Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarian — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemarian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.65K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-15 17:38:29 እንኳን በሰላምና በጤና አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡ #ፋሲካ_ፋሲካ_ፋሲካ፤ #ተዝካረ_ትንሣኤሁ_ለክርስቶስ፡፡ /ቅዱስ ያሬድ/ #ትንሣኤ_ትርጕም_በዓሉና_አከባበሩ
(«ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግስ ሲሆን፡፡ «ትንሣኤ» ማለት = መነሣት፥ አነሣሥ፥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡

«ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዓይነቱ ሲተረጐም ፭ት ክፍል አለው፡፡ ፩ኛ) «ትንሣኤ» ማለት ኅሊና ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡ ፪ኛ) «ትንሣኤ» ማለት ልቡና ማለት ነው፡፡ የዚህም ምሥጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡ ፫ኛ) «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡ ፬ኛ) «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡ የዛሬው ትምህርታችንም ይህንን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ፭ኛው)ና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጕባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፥ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡ ፠ ወደተነሣንበት ርዕስ ስንመለስ የትንሣኤ በዓል በቃሉም ምሥጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡ «#ፋሲካ_» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ «ፌሳሕ» በጽርዕ (በግሪክኛ) «ስኻ» ይባላል፡፡ በግእዝና በዐማርኛ ፍሥሕ ዕድወት = ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣ እየተቸኮለ የሚበላ መሥዋዕት፣ መሻገር፣ መሸጋገር ማለት ነው፡፡ በእንግሊዝኛ «ስኦቨር» ይሉታል፡፡ የዚህም ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነት የተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹም ደሰታ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል «ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡  በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ የምንገኝ እስራኤል ዘነፍስ የሆንን ምዕመናነ ክርስቶስ ትንሣኤውን የምናከብረው፤  በእርሱ ትንሣኤ ከኀጢአት፤ ወደ ጽድቅ፣  ከኀሳር ፥ ከውርደት፤ ወደክብር፣  ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ፤ ወደ ዘለዓለማዊ ነፃነት፣  ከአደፈ፥ ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወት፤ ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገርንበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት እናከብረዋለን፡፡ ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡ #የበዓሉ_አከባበር_«እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን»  መድኀኒታችን ሞትን በሞቱ ድል መትቶ፣ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ በሥልጣኑ የተነሣው በእለተ እሑድ፥መጋቢት 29፥ በ34 ዓ.ም እንደሆነ ታሪከ ቤተ ከርስቲያን ያስረዳል፡፡  የትንሣኤ በዓል መከበር የጀመረው በቅዱሳን ሐዋርያትና በሰብዐ አርድእት፣ ኋላም በየጊዜው በተነሡት ሊቃውንትና ምእመናን ነው፡፡ ድምቀቱና የአከባበር ሥርዐቱ ይበዛ ይቀነስ እንደሆን እንጂ መከበሩ ተቋርጦ አያውቅም፡፡ እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ኢየሩሳሌም ባሉ ታላላቅ ገዳማት ደግሞ በዓሉ እጅግ በጣም በታላቅና በልዩ ሁኔታ ይከበራል፡፡ #የበዓሉ_አከባበር_ከዋይዜማው_ጀምሮ_እስከ_ሌሊት_የሚከተለውን_ይመስላል፤  በዋይዜማው ማታ በ2 ሰዓት «ለጸሎት ተሰብሰቡ» የሚል ደወል ድምፅ ይደወላል፡፡ እንደ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ባሉ ታላላቅ አድባራት የተጋብኦ ከበሮ ይመታል፡፡  ካህናቱ ዲያቆናቱና ምዕመናኑ ነጭ ልብስ ይልበሱ፤ ጧፍ ያብሩ፤ ዲያቆናት ጥላ ያጥሉ፡፡  በላይ ቤት አቋቋም በሚቆሙ፤ የነቢያት ጸሎት የለም  /በታች ቤት/፤ የነቢያት ጸሎት (ጸሎተ ሐና፣ ጸሎተ ሕዝቅያስ፣ ጸሎተ ምናሴ፣ ጸሎተ ዮናስ፣ ጸሎተ ዳንኤል፣ ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ፣ ጸሎተ ዕንባቆም፣ ጸሎተ ኢሳይያስ፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም፣ ጸሎተ ዘካርያስ፣ ጸሎተ ስምዖን) ይድገሙ፡፡  ውዳሴ ማርያምንና ክስተተ አርያምን በዜማ ያድርሱ፡፡  ‹‹ተፈሥሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ›› የሚለውን ግጥማዊ የደስታ መዝሙር ይዘምራሉ፡፡  መልክአ ሥዕል ከትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ ድረስ አይደረስም  እሰግድ ለኪ ብለህ ተዓምረ ማርያምና ተዓምረ ኢየሱስን አንብብ እንዳበቃ ጸሎተ አኰቴት ይደርሳል፡፡  ዲያቆኑ ነጭ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ፥ አክሊል ደፍቶ፥ የመጾር መስቀል ይዞ፥ እንደ እርሱ ነጭ ልብሰ ተክህኖ በለበሱ ደማቅ የጧፍ መብራት በሚያበሩና ድባብ ፥ ጃንጥላ በያዙ ሁለት ዲያቆናት በግራ በቀኝ ታጅቦ ከመቅደስ ብቅ ብሎ በቅድስት ይቆማል፡፡ (ይህም በጌታችን መቃብር በራስጌና በግርጌ በታዩት መላእክት ምሳሌ ነው፡፡ ዮሐ.20-12) ቀጥሎም በመዝሙረ ዳዊት /መዝ.፸፯፥፳፭/ ያለውን፤ ‹‹ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤ ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤ ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ፡፡ (ትርጕም፤ እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ስካር እንደተወው ኀያል ሰውም፣ ጠላቱን በኋላው ገደለ፡፡» የሚለውን ምስባክ ይላል፤  ካህናቱና ሕዝቡ ከበሮ እየመቱና እያጨበጨቡ በእርጋታ እያጨበጨቡ የምስባኩን ተሰጥኦ ይመልሱ፡፡ ምስባኩንም በዲያቆኑ 2 ጊዜ በመላው ካህናትም 2 ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ ዲያቆኑም መላው ካህናትም አንድ ጊዜ ብለው 5 ጊዜ ይሆናል፡፡ 5,500 ዘመን ሲፈጸም በጌታችን ሞትና ትንሣኤ ዓለም ለመዳኑ ምሳሌያዊ ማስረጃ ነው፡፡  ቀጥሎም ካህኑ ትንሣኤውን የሚያበሥር ወንጌል ከማቴዎስ፣ ከማርቆስና ከሉቃስ አውጥቶ ያነባል፡፡ ከዮሐንስ ወንጌል ያለው የትንሣኤው ወንጌል ኋላ ለቅዳሴው ጊዜ ይቆያል፡፡ ዮሐ.

20፥1-9  በማስከተል ከሊቃውንት ደባትር መዘምራን የተመደበው መዘምር የዲያቆኑን መፆር መስቀል ይዞ «ትንሣኤከ ለእለ አመነ» የሚለውን እስመ ለዓለም ከቃኘ በኋላ ለበዓሉ ተስማሚ የሆነው 2 አርያም (ሃሌ ሉያ ለአብ፥… የሚለው) ተመርቶ በመቋሚያ ይዘመማል፤  በማስከተልም «ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፣ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን = ክርስቶስ ከሙታን ቀድሞ ተለይቶ ተነሥቷልና በሰንበተ ክርስቲያን ዛሬ ደስታ ሆነ፡፡...» የሚለውን አንገርጋሪ ያመለጥናል (ይመራል)፡፡ በግራ በቀኝ እየተነሣ መዘምራኑም ይዘምሙታል ይጸፉታል፤ ያለዝቡታል፤ ወዲያውም «ብርሃነከ ፈኑ፤ ለእለአመነ = ለአመነው ብርሃንህን ላክልን፡፡» የሚለውን እስመ ለዓለም እየወረቡ መብራት እያበሩ ዑደት ያደርጋሉ = ቤተ ክርስቲያኑን በውስጥ ይዞራሉ፡፡  በዚህ ጊዜ «በጨለማ የነበራችሁ ሕዝቦች ኑ የትንሣኤውን ብርሃን እዩ፣ ብርሃኑንም ወስዳችሁ የብርሃኑ ተካፋይ ሁኑ፡፡» እያለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስታዘጋጅ የሰነበተችውን ጧፍ ለምዕመናን እንዲያበሩ ታድላቸዋለች፡፡ ሕዝቦቹም ካህናቱን ተከትለው በታላቅ ደስታና ድምቀት ዑደት ያደርጋሉ፡፡ ፠ መዘምራኑና ካህናቱ ከዑደት ሲመለሱ «ይእቲ ማርያም» የተባለው የኪዳን ሰላም ይጸፋና ኪዳን ተደርሶ ሲያበቃ እንደ በማዕርግ ከፍ ያለው ካህን ዘለግ ባለ ድምፅ በንባብ የሚከተውን ፫ት ጊዜ ሲያውጅ ካህናቱና መዘምራኑም ይቀበሉታል፤  #ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን (ክርስቶስ ከሙታን መካከል ተነሣ) #በዐቢይ_ኀይል_ወሥልጣን (በታላቅ ኀይልና ሥልጣን)፤
357 views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 11:39:08 እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ዘማሪ ዘለቀ አስናቀ
በገና ዳዊት ችሮታው

@zemarian
749 views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:49:59
★ @zemarian ★
* ንሴብሖ ለእግዚአብሔር*
ጥራዝ3.ቁ7

ንሴብሖ(2) ለእግዚአብሔር(2)
ስቡሓ ዘተሰብሓ(4)) እናመስግነው(2)እግዚአብሔርን(2)
ምስጉን ነው የተመሠገነ(4)

በህብረት_እናመስግን
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ

★ @zemarian ★
1.2K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 09:42:21

1.4K views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 09:14:00

1.4K views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 08:42:43 በቴሌግራም ዘስቅለት ዘሠርክ ዜማ
1.3K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 08:42:43 Watch "#ዘስቅለት_ዘሠርክ_ዜማ
#በመምህር_ሲራክ #መዝሙረ #ማኅሌት" on YouTube


1.3K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 08:42:43 በyou tube ዘስቅለት ዘሠርክ ዜማ
1.1K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 08:42:43 በቴሌግራም ዘስቅለት ዘ፱ቱ ሰዓት ዜማ
1.0K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 08:42:43 Watch "#ዘስቅለት_ዘተስዓቱ_ሰዓት_ዜማ #በመምህር_ሲራክ #መዝሙረ #ማኅሌት" on YouTube


984 views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ