Get Mystery Box with random crypto!

❝..አዛን ለምን በኦሮምኛ አይደረግም?..❞ .. ውዝግብ ያስነሳውን የሊቃነ ጳጳሳት ሹመት የሚቃወሙ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

❝..አዛን ለምን በኦሮምኛ አይደረግም?..❞
..
ውዝግብ ያስነሳውን የሊቃነ ጳጳሳት ሹመት የሚቃወሙ የኦርቶዶክስ ሰዎች እያስጮሁት ያለው ሀሳብ ነው። እዚህ ውስጥ "አዛን" ምን ሊያደርግ እንደገባ ባላውቅም ይህ ጉዳይ በእስልምና ግልጽና የተብራራ ሀሳብ ስለሆነ ማንም ሰው በቋንቋየ አዛን ይደረግ ብሎ ጥሪ አያቀርብም። በመሠረቱ አዛን "ኑ ወደ ሰላት" የሚል ጭብጥ ያለው ጥሪ ነው። ማንኛውም ሰው ግን የትኛውንም የሀይማኖት ክፍል በቋንቋው እንዲማር እስልምና ያስተምራል። ይህ እናንተ እንዳሰባችሁት ለብሔርተኝነት ፉክክር ሳይሆን ከጥንትም ጀምሮ የሚተገበርና አላማውም ሰዎች እምነታቸውን እንዲያውቁ በማሰብ የሚደረግ መሠረታዊ ቀናዒ ተግባር ነው። እስልምና በዚህ በኩል ክፍተት የለበትም፥ ምዕመኑም ይህንን ጠንቅቆ ያውቃልና በጥቃቅን እውቀታችሁ ተመርኩዛችሁ ጥሩ ማነጻጸርያ ያመጣችሁ እየመሰላችሁ ራሳችሁን ትዝብት ውስጥ አትጣሉ..!
..
በተረፈ መሠል ጉዳይ እያነሳችሁ ስትናቆሩን ግራ እያጋባችሁንም ነው። በኛ በኩል ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያን ስለሆነና ስለማይመለከተን ነው ዝም ያልነው..?! መቸ ነው ምርኩዝ ሳታደርጉን እዚያው ችግራችሁን የምትፈቱት ግን? እናንተ እንደምታደርጉት በጠባችሁ መሀል ሁሉ ሳይድ እየያዝን እሳት እንድናቀጣጥል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ነውርማ እወቁ..!

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
http://youtube.com/@zekrmenzumaneshidatube