Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemarian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.65K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-08 21:35:11
★ @zemarian ★
#ኮነ_ዮም

ኮነ ዮም ኮነ ዮም በእንተ ልደታ ለማርያም/2/
ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወፃድቃን
ነቢያተ ከመ ትቤ/2/


በማህበረ ቅዱሳን
በህብረት_እናመስግን
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ

★ @zemarian ★
700 views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 21:35:11 ትብል ማርያም
ሰብስክራይብ



681 views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 21:35:11
★ @zemarian ★
#ሰላም_የእግዚአብሔር_ቤተሰቦች_ስርአተ_ማህሌቱ_መርሀ_ግብር

01/09/2011


ሥርዓተ ማኅሌት ዘግንቦት ልደታ ለማርያም "ግንቦት ፩"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል። ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል። እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል። ተፈጸመ ተስፋ አበው #በማርያም_ድንግል። ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
#ለማርያም ዘምሩ: #ለማርያም ዘምሩ: መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትጸውሩ።

ነግሥ
ሰላም ለልሣንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል። ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል። ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል። አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣሕል። እንበለ ባሕቲታ እኅትከ #ማርያም_ድንግል።

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት #ለማርያም_ድንግል።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ። ለወልድኪ አምሳለ ደሙ። መሠረተ ህይወት #ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ። ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ። እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ: ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርስኪ ፆርኪ: እምአንስት ቡርክት አንቲ: ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር: አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር: ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል።

ነግሥ
፪ቱ አዕሩግ አመ በከዩ ብካየ። ረከቡ ወለተ ዘታስተሠሪ ጌጋየ። ለወንጌላውያን ኲልነ ዘኮነተነ ምስካየ። ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ። ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ።

ዚቅ
ምሥራቀ ምሥራቃት መፃአ ፀሐይ: እግዝእትነ ዘመና ሙዳይ: ተወልደት ዮም ዳግሚት ሰማይ።

መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ። እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ። #ማርያም_ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ። ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ። ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
በሐኪ #ማርያም ዘገነት ኮል: ዕፀ ጳጦስ መዝገቡ ለቃል: ዕለተ ልደትኪ ዮም በጽድቅ ናብዕል።

ወረብ
በሐኪ #ማርያም ዘገነት ኮል/፪/
"ዕፀ ጳጦስ"/፪/ መዝገቡ ለቃል/፪/

መልክዐ ማርያም
ሰላም ለልሳንኪ ሙኃዘ ኀሊብ ወመዓር። ዘተነብዮ ወፍቅር። #ማርያም_ድንግል ወለተ ድኁኃን አድባር። ኅብዕኒ እምአይነ ፀር ወአንጽሕኒ እምነውር። እስመ ተስፋየ አንቲ በሰማይ ወምድር።

ዚቅ
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን: ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።

ወረብ
"መሠረታቲሃ"/፪/ ውስተ አድባር ቅዱሳን/፪/
"ወብእሲ ተወልደ" በውስቴታ/፪/

መልክዐ ማርያም
ሰላም ለአእዳውኪ እሳተ መለኮት እለ ገሠሣ። አውቃፈ ብሩር ወወርቅ ለሥርጋዌሆን ኢኃሠሣ። #ማርያም_ድንግል ለመካን ሕንባበ ከርሳ። አንጽሕኒ እግዝእትየ ለፍትወተ ዓለም እምርኲሳ። በዲበ ሥጋየ ኢትንብር ነጊሣ።

ዚቅ
ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነሰ ዘተፀነስኪ: አላ በሩካቤ ዘበሕግ: እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ።

ወረብ
"እምሐና ወኢያቄም"/፪/ ተወለድኪ/፪/
አላ በሩካቤ ዘበሕግ/፪/

መልክዐ ማርያም
ሰላም ዕብል ለድንግልናኪ ዕጽው። እንተ እምኔሁ ሠረቀ ፀሐየ መለኮት ኅትው። #ማርያም_ድንግል ዘስነ ንጽሕኪ ፍትው። ለኀዲር በበፍናው በአሕጉር ወበድው። ዕቀብኒ ወለቶሙ ለኄራን አበው።

ዚቅ
ወለቶሙ ለነቢያት ይእቲ #ማርያም: እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ #ማርያም: ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ ዕደ ሰብእ: ዕጹብ ግብረ መናሥግተ ሥጋ ኢያርኃወ: ዕጹብ ግብረ።

ወረብ
ወለቶሙ ለነቢያት እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ #ማርያም/፪/
"ደብተራ" ፍጽምት/፪/ እንተ ኢገብራ ዕደ ሰብእ/፪/

መልክዐ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ። ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ። ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ። #ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ። ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ።

ዚቅ
ርግብ ፀዓዳ ዘዕንቊ ድዳ: ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ: ተወልደት ዮም በምድረ ይሁዳ።

ወረብ
ርግብ ፀዓዳ ዘዕንቊ ድዳ ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ ወዘጳዝዮን/፪/
ዮም ተወልደት በምድረ "ይሁዳ"/፪/ በምድረ ይሁዳ ተወልደት።

አሥርቆት
ሰላም ለልደትኪ እማኅጸነ ድክምት ሥጋ። ድኅረ ኃለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ። ማርያም ሥመሪ ወጺሐኪ እንበለ ንትጋ። ለማየ ንጽሕኪ ትረስዪኒ ፈለጋ። እስመ ንጽሕ ይሁብ ሞገሰ ወጸጋ።

ዚቅ
ሐመልማላዊት ሐመልማላዊት ሐመልማላዊት ዕፅ ሙሴ ዘርእያ በደብረ ሲና: እግዝእትየ ሙዳዩ ለመና: ተወልደት ዮም እምነኢያቄም ወሐና።

ወረብ
"ሐመልማላዊት"/፪/ ዕፅ ሙሴ ዘርእያ በደብረ ሲና/፪/
ተወልደት ዮም እምነኢያቄም ወሐና/፪/

ምልጣን
ዮም ፍሥሃ ኮነ በእንተ ልደታ #ለማርያም እምሐና ወኢያቄም: ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ: አማን ተወልደት እመብርሃን።

አመላለስ
አማን በአማን/፬/
ተወልደት እመብርሃን/፬/

ወረብ
ኮነ ዮም በእንተ ልደታ #ለማርያም /፪/
ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ ነቢያተ ከመ ትቤዙ/፪/

እስመ ለዓለም
ልሳንየ ላዕላዕ ይሴብሐኪ: እግዝእትየ እብለኪ አዳም ንባብኪ ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ: ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርሥኪ ፆርኪ: እምአንስት ቡርክት አንቲ: ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር: አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር: ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል።

አመላለስ
አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር/፪/
ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል/፪/
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
@zemarian
731 views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 00:01:35 ከበዓል በኃላ ለሰርጎ , ለልጆቾ ክርስትና የዲኮር ስራ ማሰራት ይፈልጋሉ ?



ለ ሰርግ                            ለ ክርስትና
ለ ልደት                            ለ ቀለበት
ለ ገዓት                             ለ ሽምግልና
ለ ተማሪዎች ምረቃ           ለ ልጆች ልደት
ለ ቤት ምርቃት                   ለ ሆቴል ምረቃ
ለ ስብሰባ አዳራሾች          ለ ቤተሰብ ኘሮግራሞች
ለ ሰርግ ለመኪና ዲኮር
በ ቤተክርስቲያን ስርዓት ለሚፈፀሙ ሰርጎች እና ኘሮግራሞች

ለተለያዮ ዝግጅቶችም ጭምር የተለያዮ የዲኮሪሽን ስራዎችን እንሰራለን እንዲሁም የተለያዮ የዲኮር እቃዎችን እናቀርባለን !
       

     
              ይህን ይጫኑት  ...  ይህን ይጫኑት

█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█


Tel .   +251961064953
                 +251703504953
.
445 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:45:33 ምል. ዮም ፍስሐ ኮነ።መዝ.ይትፌሣሕ ሰማይ።
በመምህር ሲራክ።
1.4K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:45:32
1.3K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 17:49:51
433 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 17:49:51 ይህ ፍጹም ሊሆን እንደማይችል ሕሊናችን ሳይቀር ይመሰክርብናል፡፡ ታድያ መፍትሔው ምንድን ነው? ያልን እንደ ሆነ መፍትሔውማ ንስሐ መግባት ነው እንላለን፡፡ ንስሐ መግባት ማለት ይከተሉት የነበረውን ክፉ ተግባር ሙሉ በሙሉ እርግፍ አድርጎ  በመተው ወደ ደገኛው ተግባር መመለስ ማለት ነው፡፡ ንስሐ ማለት ትናንት በጥይት ሲጠፋ የነበሩ ወገኖች ዛሬ እሱን አቆመውና በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለው  ችግራቸውን በፍቅር ለመፍታት መወያየት መቻል ማለት ነው፡፡ ትክክለኛው  ንስሐ እንዲህ ያለው ነው፡፡

ይህንን የመሰለ ጥሩ አርአያ ያለው ንስሐ በሀገራችን በቅርቡ ሲፈጸም አይተናል፤ ይህንን ያደረጉ ወገኖች በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናቸዋለን፤ ይህን ያደረጉ ወገኖች ትክክለኛውን ትንሣኤ ተነሥተዋል፤ የትንሣኤውንም በዓል በትክክል አክብረዋል፡፡

ሆኖም ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ የሚያስገኘው ከእምነት ሲነሣ ነውና ነገሩ ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር ተብሎ በእምነት ሊደረግ ይገባል፤ ገና ወደ ጠረጴዛ ያልመጣችሁ ወገኖችም ንስሐ ገብታችሁ ወደ ውይይት እንድትመጡና የጋራ ሀገራችንን በጋራ እንድናገለግል በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናቀርባለን፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ መፎካከር ይቁም፤ መወያየት ይቅደም፤ ከሰላም፣ ከአንድነትና ከፍቅር ተጠቃሚ መሆናችንን አንዘንጋ፤ ኢትዮጵያ ለሁላችንም በቂ ብቻ ሳትሆን፤ ከበቂም በላይ ናት፡፡ ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት፤ ይህ የኔ ነው ይህ የኔ ነው በሚል ደካማ አመለካከት ራሳችንን በራሳችን አንጉዳ፣ ከእንግዲህ ወዲህ የጥይት ድምፅ ይብቃ፤ የዕለቱ ዓቢይ መልእክታችን ይህ ነው፡፡
በመጨረሻም፡-

የትንሣኤውን በዓል ስናከብር የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጨነቁትን በማጽናናት፣ እንደዚሁም የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል ይበልጥ ለማስፋትና የሀገር አንድነቱን በዕርቅ ዘላቂ ለማድረግ ቃል በመግባት የፋሲካን በዓል እንድናከብር በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
መልካም የትንሣኤ በዓል ያድርግልን!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ 
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
441 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 17:49:37 "ከእንግዲህ ወዲህ የጥይት ድምፅ ይብቃ"

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ  ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወኃምስቱ ዓመቱ ምሕረት

በስመ አብ፣ወወልድ፣ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
•  በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
•  ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
•  የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፋ የቆማችሁ፣
•  በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
•  እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵውያት በሙሉ!
ትንሣኤና ሕይወት የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
“እሙታን ተንሢኦ ሲኦለ ከይዶ በሞቱ ለሞት ደምሰሶ፡- ከሙታን ተነሥቶ ሲኦልን ረግጦ በሞቱ ሞትን ደመሰሰው” /መጽሐፈ ኪዳን/
ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሥጋ ሰብእ ተገልፆ ዓለምን ከሞተ ኃጢአት እንደሚታደግ ከጥንት ጀምሮ ነቢያት ሲያስተምሩና ሲመክሩ ኖረዋል፡፡
እግዚአብሔር በጠባዩ በደለኛውን ከቶ የማያነጻ አምላክ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአንጻሩ ደግሞ ለፍጥረቱ ፈጽሞ የማይጨክን አምላክ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ እግዚአብሔር ሰውን በፈጸመው በደል ምክንያት ቢቀጣውም የኋላ ኋላ ቅጣቱን ወደ ራሱ አዙሮ በመቀበል ሰውን በሚያስደንቅ ምሕረቱ ተቀብሎታል፡፡ በዚህም አድራጎቱ እግዚአብሔር ሕግን በማክበር፣ ፍርድን በመጠበቅ፣ ምሕረትን በማድረግ ትክክለኛነቱን በሚገርም ሁኔታ ፈጽሞ እናየዋለን፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ሲያመሰጥር እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፡-
•  “ሁሉም ኃጢአትን ሰርተዋልና የእግዚአብሔር ክብር ጐድሎአቸዋል በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ፤ እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስርያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎት ስለመተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፤ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው” ይለናል (ሮሜ. 3፡23-26)
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!!
ለጌታችን መሰቀልና መሞት መንሥኤ የሆነው የእኛው በደል ነው፡፡ በደላችን እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ አሳጥቶ ኃጢአተኞች እንድንሆን  አድርጎናል፡፡ የኃጢአት ደመወዝ ደግሞ ሞት ስለሆነ በኃጢአታችን ለሞት ተዳርገናል፡፡
በዚህ ምክንያት ከተጫነብን የሞት ዕዳ ሊገላግለን ጌታችን በእኛ ፈንታ ተሰቅሎ፣ ንጹህ ደሙንም መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ የሞት ዕዳ ከኛ እንዲነሣ አደረገልን፡፡
እግዚአብሔርም በኢየሱስ ክርስቶስ ንጹህ ደም ምክንያት ሙሉ ይቅርታን ሰጥቶ ታረቀን፤ ወደ እሱም አቀረበን፤ ተቀበለንም፡፡ እግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስን ደም በፊት ለተደረገውም ሆነ ለወደፊት ለሚሆነው ኃጢአት መደምሰሻ ወይም ማስተሰረያ አድርጎ በቀዋሚነት አጸናው፡፡
በመሆኑም ቀደምት አበውም ሆኑ ደኃርት ውሉድ የሚድኑት በኢየሱስ ክርስቶስ ንጹህ ደም መሆኑን ክርስቲያኖች ሁሉ ሊገነዘቡት፣ ሊቀበሉትና ሊያምኑበት ይገባል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ “እግዚአብሔር በዚህ መሥዋዕት እኛን በማጽደቁ ፍጹም ጻድቅ ወይም እውነተኛ መሆኑን አሳየ” በማለት ያረጋግጣልና ነው፡፡
እንግዲህ ጌታችን በዚህ መሥዋዕትነቱ የቀደመውን ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ስላስወገደው በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ቀጥሎም ከአዳም ጀምሮ እስከ ዕለተ ስቅለቱ ድረስ በሰቆቃና በስቃይ የነበሩ ነፍሳተ አበውን ወደ ጥንተ ሀገራቸው ወደ ገነት መለሳቸው፡፡
በዚህም በደልና ፍዳ ኃጢአት ሲኦልና ዲያብሎስ ተሸንፈው ባዶ እጃቸው ስለቀሩ ሲኦልን ረግጦ በሞቱ ሞትን ደመሰሰው ተብሎ የምስራቹ ተነገረን፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!!
ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን በከፍተኛ ደረጃ የምታከብረው በዓለ ትንሣኤ በእግዚአብሔር ችሎት የሚያስፈርድብንና የሚያስቀጣን በደላችን ስለተሰረዘ፣ ቅጣታችንም ስለተነሣ፣ እኛን ለመዋጥ አፋቸውን ከፍተው የሚጠብቁትን ሞትና መቃብርም ባዶአቸው የቀሩበት አምላካዊ ድል የተፈጸመበት በመሆኑ ነው፡፡ ለዚህም ማረጋገጫችን የጌታችን ትንሣኤ ነው፡፡
ጌታችንም ከመሞቱ በፊት በቃልና በተግባር ያረጋገጠልን ይህንን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን በቅዱስ ወንጌል፡- “ኃጢአትህ ተሰረየልህ ወይም ተሰረየልሽ” በማለት ኃጢአትን ሲሰርዝ አይተናል፡፡
በሰው ሁሉ ላይ የበላይነት አግኝተው በመርዛም ተግባራቸው ሰውን ሲያሰቃዩ የኖሩ ሰይጣንና ሠራዊቱ “አንተ ርኩስ መንፈስ እልሃለሁ ከሱ ውጣ” እያለ በማስወጣት ወደ ጥልቁ ሲያሠጥማቸው አይተናል፡፡
በአጋንንት ጠንቅ በልዩ ልዩ ደዌና በሽታ ተይዘው ሲሠቃዩ የነበሩ ሰዎችንም ከበሽታቸው ገላግሎ ፍጹም ጤንነት ሲሰጣቸው አይተናል፡፡
መቃብርን ቤታቸው አድርገው የነበሩትንም ሙታን “ና ውጣ ከመቃብር” እያለ ከመቃብር ሲያስነሣቸው አይተናል፡፡ የሞቱትንም “ተነሥ፤ ተነሽ” እያለ ሲያስነሣቸው ተመልክተናል፡፡ በተሰቀለበት ዕለትም በቅድስት ሀገር በኢየሩሳሌም አምስት መቶ ሙታን ተነሥተው በከተማው ውስጥ ለብዙ ጊዜ መቆየታቸውን ተምረናል፡፡
ታድያ እነዚህ አምላካዊ ድርጊቶች በሙሉ በደልና ፍዳ ኃጢአት፣ ሞትና ሲኦል፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ የእነዚህ አጋፋሪ የሆነው ዲያብሎስ ከነሠራዊቱ ተሸንፎ ባዶውን ወደ ጥልቅ መስመጡ የሚያሳዩን አይደሉምን; ልብ ብለን ከተመለከትነውና ካስተዋልነውስ ትንሣኤው የጌታችንን እውነተኝነት፣ የዲያብሎስና ሠራዊቱን ተሸናፊነት ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩን አይደሉምን;
የዚህ ሁሉ ማረጋገጫ ማተምስ የጌታችን ከሞት መነሣት አይደለምን; ከዚህ አኳያ ጌታችን ሲነሣ ብቻውን አልተነሣም እንላለን፡፡
ነገር ግን እሱ ሲነሣ ገና ሳይሞት ያስተማረው ትምህርትና የፈጸመው ተአምራት ሁሉ አብሮ ተነሥቶአል፤ ምክንያቱም ትንሣኤው የእውነተኝነቱ ማረጋገጫ ነውና፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!!
እኛ የትንሣኤ ልጆች ነን፤ ጌታችን  ሞትንና መቃብርን ድል ነሥቶ የተነሣው እኛም እሱን ተከትለን ሞትንና መቃብርን ድል እንድንነሣ እንጂ የእነሱ ሢሣይ ሆነን እንድንቀጥል አይደለም፡፡
ይሁን እንጂ እንዳለመታደል ሆኖ የሰው ልጆች ዛሬም ምርጫቸው ትንሣኤ ሳይሆን ሞት ሆኖ መገኘቱ እጅግ በጣም የሚቈጭና የሚያሳዝን ነው፡፡
ዛሬም ሰዎች እርስ በርሳቸው እየተጣሉና እየተገዳደሉ የሞትና የመቃብር ሢሣይ በመሆን ቀጥለዋል፤ ከዚህ አስከፊና ጎጂ ድርጊታቸው ለመቆጠብም ዝንባሌ አይታይባቸውም፤ ታድያ እኛ ሰዎች የሞትንና መቃብርን ጎጂነት፣ የትንሣኤንና የጤናማ ሕይወትን ጠቃሚነት ለይተን በማወቅ ለጥቅማችን መቆም የማንችል ከሆነ የጌታችን ትንሣኤ አከበርን ማለቱ ጥቅሙ የቱ ላይ ነው;
ከመገዳደልና ከመጨካከን ሳንመለስ የምናከብረው በዓልስ እግዚአብሔር ይወድልናል ወይ; ይቀበለዋል ወይ;
ይህ ፍጹም ሊሆን እንደማይችል ሕሊናችን ሳይቀር ይመሰክርብናል፡፡ ታድያ መፍትሔው ምንድን ነው; ያልን እንደ ሆነ መፍትሔውማ ንስሐ መግባት ነው እንላለን፡፡
314 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 17:38:56 #አሰሮ_ለሰይጣን_ (ሰይጣንን አሰረው) #አግዐዞ_ለአዳም(አዳምን ነጻ አወጣው)፤ #ሰላም (ሰላም ፍቅርና አንድነት) እምይእዜሰ (ከዛሬ ጀምሮ) #ኮነ (ኾነ) #ፍሥሐ_ወሰላም (ሰላምና ደስታ ኾነ)፡፡ ፠ በማዕረግ ከፍ ያለው ካህንም፤ ከላይ ያለውን ዐውጆ ሲያበቃ «#ነዋ_መስቀለ_ሰላም» እያለ መስቀል ሲያሳልም ካህናትና ሕዝቡም «#ዘተሰቅለ_ቦቱ_መድኀኔ_ዓለም» እያሉ ይሳለማሉ፡፡ በማዕረግ ከፍ ያለው ካህንም፤ «#እግዚአብሔር_ይፍታ» ይላል፡፡ ግብረ ሕማማት ሲነበብበት ከሰነበተው ጠበልም ይረጫል፡፡ የተረፈውንም ጠበል ሕዝቡ ለበረከት ወደየቤቱ ይወስደዋል፡፡ ፠ ከዚያም ልኡካኑ ለቅዳሴ ይዘጋጃሉ፤ ሊቃውንት ደባትር መዘምራንም ምስማክ፥ መወድሱን ካዜሙ በኋላ በመቋሚያ ይዘምሙታል፡፡ አያይዞም በዓመት ፫ት ጊዜ የሚዘመረውን «ይትፌሣሕ ሰማይ …» የተባለውን መዝሙር ቃኝተው ከዘመሙ በኋላ «ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፤ ተኀፂባ በደመ ክርስቶስ = ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካውን ታደርጋለች፡፡» እያሉ ይጸነጽላሉ፡፡ አያይዘውም የመዝሙሩን ሰላም (ፍጹመ ንጉሠ ኰነንዎ …)ን ይጸፋሉ፡፡ ፠ ወዲያው መንፈቀ ሌሊት ሲሆን ቅዳሴ ተቀድሶ ይቈረባል፡፡ ከዚያም ዕጣነ ሞገር = በዕጣን ፈንታ ቅኔው ተቁሞ ሠርሖተ ሕዝብ = የሕዝብ ስንብት ከሆነ በኋላ ለመፈሰክ ሕዝቡ ወደየ ቤቱ ይሔዳል፡፡ #የትንሣኤ_አከባበር_በዕለቱ ፠ ሕዝቡ በየቤቱ፣ ካህናቱም ከቤተ ክርስቲያን በየአካባቢው ባህል በተለይ አክፋዮች መጀመሪያ ቅባት አጥቶ የሰነበተ ሆድ እንዲለሰልስ የተሞቀ የተልባ ጭልቃ ይጠጣና የሹሮ ወጥ በቅቤ፣ በአይብ፣ የበረታም በዶሮ ወጥ፣ ወይም በበግና በከብት ሥጋ ወጥ ይገድፋል፡፡ ፠ በእርጎ፣ በአይብ የተደራረበ እንጀራ በግፍልፍል የሚገድፉም አሉ፡፡ በአንዳንድ የሰሜኑ ሀገራችን ደግሞ የተልባ፣ የኑግና የሱፍ ጭልቃ ከማር ጋር ታሽቶ ከተጠጣ በኋላ በእርጎ፣ በአይብ፣ በወተት፣ በቅቤና ድልህ በተቀባ እንጀራ ይገድፋሉ፡፡ ፠ በዋልድባ ገዳም ከዓመት ዓመት ምግቡ ቋርፍ ብቻ መሆኑ ይታወቃል፤ ነገር ግን ለትንሳኤ በዓል ከሃገራችን ካሉ ቦታዎች በተለየ ሁኔታ በዓሳ ይገድፋሉ፤ ዓሳው ሲዘጋጅም ሙሉ ለሙሉ ሆድ ዕቃው ሳይወጣ ተወቅጦ ነው፡፡ ፠ ሊነጋጋ ሲልም ከጾሙ አጋማሽ ጀምሮ ወንዱ ለእርድ የሚሆነውን ሰንጋውን፣ ሲቀልብ፣ በጉን ፍየሉን ሲሞክት ዶሮውን ሲመርጥ፣ ሲገዛ ሲለውጥ ሰንብቶ ነበርና በግልም በኅብረትም ያ ይታረዳል፡፡ ፠ ሴቶችም ቅቤውን ሲያነጥሩ፣ በርበሬውን ሲደልሁ፣ ለእንጀራና ዳቦ የሚሆነውን ዱቄት ሲያዘጋጁ ለጠላ የሚሆነውንም እኸል ሲያሰናዱ አይቡን በልዩ ልዩ ቅመም መጣጣ ሲያደርጉና ባዶ ማለትም ወገሚት የተባለውን በሽንኩርት፣ በጤና አዳም፣ ጣዕሙ እንዳይለወጥ ሲቀምሙ፤ እንደ መከለሻ፣ ጥቁር አዝሙድ የመሳሰሉትንም ሰንብተው ዝግጅቱ ተከናውኖ ነበር፡፡ ፠ ጧትም ይህ የመግደፊያ ዝግጅት በየቤታቸው ለሌላቸው ድኾች በየመንደሩ እየተዞረ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባለ ከሥጋውም፣ ከአይቡም፣ ከቅቤውም ከመጣጣሙም፣ ከእርጐውም ይታደላል፡፡ ፠ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባባለ በመጠራራት ዐብሮ ሲበላ ሲጠጣ ልዩ ልዩ ጨዋታ ሲጨዋወት ለንስሐ አባትና ለሽማግሌዎች፤ ለወላጅ አባትና እናት፤ ለወንድምና ለእኅት ለወዳጅ ዘመድም የአክፋይ ዳቦ፣ ወይም የሥጋ ወጥና የድሮ ወጥ፣ ግፍልፍል ሲወስድ ይሰነብታል፡፡ ፠ የቻለም ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ እየተገባባዘ በዓሉን በፍስሐና በሐሴት ሲያከብር ይከርማል፡፡ ‹‹ሕያው ተንሥአ እሙታን (ሕያው ከሙታን ተነሣ፡፡)›› /ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤    ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/  የተዘጋጀ ::
   #share
@zemarian
352 views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ