Get Mystery Box with random crypto!

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zekr_menzuma — ﷽ዚክረ መንዙማﷺ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zekr_menzuma — ﷽ዚክረ መንዙማﷺ
የሰርጥ አድራሻ: @zekr_menzuma
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.48K
የሰርጥ መግለጫ

የኛን #You_Tube ቻናል ለማግኝት ይሄን ይጫኑ⬇️👇
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ በቦት
@ZEKR_MENZUMA_bot ተጠቅመዉ ያድርሱን✍️
የመውሊድ ሀድራ ቪዲዮ በድምፅ የተቀዳ መንዙማ ያላቹ ላኩልን
{ @ZEKR_MENZUMA_bot }

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-06 09:54:17
አዲሱ መጅሊስ ውስጥ ምንድነው እየተካሄ ያለው ቆይ እንዴ..? ምንድነው አላማቸው? እኔ እነሱን ለመረዳት ብዙ ሞከርኩ ግን ፈፅሞ ሊገቡኝ አልቻሉም..? ይሄን ቪድዮ ተመልከቱት መጅሊሱ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ጋር እንዲወያዩ ያቋቋማቸው ኮሚቴዎች ከሰላም ሚኒስተር ጋር ሲወያዩ የሚያሳይ የዜና ዘገባ ነው። ሙሉ ዜናውን አዲስ ቲቪ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ገብታችሁ መመልከት ትችላላችሁ።

እኛ ከመስጂድ ፈረሳዎች በተጨማሪ ሰሞኑን ለደረሰብንን እልቂት ድምፅ ሆነው ለበደላችን መፍትሄ ያመጡልናል ብለን ስንጠብቅ...ጭራሽ "እኛ ባለፈው ጁመዓ ተቃውሞ እንዳይደረግ በደብዳቤ ለሁሉም መስጂዶች ብናሳውቅም በኛ ስር የሚተዳደሩ መስጂዶች ላይ ተቃውሞ ሳይነሳ እነዚህ ሁለት መስጂዶች ማለትም (አንዋር እና በኒ) ላይ ተቃውሞ የተነሳው በኛ ማለት በመጅሊሱ ስር ስለማይተዳደሩ ነው" ብለው ለደረሰው በደል እና ግፍ ጀስቲፋይ አድርገው ቁጭ አሉ። ለዛውም አንዋር መስጂድ ላይ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳልነበር የቪድዮ ማስረጃዎች ጭምር እያለ።

ይገርማል እኛ የደረሰብንን በደል፣ ህመም እና ግፍ ተሰምቷቸው ከመንግስት ጋር ቁጭ ብለው አውርተው ለችግሮቻችን መፍትሔ ያመጣሉ ብለን ስንጠብቅ አሁንም እነሱ የሚያሳስባቸው የብዙ መስጂዶች መፍረስ እና የምዕመን መሞት ሳይሆን ሁለት መስጂዶችን በስራቸው አለማስተዳደራቸው ነው....ብቻ ከዚህ ብኋሏ በነገሮች አዝኖ እና ተስፋ ቆርጦ ዝም ከማለት ውጪ አማራጭም የለን። ይሰለቻል
2.6K views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 15:39:23
#ፈፊሩ
በደሉ ሲገዝፍ፣ ጉልበታችን ሲከዳንና ህመሙ ሲጠናብን፤
ወደ ኃያሉ፣ አሸናፊውና ተበቃዩ ጌታ 'አቤት' ማለትና
ወደርሱ መሸሽ ብቸኛው መፍትሔ ነው።
ዩኑስን(ዐ.ሰ) ከአሳ ነባሪ ሆድ፤ ሙሳን (ዐ.ሰ) ከፊርአውን፤
ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) ከኑምሩድ እሳት ነፃ ያወጣውን
ሁደይቢያን በፈትሑ መካ የቀየረ ጌታችንን እንደ ነቢዩላህ
አዩብ (ዐ.ሰ) «ጌታችን ሆይ! ችግርናና መከራ አገኘን፤ አንተ
ደግሞ የአዛኞቹ ሁሉ አዛኝ ነህ።» እንለው ዘንድ የተገባ
ነው።
ፈፊሩ፤ የመሸሽ ዘመቻ ነው። የምንሸሸው ወደ አላህ ነው!
የምንፈጥነው ወደ መስጂድ ነው! የምንበረው ወደ ድል
ነው።
የዘመቻው ዝርዝር አተገባበርና አፈፃፀም በቀጣይ የሚገለፅ
ሲሆን፤ ዘመቻው:‐
• ፆም
• የጀምዓ ኢፍጣር
• ሰደቃ
• ዚያራ
• ዱአ
. አዝካርና ሌሎችንም ያካተተ ይሆናል።
ﻓَﻔِﺮُّﻭﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ۖ
«ወደ አላህም ሽሹ፤»
(ቁርኣን 51:50)
#የአንዋርመስጂድጭፍጨፋ #የመስጂድፈረሳ
#ሙስሊምጠልነት #ሰጋጁንገደሉት #ሸገርሲቲ
#AnwarMesjidMassacre #Islamophobia
#EthioMuslims #ፈፊሩ
1.3K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 20:44:40 በጠላት ላይ የሚደረግ ዱዓ :-

« አላሁመ ሙንዚለል ኪታብ ሰሪዐል ሒሳብ ፤ ኢህዚሚል አሕዛብ ። አሏሁመ ኢህዚምሁም ወዘልዚልሁም »

አላህ ሆይ! አንተ (ቅዱሳን) መፃሕፍትን የምታወርድ ነህ ። ምርመራህም ፈጣን ነው ። የጠላት ጭፍራዎችን አሸንፋቸው ፤ አንቀጥቅጣቸዉም ።

( ሙስሊም )
1.7K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 18:14:08
ህግ በማስከበር ስም እንደዚህ አይነት ጭካኔ ግን ለምን ዜጋ አይደለንም
1.8K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 11:00:47
ጀሚል ሪድዋንን ጌታውን ተገናኝቷል

ኢነ ሊላሂ ወኢነ ሊላሂ ራጂኡን

ያለ አባት እናትም አባትም ሆና ልጄ ደረሰልኝ እያለች አሳድጋ ወጉን ስትጠብቅ ቀጠፉባት

በፖሊስ በጥይት አጅንቱ ተዘርግፎ ነፍሱን ለማትረፍ ጳውሎስ አይ ሲ ሩም የነበረው ወንድማችን ጌታውን ተገናኝቷል።

ማረፊያህን አላህ ያሳምርልህ ደረጃህን ከሲዲቆች ከነብያቶች ተርታ ያድደግልህ
1.8K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 09:57:10
ቀብሩ ዝሁር ላይ ኮልፌ ነው። አካባቢውን ሳይዘጉት የምንችል ሰዎች አቅራቢያ በመሆን እንሸኛለን።ሁሉም ሸሂዶች እስኪደርሱና እስክንሸኛቸው በትግስትም እንጠብቅ።

ግታዬ በመልካም አቀባበል ይቀበልህ፣ የተሰዋህለት የአላህ ቤት ነውና በጠራህ ቤቱ ተዋብ፣ የአንተ ደም የድል ጮራ ይሁነን
1.8K views06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 06:33:54
ምንም ተቃዉሞ ሳይኖር ጥይት መተኮስ እንደተጀመረ ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት #shar አርጉት
1.9K viewsedited  03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 05:11:23
ጌታህ ሲመርጥህ እንዲህ ያፈጥንሃል "በኔ ሞት እንዳታዝኑ ሸሂድ መሆን ነው ምፈልገው ብሎ በተናገረ 7 ቀን እንኳን ሳይሞላው ወደ ፈለገበት አለም አመራ"
ሱብሃነክ ጌታዬ ምኞትና ፍላጎቱን ተቀበለው
1.8K views02:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 19:55:08 አንዋር መስጅድ የነበሩት እህት ወንድሞች በአሁን ሰዓት እየወጡ ነው !

ቀጣዩ መኾን ያለበት በሰላማዊ ምዕመን ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈፀሙ፣ እንዲሁም አምቡላንስ አስከሬንና ቁስለኞች እንዳያነሳ ሲከለክሉ የነበሩ የፀጥታ ኃላፊዎችን ተጠያቂ የማድረግ ሥራ ነው። ሙስሊሙ በሰላም ሰግዶ ሲመለስ ተኩስ ሲክፍቱ የሚያሳይ በቂ የቪድዮ መረጃ ተለቋል!
2.2K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 19:46:32 ከአንዋር መስጂድ እየወጡ ለሚገኙ ወንድም እና እህቶች መኪኖች የያዛችሁ ሰዎች እነሱን ሰብሰብ አድርጋችሁ ወደ ሰፈሮቻቸው የማድረስ ስራ ብትሰሩ መልካም ነው መንገድ ላይ ምን እንደሚገጥማቸው አይታወቅም የቀኑ እንግልት ይበቃቸዋል እባካችሁ
2.6K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ