Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemarian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.65K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 39

2022-09-24 20:38:11 መስቀል አበባ

መስቀል አበባ ነው ውብ አበባ
አደይ አበባ ነው ውብ አበባ

መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር አደይ አበባ ስለስቅለቱ
መስቀል አበባ እሌኒ አገኘች
አደይ አበባ ደገኛይቱ

መስቀል አበባ ጥራጊ ሞልተው
አደይ አበባ አይሁድ በክፋት
መስቀል አበባ ጢሱ ሰገደ
አደይ አበባ መስቀል ካለበት

መስቀል አበባ ወንዙ ጅረቱ
አደይ አበባ ሸለቆ ድሩ
መስቀል አበባ አሸብርቀው ደምቀው
አደይ አበባ ላንተ መሰከሩ
138 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 20:38:11
★ @zemarian ★
#ዝንቱ_መስቀል

ዝንቱ መስቀል ኀብሰተ ሕይወት አፍረየ አውነዘ ለነ ደመ ወማየ አውኀዘ ለነ/2/
ከመ ጌራ ወርቅ ጸሩይ ሥርግው ወባህርይ መስቀል ነቢሮ ያስተርኢ ላዕለ ርዕስየ/2/

በህብረት_እናመስግን
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ

★ @zemarian ★
103 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 19:42:25 Share 'መ17(1) ሥርዓተ ማኅሌት.pdf'
512 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 19:28:17
በመስከረም 8 የተካሄደው የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ኅብረት ማስጀመሪያ ሙሉ መርሐግብር በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ቅዳሜ መስከረም 14 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይተላለፋል።
ትምህርት:- ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

የዕለቱ እንግዶች:- ዲ/ን ፕ/ር እንግዳ አበበ እና ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ

የቀጣይ ሥራ ፕሮጀክት ገለጻ:- ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ
636 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 19:28:17
ኑ! መስቀልን በመስቀል አደባባይ እናክብር!
564 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 19:28:17
አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ አልተጠራም።
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
መስከረም ፲፩ ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
"""""""""""""""""""""

በአንዳንድ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ እንደተጠራ ተደርጎ እየተዘገበ ያለው ትክክለኛ ያልሆነ ዘገባ ከመሆኑም በላይ የተጠራ አስቸኳይ የምልዓተ ጉባኤ የሌለ መሆኑን እንገልጻለን።

በግንቦት ፳፻ ፲ወ፬ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተወሰነው መሰረት የጥቅምቱ ምልዓተ ጉባኤ ከመጀመሩ አስቀድሞ በህግ ነክ ጉዳዮችና ደንቦች ዙሪያ በተለይም በህገ ቤተክርስቲያን ማሻሻያዎች የተመለከቱ አጀንዳዎችን ከጥቅምቱ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ቀደም ብሎ ለመመልከት በተወሰነው መሰረት  ብፁዓን አባቶች ቀድመው በመገኘት እንዲወያዩ ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የተላለፈ የጥሪ መልዕክት  እንጂ አስቸኳይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ያልተጠራ መሆኑን እንገልጻለን።
ምንጭ የኢኦተቤክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
478 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 19:28:17
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሄደ።

ማኅበረ ቅዱሳን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማካሄድ ባቀደው አገልግሎት መሠረት የባሕር ዳር ማእከል "የተሰጠህን አደራ ጠብቅ" (፩ኛ ጢሞ. ፮ ፥ ፰) በሚል ርዕስ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኀብረት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር መስከረም ፰/ ፳፻፲፭ ዓ/ም በማእከሉ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አካሄደ። በባሕር ዳርና አካባቢው የሚገኙ ከ300 በላይ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን በተገኙበት በዚህ መርሐ ግብር ቴክኖሎጅን በመጠቀም በበይነ መረብ (Virtual) ትምህርተ ወንጌል በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ፣ የሕይወት ተሞክሮ በዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እና በዲ/ን ፕ/ር እንግዳ አበበ ቀርቧል።

ከዚህ በተጨማሪ በመርሐ ግብሩ በግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኀብረት ወደፊት ለመሥራት የታሰበው የፕሮጀክት ንድፈ ሃሳብ ቀርቦ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን ብሎም ለሀገር ያለው በጎ አስተዋጽዖ የተብራራ ሲሆን ይህን አገልግሎት የሚያደናቅፉ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የቀድሞ ምሩቃን ኃላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል።

መርሐ ግብሩ  በዓመት ፬ ጊዜ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን ይህ የመጀመሪያውና የመመስረቻው ጉባኤ በሁሉም ማእከላት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ተካሂዷል።
638 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 20:03:05
1.4K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ