Get Mystery Box with random crypto!

LEARN GUITAR 👉EMANI

የቴሌግራም ቻናል አርማ theonlyw — LEARN GUITAR 👉EMANI L
የቴሌግራም ቻናል አርማ theonlyw — LEARN GUITAR 👉EMANI
የሰርጥ አድራሻ: @theonlyw
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.61K
የሰርጥ መግለጫ

https://youtu.be/h0umrphh0b8 👈 My you tube channel

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 13:08:09 Used lead guitar የሚሸጥ inbox me


@Mytafache


0978422547
1.4K viewsedited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 13:07:48
1.2K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 13:07:48
1.1K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 17:16:15 #የሚሸጥ #ጊታር ያለው ሰው በየትኛውም ጊዜ በውስጥ ያናግረን
@Mytafache

ወይንም 0978422547 ይደውሉልን
6.1K viewsedited  14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:38:08
Amazing Grace (with lyrics) - The most BEAUTIFUL hymn!
3.1K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:51:11
#john #Newton #amazing #grace #story
2.8K viewsedited  19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:49:09 ◍◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◍
#Amazing #grace የመጨረሻ ክፍል
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈


ክፍል 4 ....

#ጆን #ኒውተን በእኩለ ሌሊት ከእንቅልፍ ሲነቃ መርከቧ በሙሉ በውሃ #ተጥለቅልቃለች ልትሰጥም ምንም አልቀራትም ነበር፣ በዚህን ጊዜ ውስጥ የነበሩ ጓደኞቹ በጣም ተደናግጠው መጮህ ሲጀምሩ #ጆን #ኒውተንም መጮህ ጀመረ ነገር ግን #የጆን #ኒውተን ከሌሎቹ ጩኸት ይለያል ፤ ያኔ በትንሽነቱ ወደ ሚያውቀው ወደ #እግዚአብሔር ነበር #ይጮህ የነበረው፣ በዛ የነበረው ሁኔታ ቢረጋጋም ወደ #ደረቅ ምድር የደረሱት #ከከባድ #የሳምንታቶች ትግል በኋላ ነበር ። #ጆን #ኒወተን #እውነተኛ #ተራኪ በሚል በግል ማስታወሻ ላይ በወቅቱ ስላጋጠማቸው ሁኔታ ሲገልጽ "#የቶሪን #ደሴትን #ከሩቅ #አየናት #ከዛም #በሚቀጥለው #ቀን #ሎግስዊሊ ወደ ተባለችው #የአየርላንድ #ባህር #ዳርቻ #መልህቃችንን ጣልን ይህም ሚያዝያ 8 ቀን፣ ከከባድ አደጋ ከተረፍን ከአራት ሳምንታት በኋላ ማለት ነው። ወደ እዚህ ደሴት ስንመጣ የመጫረሻው ምግባችን እየበሰለ ነበር በዚህ ጊዜ ነው በእርግጥም ፀሎትን የሚሰማ የሚመልስ አምላክ እንዳለ ያወኩት" ብሏል። ጆን ኒውተን ከዚህ አደጋ መከሰት በኃላ የመርከቧ ሠራተኞች በደሴቷ ነዋሪዎች እንክብካቤ ሲደረግላቸው እና መርከባቸውም #ስትጠገን እሱ ግን ከደሴቷ አቅራቢያ ወደ ሚገኘው ዴሪዩ ከተማ በመሄድ በቅዱስ #ኮሎምቦስ #ቤተክርስቲያን ፕሮግራም እንደተካፈለ እና #የአስደናቂ #ፀጋ መዝሙር የግጥሙን የመጀመሪያ #ቁጥሮች እዚያው ሆኖ እንደ ጻፋቸው ይነገራል ፤ መርከቧም ተሰርታ ወደ ሀገሩ እስኪመለስ ድረስ በዚህች ቤተክርስቲያን በቀን #ሁለት ጊዜ እየሄደ ይፀልይ ነበር። መጋቢት 10 1748 የቀሪ ዘመኑ ዳግም ውልደትን ያገኘበት ቀን እንደሆነ በማሰብ ሲያስታውሰው ኖሮአል በዚህም ምክንያት ይህች ታሪካዊ ከተማ #የአሰደናቂ #ፀጋ በመባል የምትጠራ ሲሆን ይህንንም ታሪክ ለማስታወስ ከሚያዝያ 4 አስከ 9 ድረስ የሚቆይ አስደናቂ ፀጋ ( #amazing #grace ) የተባለ #ፊስቲቫል ታዘጋጃለች። ጆን ኒውተን መርከቧ ወደ ሀገሩ መመለስ ስትጀምር መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ጀመረ ፣ ትወልድ ሀገሩ በደረሰበት ጊዜም #ሙሉ #በሙሉ ተለወጠ ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ #የቁማር ፣#የመጠጥ እና #የአመፅ #ህይወቱን አስወገደ፣ ይሁን እንጂ በባሪያ ንግድ ስራ ላይ መሰማራቱን አላቆመም ነበር፤ በ1754 በጠና ታሞ ለሞት ደርሶ ከተረፈ በኋላ የቀረውን ዕድሜ ሙሉ በሙሉ ለጌታ ቤት ለመስጠት በቤተክርስቲያን ውስጥም ጌታን ለማገልገል ለአንግሊካን ቤተክርስቲያን አመልክቶ በ 1764 መጋቢ ሆነ፤ በአገልግሎቱም ሰዎችን በመንከባከብ የታወቀ ስለነበረ በቤተክርስቲያኒቱ አማኞች ዘንድ በጣም የተከበረ ነበር። በዚያን ጊዜ #ዊልያም #ካውፐር ከተባለ ሰው ጋር በመተባበር አስደናቂ ፀጋ የሚለውን መዝሙር ጨምሮ በርካታ መዝሙሮችን ሰርተዋል። ጆን ኒውተን የባሪያ ንግድ ስራ ላይ በመስራቱ በጣም ተፀፅቶ በኋላ ላይ ይህን ስራ በመቃወም በአፍሪካውያን ላይ የሚደረገውን የባሪያ ንግድ "ተሰጣ አቋም" የሚል በራሪ ጹፎችን በማዘጋጀት ይህን ስራ በእጀጉኑ መስራት ችሎአል... ውድ የ Learn guitar emani ታከታታዮች የጆን ኒውተን ታሪክ ይህ ብቻ አይደለም እኔ ያካፈልኳችው ከብዙ በጣም ጥቂቱን ነው ፣ በመጫረሻም ጆን ኒውተን 1807 ነው ያረፈው..
ልጆች ዕድሜያቸው ገና እያለ ከዕድሜያቸው በላይ ሀላፊነት መስጠት ምን ያክል ጉዳት እንደሚያስከትል ዋጋም እንደሚያስከፍል ወላጆች ብዙ ጊዜ አያስተውሉም በጆን ኒውተን ህይወትም የደረሰበት ይህ ነበር፤ ወላጆች ለልጆቻቸው ስራ የመምረጥን ዕድል ሲያገኙ በመንፈሳዊ ህይወታቸው በጤናቸው በስነልቦናቸው በማህበራዊ ሕይወታቸው ምን አይነት ተጽዕኖ ይኖራል ብለው ሳያመዛዝኑ ፣ በጊዜያዊ ጥቅም ታውረው፣ አሉታዊ እና አዎንታዊ ተፅዕኖውን ሳይፈትሹ የሚወሰዱት እርምጃ አደጋ አለው። በሕይወት እያለች የጆን ኒውተን እናት የዘራችበት ዘር በልቡ ወስጥ ስለቀረ እንጂ የጆን ህይወት እጅግ የከፋና በጣም ከባድ ይሆንበት ነበር ነገር ግን ያኔ በውስጡ የዘረችው የእግዚአብሔር ቃል በአደጋ ጊዜ ሲጠራው ታድጎታል፤ የእግዚአብሔር ፀጋ ከኀጢአት ሁሉ ልያነፃን ዛሬም ከእኛ ጋር አለ። #ማንም #በክርስቶስ #ቢሆን #አዲስ #ፍጥረት #ነው።

◌◌◌◌◌◌◌◊◊ ◊◊◌◌◌◌◌◌◌


For any comment and suggestion, question
@Mytafache

#Refr. #book
ብርቅዬዎቹ የወንጌል አርበኞች ሁለተኛ ዕትም
Www. Wikipedia. Com
Www. Biography. Com/John Newton
2.5K viewsedited  19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 06:29:20
John newton #amazing #grace
3.3K views03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 06:27:46 ክፍል 3 ... ( #Amazing #grace)...

በ1942 ዓ.ም የኒውተን አባት ከባህር ላይ ህይወቱ ሙሉ በሙሉ በጡረታ ሲወጣ ልጁን የድርጅቱ እና የሀብቱ አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመው ፣ ይህም ለጆን ኒውተን ቀጣይ ሕይወት መንደርደሪያ ሆኖት ነበር። ጆን ኒውተን ገና የ17 ዓመት ወጣት ሳለ በጣም ችኩል የሆነ ባህሪይ ነበረው ፣ በዚህ ሁኔታ ወስጥ እያለ ሜሪ ካትሌት ከተባለች የቤተሰቡ ወዳጅ ከሆነች ሴት ልጅ ጋር በፍቅር ወድቆ ነበርና በዛን ጊዜ ከእሷ ጋር ለመቆየት ከወሰነው ወሳኔ የተነሳ ወደ ጃማይካ የሚሄደው የመርከብ ጉዞ አመለጠው። ጆን ኒውተን ከሳምንታት በኃላ ወደ ቤቱ ሲመለስ አባቱ ስርዓት መማር እንዳለበት ወስኖ ነበረና ወራትን የሚያስቆጥር ጉዞ ወደ አፍሪካ በሚሄደው መርከብ ላይ በተራ ባህረኝነት ሙያ ምንም አይነት አባታዊ ጥበቃ ሳያደርግለት ወደ ከባዱ የባህር ህይወት ብቻውን ለቀቀው። ጆን ኒውተን በዚህ ጉዞ ላይ ከነበሩት የስራ ባልደረቦቹ ጋር ተዋውቆ ነበር፤ የተዋወቃቸው ጓደኞቹ የነበሩት ሁሉ ግን መልካም የሚባል ባህርይ አልነበራቸውም በዚህም ምክንያት በትንሹም ቢሆን ፈሪሃ ልብ የነበረው ጆን ኒውተን አሁን መንፈሳዊ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ በመጣል የለየለት ጠጪ፣አጫሽ ፣ተንኮለኛ ሆነ እንዲሁም መርከቡ ወደብ በሚደርስበት ጊዜያት ከተለያዩ ሴቶች ጋር በዝሙት ህይወት ወስጥም ተዘፈቀ ፤ ጆን ኒውተን በዚህ በጣም ከባድ ሁኔታ ወስጥ እያለ መጋቢት 1744 ወደ ሌላ "ሮያል" ወደሚባል የእንግሊዝ ባህር ሀይል ወስጥ ገብቶ ነበር ነገር ግን በወቅቱ የባህር ሀይሎች የነበራቸው ጠንካራ አስተዳደራዊ ሁኔታ ለጆን ኒወተን ሱስ በጣም አስቸጋሪና ከባድ ሆኖበት ነበር ከዚህም የተነሳ ጆን ኒውተን ከባህር ሀይል ለመጥፋት ባደረገው ሙከራ ተይዞ ተቀጣ ፣ ቅጣቱም ከምዕራብ አፍሪካ ወደ አውሮፓ ባሪያዎችን በሚያመላልስ መርከብ ላይ እንዲሰራ ማድረግ ነበር ነገር ግን ጆን ኒውተን አመሉ በዚህም ሊገታ አልቻለም፤ በመርከቡ ላይም በሰካራምነቱ እና በአመፀኛነቱ በሠራተኞች ሁሉ የተጠላ ከመሆኑ የተነሳ መርከቧ ሴራሊዮን ስትደርስ በዚያ ባሪያ አስተላላፊ ለነበረው አሞስ ከሌዌ ለተባለ ሰው አሳልፈው ሰጡት በሴራሊዮም ሁለት በጣም አስከፊ ዘመናትን አሳልፎአል ፤ ያንን አስከፊ ጊዜ ጆን ኒውተን ሲገልጽ " #የባሮች #አገልጋይ #ነበርኩ" ብሏል። ጆን ኒውተን በዚህን ወቅት በጣም ተርቦ ፣ታሞ ፣ተጎሳቁሎም ነበር ፤ የቀድሞ መንፈሳዊ ህይወቱንም በትንሹ ማሰብ እንደጀመረ ይነገራል በዚህ ሁኔታ እያለ አባቱ ልጁን ኒውተንን ይፈልገው ጀመረ ለቀድሞ ወዳጆቹም አሳውቆ እነሱም አፈላልገው አግኝተውት ከነበረበት የግዞት ህይወት በማምለጥ ግሬይ ሆንድ በተባለች የግንድ ቅርፊት በጫነች መርከብ ወደ እንግሊዝ ጉዞ ይጀምራሉ፤ እየተጓዙ ሳሉ መጋቢት 10 / 1748 ወደ አየርላንድ ባህር ዳርቻ ከተማ እየተጠጉ ሲመጡ ድንገት በጣም ኃይለኛ ማዕበል ተነሳ ፣ መርከባቸውንም እስክትሰጥም ድረስ ያንገላታት ጀመረ... #ይቀጥላል


@Mytafache
3.4K viewsedited  03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ