Get Mystery Box with random crypto!

የሱመያ መስጅድ ሚናራ መስቀል ሆነ እንዴ??? ——————————————————————- ከ9 ዓመት በፊ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የሱመያ መስጅድ ሚናራ መስቀል ሆነ እንዴ???
——————————————————————-
ከ9 ዓመት በፊት አንድ በኬኒያ ናይሮቢ በአማርኛ ቋነቋ ታትሞ በነፃ የሚታደል መፅሄት አግኝቼ አነበበኩ ።መፅሄቱ የኢየሱሳዊያኑ ነው።

ኬኒያ እንደሚታተም እና መፅሄቱ የኢየሱሳዊያን መሆኑ እንጂ የትኛው ድርጅት እንደሚያሳትመው ማን እንደሚያከፋፍለው አይታወቅም።

ይህ መፅሄት በውስጥ ገፁ የአፍሪካን ካርታ ያስቀምጥ እና እነሞሮኮ አልጀሪያ ግብፅ ሱዳን ቱኒዚያ ጅቡቲ ሶማሊያማሊ ናይጀሪያ እና ሙስሊም በዝ አገራትን በጥቁር አቅልሞ ሌሎች ክርስቲያን በዝ ብሎ ያሰባቸውን ነጭ ቀብቷል።

ለስእሉ ማብራሪያ ሲያስቀምጥ

-ጥቁር የተቀቡት አሁን በጨለማ ውስጥ ያሉ ኢየሱስ ያልተሰበከባቸው ኋላቀር የሙስሊም አገራት።
-ነጭ የተቀቡት ብርሃን የደረሳቸው ኢየሱስን የተቀበሉ ሱልጡን ህዝቦች መገኛ ይላል።

ከዚያ በቀጣዩ ገፅ አንድ ፎቶግራፍ አስቀምጧል ምስሉ ላይ አንድ መስጅድ እና ቤተክርስቲያን ጎን ለጎን ይታያሉ ሚናራው ረጅም ሲሆን የበተስኪያኑ ደወል ቤት ከመስጊዱ አንፃር አጠር ይላል።

ማብራሪየ‍ኣውእንዲህ ይላል

ይህ ከላይ የምታዩት ምስል የተነሳው ግብፅ ካይሮ ሲሆን እስላሞች ክርስቲየኖችን እንዴት እንደሚጨቁኑ ያሳያል ። በምስሉ ላይ እንደምታዩት መስጊዱ ከቤተክርስቲያኑ ከፍ ብሎ ይታያል ።ይላል።

ደግሜ አነበብኩት አልገባኝም ለሶስተኛ ጊዜ አነበብኩት አልገባኝም ምን ማለት ፈልጎ ነው ???መስጅዱ የቤተስኪያኑ ደዎል ቤት ከፍ ብሎ እንዳይሰራ ከልክሎ ነው?መስጅዱ በተስኪያኑ ከተሰራ በኋላ ሆን ብሎ ከጎኑ ተገንብቶ ነው? ምንድነው ሃሳቡ ሳይገባኝ ተውኩት።

በዛ ላይ በተስኪያኑ የቂብጥ ኦርቶዶክሳዊየኑ ነው መፅሄቱ ደሞ የኢየሱሳዊያኑ እውን ኢየሱሳዊያኑ ለ ኦርቶዶክሳዊያን ተቆርቁረው ወይስ???? አልገባኝም ነበር።

ግን ትላትና ወደመገናኛ ለጉዳይ ስሄድ ሱመያ መስጅድ አካባቢ መንገድ ተጨናንቆ ለአፍታ ቆም አልኩ እና አይኔን ወደመስጅዱ ወርወር ባደርግ ያ ከ9 አመታት በፊት መልስ ያላገኘሁለት የመፅሄቱ ግራ ዘመም ሃሳብ ተገለፀልኝ።

ነገሩ እንዲህ ነው መገናኛ ሱመያ መስጅድ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ጥቂት ሰፋ ያሉ እና አይንገብ መስጅዶች መካከል አንዱ ነው።

የምንወዳቸው የአንድነት አባት የጀግንነት ተምሳሌት የተግባር ሰው ታላቁ ዓሊም ሸኽ ሰኢድ ሱመያ (አላህ ይማራቸው) ያቀኑት መስጅድ ነው።

ይህ ውብ መስጅድ እንዲሁ በዋዛ አልተገኘም በጨቋኞች እንቢተኝነት በተነሳ ግርግር ደም ተከፍሎበታል ።

ይህን የሚያውቁቱ ኢየሱሳዊያን ከዚህ መስጅድ አጠገብ ከ200 ሜትር በታች በሆነ እርቀት ቸርች ከመገንባት አልፈው እነሱ አናሳ በሚሆኑበት ቦታ ላይ ጭቆና ያሉትን ተግባር ፈፅመው ሳይ ገረመኝም ገባኝም።

ግን ደግሞ ኢየሱሳዊያኑ ይህን መስራታቸው ሳይሆን ሱመያን የመሰለ መስጅድ መስራት የቻለው ህዝበ ሙስሊም ይህን ያህል ዘመን ሚናራ መስራት ለምን አቃተው።

ሚናራ ቅንጦት አይደለም
ሚናራ ዳኢ ነው
ምልክቴ እና አርማየም ነው
ሰዎች ምልክቴ ያሉትን መስቀል በመስጅድ አናት ላይ መሳየት ችለው እኛ ሚናራ መስራት ለምን አቃተን?