Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemarian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.65K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-04 21:06:05 ወረቦቹ በyou tube ይኸው
240 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:06:05 Watch "#ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘመጋቢት_መድኃኔዓለም(፳፯) #በመምህር_ሲራክ አዘጋጅ፦ ዲ/ን ሱራፊ #በመዝሙረ_ማኅሌት" on YouTube


250 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:06:05 በቴሌግራም ደሞ ይኸው
246 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:06:05 በ you tube ይኸው
248 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 22:52:43 አስደሳች ዜና 


ከዚህ በፊት በገና በመስራት እና በየአላቹበት በማቅረብ የሚታወቀው ድህንፃ አውን ደግሞ ለውድ ኦርቶዶክሳዊ በሙሉ ለሰራ ፈጣሪዎች እና ስራ ለመፍጠር ላሰባቹ በሙሉ የምስራች ይዞላቹ ቀርቦል !


ሻማ ለማምረት
ጡዋፍ ለማምረት
ፈሳሽ ሳሙና(ላርጎ)
የተለያዩ ስራዎችን ጭምር..

እንዲሁም ሱቅ ከፍታቹ እቃ ማግኘት ላልቻላቹ በሙሉ ድህንፆ እናንተን ለማገዝ ዝግጅቱን ጨርሶል ወደናንተ ቀርቦላችዋል !

ስልክ . +251901570787



      የ Telegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ  !    


     
              ይህን ይጫኑት  ...  ይህን ይጫኑት

█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█

 
.
130 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 17:36:51
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መንከባከቢያ በመገኘት በዚያ የሚገኙ ደካሞችን በመጎብኘት ትምሕርትና ቡራኬ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
561 views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:44:29 "በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጣ"
(ሽራፊ ሃሳብ 1 ከኒቆዲሞስ ምንባብ)

ኒቆዲሞስ በውድቅት ሌሊት ወደ ጌታችን መጣ። ሌሊት እንግዲህ በቂ ብርሃን የሌለበት ፣ እንቅፋት የሚበዛበት ፣ ጭልም የሚልበት ፣ ግራ ቀኝ ቢያዩ ሰው የሚታጣበት ፣ ማጅራት ከሚመቱ ወንበዴዎች በቀር በመንገድ ሌላ ሰው የማያጋጥምበት ፣ ብርድና ቆፈን ሰውነትን የሚያስጨንቅበት ሰዓት ነው። ይህ የአይሁድ መምህር በሌሊት የመጣበት ምክንያቱ ብዙ ሲሆን ለእምነት ማነስ ማሳያ የሚሆን ሰው ነው።

ዛሬ ደግሞ ለአፍታ ኒቆዲሞስን "በሌሊት ወደ ኢየሱስ በመምጣቱ" በጥቂቱ እናመስግነው።  ብዙ እግሮች ወደ ኃጢአት በሚሮጡባት ሌሊት ወደ ክርስቶስ የሮጠውን ይህንን ሰው እስቲ እናድንቀው!  ይህንን የሌሊት ግርማ ሳይበግረው ወደ ኢየሱስ የተጓዘ የጨለማ ተጓዥ ፣ ይህንን ሰዓታት ቋሚ ፣ ይህንን ማሕሌት ቋሚ በጥቂቱ ብናመሰግነው ምን አለ? ከጌታ ፊት ቆሞ ቅኔ የተመራውን ፣ ስለ ልደት እየተናገረ ስለ ጥምቀት የሚያመሰጥረውን የፈጣሪን ቅኔ ተቀብሎ ሊያዜም ከጀመረ በኋላ መቀበል ሲያቅተው ጌታችን  "አንተ የአይሁድ መምህር ስትሆን ይህንን አታውቅምን?" ብሎ የገሠፀውን ኒቆዲሞስን እስቲ ዛሬ በበጎነቱ አርኣያ እናድርገው።

በሕይወታችን ውስጥ የተስፋ ብርሃን ጭልም ባለብን ጊዜ ፣ እንቅፋት በበዛብን ወቅት ፣ ግራ ቀኝ አይተን ሰው ባጣንበትና ብቸኝነት በዋጠን ሰዓት ፣ ክፉ ከማድረግ በማይመለሱ ጨካኞች በተከበብን ሰዓት እኛስ ወዴት እንሔዳለን?

ሕይወቱ "ሌሊት" የሆነበት ሰው ሁሉ  ወደ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ቢሔድ እንደሚሻለው ከኒቆዲሞስ የተሻለ ምሳሌ የለም። ሕይወቱ የጨለመ ባይሆን እንኳን ልቡ የጨለመበት ፣ በኃጢአት ጠል የጠቆረ ፣ በበደል ብርድ ቆፈን እጅ እግሩ የታሰረ ከእኛ መካከል ስንት አለ?

እመነኝ ፣ ተስፋ ቆርጠህ ቁጭ ብለህ እስከሚነጋልህ ብትጠብቅ አይነጋም። ይልቅ ተነሥና "በሌሊት ወደ ክርስቶስ ሒድ" እርሱ ተስፋ ለቆረጠው ማንነትህ ዳግመኛ መወለድ እንዳለም ይነግርልሃል። ኒቆዲሞስ ጌታችንን ሊያየው ሔዶ  ራሱ ታይቶ እንደመጣ አንተም ወደ እርሱ የቀረብህ እንደሆነ ራስህን ታያለህ።

በ"ሌሊት" ውስጥ ለሚኖር ሰው ነግቶ ፀሐይ ትወጣልኛለች ብሎ ከሚጠባበቅ ይልቅ በሌሊት እንደ ኒቆዲሞስ ተነሥቶ ወደ ጽድቅ ፀሐይ ወደ ክርስቶስ ቢሔድ ይሻለዋል።  ወደ እርሱ ለሚሔድ ሰው ሌሊቱ ይነጋል ፣ ክርስቶስ ያለበት ሌሊት ከቀን ይልቅ ብሩሕ ነው ፣ እውነተኛው ብርሃን ያለበት ጨለማም ጨለማ አይደለም። ስለ እርሱ "ጨለማም በአንተ ዘንድ አይጨልምም" ተብሎ ተጽፎአልና።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 16 2010
ኒቆዲሞስ
ናይሮቢ ፣ ኬንያ
226 views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:44:24 +++ የኒቆዲሞስ ክርስትና +++

ኒቆዲሞስ የሚለው ስም በዮሐንስ ወንጌል ብቻ ከተጻፉ ስሞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የዚህን ሰው ስም ባነሣበት ሥፍራ ሁሉ ‹አስቀድሞ በሌሊት የመጣው› የምትል ቅጽል ያስቀድማል፡፡ ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ ነው፡፡ በሀብቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ባለጸጋ ፣ በሹመቱ የአይሁድ ሸንጎ /synagogue/ አባል ፣ በትምህርቱ ደግሞ ጌታችን ራሱ እንደመሰከረለት ‹የእስራኤል መምህር› የሆነና አዋቂ ነው፡፡ የአይሁድ አለቃ ፣ የእስራኤል መምህር ኒቆዲሞስ ጌታችን ራሱ ለብቻቸው በቃል ምልልስ እያናገረ ጥያቄያቸውን እየመለሰ ካስተማራቸው ጥቂት ዕድለኛ ሰዎች አንዱም ነው፡፡ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅነት ያገኘንበትን ምሥጢረ ጥምቀት በጥልቀት እና በዝርዝር የተማረው የመጀመሪያው ሰውም ኒቆዲሞስ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ጌታችን ጥምቀትን በተግባር ሲመሠርት የዓይን ምስክር እንደነበረ ሁሉ ጥምቀት በትምህርት ስትመሠረት ደግሞ የዓይን ምስክሩ ኒቆዲሞስ ነው፡፡

በትምህርቱ መካከልም ባቀረበው ጥያቄ ‹ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ ስለ መወለድ› ጌታችን በምሳሌ አድርጎ ያስተማረው ሲሆን አላምን ብሎ ‹እንዴት ሊሆን ይችላል?› ብሎ ሲከራከር ደግሞ ገሥጾታል፡፡ ዛሬም ድረስ ኒቆዲሞስ መልስ ከተሠጣቸው በኋላ የሚነታረኩ ተከራካሪዎች ምሳሌ ሆኖ በሊቃውንት ይጠቀሳል፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያምን የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት በሙሉ ልብ በመቀበሏ በምናመሰግናት ጊዜም ‹እንደ ዘካርያስ ሳትጠራጠሪ እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ ቃሉን የተቀበልሽ› እያልን መሆኑ ይህን እውነታ ያጎላዋል፡፡

ኒቆዲሞስ ወደ ክርስትና ከመጣበት መንገድ ጀምረን በዮሐንስ ወንጌል ስንከተለው ቀስ በቀስ እያደገ የመጣ የመንፈሳዊነት ደረጃን እናገኛለን፡፡ የኒቆዲሞስ ክርስትና እንደ ወጣኒ (ጀማሪ) እንደ ማዕከላዊና እንደ ፍጹም በሦስት ደረጃዎች ላይ የሚታይ ሕይወት ሆኖ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ እንደሚከተለው እንመልከተው፡፡

ወጣኒው (ጀማሪው) ኒቆዲሞስ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ሳለ ያደረገውን ተአምር ተመልክተው ብዙ ሰዎች በስሙ አምነው ነበር፡፡ ያ ወቅት ጌታችን በቃና ዘገሊላ ሠርግ ቤት ውኃን ወይን ያደረገበትና ፣ በቤተ መቅደስ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ገሥጾ ያስወጣበት ነበር፡፡ ይህንን ምልክት ተከትለው ካመኑበት ብዙ ሰዎች አንዱ ታዲያ ኒቆዲሞስ ነበር፡፡ ይህ ሰው በጌታችን ቢያምንም ባመነበት ወቅት እምነቱን በልቡ ብቻ ይዞ አቆይቶ ነበር፡፡ ከዚያም በአሳቻ ሰዓት በማታ ወደ ጌታችን መጣና ‹መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን› አለው፡፡ ኒቆዲሞስ ጌታችንን እግዚአብሔር በረድኤቱ ተአምራትን እንዲያደርጉ ከሚያስችላቸው ጻድቃን እና ነቢያት ለይቶ አላየውም ነበር፡፡ ንግግሩም ከእርሱ ጋር ምልክቱን አይተው አምነው ከነበሩት ሰዎች ቁጥር መሆኑን በሚያሳይ መንገድ ‹እናውቃለን› የሚል የብዙዎች ወኪልነት ንግግር ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር እንግዲህ አምላካችን በዝርዝር ያስተማረው፡፡

ኒቆዲሞስን እንዲህ በሌሊት ያስመጣው ምንድር ነበር? ክርስቶስን በቀን በአደባባይ ሊያናግረው አይችልም ነበር? እሱ እንደሆነ በሔደበት መንገድ የሚለቀቅለት የአይሁድ አለቃ ነውና ጌታችንን ለማግኘት ሰዎች አገዱኝ ሊል አይችልም፡፡ ይህ እንግዲህ የኒቆዲሞስ የመጀመሪያው የክርስትና ደረጃ ነበር፡፡ እሱ አምላካችንን ስላደረገው ተአምር ሊያደንቀው ፈልጓል ‹እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው› ብሎ አመስግኖታል ፤ ሊከተለው ግን አልፈለገም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከጌታችን ጋር ሆኖ ሰዎች እንዲያዩት አልፈለገም፡፡ የጌታ ተከታይ ፣ ደቀመዝሙር ሆኖ መታሰብ አልፈለገም ፣ ጉዳዩ ክብሩን የሚነካበት መሰለው፡፡ የተማረ ነውና ‹ገና ይማራል እንዴ› ብለው እንዳይንቁት ለክብሩ ሳሳ ፣ በዚያ ላይ ደግሞ ጌታችን በአይሁድ ሹማምንት ዓይን የተናቀ ነበር፡፡ እርሱ ‹ግንበኞች እንደናቁት ድንጋይ› ነበር፡፡ ‹‹የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።›› ይላል ነቢዩ፡፡ /ኢሳ. ፶፫፥፫/ ታዲያ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ መታየት በዚያን ወቅት የሚያስከብር ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህ ፈራ ተባ እያለ በጨለማ መጣ፡፡

ወደ ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚመጣ ሰው አንዱ ፈተናው ይኼ ነው፡፡ ክርስትናችን በሰዎች ፊት የታወቀ እንዲሆን ፈቃደኞች የማንሆን ብዙዎች ነን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሰው ተብሎ ላለመታየት የሚሸሹ ብዙዎች ናቸው፡፡ ማዕተብ ማድረግ ፣ በቤተ ክርስቲያን አጠገብ ሲያልፉ መሳለም ፣ በአበው ትውፊት ጽዋዕ መጠጣት ወዘተ ማድረግ የሚከብዳቸው የሚጨነቁና የሚያፍሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ በሚሠሩበት መሥሪያ ቤት አካባቢ ስለ ሃይማኖታቸው ባይታወቅ የሚመርጡ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔዳቸው ባይሰማ ደስ የሚላቸው ኒቆዲሞሶች ብዙኃን ናቸው፡፡

የኒቆዲሞስ ችግር በክርስትናው ማፈሩ ብቻ አልነበረም፡፡ ክርስትና የሚያመጣበትን መዘዝ መፍራቱም ጭምር ነው፡፡ አይሁድ ‹‹እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኩራብ ይውጣ›› የሚል ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ (ዮሐ. ፱፥፳፪) በዚህ ሕግ ምክንያት በጌታችን አምነው እንኳን ስለ እርሱ ለመመስከር የሚፈሩ ብዙዎች ነበሩ፡፡ ‹‹ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና።›› (ዮሐ. ፲፪፥፵፪)

ኒቆዲሞስ ወደ ጌታ መጥቶ መማሩ እንዲታወቅ ያልፈለገውም ለዚህ ነበር፡፡ ለክርስትናው ምንም ዓይነት ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ለማድነቅ እንጂ መከራን ለመቀበል አልተዘጋጀም፡፡ ይህ ዓይነቱ ችግር ሌላው የክርስቲያናዊ ሕይወት ፈተና ነው፡፡ ሐዋርያው የክርስትናችንን ዓላማ ሲገልጥ ‹‹ስለ እርሱ ደግሞ መከራን ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፡፡›› ብሏል፡፡ (ፊል. ፩፥፳፱) ብዙዎቻችን ክርስትናችንን እንፈልገዋለን ፤ ሆኖም በክርስትናችን ምክንያት ቅንጣት መከራ እንኳን እንዲነካን አንፈልግም፡፡ በእግዚአብሔር በማመን ውስጥ ፈተናም አለ፡፡ ራሳችንን በእውነት ክርስቲያን ነኝ ብለን ለመጠየቅ ብንፈልግ አብረን መጠየቅ ያለብን በእውነት መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ወይ ማለት ጋር ነው፡፡ በእግዚአብሔር በማመናችን ምክንያት ምን የከፈልነው ዋጋ አለ? ለእርሱ ብለን የተውነው ነገር ምንድን ነው? ለእሱስ ብለን ያጣነው ነገር ይኖር ይሆን? ምንም ነገር ከሌለ ክርስትናችን ገና ያልጠነከረ ነው ማለት ነው፡፡

ማዕከላዊው ኒቆዲሞስ

ፈሪሳዊያንና የካህናት አለቆች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዘውት እንዲመጡ ሎሌዎች ላኩአቸው፡፡ እነዚህ ሎሌዎች ጌታችንን ይዘው እንዲመጡ ቢላኩም በጌታችን ጣዕመ ትምህርት ተደንቀው ተመስጠው ሲማሩ ውለው ባዶ እጃቸውን ተመለሱ፡፡ አይሁድ ‹ያላመጣችሁት ስለ ምንድን ነው?›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹‹እንደዚህ ሰው ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም›› ብለው መለሱ፡፡ ይህን ጊዜ አይሁድ ተቆጥተው ሎሌዎቹን ‹‹እናንተ ደግሞ ሳታችሁ? ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን መካከል በእርሱ ያመነ ሰው የለም፡፡ ሕዝቡም ያመነበት ሕግ የማያውቅ ርጉም ስለሆነ ነው›› ብለው ገሠጹአቸው፡፡ እናንተ ያመናችሁት ባለማወቃችሁ ነው ፤
221 views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 06:30:26 ዘማሪት መስከረም ወልዴ
ክራር ኢዮሲያስ አበራ
@zemarian
318 views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 21:48:40 ኒቆዲሞስ
ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡

               ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡
@zemarian
674 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ