Get Mystery Box with random crypto!

#ፈፊሩ በደሉ ሲገዝፍ፣ ጉልበታችን ሲከዳንና ህመሙ ሲጠናብን፤ ወደ ኃያሉ፣ አሸናፊውና ተበቃዩ ጌታ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

#ፈፊሩ
በደሉ ሲገዝፍ፣ ጉልበታችን ሲከዳንና ህመሙ ሲጠናብን፤
ወደ ኃያሉ፣ አሸናፊውና ተበቃዩ ጌታ 'አቤት' ማለትና
ወደርሱ መሸሽ ብቸኛው መፍትሔ ነው።
ዩኑስን(ዐ.ሰ) ከአሳ ነባሪ ሆድ፤ ሙሳን (ዐ.ሰ) ከፊርአውን፤
ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) ከኑምሩድ እሳት ነፃ ያወጣውን
ሁደይቢያን በፈትሑ መካ የቀየረ ጌታችንን እንደ ነቢዩላህ
አዩብ (ዐ.ሰ) «ጌታችን ሆይ! ችግርናና መከራ አገኘን፤ አንተ
ደግሞ የአዛኞቹ ሁሉ አዛኝ ነህ።» እንለው ዘንድ የተገባ
ነው።
ፈፊሩ፤ የመሸሽ ዘመቻ ነው። የምንሸሸው ወደ አላህ ነው!
የምንፈጥነው ወደ መስጂድ ነው! የምንበረው ወደ ድል
ነው።
የዘመቻው ዝርዝር አተገባበርና አፈፃፀም በቀጣይ የሚገለፅ
ሲሆን፤ ዘመቻው:‐
• ፆም
• የጀምዓ ኢፍጣር
• ሰደቃ
• ዚያራ
• ዱአ
. አዝካርና ሌሎችንም ያካተተ ይሆናል።
ﻓَﻔِﺮُّﻭﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ۖ
«ወደ አላህም ሽሹ፤»
(ቁርኣን 51:50)
#የአንዋርመስጂድጭፍጨፋ #የመስጂድፈረሳ
#ሙስሊምጠልነት #ሰጋጁንገደሉት #ሸገርሲቲ
#AnwarMesjidMassacre #Islamophobia
#EthioMuslims #ፈፊሩ