Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemarian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.65K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-08 14:28:20 ዘማሪት ማህሌት
175 views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 14:25:10 ገጣሚ ትግስት
190 views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 21:13:51 ዘማሪት ሄላገነት ንጉሱ
መሠንቆ ዳዊት ችሮታው
@zemariian
762 views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 21:13:25 ተመከር ሰው ሆይ
ዘማሪ ሚኪያስ /ትንሹ ይልማ/
ክራር ኢዮሲያስ አበራ
@zemarian
766 viewsedited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 06:06:08 #ሆሳእና_ለወልደ_ዳዊት

ሆሳዕና /2/ ለወልደ ዳዊት/2/

አባቶች እናቶች ህፃናት በሙሉ/2/
ለዓለም መድኀኒት ሆሳእና በሉ/2/

በአህያዋ ጀርባ አምላክ ቁጭ አለና/2/
አሳየ ለህዝቡ ታላቁን ትህትና/2/

ቤተ መቅደስ ገብቶ የሰላሙ ዳኛ/2/
ይውጡ ብሎ አዘዘ ሌባና ቀማኛ/2/

አንቺ ኢየሩሳሌም በጣም ደስ ይበልሽ/2/
ንጉስ በአህያ ላይ ይኸው መጣልሽ/2/

https://t.me/zemarian
348 views03:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 19:58:46 #መድኃኔ_ዓለም
"እርሱ በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን" (ዮሐ 4÷42)

ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው መድኃኒትነቱ በጥቂት ሰዎች ብቻ የተገደበ፤እንደነ ኢያሱ በእስራኤል ዘሥጋ ማዳን ብቻ የተገለጠ ሳይሆን፤በሥጋ፣ በመንፈስና በነፍስ ማዳን ላይ የተመሠረተ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ፤ ያውም ከአዳም ጀምሮ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ለሚነሳው ትውልድ ሁሉ የሆነ ማዳን ነው፡፡

ስለዚህም መድኃኒትነቱ ውሱን እንዳልሆነ ለማጠየቅ ˝ኢየሱስ˝ የሚለው በምልኣት ሲገለጥ ˝የዓለም-መድኃኒት˝ ብለን እንጠራዋለን፡፡

ዓለም ማለት ዘመድ፤ ዘመደ ፍጥረት ፤ሰማይ ከነግሡ ምድር ከነልብሱ፤ሰማይ ከነደመናው ምድር ከነጉተናው ማለት ሲሆን ሁሉን የጠቀለለ ስም ነው፡፡
በሊቃውንቱ ሃያ ዓለማት እና ሃያ አየራት እንዳሉ ይገለጣል፤ሃያ ዓለማት የሚባሉትም ዘጠኝ ዓለመ እሳት፤አምስት ዓለመ ምድር፤አራት ዓለመ ማይ እና ሁለት ዓለመ ነፋስ ናቸው፤(9+5+4+2=20)፤አየራቱም በዚህ ልክ ናቸው ይላሉ (ቅዳሴ.ማር አንድምታ)፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል ዓለሙን ሁሉ ለማዳን ነው ሲባል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን በአዳም ምክንያት ተረግሞ የነበረውን ዓለም ለሰው ልጆች በግዛት መልክ ተስጥቶ የነበረውን ሁሉ ዓለም ለመባረክ መሆኑንም ማወቅ ያስፈልጋል፤ለአዳም "ከሰማይ በታች ከምድር በላይ ያለውን ሁሉ ብላ ጠጣ ግዛ ንዳ" (ዘፍ 1÷29-31) ተብሎ መሰጠቱ ይታወቃል፤ይህም በረከት ነው፡፡
አዳም ያልታዘዘውን ዕፀ በለስ በልቶ ሲረገም ደግሞ የእርሱ የሆነው ሁሉ አብሮ ተረግሟል፤
ለዚህም "ካንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን" (ዘፍ 3÷17) የሚለው ቃል ማረጋገጫችን ነው፡፡

ነቢዩ ኢሳይያስም፡-
"ምድርም አለቀሰች ረገፈችም ፤ዓለም ደከመች ረገፈችም፤የምድርም ሕዝብ ታላላቆች ደከሙ" በማለት በኢየሩሳሌም ምርኮ አንፃር የነበረውን የዓለምን ስቃይ አመልክቶናል (ኢሳ 24÷4)፡፡

ነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤልም፡-
"ወሶበ ዐለወ አቡነ አዳም ኮነ ፍናዊሁ ለዓለም መብእሰ ወጐጻጒጸ" "አዳም ትእዛዙን ባፈረሰ ጊዜ የዚህ ዓለም ጎዳናው ጒድጓድ ሆነ፤ጠባብ ያነሰ የከፋ መከራው የበዛ፤ ፃር ጋር የተመላ ሆነ" (ዕዝ.ሱቱ 5÷2)፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፡-
"ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ" (ሮሜ 5÷12)፡፡

ጌታችንም ለሐዋርያት ሲያስተምር፡-
"ርእዮ ለዓለም በማእሰረ ኃጢአት እንዘ ይትኀጐል፤ፈቂዶ ይፈውስ ትዝምደ ሰብእ…." "ዓለም በኃጢአት ማሰሪያ ተይዞ ሲጎዳ አይቶ የሰውን ባህርይ የሰውን ነገድ ይፈውስ ዘንድ …" ብሏል (ትምሕርተ ኅቡአት)፡፡

ስለዚህ ለአዳም የተሰጠ ዓለም በአዳም ምክንያት የተረገመ ሆኖ ነበር፤ ዓለማችን በአዳም ምክንያት መከራንና ሞትን ተቀብላ አስተናገደች፤ይህ መርገም ለዓለም አንዲወገድላት ሌላ ሁለተኛ አዳም ያስፈልግ ነበር፤ እሱም "የዓለም መድኃኒት" መሆን አለበት፤ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጣ፤ ዓለምን በደሙ ፈሳሽነት አጠባት፤ በሰው ውስጥ የሚገኙትን አራቱን ባህርያት አደሳቸው፤ ተረግማ የነበረችው ምድር በጌታ ደም ታጥባ ፋሲካን አደረገች ("ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተኀፂባ በደመ ክርስቶስ" እንዲል ቅ.ያሬድ)፤ ክርስቶስ መርገማችንን ቀበረልን፤ ልጅነታችንን መለሰልን!!!

ዛሬ በዚህ ደም ታጥበን ነጽተን መንግሥቱን እንጠባበቃለን

ፍቅሩንና መከራውን እያሰብን
ቁስሉንና ሞቱን እያስታወስን እንማፀናለን

ለዓለም ቤዛነት መስቀል ላይ የተፈተተው ጌታ ዛሬም እንደማይተወን እናምናለን

ስለዚህም እንዲህ እያልን እንለምነዋለን፦

መድኃኔ ዓለም ሆይ!
• 6,666 ጊዜ ስለተገረፈው ጀርባህ
• ስለተቸነከሩት እጆችህና እግሮችህ
• ስለተወጋው ጎንህ
• ስለ ቅዱስ ሥጋህና ስለ ክቡር ደምህ
• በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ስለወለደችህ ስለ እናትህ ስለ ማርያም ብለህ
ይቅር በለን!!!

አሜን!!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
የመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የመጽሐፍ መምህር
633 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 00:07:10 አስደሳች ዜና 


ከዚህ በፊት በገና በመስራት እና በየአላቹበት በማቅረብ የሚታወቀው ድህንፃ አውን ደግሞ ለውድ ኦርቶዶክሳዊ በሙሉ ለሰራ ፈጣሪዎች እና ስራ ለመፍጠር ላሰባቹ በሙሉ የምስራች ይዞላቹ ቀርቦል !


ሻማ ለማምረት
ጡዋፍ ለማምረት
ፈሳሽ ሳሙና(ላርጎ)
የተለያዩ ስራዎችን ጭምር..

እንዲሁም ሱቅ ከፍታቹ እቃ ማግኘት ላልቻላቹ በሙሉ ድህንፆ እናንተን ለማገዝ ዝግጅቱን ጨርሶል ወደናንተ ቀርቦላችዋል !

ስልክ . +251901570787



      የ Telegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ  !    


     
              ይህን ይጫኑት  ...  ይህን ይጫኑት

█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█

 
.
68 views21:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:06:07 እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡
#ጥንተ_ስቀለት
#ክርስቶስ_የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን #ከሆነ _እንደገና_በሌላ_ጊዜ_በዓለ_ስቅለትን_ማክበር_ለምን_አስፈለገ?
#ጥንተ_ትንሣኤ

#ጥንተ_ስቀለት
የጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በመጋቢት ፳፯ ቀን ሰማያዊ አምላክ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ ሕማማተ መስቀልን በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው #በገዛ_ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉም በዓለ መድኃኔዓለም እየተባለ በየዓመቱ #በመድኃኔዓለም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከበራል ፡፡ የመጋቢት ጽንሰት ( ብሥራት ) ታሕሣስ 22 እንደሚከብረሁ ሁሉ ማለት ነው ፡፡
፠#ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ከሆነ እንደገና በሌላ ጊዜ በዓለ ስቅለትን ማክበር ለምን አስፈለገ?
ክርስቶስ የተሰቀለው በዕለተ ዓርብ ሲሆን ከመቃብር የተነሣውም በዕለተ እሑድ በመሆኑ #ስቅለት ከዕለተ ዓርብ፣ #ትንሣኤም ከዕለተ እሑድ፣ #ዕርገት ደግሞ ከዕለተ ሐሙስ እንዳይወጡ፤ ሌሎቹም በዓላትና አጽዋማት በተወሰነላቸው ቀን እንዲውሉ ማድረግ ይቻል ዘንድ የቀድሞ አባቶችና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሰባት አዕዋዳት አዘጋጅተው እና ቀምረው ሁሉም ሥርዓቱን ጠብቆ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቀን እንዲከበር የወሰኑ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት ጥንተ ስቅለቱ መጋቢት ፳፯ ቀን በየዓመቱ እየታሰበ በዓለ ስቅለቱ ደግሞ ከሰሙነ ሕማማቱ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በዕለተ ዓርብ በጾምና በጸሎት እንዲሁም በአክፍሎትና በስግደት እንዲከበር በማድረግ ሕግና ሥርዓት ስለሠሩ በዚሁ መሠረት ይፈጻማል::
#ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጌታችን #የጽንሰቱ_በዓል በታላቅ ድምቀት የሚከበርበት ቀን ከመሆኑ የተነሣ በዓሉን በዓል ተጭኖት ነው እንጂ ፫ኛው ቀን መጋቢት ፳፱ኝም ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣበት #ጥንተ_ትንሣኤ በመሆኑ እንደ ጥንተ ስቅለቱ ሁሉ ጥንተ ትንሣኤውም ከበዓለ ጽንሰቱ ጋር አብሮ የሚታሰብ መሆኑን ልንዘነጋው አይገባንም፡፡
#በኢትዮጵያ_በዋነኛነትና_በግንባር_ቀደምትነት_የስቅለት_በዓል_የሚከበርበት
#ታላቁ ገዳም #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡
#142 ዓመታትን ያስቈጠረው ጥንታዊው የጮቢ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም፡፡ በ1868ዓ.ም. የተመሠረተ፡፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን በጀልዱ ወረዳ በጮቢ የሚገኝ፡፡
#በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት ጥቂቶቹ፤
፤ ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳምና
ኤልሻማ ደብረ ማኅቶት መድኀኔዓለም ቤ.ክ.
፠ አንድ ላይ ያሉት፤
✤1. ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳም፤
✤2.ላሊበላ መድኀኔዓለም
✤3. ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም
✤4. መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም፤ ጣና
✤5. ሽረ እንዳሥላሴ መድኀኔዓለም ወመስቀል ክብራ
✤6. ቆላድባ መድኀኔዓለም፤ ጎንደር ከተማ አጠገብ
✤7.ቦሌ ደብረ ሳሌም መጥምቁ ዮሐንስ፤ (ቦሌ የመድኀኔዓለም ታቦት )
✤ 8.ድሬዳዋ መድኀኔዓለም
✤9.#ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔዓለም ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ፤ የ 110 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡)
የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡ ጽዶቹ ሳይቀሩ በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፤ በቀድሞ ዘመን መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ የሚቀድስበት፤ 3 ጳጳሳትን ያፈራ፣ ……. ደብር ነው፡፡
✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡)
10 #መናገሻ_ጋራ_መድኀኔዓለም፤ ግማደ መስቀሉ ያረፈበት፤ ቀድሞ የቅዳሴ ቤቱን ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቀድሞ የልደታ ቤ.ክ) በአካል በመገኘት በመስቀሉ የባረከው፤ በድርሳነ ራጕኤል ላይ የተገለጸና ቅዱስ ራጕኤል የማይለየው፤ በአረማዊው ግራኝ ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ካህናቱን መነኮሳቱንና ምዕመናኑን እንደያዘ በምድር ውስጥ ገብቶ የተሰወረበት በሥጋ ዕረፍተ ሞት ያልተገቱ ሥውራን ግሩማን አበው የሚኖሩበት "ዛቲ ይእቲ አምባ ማርያም መካነ ክብሮሙ ወጸሎቶሙ ለቅዱሳን ወለነገሥታተ ኢትዮጵያ በሐ በልዋ ተሳለምዋ ጊሱ ሐቤሃ ኢትርሐቁ እምኔሐ" ብለው አበው ያወደሷት የጸሎት የአርምሞና የትኅርምት ቦታ፡፡
11. #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል (መድኀኔዓለም ቤ.ክ)፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት ወሎ፤ ወግዲ፤ ወለቃ ወንዝ አጠገብ፤ የበረሃው ዕንቊ ገዳም፤ አባ ጽጌ ድንግል የፈለፈሉት ባለ 3 መቅደስ እጅግ ሰፊ ዋሻ ቤ.ክ፡፡
12. #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔዓለም ቤ.ክ፥ አዲስ አበባ፤ በአዲስ አበባ ከተመሠረተ ከ1826 ዓ.ም ጀምሮ ፍልሰት ሳያጋጥመው በመቆየቱ፤ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤ.ክ፡፡ (ነገር ግን በመሃል ፍልሰት እያጋጠማቸው እንጂ በአዲስ አበባ ከ1600 ዓመታት በፊት ደብረ ኤረር፣ የካ ዋሻ ተክለሃይማኖትና /ኋላ የካ ሚካኤል/ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን፤ እንዲሁም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት መመሥረታቸውን ልብ ይሏል)
#በዓለም አቀፍ ደረጃ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርባችው ፪ቱ ታላላቅ ገዳማት
፩ኛ. ኢየሩሳሌም ዴር ሡልጣን
፪ኛ. #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
Watch "#መድኃኒዓለም_ዘቆምከ #በመዝሙረ_ማኅሌት #በማኅበረ_ቅዱሳን_የተዘጋጀ" on YouTube




https://www.facebook.com/109229901640650/posts/126032596627047/

Telegram https://t.me/zemariian
370 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:06:07 ሕዝቡ {በርባን ይፈታልን ክርስቶስ ግን ይሰቀል }ማለታቸውን ስንሰማ ሁላችንም ማዘናችንና <ምን አይነት ክፉዎች ናቸው }ብለን መውቀሳችን አይቀርም ። ወዳጄ ሆይ እባክህን እሰኪ አይሁድንና ጲላጦስን ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያ ትምህርትቤት መምህር የነበረው ሊቅ <<በስጋው ክፉ ነገርን የሚሠራ ሁሉ በርባንን ፈቶ ክርስቶስን አሰረው ።መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ ክርስቶስን ፈቶ በርባንን አስሮታ ልይላል ።}} ወዳጄ ሆይ አንተ በሰውነትህ ላይ ፈተህ የለቀከው ማንን ነው ?በርባንን ነው ወይስ ጌታን ነው ?በርባንን ፈተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሃ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው ።<በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው >ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግ ና እጅህን መታጠብ አይበጅህም ። ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈተኽ በርባን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል ።!
{የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ስጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉት }}ተብሎ ተጽፏልና (ገላ 5፥24)

#ሕማማት
270 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:06:05 በቴሌግራም ደሞ ይኸው
241 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ