Get Mystery Box with random crypto!

የኢኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፱ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች። ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ | መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የኢኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ፱ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች።


ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለዘጠኝ አህጉረ ስብከት የተመረጡት ፱ ቆሞሳት ዛሬ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተፈጸመ ሥርዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ እድ በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመዋል።

ከሌሊቱ ፱ ስዓት ጀምሮ በተከናወነው ሥርዓተ ሢመት ላይ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች።፣ ግብዣ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡ ሊቃውንት፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ምእመናን ተገኝተዋል።

በዚህም መሠረት የሚከተሉት አባቶች በቅድስት ቤተክርስቲያን የተሰጣቸውን ሥያሜ ይዘው ለተጠቀሱት አህጉረ ስብከት ተመድበዋል።

፩-  ቆሞስ አባ ክንፈገብርኤል ተክለማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ተብለው ተሠይመው ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

፪-  ቆሞስ አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተብለው ተሠይመው ለምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት

፫-  ቆሞስ አባ ስብሐትለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተብለው ተሠይመው ዳውሮና ኮንታ ሀገረ ስብከት

፬-  ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተብለው ተሠይመው ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት

፭-  ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስም ተብለው ተሠይመው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት