Get Mystery Box with random crypto!

'በእርሻ ማሳዎቻችሁ ላይ የሚፈራረቁትን ወቅቶች ሁልጊዜ በፀጋ እንደምትቀበሉዋቸው ሁሉ የልቦቻችሁን | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

"በእርሻ ማሳዎቻችሁ ላይ የሚፈራረቁትን ወቅቶች ሁልጊዜ በፀጋ እንደምትቀበሉዋቸው ሁሉ የልቦቻችሁን የሀዘን ወቅቶችም  በፀጋ መቀበል ይኖርባችኋል።"
ካህሊል ጂብራን

"ሰዎች ፍቅር እውር ነው ይላሉ። እንዲህም የሚሉት የፍቅርን ትርጓሜ ስላላወቁ ነው። እኔ ግን እላችኋለሁ ፍቅር ብቻ ነው አይን ያለው። ከፍቅር ውጪ ሌላው በሙሉ እውር ነው። "
ኦሾ

"የእኛ ህይወት ግማሹን የምንወዳቸውን ሰዎች ለማግኘት እየጠበቅን፤ ግማሹ ደግሞ የምንወዳቸውን ስንሰናበት እናሳልፋለን።”
ቪክቶር-ሁጎ

"ሰዎች ብርቱዎችን ይጠላሉ ግን ይታዘዛላቸዋል ፤ ደካሞችንም ይወዳሉ ግን ይንቋቸዋልም! "
ዶስቶቭስኪ

"በብርሃን ስትሆን ሁሉ ነገር ይከተልሃል:: ጨለማ ውስጥ ከሆንክ ግን ጥላህ እንኳን አይከተልህም።"
  ሂትለር

‹‹ ቁንጅና ያለው ፊት ላይ አይደለም፡፡ ቁንጅና በውስጣችን የሚገኝ የልብ ብርሃን ነው፡፡ ››
ካህሊል ጂብራን

"የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ። ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።"
-ዊሊያም ሼክስፒር

"አዋቂ ሆኖ ለመታየት የምናደርገው ጥረትና ከንቱ ድካም አላዋቂ አድርጎ ያስቀረናል"
         ሶቅራጥስ

"ሌሎችን የሚያሸብር ሁሉ እርሱ ራሱ በማያቋርጥ ፍርሃት የተዋጠ ነው።"
ክላውሲያ

"የሰው ልጅ የሚሰቃየው ራሱ ባጠረው አጥር ራሱ በገነባው ቅጥር ራሱ በሸበበው ውትርትር ነው። የዘር፣ የሃይማኖት፣ የርዕዮተ አለም ፣... የፍልስፍና አጥር። የብቸኝነት፣ የአውሬነት፣ የወፈፌነት ፣ ... አስማት የሚመስል አጥር።" ...
 ይስማዐከ ወርቁ

"ቤትህን ፅዱ አድርግ ልክ እንግዳ ትጠብቅ
ይመስል፣ ልብህን ፅዱ አድርግ ልክ ሞትህን ትጠብቅ ይመሰል"
አረቦች

“ሰው የሚማረው አንድም በፊደል፣ አንድም በመከራ ነው፣ አንድም በሳር “ሀ” ብሎ፣ አንድም በኣሳር “ዋ” ብሎ።”
ፀጋዬ ገ/መድህን

@zephilosophy
@zephilosophy