Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemarian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.67K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-06 16:41:43
#ዮሐንስ ፡ አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በ ፡ አቤል ፡ በገና


179 views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 20:18:02 ሰበር_ዜና 
ቅዱስ ሲኖዶስ የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫን አካሔደ !!!


* ሲመታቸው ሐምሌ 9 ይከናወናል ፤
* ከነገ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠና ይገባሉ፤

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በአካሔደው ልዩ ስብሰባ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በተደራቢነት ተይዘው ለቆዩ ክፍት በኾኑና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ የሚመደቡ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳትን ምርጫ አካሒዷል፡፡

በዚኽም መሠረት፡-
#ለኦሮሚያ_ክልል_ሰባት_አህጉረ_ስብከት

1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ - ምዕራብ አርሲ - ሻሸመኔ ሀገረ ስብከት
2. አባ ወልደ ገብርኤል አበበ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
3. አባ ጥላሁን ወርቁ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
4. አባ ዓምደ ሚካኤል ኀይሌ - ሆሮ ጉድሩ ወለጋ - ሻምቡ ሀገረ ስብከት
5. አባ ኀይለ ማርያም ጌታቸው - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
6. አባ ተክለ ሃይማኖት ገብሬ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
7. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

#ለደቡብ_ኢትዮጵያ_ሁለት_አህጉረ_ስብከት

8. አባ ክፍለ ገብርኤል ተክለ ሐዋርያት - ጌድኦ አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት
9. አባ ስብሐት ለአብ ወልደ ማርያም - ዳውሮ እና ኮንታ ሀገረ ስብከት


ምንጭ :- የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
964 views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 20:14:50 Watch "#አመ_ለሰኔ_፳፱_በዓለ እግዚአብሔር
#መምህር_ሲራክ #መዝሙረ_ማኅሌት" on YouTube


883 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 21:40:44
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የመጪዉ 10 ዓመታት የመሪ እቅድ ሥልጠና በብፁዕ ቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ በረከት ተከፈተ::

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በመሪ እቅድ መምሪያ አሰናጅነት የ10 ዓመታት መንፈሳዊና ዘላቂ የልማት ግቦች ሀገር ዐቀፍ ጉባኤ በእግዚአብሔር ኃይል ጠንካራና ሁለገብ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረ ሰብን ለመገንባት እንተጋለን በሚል ርዕስ ለመላው ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና ተወካዮች ከሰኔ 26 እስከ 28 ቀን 2015 ዓ,ም የሚቆይ የ3 ቀናት ሥልጠና በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ አዳራሽ እየተሰጠ ነው ::

በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን በመሪ ዕቅድ ዋና መምሪያ ኃላፊ በክቡር ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ ገለጻ ተደረጓል።

ቀጥሎም በብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልእክት ከተለላልፈ በኋላ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሰፊ ቃለ ምዕዳንና ቡረኬ ከሰጡ በኋላ ጉባኤው ተከፍቷል

የብፁዕ ወቅዱስነታቸው ቡራኬ ይድረሰን!

ምንጭ፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
1.4K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 21:40:43 ‹‹እለ ይዘርኡ በአንብዕ ወበኃሤት የአርሩ፤ በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይሰበስባሉ›› (መዝ.፻፳፭፥፭)

ስንዱ እመቤት በሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የወቅቶች አከፋፈል መሠረት ከሰኔ ፳፮ ቀን እስከ መስከረም ፳፭ ያለው ጊዜ ዘመነ ክረምት ይባላል፡፡

“ክረምት” የሚለው ቃል ‘ከርመ፣ ከረመ’ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ወርኃ ዝናም፣ ወርኃ ነጎድጓድ፣ ዘመነ ባሕር፣ ዘመነ ነጎድጓድ፣ ዘመነ አፍላግ፣ ዘመነ ጠል፣ ዘመነ ደመና፣ ዘመነ መብረቅ… ማለት ነው፡፡ (ጥዑመ ልሳን ያሬድና ዜማው) ይህ ወቅት ከትርጓሜው እንደምንረዳው የሰው ልጅን ጨምሮ ተንቀሳቃሽ ለሆኑ ፍጥረት ሕይወት ከባድ የሚሆንበት ግን ደግሞ ለመኖር የሚያስችለውን ልብሱንና ጉርሱን የሚያገኘው በክረምት አማካኝነት እንደሆነ ከጥቅሱ እንረዳለን፡፡

ዘመነ ክረምት፡- የዝናም፣ የዘርና የአረም ወቅት በመሆኑ ምድር በጠል ዝናም ትረካለች፡፡ ዕፅዋት አዝርዕትና አትክልት በቅለው፣ ለምልመው የሚያድጉበት፣ ምድር አረንጓዴ ለብሳ በሥነ ጽጌያት የምታሸበርቅበት ወቅት ቢሆንም በሀገራችን አብዛኛው የግብርና ሥራ የሚከወንበት ጊዜ ስለሆነ በላይ ዝናቡ በውስጥ ርኃቡ በታች ዳጡ ማጡ የሚፈትነበት የመከራ ወቅት ነው፡፡ ‹‹እለ ይዘርኡ በአንብዕ ወበኃሤት የአርሩ፤ ሶበሰ የሐውሩ ወፈሩ እንዘ ይበክዩ ወፆሩ ዘርኦሙ፤ ወሶበ የአትው መጽኡ እንዘ ይትፌሥሑ፤ በሔዱ ጊዜ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ›› በማለት ቅዱስ ዳዊት ይናገራል፡፡ (መዝ.፻፳፭፥፭) ‹‹…….ክረምት ነበርና ስለውርጩ ጽናት ይንቀጠቀጡ ነበር›› እንዳለ ዕዝራ፡፡ (ዕዝ. ካል. ፱፥፲፩)

ወርኃ ክረምት የክርስትና ምሳሌ ነው፤ በክረምት ወር ገበሬ ብርዱንና ዝናሙን ሳይሰቀቅ ለሥራ ይሰማራል፤ በጋው እንደሚመጣ የደከመበትን፣ ዝናቡንና ርኃቡን፣ ድጡን ማጡን የታገሠበትን የድካሙን ፍሬ እንደሚያጭድ፣ ዘጠኝ ወር በጋም ፍሬውን እንደሚመገብ አምኖ የክረምቱን መከራም ይታገሣል፡፡ ክርስቲያንም በዚህ ምድር ላይ የሚደርስበትን መከራ ሁሉ ይታገሣል፤ በጸጋ የሚቀበለው በዚያኛው ዓለም ስለሚያገኘው ተድላና ደስታ ነው፡፡ ‹‹በዚህ ዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›› የሚለውን አምላካዊ ቃል ያውቃሉና፤ (የሐ.፲፮÷፳) ‹‹ዝግባውም የክረምት ዝናብ በእርሱ ላይ ካልወረደ ከሥሩ ይነቀላል›› እንደተባለው ያለዝናም ዝግባ፣ ያለመከራ ክርስትና እንደሌለ እንረዳለን፡፡ (፩ኛመቃ.፰፥፴፬)

አምላካችን እግዚአብሔር ለኖኅ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት በጋና ክረምቱ፣ ብርድና ሙቀቱ፣ ቀንና ሌሊቱ በተወሰነላቸው ጊዜ እየተፈራረቁ ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲሰጡ አድርጓቸዋል፡፡(ዘፍ.፰፥፳፪)

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅቶችን መሠረት አድርጋ ጌታዋን አብነት አድርጋ በወቅቶች እየመሰለች ወንጌልን ታስተምራለች፡፡ እናም የክረምቱን ዝናም፣ ነጎድጓድ፣ ጭቃውን፣ ብርዱን፣ ጨለማውን፣ ጎርፉን ወዘተ በክርስትናው መከራ እየመሰለች ስታስተምር እንዲሁም በዘሩ ቃሉን፣ በልምላሜው ተስፋውን፣ በመከሩ ምጽአቱን፣ በፍሬው መንግሥተ ሰማያትን እየመሰለች ትሰብክበታለች፡፡ ለዚህም አብነቷ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ወጸልዩ ባሕቱ ከመ ኢይኩን ጉያክሙ በክረምት ወበሰንበት፤ ነገር ግን ስደታችሁ በክረምት በሰንበት እንዳይሆንባችሁ ለምኑ›› በማለት አስተምሯልና፡፡ (ማቴ.፳፬፥፳) ለምን ቢሉ ክረምት ላዩ ውኃ ታቹ ውኃ ነው፤ አያሸጋግርምና ሰንበትም ዕለተ ዕረፍት ስለሆነ መንገድ ቢስቱ የሚያመላክት አይገኝምና፤ አንድም ‹‹ዐርፋለሁ ባለበት ጊዜ ስደት ቢመጣ ከቀቢጸ ተስፋ ይደርሳልና በሰንበትና በክረምት እንዳይሆንባችሁ ጸልዩ›› አለ፡፡

ቤተ ክርስቲያን ወቅቶችን እንዲህ በመከፋፈል በወቅቱ ከሚታየው የተፈጥሮ ሁኔታ ጋር ምእመናን ሕይወታቸውን እንዲመረምሩና ለንስሓ እንዲበቁ አጥብቃ የምታስተምራቸው ለዚህ ነው፡፡ በተለይ ቅዱስ ያሬድ በድርሰቶቹ ከደመናው፣ ከዝናቡ፣ ከልምላሜው፣ ከአበቦች፣ ከፍሬው ወዘተ እያስማማ ልብን በሚማርክ ዜማ በብዙ መልኩ አስተምሮናል፡፡ ‹‹ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሁ ነድያን፤ ይጸግቡ ርኁባን፤ የዝናም ድምፅ ተሰማ፤ ዝናም በዘነመ ጊዜ ችግረኞች ይደሰታሉ፤ ረኃብተኞችም ይጠግባሉ›› ሲል ያሰናስለዋል፡፡

የክርስትናችን ክረምት አልፎ ለመከር እንድንበቃ፣ ስደታችን በሰንበትና በክረምት ሆኖብን በቀቢጸ ተስፋ እንዳንጠፋ፣ በቅጠል ወራት ሳይሆን በፍሬ ወራት እያለቀስን ተሰማርተን፣ ደስ እያለን እንድንመለስ አብዝተን እንጸልይ፡፡ ‹‹እነሆ ክረምት ዐለፈ፤ ዝናቡም አልፎ ሄደ›› እንዳለ ጠቢቡ ሰሎሞን የክርስትናችን ክረምት የመከራችን ዝናብ ከእኛ ላይ በቶሎ ያልፋል፡፡ (መኃ.፪፥፲፩)

አምላካችን እግዚአብሔር መከራና ችግሩን ያሳልፍልን፤ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
1.2K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 12:54:50 ዘምሩ ለእግዚአብሔር
2.0K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 20:15:24
#የእንኳን_አደረሳችሁ_መልዕክት
#share #share #share
#felegeselam2
#አብርሂ_ፈለገ_ሰላም
2.3K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 20:15:24    ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥
#ሕንጸተ_ቤተ_ክርስቲያን( ከሰኔ  20_ 21 )
   ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥
       
በመጽሐፈ ስንክሳር እንደ ተመዘገበልን ሰኔ ፳ (20) ቀን በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ ሀገር የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውሃ በሦስት ድንጋዮች በተወደደ ልጇ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የታነጸበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ከሚከብሩ ከእመቤታችን 33 በዓላት አንደኛው ነው፡፡
ጌታችን በዐረገ በስምንተኛው ዓመት ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ገብተው በክርስቶስ ስም አሳምነው ብዙ አሕዛብን ካጠመቁ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩላቸው ወደዱ፡፡ በዚህ ጊዜ ርዕሰ ሐዋርያት እያለ እኛ መሥራት አይገባንም ብለው ለሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ እርሱም ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር መጥቶ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ ጋር በኢየሩሳሌም ተገናኙ፡፡
በዚያም በአንድነት ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ ጌታችን የሞቱትን አስነሥቶ፣ ያሉትንም ጠርቶ ቅዱሳን ሐዋርያትን በፊልጵስዩስ አገር ሰብስቦ ‹‹በእናቴ በድንግል ማርያም ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚሠራዉን የአብያተ ክርስቲያናት ሥራ ላሳያችሁ ፤ ሥርዓቱንም ላስተምራችሁ ሰብስቤአችኋለሁ›› ብሎ ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡ በዚያ ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮችንም የተራራቁትን አቀራርቦ ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፤ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡
ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሰም እሳት ሲያገኘው እንዲለመልም፣ ድንጋዩ በእጃቸው ላይ እየተሳበላቸው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ፈጽመዉታል፡፡ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራዉም ጌታችን በዐረገ በ፲፱ኛው፤ እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ሲኾን፣ በ፳፩ኛው ቀን (በማግሥቱ) ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችን ጋር ከሰማየ ሰማያት መጥቶ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ኾኖ ቀድሶ ካቈረባቸው በኋላ ‹‹እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ፤ ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ›› ብሎ አዝዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡
ይህ ታሪክ ብዙ ምሳሌዎች አሉት፡፡ ይኸውም፡- የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ቁመት በነገሥታት ዘመን የነበሩ የ፳፬ቱ ነቢያት፤ አንድም የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ሲኾን፣ ወርዱ ደግሞ የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፡፡ ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴ አምሳል ሲኾኑ፣ ከታች አቀማመጣቸው ሦስት፤ ከላይ ሕንጻቸው አንድ መኾኑ የሥላሴን ሦስትነትና አንድነት ያመለክታል፡፡

የሠሩትም ሦስት ክፍል አድርገው ሲኾን፣ ይህም የመጀመሪያው የታቦተ አዳም፤ ሁለተኛው የታቦተ ሙሴ፤ ሦስተኛው የታቦተ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ዳግመኛም የሦስቱ ዓለማት ማለትም የመጀመሪያው የጽርሐ አርያም፣ ሁለተኛው የኢዮር፣ ሦስተኛው የጠፈር ምሳሌ ነው፡፡

አንድም መጀመሪያው የኤረር፣ ሁለተኛው የራማ፣ ሦስተኛው የኢዮር አምሳል ነው፡፡ በኤረር፡- መላእክት፣ መኳንንት፣ ሊቃናት፤ በራማ፡- ሥልጣናት፣ መናብርት፣ አርባብ፤ በኢዮር፡- ኃይላት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌል ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ዘጠኙ ነገደ መላእክት የዘጠኙ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን (መዓርጋተ ክህነት) አምሳል ሲኾኑ፣ ይኸውም መላእክት – የመዘምራን፤ መኳንንት – የአናጕንስጢሳውያን፤ ሊቃናት – የንፍቀ ዲያቆናት፤ ሥልጣናት – የዲያቆናት፤ መናብርት – የቀሳውስት፤ አርባብ – የቆሞሳት፤ ኃይላት – የኤጲስ ቆጶሳት፤ ሱራፌል – የጳጳሳት፤ ኪሩቤል – የሊቃነ ጳጳሳት አምሳሎች ናቸው፡፡
ይህም በታች (በምድር) የሚኖሩ ደቂቀ አዳም ከቅዱሳን በቀር ወደ ላይ (ወደ ሰማይ) መውጣት እንደማይቻላቸው፣ ከመዘምራን እስከ ጳጳሳት ድረስ ያሉ ካህናትም ከእነርሱ በላይ ያሉትን መዓርግ መሥራት (መፈጸም) እንደማይቻላቸው ያጠይቃል፡፡ እንደዚሁም በላይ የሚኖሩ መላእክት ወደ ታች መውረድ እንደሚቻላቸው ሊቃነ ጳጳሳትም ከእነርሱ በታች ያሉ ካህናትን ተልእኮ መፈጸም (መሥራት) እንደሚቻላቸው ያስረዳል፡፡
በጽርሐ አርያም መንበረ ብርሃን (የብርሃን መንበር)፤ ታቦተ ብርሃን (የብርሃን ታቦት)፤ መንጦላዕተ ብርሃን (የብርሃን መጋረጃ)፤ እንደዚሁም ፬ ፀወርተ መንበር (መንበሩን የሚሸከሙ)፤ ፳፬ አጠንተ መንበር (መንበሩን የሚያጥኑ) መላእክት አሉ፡፡ ጽርሐ አርያም – የመቅደስ፤ መንበረ ብርሃን – የመንበር፤ መንጦላዕተ ብርሃን – የቤተ መቅደሱ መጋረጃ፤ ፬ቱ ፀወርተ መንበር – የ፬ቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወይም የመንበሩ እግሮች፤ ፳፬ቱ አጠንተ መንበር – የጳጳሳት (የኤጲስ ቆጶሳት) አምሳሎች ናቸው፡፡

   #ሰኔ ጎልጎታ፦ በሌላ በኩል ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህ ቀን (ሰኔ 21) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ ላይ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሏታል::

የድንግል እመቤታችን ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን:: !!!
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን !!!
በዘመናችን የመጣብንን ወረርሽኝ በቸርነቱ ያስታግስልን አሜን!!!!
✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥ ✥
2.2K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 20:15:24 እስመ አነሂ ስሕትኩ አበው ቅዱሳን አርትዑ በመንፈስ ቅዱስ።
1.4K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 02:04:53

106 views23:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ