Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemarian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.93K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-24 20:56:38 ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፤
*******

ሐምሌ ፲፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም አዲስ አበባ
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

1. በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነ ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙኃን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም በዚህ የዶግማና የቀኖና ጥሰት ተግባር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእጅጉ አዝኗል፡፡

2. በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል፡፡

3. የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡

4. በየደረጃ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምዕመናን ከአሁን ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው ፈተና በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን በመቆም ላሳያችሁት ጽናት እያመሰገንን አሁንም በደረሰው ፈተና እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

6. ምንም እንኳን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ጥሪው በደብዳቤ የተላለፈ ቢሆንም የመልእክቱ በፍጥነት መድረስ ካለው ስጋት አንጻር የችግሩን ተደጋጋሚነትና አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃላችሁ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡


7. ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ሚዲያዎችና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ይህን መልዕክት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መልእክቱን በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም.
798 views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 20:17:23
#ፍልሰታን_በንስሐ_እንቀበላት
861 views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 22:55:16 ዘማሪ ሚኪያስ
ክራር ኢዮሲያስ አበራ
@zemarian
1.2K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 22:55:16 ሐምሌ 19
እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል አደረሳችሁ::
☞ በዚህ ዕለት ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት እየሉጣን
ከእሳት አድኗቸዋል::
✞ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም/ጣሊያን/ አንጌቤን ሲሆን አባቱ ቆዝሞስ እናቱ ደግሞ ኢየሉጣ ትባላለች፡፡
በዘመነ ሰማዕታት በጨካኙና በአረመኔው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ
መንግሰት በ ፫፻፫ /303/ ዓ.ም አብያተክርስቲያናት ይውደሙ አብያተ ጣዖታት ይስፋፉ የሚል አዋጅ ታወጀ፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ ቅድስት ኢየሉጣም የ ፫ /3/ ዓመት ሕጻን ልጇን ቂርቆስን ይዛ ወደ ኢቆንዩን የምትባል ከተማ ሸሸች፡፡
☞ መስፍነ ብሔሩ እለእስክንድሮስ ክርሰቶስን ካጂ ለጣዖት ስገጂ ቢላት
"ዓይን እያለው ለማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ በቃልህ አዘህ በእጅህ ሰርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም" አለች::
አይሆንም ካልሽማ በሰይፍ ትቀጫለሽ ብሎ አስፈራራት እስኪ ይህን ሕፃን ጠይቀው አለችው አንተ ሕፃን ወርቅ እሰጥሀለሁ ለዚህ ጣዖት ስገድ አለው::
መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና "ራሳቸውን ማዳን ለማይችሉ ርኩሳን ጣዖታትህ አልሰግድም" አለው::
ተበሳጭቶም የብረት ጋን ውስጥ ውኃ አስፈላ የፍላቱም ድምፅ እንደ ክረምት ነጎድጓድ 24ምዕራፍ ድረስ ይሰማ ነበር::
ሊከቷቸው ሲወስዷቸው እየሉጣ ልቧ በፍርሀት ታወከ ሕፃኑ ቂርቆስም እናቴ ሆይ አትፍሪ አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንስ ያድነን የለምን ? እያለ ልብሷን እየጎተተ ከእሳቱ ቀረቡ ወደ ጋን ውስጥም ከተቷቸው::
✞ ያን ጊዜ ጌታ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ ውኃውን አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል::በወጡም ጊዜ ልብሳቸው ሳይበሰብስ ሰውነታቸው ሳይሸበሸብ ቢያዩ ከአሕዛብ ብዙዋቹ አምነው ሰማዕትነት ተቀብለዋል::
✞የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ፈጥኖ ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስና የቅድስት እየሉጣ ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን::
<<ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
<<ወለ ወላዲቱ ድንግል>>
<<ወለ መስቀሉ ክቡር>>
1.3K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 22:55:16
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እና ቂርቆስ ወኢየሉጣ ዓመታዊ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን

የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን ።
ዝግጅት ክፍሉ።
@zemarian
905 views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 22:55:16 @zemarian
888 views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 22:55:16 @zemarian
843 views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 22:55:15
@zemarian
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ገብርኤል "ሐምሌ ፲፱"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ: በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ: ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ለዓለም ወለዓለመ ዓለም: ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል: ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል: ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ: በአሐቲ ቃል።
@zemarian
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት #ለቂርቆስ ሕጻን፡፡
@zemarian
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ #ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ።
@zemarian
ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት #ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።
@zemarian
ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ: ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም
መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።
@zemarian
መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ #ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡

ዚቅ
#ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: #ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።
@zemarian
ወረብ
"#ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/
ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን #ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ።

ዚቅ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት።

ወረብ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/
ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/
@zemarian
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን #ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ።

ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/
ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ #ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ።
@zemarian
ዚቅ
በጸሎቱ ለቅዱስ #ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡

ወረብ
በጸሎቱ ለቅዱስ #ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/
ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር #ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡

ዚቅ
በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: #ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡

ወረብ
በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ/፪/
ባርካ #ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/
@zemarian
መልክዐ ኢየሉጣ
ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: #ኢየሉጣ ቅድስት #ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: #ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ #ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡

መልክዐ ገብርኤል
ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: #ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ።
@zemarian
ዚቅ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት።

ወረብ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት #ሊቀ_መላእክት/፪/
እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/

ምልጣን
ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ።

አመላለስ
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/
@zemarian
ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/
ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
@zemarian
እስመ ለዓለም
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ #ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡
@zemarian
ወረብ
ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/
እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/

አመላለስ
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/

======== @zemarian ======
===========
1.5K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-16 11:23:14 ፮- ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ተብለው ተሠይመው በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

፯-  ቆሞስ አባ ዘተክለሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ተብለው ተሠይመው በሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት

፰-  ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተብለው ተሠይመው በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት

፱-  ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ተብለው ተሠይመው በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል።

ምንጭ: ሕዝብ ግንኘነት መምሪያ
2.9K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-16 11:23:14
የኢኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ፱ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች።


ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለዘጠኝ አህጉረ ስብከት የተመረጡት ፱ ቆሞሳት ዛሬ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተፈጸመ ሥርዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ እድ በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመዋል።

ከሌሊቱ ፱ ስዓት ጀምሮ በተከናወነው ሥርዓተ ሢመት ላይ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች።፣ ግብዣ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡ ሊቃውንት፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ምእመናን ተገኝተዋል።

በዚህም መሠረት የሚከተሉት አባቶች በቅድስት ቤተክርስቲያን የተሰጣቸውን ሥያሜ ይዘው ለተጠቀሱት አህጉረ ስብከት ተመድበዋል።

፩-  ቆሞስ አባ ክንፈገብርኤል ተክለማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ተብለው ተሠይመው ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

፪-  ቆሞስ አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተብለው ተሠይመው ለምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት

፫-  ቆሞስ አባ ስብሐትለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተብለው ተሠይመው ዳውሮና ኮንታ ሀገረ ስብከት

፬-  ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተብለው ተሠይመው ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት

፭-  ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስም ተብለው ተሠይመው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
2.4K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ