Get Mystery Box with random crypto!

ከመንግስት አካል ጋር ያለውን ጠብ በተቻለ መጠን በራሳችሁ መንገድ እዚያው ለመፍታት ሞክሩ። በዚህ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

ከመንግስት አካል ጋር ያለውን ጠብ በተቻለ መጠን በራሳችሁ መንገድ እዚያው ለመፍታት ሞክሩ። በዚህ መሀል መስሊሙ ምንም የሚያገባው ነገር የለም። በጉዳዩ ውስጥ ደም ለማፍሰስ አይደለም ጎራ ለይቶ አስተያየት ለመስጠትም አያስፈልገውም። በግድ ጠላት የማብዛት ስትራቴጂም ለምን እንደምትከተሉ አይገባኝም፥ በቂ ጠላት አላችሁ የማይመለከተውን ሁሉ እየጎተታችሁ ሚስኪን ስለመግደል አትዘባበቱ። ይህ ዛቻ የት አካባቢ እንደሚፈጸም ከልምድ ስለምናውቀው ትንሽም ቢሆን ማስጠንቀቅ ይኖርብናል። ከ300 ሺ በላይ ተከታታይ ያለው፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ የፈለገው ሊቃነ ጳጳሳት ጋ በቀላሉ በስልክ ማነጋገር የሚችል አልፎም አንዳንዴ መልዕክት በደብዳቤ የሚቀበልና የሚያደርስ ሲያሻውም ሙልጭ አድርጎ በዱርየ ቃላት የሚሳደባቸውና "ጎሽ" የሚሉ በርካታ መንጋዎች ያሉት ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ነው። በቅስቀሳው ብዙ ምዕመን ዘንድ የሚደርስ ግለሰብም ጭምር ነውና በሱ ሳቢያ ሙስሊሙ ላይ የሚፈጠሩ ግፎች አብዝተው ያሰጉኛል።
___________
https://t.me/ZEKR_MENZUMA