Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ፍጹም ሊሆን እንደማይችል ሕሊናችን ሳይቀር ይመሰክርብናል፡፡ ታድያ መፍትሔው ምንድን ነው? ያል | መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

ይህ ፍጹም ሊሆን እንደማይችል ሕሊናችን ሳይቀር ይመሰክርብናል፡፡ ታድያ መፍትሔው ምንድን ነው? ያልን እንደ ሆነ መፍትሔውማ ንስሐ መግባት ነው እንላለን፡፡ ንስሐ መግባት ማለት ይከተሉት የነበረውን ክፉ ተግባር ሙሉ በሙሉ እርግፍ አድርጎ  በመተው ወደ ደገኛው ተግባር መመለስ ማለት ነው፡፡ ንስሐ ማለት ትናንት በጥይት ሲጠፋ የነበሩ ወገኖች ዛሬ እሱን አቆመውና በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለው  ችግራቸውን በፍቅር ለመፍታት መወያየት መቻል ማለት ነው፡፡ ትክክለኛው  ንስሐ እንዲህ ያለው ነው፡፡

ይህንን የመሰለ ጥሩ አርአያ ያለው ንስሐ በሀገራችን በቅርቡ ሲፈጸም አይተናል፤ ይህንን ያደረጉ ወገኖች በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናቸዋለን፤ ይህን ያደረጉ ወገኖች ትክክለኛውን ትንሣኤ ተነሥተዋል፤ የትንሣኤውንም በዓል በትክክል አክብረዋል፡፡

ሆኖም ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ የሚያስገኘው ከእምነት ሲነሣ ነውና ነገሩ ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር ተብሎ በእምነት ሊደረግ ይገባል፤ ገና ወደ ጠረጴዛ ያልመጣችሁ ወገኖችም ንስሐ ገብታችሁ ወደ ውይይት እንድትመጡና የጋራ ሀገራችንን በጋራ እንድናገለግል በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናቀርባለን፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ መፎካከር ይቁም፤ መወያየት ይቅደም፤ ከሰላም፣ ከአንድነትና ከፍቅር ተጠቃሚ መሆናችንን አንዘንጋ፤ ኢትዮጵያ ለሁላችንም በቂ ብቻ ሳትሆን፤ ከበቂም በላይ ናት፡፡ ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት፤ ይህ የኔ ነው ይህ የኔ ነው በሚል ደካማ አመለካከት ራሳችንን በራሳችን አንጉዳ፣ ከእንግዲህ ወዲህ የጥይት ድምፅ ይብቃ፤ የዕለቱ ዓቢይ መልእክታችን ይህ ነው፡፡
በመጨረሻም፡-

የትንሣኤውን በዓል ስናከብር የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጨነቁትን በማጽናናት፣ እንደዚሁም የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል ይበልጥ ለማስፋትና የሀገር አንድነቱን በዕርቅ ዘላቂ ለማድረግ ቃል በመግባት የፋሲካን በዓል እንድናከብር በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
መልካም የትንሣኤ በዓል ያድርግልን!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ 
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ