Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_students_association — የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_students_association — የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_students_association
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.94K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ አማራ ተማሪዎች መብት እንታገላለን

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-12 07:36:00
ፋኖነት ሕይወቱ ነው!

ከምርጫ 97 ማግስት ገና በልጅነቱ ነው የአርበኝነት ትግሉን የተቀላቀለው! በአማራ ተጋድሎ ምልክት የነበረው የጎቤ ጦር አካል ነበር። ያውም ቀኝ እጁ!
በአርበኝነት ትግሉ ደጀኔ ማሩን ሊያፍኑ የመጡ አንድ መኪና የአፋኝ ቡድን አባላት መንገድ ላይ ተመትተው አላማቸው የከሸፈው አጋዬ በሚመራው ጦር ነበር።

ከተመቱት መካከል የቆሰሉትን ታዲያ ከሕዝብ መኪና ጠይቀውም ወደ ጎንደር ሆስፒታል ልከዋቸዋል። መንግስት የተባለው "ሽፍታ" ብሎ አስከሬን በሚጎትትበት ወቅት ፋኖዎቹ እነ አጋዬ ሊገድላቸው የመጣን ቁስለኛ አሳክመዋል።

በ2008 ዓ/ም በነበረው ንቅናቄ ወደ አማራ ክልል መጥተው ንፁሃንን ሊያፍኑ የትህነግ የትህነግ የአርማጭሆን በርሃ ሳያልፉ መምገድ ላይ የቀሩት በእነ አጋዬ ጦር ነበር። እነ አጋዬ ጫካ ሆነውም የከተማውን ሕዝብ ጠብቀዋል።

አጋዬ አድማሱ ለእስር ተዳርጎ ማዕከላዊና ሌሎች እስር ቤቶችንም አይቷል። ሲመለስ ወደ ግብርና ስራው ገብቷል። ጠላት ሲመጣ ደግሞ የግብርና ስራውን ትቶ በርካታ ጀብዱዎችን ሰርቷል። ዛሬ የአማራ ክልል በሕልውና ትግሉ ላደረገው አስተዋፅኦ ሸልሞታል። ሲያንሰው ነው! አጋዬ የሕልውና ትግሉ ፋኖ ብቻ አይደለም። ፋኖነት ያደገበት ነው። ፋኖነት የኖረበት ሕይወቱ ነው!

https://t.me/Amhara_students_association
2.1K viewsedited  04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 07:35:17 ለ32ኛ ዙር የአማራክልል መደበኛ ፖሊስ ምዝገባ ተጀምሯል

#የመመልመያ_መስፈርቶች

1)ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ / የሆነች

2) ከሚኖርበት ቀበሌ 2 አመት እና ከዛ በላይ የኖረና የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል /የምትችል

3)ለሀገሪቱ ህጎች ታማኝና ተገዥ የሆነ/የሆነች

4)ከማንኛውም ደባል ሱስ ነጻ የሆነ/ች

5, የአማራ ክልል መደበኛ ፖሊስ ሆኖ ለመስራት ፍላጎት ያለው ያላትና ለመሰልጠን ፍቃደኛ የሆነ / ች በክልሉ ዞኖች ፣ወረዳዎች ተመድቦ መስራት ፍቃደኛ የሆነ/ች

6) መልካም ስነ_ምግባሩ / ሯ የተመሰከረትላት / ለት

7)በማኛውም ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ / ያልተቀጣች ክርክር የሌለበት

8/የትምህርት ደረጃው በድሮው 1ዐኛ ያጠናቀቀ እና የማትሪክ ውጤት ማቅረብ የሚችል በአዲሱ 12ኛ ክፍል እና በዚያ በላይ

9)ዕድሜ ከ18 ዓመት ያላነሰች ከ25 ዓመት ያልበለጠች

10) ማሰልጠኛ ማዕከሉ በስልጠና ወቅት የሚያቀርበውን ምግብ ለመመገብ ፍቃደኛ የሆነ /ች

11)የተሟላ ቁመናና ጤና ያለው / ያላት በህክምና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

12) ቁመት ለወንድ 1.65 ሜትር ለሴት 1.55 ሳ.ሜትር እና በላይ የሆነ/የሆነች

13) ክብደት ለወንድ ከ50 ኪ .ግራም ያላነስ ከ70 ኪ.ግራም ያልበለጠ _ ለሴት ከ45 ኪ.ግራም
ያላነሰች ከ65 ኪ.ግራም ያልበለጠች

14) ሴት ተመልማዮች ከእርዝና ነጻ ማረጋገጫ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በኮሌጁ ህክምና
በድጋሜ የሚረጋገጥ ይሆናል፤

15) በክልሉ ውስጥ በየትኛውም ቦታ ተመድቦ/ባ/ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነች!
16) የክልሉን የስራ ቋንቋ መፃፍ እና መናገር የሚችል/የምትችል
17) ከስልጠና በኀላ 7 አመት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች ውል የሚወስድ
ምዝገባ ከግንቦት 1እስከ ግንቦት 25/9/2014 ዓ,ም

️ መመዝገብ የምትፈልጉ የደብረማርቆስ ወጣቶች በአቅራቢያችሁ ባሉ የደብረማርቆስ ፖሊስ ጣቢያዎች በስራ ሰዓት በመሄድ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1.6K viewsedited  04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 16:45:35
የቀድሞዉ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙን ግለ ታሪክ የማስታወሻ መጽሐፍ እየተመረቀ ነዉ!

በዶ/ር ሞላ ፈለቀ የተጻፈዉ ይህ የማስታወሻ መጽሐፍ የኮሚሽነር አበረ አዳሙን ከትዉልድ ቀያቸዉ እስከ በረሃ ትግላቸዉ ብሎም ህይወታቸው እስካለፈበት ዕለት የሚያትት ሲሆን ይህ መጽሐፍ በሃሳብ ሙሉ እንዲሆን የተለያዩ ማስረጃዎችም ተካተዉበታል።

በዚህ የመጽሐፍ ምረቃም የኢፌዲሪ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌዉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ፤ፕሮፌሰር ሲሳይ አውጋቸውና የተለያዩ ከፍተኛ የክልል አመራሮች ምሁራኖች ተገኝተዋል።

የመጽሐፍ ምረቃዉን ሙሉ ፕሮግራም በአሻራ ሚዲያ ይጠብቁን።

( አሻራ ሚዲያ )
1.7K views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 09:07:03 በጎንደር በተከሰተው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ 373 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል - የአማራ ክልል ሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደህንነት ቢሮ
**

በጎንደር በተከሰተው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ ሚና የነበራቸው 373 ግለሰቦች በፀጥታ መዋቅሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአማራ ክልል ሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደህንነት ቢሮ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቡድን በመንቀሳቀስ ለዝርፊያ እና ለቃጠሎ ተሰማርተው በመገኘት እና የግጭቱ ፊትአውራሪ በመሆን ለተፈጠረው ግጭት ምክንያት መሆናቸውን የቢሮው ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ጉዳዩ እንደተከሰተ ፈጣን እርምጃ ባለመውሰድ፣ ትዕዛዝ በመጠበቅ እና በቸልተኝነት በመመልከት ለችግሩ መባባስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሚና በተጫወቱ የፀጥታ መዋቅር እና የፖለቲካ አመራር ላይም ከእስር ጀምሮ በሕግ ለመጠየቅ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በጎንደር ከተማ የፀጥታ ችግሩ እንዲያገረሽ የሚሠሩ ኃይሎችን እንደማይታገስ ነው የአማራ ክልል ሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደህንነት ቢሮ ያሳሰበው።

በከተማው የፀጥታ ችግር ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እየተሠራ ስለሚገኘው የሰላም ማረጋገጥ ተግባራት ላይ መግለጫ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ሰጥተዋል።

ከሚያዝያ 18 ጀምሮ ለጎንደር የፀጥታ ችግር መነሻ እና መባባስ ምክንያቶችን ለመቅረፍ በርካታ ተግባራት እየተሠሩ ቢሆንም ከውስጥ እና ከውጭ፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ጭምር በሚታየው ገፊ ምክንያቶች አለመረጋጋቱ እስከ ትናንት ሚያዝያ 20 ድረስ ቀጥሎ ከ20 በላይ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች በመካከለኛ እና ከፍተኛ ሁኔታ ቃጠሎ መከሰቱን እንዲሁም 11 ቤቶች በከፊል እና በሙሉ መዘረፋቸውን ገልጸዋል።

በጉዳቱ እስከ አሁን ከሁለቱ እምነቶች 14 ዜጎች ሕይወታቸው ማለፉን እና ከእዚህ ውስጥ 7 አስከሬኖች ቤተሰቦቻቸው የሆስፒታል መረጃዎችን በማቅረብ ወስደዋቸዋል።

ከቀላል እስከ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው 118 ሰዎች ደግሞ ሕክምና ላይ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል።

በከተማው ከምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ የተሽከርካሪ እና የግለሰብ እንቅስቃሴ ገደብን ጨምሮ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስን፣ የፀጥታ መዋቅር አልባሳት ለብሶ መገኘት፣ ከከተማ የሚገባም ሆነ የሚወጣ መሣሪያ መከልከሉም ተገልጿል።
1.8K viewsedited  06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 18:02:19 ወራቤ ዩንቨርሲቲ ያላችሁ??
1.4K views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 18:01:46 #በደባርቅ_ከተማ_ተከስቶ_የነበረዉ_መጠነኛ_የጸጥታ_ችግር_ወደነበረበት_ሰላምና_መረጋጋት_ተመልሷል!

ረፋድ 2፡50 ገደማ በከተማዉ ቀበሌ 01 በምትገኘዉ የጎጢት ማርያም ቤተክርስቲያን የተከሰተዉን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ የተፈጠረዉ መጠነኛ የፀጥታ ችግር በአካባቢዉ ወጣቶች፣ በሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሃይል፣ በአካባቢዉ ሚሊሻና መላዉ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረገዉ ብርቱ ጥረት ወደነበረበት ሰላምና መረጋጋት ተመልሷል፡፡ እሳቱም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል፡፡

የመንግስት የጸጥታ መዋቅር ከአካባቢዉ ህዝብ ጋር በመቀናጀት አጥፊዎችን ለማሳዎቅና በቁጥጥር ስር ለማዋል ስምሪት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን፤ የጸጥታ ምክር ቤቱ የችግሩን ምንጭ፣ የደረሰበትን ዉጤት አስመልክቶ የሚሰጠዉን መግለጫ ተከታትለን የምናሳዉቅ ይሆናል፡፡

ይሁን እንጅ አካባቢዉ ጠላት በቅርብ ርቀት የሚገኝበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለጠላት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ፤ ህዝባችን አብሮ የመኖር እሴቱን ለማጠናከር አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት ለአካባቢዉ ሰላምና መረጋጋት የበኩሉን እንዲዎጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን
ሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም
ደባርቅ፡
1.4K viewsedited  15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 22:39:24 ጎንደር እና የዛሬ ውሎ ትክክለኛ መረጃ!

በዛሬው ዕለትም በጎንደር ተኩስ ይሰማል እያሉ የሚፅፉት ሀሰት ነው። ዛሬ ምንም አይነት ተኩስ አልነበረም።

የእምነት አባቶችና ነዋሪዎች ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ነዋሪዎች የእምነት ልዩነት ሳይገድባቸው ተጎጅዎችን በማበረታታትና በመጠየቅ ላይ ናቸው።

የአገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት አባቶች፣ በውይይት የተሳተፉ አካላት ችግሩ ወደተፈጠረበት ቦታ ሄደው አይተዋል።

ችግሩ ተፈጠረ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ የፀጥታ አካላት በየአካባቢው ሰላም በማስከበር ላይ ይገኛሉ። በርካታ ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።
1.3K viewsedited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 23:03:56
የጎንደርን ሰላም ለማናጋት ጠላት የሸረበው ሴራ በማኅበረሰቡ እና በጸጥታ ኀይሉ ጥረት ሳይሳካ መቅረቱን የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ።
***
በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን የጸጥታ መደፍረስ አስመልክቶ የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ግጭቱ የተፈጠረው በጎንደር ከተማ የአንድ ታላቅ የሃይማኖት አባት ሥርዓተ ቀብር በሚፈፀምበት ወቅት ግለሰቦች ባነሱት አለመግባባት እንደሆነ አስረድተዋል።

አቶ ደሳለኝ እንዳሉት ግጭቱ የተፈጠረው የክርስትና እና የእስልምና እምነት በሚያመልኩባቸው አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ለሥርዓተ ቀብር የሚሆን ድንጋይ ለማንሳት በነበረው ሂደት ሀብቱ የኛ ነው በሚል ግጭቱ መነሳቱን ገልጸዋል።

በግለሰቦች የተነሳው አለመግባባት የተለየ ተልዕኮ በነበራቸው አካላት ሰፍቶ የቡድን መልክ በመያዝ የከተማዋን ጸጥታ ለማድፍረስ መሞከሩን ነው ያስረዱት።

የሁለቱ እምነት ተከታዮች የቆየ ጠንካራ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል እንዳላቸው የገለጹት ኀላፊው ጉዳዩ በምክክር እና በመግባባት የሚፈታ ቢሆንም ጠላት ጉዳዩን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት አድርጓል ነው ያሉት።

የተለየ ተልዕኮ የነበረው ቡድን አጋጣሚውን በመጠቀም አካባቢው ወደ አለመረጋጋት እንዲገባ ቢሞክርም በሁለቱ እምነት ተከታይ ወጣቶች እና በፀጥታ ኀይሉ ጥረት ጉዳዩ ሳይሳካ መቅረቱን ነው ለአሚኮ የተናገሩት።

አቶ ደሳለኝ ጉዳዩን ለማረጋጋት የተቻለ ቢሆንም አሁንም ችግር ለመፍጠር የሚሞክር አካል ካለ ያለምህረት ሕጋዊ እርምጃ የፀጥታ ኀይሉ እንዲወሥድ መታዘዙን አስረድተዋል። መረጃው የአሚኮ ነው።
1.3K viewsedited  20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:33:56
«እንኳን ወደ ኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ ፊንፊኔ በደህና መጡ!»

በአዲስአበባ በቂርቆስ ክ/ከተማ የተሰቀለ ቦርድ!
1.1K viewsedited  05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 07:45:41
በህወሓት ስር ያለችው ትግራይ መቀሌ ለኗሪዎቿ ሲኦል ሆናለች የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች:: መረጃው የድምጸ ወያኔ ነው መንጋ የህወሓት ደጋፊ ዲያስፓራ ይህ አይገባውም ጉዳዩ ከህዝቡ ሳይሆን ከህወሓት ነው

-የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ስርቆትና በመንገድ ላይ ሃንግ መበራከቱን ገለፁ።

-ሌሊት በጣም በብዙ አካባቢዎች ጣራ ላይ ያሉ የዲሽ እቃዎች ይሰረቃሉ።ሮቶ፣ቤት ውስጥ በመግባትም ጀሪካን እንኳን ሳይቀር ይሰረቃል።

-ቤት ግቢ ሰብረው በመግባት መዝረፍ እና መንገድ ላይ ሴቶችን አስቁመው ሃንግ የሚያደርጉ አሉ።

-ህዝቡ በጣም ቸግሮታል፣ሰው የሚሰርቁ ወደ ህግ ቢያቀርብ እንኳን የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች #በነፃ ይለቋቸዋል።ህዝቡ ሰሚ አጥታል።እንዲህ ከቀጠልን አስጊ ነው፣ሰሚ የለም።

-የመቀሌ ከተማ የፀጥታ አስተባባሪ አቶ ተስፋይ ገ/ማርያም በያዝነው ወር በከተማው በመሳርያ የታገዘ ትልልቅ ወንጀሎች ተፈፅመዋል ብለዋል።

እንግዲህ በህወሓት ስር ያለ ህዝብ በዚህ ሁኔታ ላይ ነው።
1.1K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ