡

#ዕውቀት!? ዕውቀትም አይደለም፤ እውቀት ጥሩ የሚሆነው መልካም ሰው ሲያገኝ ነው፡፡

#ጉብዝና (Courage)!? እሱም አይደለም፤ ጉብዝና ጥሩ የሚሆነው ለጥሩ ዓላማ ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ሂትለር ጎበዝ (Couragous) ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ የእሱ ጉብዝና መጥፎ ጉብዝና ነው፡፡

እና ታዲያ ምንድን ነው? ለካንት መልሱ ቀላል ነው - በዚህ ዓለም ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በራሱ መልካም የሆነ ነገር አንድ ብቻ ነው፤ እሱም "ቅንነት/Good will" ነው፡፡ ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉብዝና ቅንነት ላይ ካላረፉ አደገኛ ይሆናሉ፡፡

ይሄም ማለት በካንት የሥነምግባር አስተምህሮ
(Deontological Ethics) መሰረት አንድ ነገር ጥሩነቱ የሚለካው በውጤቱ (ጥቅም ወይም ደስታ ስለሚሰጥ) ሳይሆን በዓላማው (በሞቲቩ) ነው፡፡ እስቲ አንድ ምሳሌ እናንሳ፦

#ለምሳሌ፣ ኤልሳ የምትባል ልጅ ዋና እየተለማመደች እያለች ውሃ ውስጥ ስትሰምጥ ሄለን አየቻት፡፡ ወዲያውም ሄለን የኤልሳን ህይወት ለማዳን ውሃው ውስጥ ዘላ ገባች፡፡ ውጤቱ ግን በጣም የሚያሳዝን ሆነ ― ኤልሳ በሄለን እጅ ላይ ሞተች፡፡ ይሄንን የሄለንን ተግባር በምንድን ነው የምንመዝነው/ የምንዳኘው?

* በውጤቱ ይሆን?! ውጤቱማ ሄለንን ወንጀለኛ ያደርጋታል፡፡

* በዓላማው (በሄለን ሞቲቭ) ማለትም "ነፍስ የማዳን" ዓላማ ይሆን?! ይሄ ጥሩ መለኪያ ይመስላል፡፡ ሆኖም ግን፣ በዚህ የሄለን ዓላማ ላይ ራሱ ጥያቄዎች ይነሳሉ፦

የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ (motive) መነሻው ምንድን ነው?! ለካንት ወሳኙ ጥያቄ ይሄ ነው፡፡ የአንድን ድርጊት ጥሩነትና መጥፎነት የምንለካው በውጤቱ ሳይሆን በሐሳቡ/ በዓላማው ቢሆንም፣ የዓላማውስ መነሻ ምንድን ነው?! የሚለው ጥያቄ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ፣ የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ (motive) መነሻው ምንድን ነው?! አራት መላምቶችን እናስቀምጥ፦

* የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ ኤልሳን ስለምታውቃት (የጎረቤት ልጅ ስለሆነች ወይም የብሄሯ ልጅ ስለሆነች) ከሆነ፣ የሄለን ተግባር መልካም ሥራ አያስብለውም፤ ያ "የሞራል ተግባር" አያስብለውም፡፡ ምክንያቱም፣ የሞቲቩ መነሻ Inclination ነው፡፡

* የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ መነሻው "ማንኛውም ሰው በሞት አፋፍ ላይ ያለን ሌላ ሰው የመርዳትና የማዳን ግዴታ አለበት" የሚለውን የመንግስት ህግ ለማክበር ከሆነ፣ አሁንም የሄለን ተግባር መልካም ሥራ አያስብለውም፡፡ ምክንያቱም፣ የሞቲቩ መነሻ ውጫዊ (in accordance with Duty) ነው፡፡

የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ መነሻው "ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" የሚለውን ሃይማኖታዊ ህግ ለማክበርና ገነት ለመግባት ከሆነ፣ አሁንም የሄለን ተግባር መልካም ሥራ አያስብለውም፡፡ ምክንያቱም፣ የሞቲቩ መነሻ አሁንም ውጫዊና ቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ መነሻው "በሞት አፋፍ ላይ ያለን ሰው የመርዳትና የማዳን ውስጣዊ የሞራል ግዴታ አለብኝ" ከሚል ከሆነ ትክክል ነች፤ ይሄም ሄለንን "መልካም ሰው" ያስብላታል፡፡ ምክንያቱም፣ የሞቲቩ መነሻ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመረኮዘ ንፁህ ውስጣዊ የቅንነት ግዴታ (motive from Duty/the moral law within) ስለሆነ፡፡

ካንት በዚህ ቅንነት (Good Will) ላይ በተመሰረተው ውስጣዊ የሞራል ግዴታ አብዝቶ ይመሰጣል፡፡ ለዚህም ነው ካንት እንዲህ በሚል ንግግሩ ይበልጥ የሚታወቀው፦

"ሁልጊዜ በህይወቴ የሚያስደምሙኝ ሁለት ነገሮች አሉ፤ እነሱም ከላይ በከዋክብት የተንቆጠቆጠው ሰማይና በውስጤ ደግሞ ያለው የሞራል ህግ the moral law within me!! ናቸው።"

@Zephilosophy
@Zephilosophy
382 viewsedited  17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 20:46:44
372 views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 05:18:41 ከፍቅር ወደ አፍቃሪነት

ምንጭ ፦ ነፃነት (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዘላለም ንጉሴ

ፍቅር ሁለት ፍፁም የተለያዩ እንደውም ሙሉ ለሙሉ ተቃራኒ ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ አንዱ ትርጉም ፍቅር በፍቅር ግንኙነት መልኩ ሲገለጽ እና ሌላው ደግም ፍቅር በራሱ ህልውና ይዞ ሲገኝ ነው:: ፍቅር ወደ ፍቅር ግንኙነት በሚለወጥበት ወቅት ባርነት ይሆናል፡፡ ምክንያቱም የምንጠብቃቸውና የሚጠበቁብን ነገሮች እንዲሁም መረበሽ እና ፍርሀትን ይፈጥሩብናል:: ከሁለቱም ወገንም እኔ እበልጥ ስሜት ይመጣል፡፡ የኃይል እሽቅድምድም ይሆናል:: የፍቅር ግንኙነት ትክክል አይደለም፡፡ ፍቅር ሀልውና ይዞ ሲገኝ ግን ሙሉ በሙሉ የተለየ ነገር ይሆናል፣ ስታፈቅር ከፍቅር ሌላ የፍቅር ግንኙነት እየፈጠርክ አይደለም ማለት ነው:: ፍቅርህ እንደ አበቦች ጥዑም መዓዛ ይሆናል። የፍቅር ግንኙነት አይፈጠር፣ ይህን አድርግ፣ ባህሪህ እንዲህ ይሁን አይልህም፡፡ ከአንተ ምንም አይፈልግም። ያካፍላል። በማካፈሉም ምንም ሽልማት አይፈልግም፡፡ ማካፈሉ በራሱ ሽልማት ነው፡፡

ፍቅር ለአንተ እንደ አበቦች መዓዛ በሚሆንበት ጊዜ ታላቅ ውበት ይኖረዋል ከሰብዓዊነት በላይ የመጠቀ መለኮታዊ ነገር ይኖረዋል።

ፍቅር ብቻውን ከመጣብህ ምንም ልታደርገው አትችልም፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ አሳርን አያመጣም አንተም በማንኛውም ሰው እንድትታሰር አይፈቅድም።

ግን ከልጅነት አንስቶ የፍቅር ግንኙነቶችን የመፍጠር ልምድ አለህ፡፡ ከማታውቀው ወንድ ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ትፈጥራለህ። አባትህ መሆኑን በፍፁም ርግጠኛ ልትሆን አትችልም፡፡

አንድ የሰዎችን መዳፎች በመመልከት ዕጣ ፈንታቸውን ስለሚተነብይ ሰው የሰማሁት ታሪክ አለ፡፡ በእጅ መዳፍ ንባብና በአስትሮሎጂ በመሳሰሉት እንዲሁም በእግዚአብሔርም የማያምን አንድ ወጣት ወደዚሁ ሰው ይሄድና፣ «ሳይንስህ ትክክል ከሆነ እጄን አንብብና አባቴ የት እንደሚገኝ ንገረኝ አለው፡፡»

አዋቂውም መዳፉን ተመልክቶ እንዲህ አለው «አባትህ አሳ እያጠመደ ነው::» ወጣቱ ኢአማኒ ሳቀ፡፡ «እኔ የምለው ይህንኑ ነው፤ የማይረባ ሥራ ነው:: አባቴ ከሞተ ሶስት ዓመት ሆኖታል፤ ዛሬ እንዴት አሣ ለማጥመድ ይሔዳል?

አዋቂውም ሲመልስ፣ «ይህ እኔን አያገባኝም፣ እውነቱ ግን ያ የሞተው ሰው አባትህ ያለመሆኑ ነው፡፡ ትክክለኛ አባትህ አሳ እያጠመደ ነው:: ወደ እናትህ ሂድና ጠይቃት፡፡ ታማኝና እውነተኛ ከሆነች የሞተው ሰው አባትህ እንዳልሆነ ትነግርሀለች:: አንተ ግን አባትህ ነው ስለተባልክ ከእሱ ጋር የአባትና የልጅ ፍቅር ግንኙነት ፈጥረሀል።

ሕይወታችሁ በሙሉ በብዙ ዓይነት ግንኙነቶች የተሞላ ነው:: ይህ መሰል ግንኙነቶች ደግሞ እውነትም ይሁን ሀሰተኛ፣ እጅግ ውስብስብ የሆነ ስነ-ልቦናዊ ባርነትን ይፈጥራል። ወይ ሌላውን ባርያ ታደርጋለህ፡፡ ወይንም ራስህ ባርያ ትሆናለህ፡፡

ሌላው መታወስ ያለበት ነጥብ ደግም ራስህን ባርያ ሳታደርግ ሌላውን ሰው ባርያ ማድረግ አትችልም። ባርነት ባለሁለት ስለት ሰይፍ ነው:: አንደኛው የበለጠ ጠንካራ፣ ሌላው የበለጠ ደካማ ሊሆን ይችላል፣ ግን በሁሉም የፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ አንደኛው አሳሪ ሌላው ታሳሪ ይሆናል። ከእሱ አንፃር ሲመለከተው እሱ አሳሪው አንተ ደግሞ ታሳሪ ትሆናለህ:: የሰው ልጅ ይህን በመሰለ ሀዘንና ሰቆቃ የመኖሩ ዋነኛ ሀቅና ምክንያት መካከል አንዱ ይኸው ነው፡፡

ጥላቻ ደግሞ ከፍቅርህ የጠነከረ ግንኙነት ይፈጥራል ምክንያቱም ፍቅርህ ከአንገት በላይ ነው፡፡ ጥላቻህ እጅግ ጥልቅ ነው:: ጥላቻህን የወረስከው ከእነስሳዊነት ባህሪህ ነው:: ፍቅርህ ለመጪው ሕይወትህ ያለህ ብቸኛ እምቅ ኃይልህ ነው፡፡ እውን የሆነ ክስተት ሳይሆን ወደፊት ፍሬ የሚያፈራ ዘር ነው:: ጥላቻህ ግን ሙሉ በሙሉ በተግባር ላይ የሚገኝ፣ እጅግ የጎለመሰ ያለፈው የብዙ ሺህ ዓመት ታሪክህ ህያው ቅርፅ ነው:: የሚያድግበት ጊዜና ቦታ የነበረው። ለውጡ መከሰት የሚጀምረው ግን በሰው ልጆች ላይ ነው፡፡

ግን ማንንም እኔን ከመጥላት ማገድ አልችልም ስለዚህ ማንም ሰው እንዲያፈቅረኝ ማድረግ አልችልም፡፡ ልገልፀው የምችለው ነገር ቢኖር ጥላቻም ሆነ ፍቅር የግንኙነት መልክ በሚይዝበት ጊዜ ንፅሕናውን እንደሚያጣ ብቻ
ነው፡፡

ፍቅርህን ህልውናህ አድርገው፡፡ ፍቅር እንዲይዝህ ሳይሆን አፍቃሪ እንድትሆን ጣር፤ ፍቅር ባሪያህ ነው፡፡ ለአንተ ፍቅር የሀልውናህ ጥፁም መዓዛ ነው፡፡ ብቻህን ብትሆን እንኳን በአፍቃሪ ኃይል ትከበባለህ፡፡ የሞተ ነገርን ለምሳሌ ግዑዝ ወንበርን ብትዳስስ እንኳን ከእጅህ ፍቅር ይፈልቃል፡፡ ፍቅርህን የምትሰጠው ለምንም ወይንም ለማንም ሊሆን ይችላል::

በፍቅር ስሜት ውስጥ መሆን የለም እያልኩ አይደለም፡፡ ዳሩ ግን በፍቅር ስሜት ውስጥ መኖር የምትችለው የቀድሞውን የፍቅር ግንኙነት አስተሳሰብህን በምትተውበት ጊዜ ነው:: ፍቅር በሰዎች መሀል የሚመሰረት ግንኙነት ዓይደለም።

ሁለት ሰዎች አንድ ላይ እጅግ አፍቃሪ ሊሆኑ ይችላሉ:: አፍቃሪነታቸው በጨመረ ቁጥር በመካከላቸው የሚፈጠረው የፍቅር ግንኙነት ይጠፋል። አፍቃሪነታቸው በጨመረ መጠን፣ አንዳቸው ከሌላቸው የሚፈልጉትንና አንዳቸው በሌላቸው የሚጥሉት ተስፋ ይቀንሳል፡፡ ውስጥም ይገባሉ፡፡

በውል ሳይተዋወቁ ፍቅርን ብቻ እያሰቡ ሲወዳደሱ በመጨረሻ መወቃቀስ ይጀምራሉ፡፡ ለዚህም ነው ምንም ዓይነት ተስፋ ማድረግ እንደማያስፈልግ ልታስታውስ የምፈልገው:: ፍቅር የራስህ ውስጣዊ እድገት መሆኑን አውቀህ አፍቅር። ፍቅርህ ወደላቀ ብርሀን፣ ወደላቀ እውነትና ነፃነት ከፍ ያደርግሀል፡፡ ግን የፍቅር ግንኙነት አትፍጠር::

አንድ ነገር ብቻ አስታውስ፣ ፍቅር ማንኛውንም ዓይነት መጥፎ ነገር የማጥፋት አቅም አለው፣ ፍቅርን ወደ ፍቅር ግንኙነት እንዲለወጥ ከፈቀድክለት ግን፣ ፍቅር ይጠፋና የጓደኝነት ስሜት በውስጥህ ያለው ውብ ባህሪ ሲሆን ጓደኝነት ግን ወደ ትስስር ያመራል።

ስለዚህ ፍቅር መልካም ነገር ነው፡፡ እንደውም ፍቅር የሌለበት ነገር ሁሉ ስህተት ነው፡፡ ግን ፍቅር ከፍተኛ ዋጋ በመሆኑ ከማንኛቸውም ዓይነት በካይ መርዘኛ ነገሮች መጠበቅ አለበት፡፡ ትስስር ይበክለዋል። ዓለም በግለሰቦች የተሞላች እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ «ጥንድ» የሚለው ቃል እንኳን ይዳኛል፡፡ የሁለት ግለሰቦችን ህልውና አጠፋችሁ ማለት ነው:: ጥንድ በራሱ ውበት የለውም፡፡

ዓለም በግለሰቦች ብቻ የተሞላች ትሁን፡፡ ፍቅር በራሱ ጊዜ ጎምርቶ ሲፈነዳ ፍቅርን ዘምሩት ፣ ጨፍሩት፣ ኑሩት፣ ግን ፍቅርን ወደ ሰንሰለት አትለውጡት፡፡ ሰውን በባርነት ለመያዝ አትሞክሩ፣ ሌላም ሰው በባርነት እንዲይዛችሁ አትፍቀዱ። ነፃ ግለሰቦችን የያዘች ዓለም በትክክል ነፃ አለም ትሆናለች።

መፈለግ (መውደድ/ ከሰዎች ታላላቅ ፍላጎቶች አንዱ ነው። ስለዚህ ፍቅር ህልውናን ይዞ ይኖራል። የሰው ልጆች እስካሉ ድረስ የፍቅርን ያህል ትልቅ ነገር አያገኙም። በምድር ላይ የሚገኝ ግን የምድር ያልሆነ ነገር ነው:: በፀሐይ ፊት እንደንስር የምትበሩበት ክንፍ ይሰጣችኋል።

ያለ ፍቅር አክናፋት አይኖሯችሁም። እጅጉን አስፈላጊ የመንፈስ ምግብና ተፈላጊ ነገር ከመሆኑ የተነሳ በዙሪያው ችግሮች ይከቡታል። ፍቅረኛህ ወይንም ፍቅረኛሽን ነገ የራስህ /ሸ/ ማድረግ ትፈልጋላችሁ ውብ ነገር አሳልፋችኋል፣ ለነገ ደግሞ ትጨነቃላችሁ::

@Zephilosophy
@Zephilosophy
447 viewsedited  02:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 18:49:17 የነፃነት ሦስት አውታሮች

ምንጭ ፦ ነፃነት (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዘላለም ንጉሴ

ነፃነት ባለሦስት አውታር ክስተት ነው፡፡ የመጀመሪያ አካላዊ አውታር ነው፡፡ አካላዊ ባርነት ውስጥ ልትገባ ትችላለህ፣ ለብዙ ሺህ ዓመታትም፣ ሰው እንደማንኛውም ቁሳቁስ ገበያ ወጥቶ ሲሸጥ ቆይቷል:: በዓለም ዙሪያ ነበሩ። ሰብዓዊ መብቶቻቸው አይከበሩላቸውም፣ በሰው ደረጃ ሳይሆን በከፊል ሰውነት ይታዩም ነበር:: አሁንም ቢሆን ሰዎች በከፊል ሰውነት ይታያሉ፡፡ ህንድ ውስጥ ሱድራዎች ወይንም የማይነኩት በመባል የሚታወቁ ህዝቦች አሉ:: የሀንድ ህዝቦች አሁንም በአብዛኛው ባርነት ውስጥ ይኖራሉ:: መማርና፣ ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት በባህል ከተወሰነላቸው ሙያ ውጭ ሌላ ሙያ ውስጥም መግባት አይችሉም፡፡ እነሱን መንካት ሳይቀር ያቆሽሻል ተብሎ ስለሚታሰብ የነካቸው ሰው ወድያውኑ ገላውን መታጠብ አለበት፡፡ እንኳን አካሉን ይቅርና ጥላውን እንኳን ከነካኸው መታጠብ ይኖርብሀል።

በዓለም ዙሪያ፣ የሴት ልጅ ሰውነት ከወንድ ልጅ እኩል አይቆጠርም፡፡ ከወንድ እኩል ነፃነት የላትም፡፡ ቻይና ውስጥ ለብዙ ምዕተ ዓመታት ባል ሚስቱን መግደል ይችል ነበር፡፡ ምክንያቱም የግል ንብረቱ ነች። ልክ ወንበርህ፣ ጠረጴዛህና ቤትህ ንብረትህ በመሆናቸው ልታቃጥላቸው ወይንም ልታወድማቸው እንደምትችል ሁሉ ሚስትህም ላይ ይኸው መብት ይኖርሀል። በቻይና ህግ ሚስቱን ለሚገድል ባል መቀጫ የሚሆን ህግ አልወጣም፣ ምክንያቱም ሴት ልጅ ነፍስ የላትም ተብሎ ይታሰባል። ሴት ልጆችን የምታመርት መሣሪያ እንጂ ሌላ አይደለችም።

ስለዚህ አካላዊ ባርነትና አካላዊ ነፃነት አሉ፡፡ አካላዊ ነፃነት ማለት ያለመታሰር ከሌላ ከማንም አካል ዝቅ ተደርጎ አለመታየት፣ አካልን በተመለከተ እኩልነት ማግኘት ማለት ነው። ግን ዛሬ ድረስ እንኳን ይህ ነፃነት በሁሉም ሥፍራ አይገኝም፡፡ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም፡፡

አካላዊ ነፃነት ማለት ጥቁርና ነጭ፣ የወንድና የሴት ወይንም የሱ አይነት ልዩነቶች ያለመኖር ማለት ነው፡፡ ማንም ሰው ንፁህ አይደለም ማንም ሰው ቆሻሻ አይደለም አካላቶች አንድ ናቸው፡፡

የሁለተኛው አውታር፣ የስነልቦና ነፃነት ነው:: በዓለም ዙሪያ ስነልቦናዊ ነፃነት ያላቸው ግለሰቦች እጅግ ጥቂት ናቸው:: ምክንያቱም አንድ ሰው የአንድ ርዕዮተአለም ተከታይ ከሆነ ስነልቦናዊ ነፃ አይደለም። የልጆች አስተዳደጋችን ባጠቃላይ ባርነት ውስጥ የሚያስገባቸው ነው። የፖለቲካ የማሕበረሰብና የግል አስተሳሰቦች ባሪያ እናደርጋቸዋለን፡፡ በራሳቸው እንዲያስቡ፤ በራሳቸው እውነትን እንዲፈልጉ እድል አንሰጣቸውም:: መልክ እንገልፅላቸዋለን:: ወላጆች ለልጆቻቸው ስለእግዚአብሔር ያስተምሯቸዋል፣ ግን ስለእግዚአብሔር የሚያውቁት ምንም ነገር የለም።

ራስህ የማታውቀውን ነገር ለልጆችህ እያስተማርካቸው ነው:: የአንተ አእምሮ በወላጆችህ የተቀረፀ ስለሆነ አንተም የልጆችህን አእምሮ እየቀረፅክ ነው:: በዚህ ሁኔታ በሽታው ከአንድ ትውልድ ወደሌላው ትውልድ ይተላለፋል፡፡

ስነልቦናዊ ነፃነትን ማምጣት የሚቻለው፣ ልጆች እንዲያድጉ ሲፈቀድላቸው፣ የበለጡ ጥበበኞች ሆነው እንዲያድጉ ዕርዳታ ሲደረግላቸው፣ የበለጠ አስተዋይ፣ ንቁ እና አመዛዛኝ ሆነው እንዲያድጉ ሲፈቀድላቸው ነው:: በምንም ዓይነት እምነት እንዲያዙ ማድረግ አይገባም፡፡ እውነቱን በራሳቸው መርምረው እንዲደርሱበት የተቻለውን ያህል ልባቸውን ማነሳሳት እንጂ በምንም ነገር እንዲያምኑ ማስተማር አይገባም፡፡ ከመጀመሪያውኑ፣ «የራሳችሁ እውነት፣ የራሳችሁ ግኝት ነፃ ያወጣችኋል። ከዚህ ነፃ ሊያወጣችሁ የሚችል ምንም ነገር የለም»

እውነትን መዋስ አይቻልም:: ከመጽሐፎች አይጠናም፡፡ ማንም ስለእውነት ሊነግራችሁ አይችልም፡፡ እውነት በሕይወት ህላዌ ውስጥ ፈልገህ ለማግኘት፣ ራስህ ማስተዋልህን መቅረፅ አለብህ:: አንድ ታዳጊ ለነገሮች ክፍት፣ ተቀባይ፣ ንቁ እንዲሆን ከተደረገና፣ ነገሮችን እንዲፈትሽ ማበረታቻ ከተሰጠው፣ ስነልቦናዊ ነፃነትን ለማግኘት ይችላል። ስነልቦናዊ ነፃነትን ተከትሎም ከፍተኛ ሀላፊነት ይመጣል። ይህን ልታስተምረው ይገባሀል፣ የስነልቦናዊ ነፃነት ጥል ሆኖ ይከሰታል። ካስተማርከው ያመሰግንሀል። ካልሆነ ግን ቤተሰቦቹ አእምሮውን በመሰላቸው በመቅረፅ፣ ነፃነቱን እንዳንኮታኮቱበት ማንኛውም ታዳጊ ህፃን በወላጆቹ ላይ ንዴት ያድርበታል፡፡ ገና ምንም ጥያቄ ሳይጠይቃቸው በፊት እነሱ አእምሮውን በመልሶች ሞልተውታል ምክንያቱም መልሶቹ የራሱን ልምዶች መሠረት ያደረጉ አይደሉም፡፡

ሶስተኛ አውታር የነፃነት ፍፁማዊነት ነው:: ይህም አንተ አካልህና አዕምሮህ ያለመሆንህንና፣ ንፁህ ሀሳብ መሆንህን ማወቅ ነው፡፡ እውቀት ከመስጠት እንደሚገኝ ማወቅ ነው፡፡ ይህ ከአካልህ ይለይሀል፣ ከህሊናህም ይለይሀል፣ እናም አንተ በንፁህ ሀሳብና በንፁህ እውቀት መልክ ብቻ ህልውና ይኖርሀል። ይህ መንፈሳዊ ነፃነት ነው፡፡

ለአንድ ግለሰብ የሚያስፈልጉት ሶስቱ መሠረታዊ የነፃነት አውታሮች እነዚህ ናቸው፡፡

ሰዎች በጠቅላላ እንደአንድ ሲታዩ ነፍስም ሆነ ህሊና የላቸውም፡፡ ይህ አንድ የሰው ልጅ ህልውና አካልም የለውም፣ ስም ብቻ ሆኖ ይገኛል፡፡ ቃል ብቻ ነው ለጠቅላላው አንድ ህልውና ነፃነት አያስፈልገውም፡፡ ሁሉም ሰው ነፃ ሲሆን፣ ጠቅላላው አንድ ነፃ ይሆናል፡፡ ግን በቃላት የተገዛን ከመሆናችን የተነሳ፣ ቃላት ምንም ጭብጥ እንደሌላቸው እንዘነጋለን፡፡ ጠ ቅላላው አንድ፣ ማለትም ህብረተሰቡ፣ ማህበረሰቡ፣ ሀይማኖት ቤተክርስቲያኑ ሁሉም ቃላት ብቻ ናቸው:: ከበስተጀርባ ምንም እውነት ነገር የለም፡፡

አንድ ትንሽ ታሪክ ትዝ አለኝ። «ኤሊስ ኢን ወንደርላንድ» በተባለው በሉዊስ ካሮል በተፃፈው መጽሐፍ ላይ፣ ኤሊስ ንግስቲቱ ወደምትኖርበት ሥፍራ ትመጣለች። በደረሰች ጊዜ ንግስቲቱ እንዲህ ብላ ትጠይቃታለች፡፡ «ወደ እኔ ስትመጪ መልዕክተኛ አግኝተሻል»
ልጅትም ስትመልስ፣ «ማንንም»
ንግስቲቱም «ማንንም» ማለት የሰው ስም መሰላት፣ «ታዲያ ማንንም እስካሁን እዚህ ያልደረሰው ለምንድነው» ብላ ጠየቀቻት፡፡

ልጅትም፣ «ማዳም፣ ማንንም ማለቴ እኮ ማንንም ነው» አለቻት»

ንግስቲቱም እንዲህ አለች፣ «የማይረጋ ነገር አትንገሪኝ ገብቶኛል፡ ማንንም ከማንንም ሌላ ሊሆን አይችልም፣ ስለዚህ ከአንቺ በፊት እዚህ መድረስ ነበረበት። ማንንም ሲራመድ ከአንቺ ይልቅ ቀሰስተኛ ነው ማለት

አሊስም ስትመልስ፣ «ማንንም ከእኔ ይልቅ ቀሰስተኛ ሆኖ አላየሁም» በዚህ መልኩ ውይይቱ ይቀጥላል። በንግግራቸው ላይ ግን «ማንንም » አንድ ሰው ይሆንና፣ አሊስ ንግሥቲቱን ማሳመን ያቅታታል፡፡

ጠቅላላው አንድ እጅግ አደገኛ ሀሳብ ሆነ። በጠቅላላው ሰም፣ ግለሰቡ ማለትም እውነት ዘወትርም መስዋዕት ይደረጋል፡፡ እኔ ይህን ሃሳብ
በፍፁም እቃወመዋለሁ።

ሕዝቦች በህዝብ ስም ግለሰቦችን ሆነዋል። «ህዝብ» ግን ከቃላት አያልፍም በካርታ ላይ ተስለው የምናያቸው መስመሮች በምድር ላይ የሉም:: ጨዋታዎች ናቸው:: በእነዚያ መስመሮች የተነሳ ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ሞተዋል። በሌሎች መስመሮች ያሉ ሠዎችም ሞተዋል። እናንተ ደግም የሞቱትን የሀገር ጀግኖች ትሏቸዋላችሁ::

@Zephilosophy
@Zephilosophy
113 views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ