Get Mystery Box with random crypto!

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zekr_menzuma — ﷽ዚክረ መንዙማﷺ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zekr_menzuma — ﷽ዚክረ መንዙማﷺ
የሰርጥ አድራሻ: @zekr_menzuma
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.48K
የሰርጥ መግለጫ

የኛን #You_Tube ቻናል ለማግኝት ይሄን ይጫኑ⬇️👇
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ በቦት
@ZEKR_MENZUMA_bot ተጠቅመዉ ያድርሱን✍️
የመውሊድ ሀድራ ቪዲዮ በድምፅ የተቀዳ መንዙማ ያላቹ ላኩልን
{ @ZEKR_MENZUMA_bot }

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-02-20 16:03:04
#ለሀድራ_አሽቆች_ብቻ

የተለያየ አይነት መጠን ያላቸውን ድቤዎችን እንሸጣለን መግዛት ለምትፈልጉ በዉስጥ ያናግሩን
@ABD_ABD2
ስልክ
0966807265
ክፍለ ሀገር ላላቹም እንልካለን
አድራሻችን
አዲስ አበባ
#አቶቢስ_ተራ
604 views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 07:42:25
ከመንግስት አካል ጋር ያለውን ጠብ በተቻለ መጠን በራሳችሁ መንገድ እዚያው ለመፍታት ሞክሩ። በዚህ መሀል መስሊሙ ምንም የሚያገባው ነገር የለም። በጉዳዩ ውስጥ ደም ለማፍሰስ አይደለም ጎራ ለይቶ አስተያየት ለመስጠትም አያስፈልገውም። በግድ ጠላት የማብዛት ስትራቴጂም ለምን እንደምትከተሉ አይገባኝም፥ በቂ ጠላት አላችሁ የማይመለከተውን ሁሉ እየጎተታችሁ ሚስኪን ስለመግደል አትዘባበቱ። ይህ ዛቻ የት አካባቢ እንደሚፈጸም ከልምድ ስለምናውቀው ትንሽም ቢሆን ማስጠንቀቅ ይኖርብናል። ከ300 ሺ በላይ ተከታታይ ያለው፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ የፈለገው ሊቃነ ጳጳሳት ጋ በቀላሉ በስልክ ማነጋገር የሚችል አልፎም አንዳንዴ መልዕክት በደብዳቤ የሚቀበልና የሚያደርስ ሲያሻውም ሙልጭ አድርጎ በዱርየ ቃላት የሚሳደባቸውና "ጎሽ" የሚሉ በርካታ መንጋዎች ያሉት ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ነው። በቅስቀሳው ብዙ ምዕመን ዘንድ የሚደርስ ግለሰብም ጭምር ነውና በሱ ሳቢያ ሙስሊሙ ላይ የሚፈጠሩ ግፎች አብዝተው ያሰጉኛል።
___________
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
394 viewsedited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 07:21:11 Channel name was changed to «﷽ዚክረ መንዙማﷺ»
04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 09:37:28
እስልምና ካስተማረን ውብ ባህሪያት አንዱ በማይመለከትህ ጉዳይ ውስጥ አለመግባትን ነው
ለዚህም ይመስለኛል በቤተክርስቲያን ጉዳይ አብዛኛው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ የቤተክርስቲያኗን ደህንነትና አንድነት ጸንቶ እንዲቆይ ህዝቡ በአንድነት እጅ ለእጅ እንዲያያዝ ከልባችን እየተመኘን ያለነው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ ክፉ እንዲነካት አይፈልግም
ግን አሁን አሁን ጭር ሲል የማይወዱ አንዳንድ መምህር መሳይ መምህሮች በግድ ተናገሩ እያሉን ነው
አባቴ ስው ቤት እንደለመደብህ ዘው ከምትልና በማታውቀው ጉዳይ ከምትዘባርቅ ቤትህ ውስጥ ያለው ችግር ቀድመህ ፍታ!!!!!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሶች እጅ ለእጅ ተያያዙ አንድ ሁኑ አትለያዩ በተረፈ አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

Join Tg
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
2.4K viewsedited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 09:35:45
❝..አዛን ለምን በኦሮምኛ አይደረግም?..❞
..
ውዝግብ ያስነሳውን የሊቃነ ጳጳሳት ሹመት የሚቃወሙ የኦርቶዶክስ ሰዎች እያስጮሁት ያለው ሀሳብ ነው። እዚህ ውስጥ "አዛን" ምን ሊያደርግ እንደገባ ባላውቅም ይህ ጉዳይ በእስልምና ግልጽና የተብራራ ሀሳብ ስለሆነ ማንም ሰው በቋንቋየ አዛን ይደረግ ብሎ ጥሪ አያቀርብም። በመሠረቱ አዛን "ኑ ወደ ሰላት" የሚል ጭብጥ ያለው ጥሪ ነው። ማንኛውም ሰው ግን የትኛውንም የሀይማኖት ክፍል በቋንቋው እንዲማር እስልምና ያስተምራል። ይህ እናንተ እንዳሰባችሁት ለብሔርተኝነት ፉክክር ሳይሆን ከጥንትም ጀምሮ የሚተገበርና አላማውም ሰዎች እምነታቸውን እንዲያውቁ በማሰብ የሚደረግ መሠረታዊ ቀናዒ ተግባር ነው። እስልምና በዚህ በኩል ክፍተት የለበትም፥ ምዕመኑም ይህንን ጠንቅቆ ያውቃልና በጥቃቅን እውቀታችሁ ተመርኩዛችሁ ጥሩ ማነጻጸርያ ያመጣችሁ እየመሰላችሁ ራሳችሁን ትዝብት ውስጥ አትጣሉ..!
..
በተረፈ መሠል ጉዳይ እያነሳችሁ ስትናቆሩን ግራ እያጋባችሁንም ነው። በኛ በኩል ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያን ስለሆነና ስለማይመለከተን ነው ዝም ያልነው..?! መቸ ነው ምርኩዝ ሳታደርጉን እዚያው ችግራችሁን የምትፈቱት ግን? እናንተ እንደምታደርጉት በጠባችሁ መሀል ሁሉ ሳይድ እየያዝን እሳት እንድናቀጣጥል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ነውርማ እወቁ..!

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
http://youtube.com/@zekrmenzumaneshidatube
2.0K viewsedited  06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 07:47:19
ሀጅ ካሚል አህመድ፣ ለ42 ዓመታት በጅማ ከተማ ሙኒር መስጂድ በሙአዚንነት አገልግለዋል። ተዛማጅ የዒልም ምግገባ ሲሰጡም ቆይተዋል። በግፍ ሳቢያ ከሚወዱት ተግባር ሳይቋረጡ፣ በፅናት ሲኻድሙ ቆይተዋል። ሀጅ ካሚል የክብርት ወ/ሮ Muferihat Kamil Ahmed አባትም ናቸው።

ዛሬ ለህልፈት መብቃታቸው ተነግሯል። ዛሬ አዲስ-አበባ አንዋር-መስጅድ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ይስሰገድባቸዋል ተብሏል። ኸይር ስራቸውን አላህ ይቀበላቸው፣ ለወዳጅ ዘመድ መፅናናት ይኹን። ኢና ሊላሂ ወኢናኢለይሂ ራጂዑን!

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
http://youtube.com/@zekrmenzumaneshidatube

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

Join Tg
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
2.9K views04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 10:06:14
729 views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 10:06:12 የሱመያ መስጅድ ሚናራ መስቀል ሆነ እንዴ???
——————————————————————-
ከ9 ዓመት በፊት አንድ በኬኒያ ናይሮቢ በአማርኛ ቋነቋ ታትሞ በነፃ የሚታደል መፅሄት አግኝቼ አነበበኩ ።መፅሄቱ የኢየሱሳዊያኑ ነው።

ኬኒያ እንደሚታተም እና መፅሄቱ የኢየሱሳዊያን መሆኑ እንጂ የትኛው ድርጅት እንደሚያሳትመው ማን እንደሚያከፋፍለው አይታወቅም።

ይህ መፅሄት በውስጥ ገፁ የአፍሪካን ካርታ ያስቀምጥ እና እነሞሮኮ አልጀሪያ ግብፅ ሱዳን ቱኒዚያ ጅቡቲ ሶማሊያማሊ ናይጀሪያ እና ሙስሊም በዝ አገራትን በጥቁር አቅልሞ ሌሎች ክርስቲያን በዝ ብሎ ያሰባቸውን ነጭ ቀብቷል።

ለስእሉ ማብራሪያ ሲያስቀምጥ

-ጥቁር የተቀቡት አሁን በጨለማ ውስጥ ያሉ ኢየሱስ ያልተሰበከባቸው ኋላቀር የሙስሊም አገራት።
-ነጭ የተቀቡት ብርሃን የደረሳቸው ኢየሱስን የተቀበሉ ሱልጡን ህዝቦች መገኛ ይላል።

ከዚያ በቀጣዩ ገፅ አንድ ፎቶግራፍ አስቀምጧል ምስሉ ላይ አንድ መስጅድ እና ቤተክርስቲያን ጎን ለጎን ይታያሉ ሚናራው ረጅም ሲሆን የበተስኪያኑ ደወል ቤት ከመስጊዱ አንፃር አጠር ይላል።

ማብራሪየ‍ኣውእንዲህ ይላል

ይህ ከላይ የምታዩት ምስል የተነሳው ግብፅ ካይሮ ሲሆን እስላሞች ክርስቲየኖችን እንዴት እንደሚጨቁኑ ያሳያል ። በምስሉ ላይ እንደምታዩት መስጊዱ ከቤተክርስቲያኑ ከፍ ብሎ ይታያል ።ይላል።

ደግሜ አነበብኩት አልገባኝም ለሶስተኛ ጊዜ አነበብኩት አልገባኝም ምን ማለት ፈልጎ ነው ???መስጅዱ የቤተስኪያኑ ደዎል ቤት ከፍ ብሎ እንዳይሰራ ከልክሎ ነው?መስጅዱ በተስኪያኑ ከተሰራ በኋላ ሆን ብሎ ከጎኑ ተገንብቶ ነው? ምንድነው ሃሳቡ ሳይገባኝ ተውኩት።

በዛ ላይ በተስኪያኑ የቂብጥ ኦርቶዶክሳዊየኑ ነው መፅሄቱ ደሞ የኢየሱሳዊያኑ እውን ኢየሱሳዊያኑ ለ ኦርቶዶክሳዊያን ተቆርቁረው ወይስ???? አልገባኝም ነበር።

ግን ትላትና ወደመገናኛ ለጉዳይ ስሄድ ሱመያ መስጅድ አካባቢ መንገድ ተጨናንቆ ለአፍታ ቆም አልኩ እና አይኔን ወደመስጅዱ ወርወር ባደርግ ያ ከ9 አመታት በፊት መልስ ያላገኘሁለት የመፅሄቱ ግራ ዘመም ሃሳብ ተገለፀልኝ።

ነገሩ እንዲህ ነው መገናኛ ሱመያ መስጅድ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ጥቂት ሰፋ ያሉ እና አይንገብ መስጅዶች መካከል አንዱ ነው።

የምንወዳቸው የአንድነት አባት የጀግንነት ተምሳሌት የተግባር ሰው ታላቁ ዓሊም ሸኽ ሰኢድ ሱመያ (አላህ ይማራቸው) ያቀኑት መስጅድ ነው።

ይህ ውብ መስጅድ እንዲሁ በዋዛ አልተገኘም በጨቋኞች እንቢተኝነት በተነሳ ግርግር ደም ተከፍሎበታል ።

ይህን የሚያውቁቱ ኢየሱሳዊያን ከዚህ መስጅድ አጠገብ ከ200 ሜትር በታች በሆነ እርቀት ቸርች ከመገንባት አልፈው እነሱ አናሳ በሚሆኑበት ቦታ ላይ ጭቆና ያሉትን ተግባር ፈፅመው ሳይ ገረመኝም ገባኝም።

ግን ደግሞ ኢየሱሳዊያኑ ይህን መስራታቸው ሳይሆን ሱመያን የመሰለ መስጅድ መስራት የቻለው ህዝበ ሙስሊም ይህን ያህል ዘመን ሚናራ መስራት ለምን አቃተው።

ሚናራ ቅንጦት አይደለም
ሚናራ ዳኢ ነው
ምልክቴ እና አርማየም ነው
ሰዎች ምልክቴ ያሉትን መስቀል በመስጅድ አናት ላይ መሳየት ችለው እኛ ሚናራ መስራት ለምን አቃተን?
740 views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 06:54:38 ሀበሻ ኢጅቲማ ታህሳስ 28-29-30
ዘንድሮም ሊካሄድ ነው!

ታላቁ የአለም ኢጅቲማዕ በውቢቷ ቡታጅራ ታህሣሥ 28 29 እና 30 ከ20 በላይ የአለም ሀገራት ከተወጣጡ ከ8ሺ በላይ ጀመአዎች(ጀመአ ነው ያልኩት ሰዎች አላልኩም ) ይገኙበታል ልቡን አንድ አድርጎ ስለ ኡመቱ ይወያያል ዱአ እና ዳዕዋ ያደርጋል ሙሀባ ይዘንባል የአላህ ራህመት ይወርዳል ሀበሻ ትደሰታለች እኛም ኢማናችን ታድሶ እንደሰታለን ኢንሻአላህ

ከኢጅቲማው በፊት ፊሰቢሊላህ መውጣት ለኢጅቲማው ሩህ ነውና በቻልነው 4ወር 40ቀን ወይም 3ቀን ወጥተን ኢማናችንን አድሰን ለኢጅቲማው ሩህ እናበጅለት

ሰይዳችን(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) 124ሺ ሰሃቦቻቸውን ሙሉ ኢጅቲማዕ ሰብስበው ነበር ሰሀቦቹም ዳዕዋ ለማድረግ በአለም ላይ ተበትነው ነበር እኛም ኢንሻአላህ ከኢጅቲማው በኋላ አለምን እየዞርን ዳዕዋ የምናረገበትን እድል አላህ ያመቻችልን

ይሄን መልዕክት ላልደረሳቸው አድርሱልኝ

ቡታጅራ አንቀርም እዛው እንገናኝ

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
http://youtube.com/@zekrmenzumaneshidatube

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

Join Tg
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

http://youtube.com/@zekrmenzumaneshidatube
751 views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 12:25:22 አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡
||
ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን...
*
እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:-
«አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል።

ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል።
:
ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ።
:
እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል...
ሃሃሃ!

ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው...
:
ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ...
(ያዝ እንግዲህ¡)

በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው።

ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት።
ሃሃ!
:
ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት።

ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ።

ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል።

ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው።
እህእ!
:
ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ።

ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ።

ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ።
:
ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም።
ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም።
አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ

ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ።
እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ።
ሃሃሃ!
:
ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ።
በዚህ መልኩ ሁሉም ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...»
ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ።
:
መቼም ይህንን አንብቦ ያልሳቀ ካለ እኔንጃ

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
http://youtube.com/@zekrmenzumaneshidatube

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

Join Tg
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
1.0K viewsedited  09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ