Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሄደ። | መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሄደ።

ማኅበረ ቅዱሳን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማካሄድ ባቀደው አገልግሎት መሠረት የባሕር ዳር ማእከል "የተሰጠህን አደራ ጠብቅ" (፩ኛ ጢሞ. ፮ ፥ ፰) በሚል ርዕስ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኀብረት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር መስከረም ፰/ ፳፻፲፭ ዓ/ም በማእከሉ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አካሄደ። በባሕር ዳርና አካባቢው የሚገኙ ከ300 በላይ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን በተገኙበት በዚህ መርሐ ግብር ቴክኖሎጅን በመጠቀም በበይነ መረብ (Virtual) ትምህርተ ወንጌል በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ፣ የሕይወት ተሞክሮ በዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እና በዲ/ን ፕ/ር እንግዳ አበበ ቀርቧል።

ከዚህ በተጨማሪ በመርሐ ግብሩ በግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኀብረት ወደፊት ለመሥራት የታሰበው የፕሮጀክት ንድፈ ሃሳብ ቀርቦ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን ብሎም ለሀገር ያለው በጎ አስተዋጽዖ የተብራራ ሲሆን ይህን አገልግሎት የሚያደናቅፉ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የቀድሞ ምሩቃን ኃላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል።

መርሐ ግብሩ  በዓመት ፬ ጊዜ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን ይህ የመጀመሪያውና የመመስረቻው ጉባኤ በሁሉም ማእከላት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ተካሂዷል።