Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemarian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.65K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-14 08:42:42 በyou tube ዘስቅለት ዘ፱ቱ ሰዓት ዜማ
907 views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 00:36:16 ከበዓል በኃላ ለሰርጎ , ለልጆቾ ክርስትና የዲኮር ስራ ማሰራት ይፈልጋሉ ?



ለ ሰርግ                            ለ ክርስትና
ለ ልደት                            ለ ቀለበት
ለ ገዓት                             ለ ሽምግልና
ለ ተማሪዎች ምረቃ           ለ ልጆች ልደት
ለ ቤት ምርቃት                   ለ ሆቴል ምረቃ
ለ ስብሰባ አዳራሾች          ለ ቤተሰብ ኘሮግራሞች
ለ ሰርግ ለመኪና ዲኮር
በ ቤተክርስቲያን ስርዓት ለሚፈፀሙ ሰርጎች እና ኘሮግራሞች

ለተለያዮ ዝግጅቶችም ጭምር የተለያዮ የዲኮሪሽን ስራዎችን እንሰራለን እንዲሁም የተለያዮ የዲኮር እቃዎችን እናቀርባለን !
       

     
              ይህን ይጫኑት  ...  ይህን ይጫኑት

█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█


Tel .   +251961064953
                 +251703504953
.
93 views21:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 21:18:56 ኪራላይሶ
በዘማሪ ብርሃኑ ጫኔ
ክራር ኢዮሲያስ አበራ
@zemarian
444 views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 21:18:56 #ዓርብ
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

@zemarian
428 viewsedited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 21:18:56
421 views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:41:18 ዘማሪ ዲያቆን በሃይሉ ተበጀ
@zemarian
488 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:41:17
#ዓርብ
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

@zemarian
488 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:41:17 የጉልባን ታሪክ
@zemarian
➛ ጉልባን ከባቄላ ክክ ከሰንዴ ወይም ከተፈተገ ገብስ እና ከሌሎችም ጥራጥሬዎች ጥሬውን ወይም ከክቶ እንደ ንፍሮ ተቀቅሎ የሚዘጋጅ ምግብ ነው ። የዕለተ ሐሙስ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመ በኋላ ምእመናን ወደ ቤታቸው ሄደው ጉልባን ሠርተው ይመገባሉ ። ለዚህም ሁለት ትውፊታዊ መሠረት እንዳሉት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያስረዳሉ እንመልከት፦ ፩ የኦሪት ምሳሌ ለመፈጸም እስራኤል ለ215 ዓመታት በግብጻውያን በባርነት ተይዘው በግፍ ተጨቁነው መኖራቸው ይታወቃል የእግዚአብሔር ፍቃድ ሁኖ እግዚአብሔር ሙሴን ፈርኦንን ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል ብለህ ንገረው ብሎት ነበር ። ሙሴም ፈርኦንን እግዚአብሔር ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል አለው ፈርኦንም እስራኤል እለቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማነው ? እግዚአብሔርን አላቅም እስራኤንም ደግሞ አለቅም በማለት አሻፈረኝ ብሎ ነበር ። እግዚአብሔርም የኃይል ስራውን በሙሴ አሳየ በመጨረሻም እምቢ ሲል እግዚአብሔር ከእንስሳትም ከሰውም ወገን በመልአክ በሞተ በኩር ግብጽ ተቀሰፈች በዚህም ፈርኦን ደንግጦ ሕዝበ እስራኤል ለመልቀቅ ተገዷል ። በዚህ ጊዜ ህዝቡ ለመውጣት ስለቸኮሉ በቤት ያለውን እህል ያልተፈጨውን ንፍሮ ቀቅለው የተፈጨውን ቂጣ ጋግረው በልተው ነው ጉዞ የጀመሩት ። እስራኤልም ከግብፅ ከወጡ በኋላም የነጻነት በዓላቸውን ሲያከብሩ ያልቦካ ኪጣ ጋግረው ንፍሮ ቀቅለው በግ አርደው ከባርነት በወጡበት ዕለት የነበረውን ሁኔታ ያስቡ ዘንድ ታዘዋል ። (ዘጸ ፲፫ ፥፩) ፋሲካ የሚለውም '' ፓሢሕ '' ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ማለፍ መሻገር ማለት ነው ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሴተ ሐሙስ በአልዓዛር ቤት ተገኝቶ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ይህን በዓል አክብሯል ። እኛም አሰቀድሞ በሙሴ ላይ አድሮ ሕገ ኦሪትን የሠራ ሕዝቡንም መርቶ ከነዓን ያደረሰው እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሰውን ስጋ ለብሶ ክርስቶስ ተብሎ መገለጡን በማመን ፤ ክርስቶስ ራሱ አዲሱን ሕግ ከመሥራቱ አሰቀድሞ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን እንዳከበረ ሁሉ እኛም አዲስ ኪዳን ጥላ /ምሳሌ/ የሆነውን ሥርዐት እኛ ጉልባን በመመገብ ለመታሰቢያ እናደርጋለን ።
፪ የኀዘን ሳምንት መሆኑን ለማጠየቅ ፦ እንደ ሀገራችን ባሕል ንፍሮ እንባ አድርቅ ይሉታል ። ብዙ ጊዜም ለለቀስተኞች ይሠራል ። አንድም ሞት ተናግሮ አይመጣምና ሞት በድንገት ሲመጣ ለእንግዳ መሸኛ ቶሎ ሊደርስ የሚችል ምግብ ንፍሮ ስለሆነ በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ለልቅሶ ቤት ንፍሮ የመቀቀል ልማድ አለ ።
➛ በሰሙነ ሕማማት ወቅት ምዕመናን በጌታችን መከራ ፣ ሞት እና በድንግል ማርያም ኀዘን ምክንያት ኀዘንተኞች ስለሆኑ ይህንኑ ለማመልከት ጉልባን ይመገባሉ ። የጉልባን ክርስቲያናዊ ትውፊት ይህንን ይመስላል እኛ ምዕመናን በቤተችን እንዲሰራ በመጠየቅ በመስራት ይህን ትውፊት ማስቀጠል ይኖርብናል ።
358 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:41:17 መምህር ኤርምያስ በገና a
ኬብሮም የዜማ መሣርያ ማሠልጠኛ እና ማምረቻ ተቋም ባለቤት
@zemarian
270 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:41:17
#ሐሙስ
#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

@zemarian
265 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ