Get Mystery Box with random crypto!

LEARN GUITAR 👉EMANI

የቴሌግራም ቻናል አርማ theonlyw — LEARN GUITAR 👉EMANI L
የቴሌግራም ቻናል አርማ theonlyw — LEARN GUITAR 👉EMANI
የሰርጥ አድራሻ: @theonlyw
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.61K
የሰርጥ መግለጫ

https://youtu.be/h0umrphh0b8 👈 My you tube channel

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-14 23:50:31
4.2K views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 23:44:50 ክፍል 2 #amazing #grace..

ሰላም የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ እያልኩ ከ #amazing #grace (አስደናቂው ፀጋ) መዝሙር ጀርባ ያለውን አስደናቂ ታሪክ እየተመለከትን ነው ያለነው በመጀመሪያ ክፍል እንደ መግቢያ ስለ ጆን ኒውተን ተመልክተን ነበር ጆን ኒውተን ገና ትንሽ እያለ ነበር በጣም የሚወዳትን እናቱን በሞት ያጣው ከዚያ በኋላ የጆን ኒወተን ሕይወትስ ምን ሆነ አስደናቂው ፀጋ(#amazing #grace) የሚለውን መዝሙር እንዴት ዘመረ የሚለውን ከዚህ በሚቀጥሉት ክፍሎች የማቀርብ ይሆናል እንድትከታተሉ ይሁን...

#ጆን #ኒውተን ገና ትንሽ ልጅ እያለ ነበር በጣም የሚወዳትን እናቱን በሳንባ ነቀርሳ በሽታ ያጣው የጆን ኒውተን እናት #ኤልሳቤጥ በጣም የተባረከች ለጌታ በጣም መልካም #ልብ ያላት ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ የሚያስደስታት በጣም #መልካም እናት ነበረች በተቃራኒው ደግሞ የጆን አባት #እምብዛም ለእግዚአብሔር መልካም #ልብ አልነበረውም ነገር ግን የጆን ኒውተን እናት ከመሞቷ በፊት ሁሌ ቤተክርስቲያን ስትሄድ #ጆን #ኒውተንን ይዛው ነበር የምትሄደው ይህም ጆን ገና በልጅነቱ ለጌታ መልካም ልብ እንዲኖረው አድርጎታል #ጆን #ኒውተን #በቤተክርስቲያን ውስጥ በሰንበት መገኘት, #ቃል #ማጥናት, ከእናቱ ጋር ዘወትር #ቤተክርስቲያን መሄድ በጣም ይወድ ነበር , #መንፈሳዊ #መዝሙሮችን ደግሞ ይዘምር ነበር ጥሩ መንፈሳዊ #ሕይወትም ነበረው ነገር ግን ይህ የሆነው በጣም የሚወዳት እናቱ እስከነበረችበት ጊዜ ነበር ልክ እናቱ ኤልሳቤጥ በሞት አንደተለየችው ግን ጆን ኒውተን ሌላ ሕይወት ውስጥ ሊገባ ተገደደ.. ለመንፈሳዊ ነገርም ለሌላው ነገርም ብዙም ያልነበረው የጆን አባት ልጁን #ለሁለት #አመታት #አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲቆይ አድርጎታል ከዚያ በኋላ የጆን አባት ሌላ ሚስት አገባ በዚህም ምክንያት የጆን አባት ኦሊቭ (olive) ወደምትባል አገር ሲጓዝ ጆን ከእንጀራ እናቱ ጋር እና ከአባቱ ጋረ አብሯቸው ተጉዟል የጆን አባት በጣም ሀይለኛ የመርከብ #ካፕቴን ነበረ በጣም እረጅም ጉዞዎችን በባህር ላይ ያሳልፋል ...#ጆን #ኒውተን አስራ #አንድ #አመት ሲሞላው የአባቱን ስራ በመቀላቀል እሰከ አስራ ሰባት ዓመቱ መሠረታዊ የባህርተኝነት ትምህርቶችን በመቅሰም ስድስት በጣም ታላላቅ የባህር ላይ ጉዞዎችን ማድረግ ችሏል.. በዚህን ጊዜ ጆን ኒውተን እራሱን እየቻለ ሲመጣ አንዳንድ #life በባህር ላይ ጉዞ መመልከት ጀመረ ብዙ ብር ይመጣለትም ነበር ጆን ቀስ በቀስ በዚህ አለም ሀሳብ #እየተያዘ #ሄደ.. በዚህ ሁኔታ እያለ ግን አንድ አዲስ ነገር በ1742 ተፈጠረ ምን ይሁን??? ... #ይቀጥላል ..... ውድ የ LEARN Guitar Emani ቤተሰቦች በቀጣይ ቀጣዩን ክፍል አቀርብላችዋለሁ እስከዛው ሰላም ቆዩ ለየትኛውም ጥያቄ ወይንም አስተያየት

@Mytafache
3.8K viewsedited  20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 20:45:03
2.5K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 20:43:06 አስደናቂው ፀጋ ( Amazing grace)... ክፍል #አንድ

በዓለም ዙርያ በጣም እጅግ ተወዳጅ
እና በጣም የሚታወቅ ነው በየዓመቱ 10 ሚሊዮን ያህል ጊዜ በዓለም ዙርያ በቤተክርስቲያን ጉባኤዎች ላይ እና በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ ይዘመራል ተብሎ ይነገራል በመንፈሳዊ ዓለም እንዲሁም በ secular ዓለም በጣም ተጽዕኖ ፈጥሯል በቤተክርስቲያንም, በዘፋኞች ዘንድም በጣም ይዘመራል አስደናቂው ፀጋ (Amazing grace) .. ወድ የዚህ ቻናል ተከታታዮች እንዲሁም በየትኛውም አጋጣሚ ይህን ታሪክ የምታነቡ የጌታ ሰላም እና ፀጋ ይብዛላችሁ እያልኩ ከላይ እንደጀመርኩ አስደናቂው ፀጋ ከሚለው መዝሙር ጀርባ ያለውን አስደናቂ ምስክርነት ከዚህ በመቀጠል በጹሑፍ አስቀምጣለሁ እንዲሁም መዝሙሩን ጊታራችንን ይዘን ለማምለክ ኮርዱን በታሪኩ መጨረሻ ላይ አስቀምጣለሁ እስከ መጨረሻ እንድታነቡት በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ መልካም ነገር አለውና አስደናቂው ፀጋ (amazing grace) በታሪክ በጣም እጅግ ተወዳጅ መዝሙር ሲሆን በዚህ መዝሙር ምክንያት በጣም ብዙ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች ተስፋቸው እንደገና ለምልሟል በጣም ብዙ ያዘኑ ልቦች ተጽናንተዋል ብዙ ሰዎች ይህን አስደናቂውን ፀጋ አይተው ጌታን እንደግል አዳኛቸው አድረገው ተቀብለዋል ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን በዘመናት መካከል እንደዚህ አይነት መልካም ነገር የሚያደርግ እሱ ብቻ ሰለሆነ ይህ ብቻ አይደለም ይህ መዝሙር በታሪክ በታላላቅ ክስተቶች ወቅት በጣም በሚደንቅ ሁኔታ ተዘምሮአል አንዳንዶቹን ብንመለከት

በአሜሪካውያኑ እርስበርስ ጦርነት ጊዜ
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው ማርቲን ሉተር ኪንግ #ህልም #አለኝ ባለበት በተቃውሞ ሰልፍ ላይ
የጀርመን ግንብ በፈረሰበት ጊዜ 2011 በደረሰው የሽብር ጥቃት ያዘኑትንና ልባቸው የተሰበረውን ሰዎች ለማጽናናት ተዘምሮአል
እንዲሁም ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ከእስራት በተፈቱ ጊዜ...

የዚህ ተወዳጅ መዝሙር ዘማሪ በጣም የሚገርመው በጣም ቁማርተኛ, በጣም ሱሰኛ በዝሙት የታወቀ ነበር በባሪያ ንግድ ተሰማርቶ የሰራም ነበር
እ.ኤ.አ ሐምሌ 24 1725 በለንደን ተወለደ "ጆን ኒውተን"
ጆን ኒውተን አባቱ የመርከብ ካፕቴን ነበረ ጆን ኒውተን የበኩር ልጅም ነበረ እናቱ ኤልሳቤጥ ትባላለች እጅግ በጣም ጠንካራ መንፈሳዊ ሴት ነበረች ጆን ኒውተን እናቱ ቤተክርስቲያን መሄድ ስለምትወድ ከእሷ ጋር አብሮ በመሄድ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማ ነበረ እንዲሁም መንፈሳዊ መዝሙር በቃሉ ይዘምር ነበረ ጥሩ መንፈሳዊ ህይወት ነበረው ነገር ግን በዚህ ጥሩ ሁኔታ እያለ አንድ ከባድ ነገር ተፈጠረ በጣም የሚወዳት እናቱ በሳንባ ነቀርሳ በሽታ ሞተች በጣም የሚያሳዝነው ጆን ኒወተን በዚያን ጊዜ ዕድሜው ገና ሰባት አመቱ ነበር እንዲያውም ገና ሰባት አመት ሊሞላው ሁለት ሳምንት ሲቀረው ነበር እናቱን ያጣው በዚህ ልጅነቱ እናቱን ማጣት ምን ያክል ከባድ ሊሆንበት እንደሚችል መገመት አይከብድም....ይቀጥላል

በቀጣይ ክፍል በጆን ኒውተን ሕይወት ምን ተፈጠረ የሚለውን የማቀርብላችሁ ይሆናል

https://t.me/theonlyw

For any question and suggestion


@Mytafache
2.4K viewsedited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 08:02:34
አዲስ #used 7000 ጀምሮ አለ ይደውሉልን 0978422547


በተጨማሪ @Enkuyeeeyene

@Mytafache

መልእክት መላክ ይቻላል
8.2K views05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ