Get Mystery Box with random crypto!

Yalelet Wondye Gebeyehu

የቴሌግራም ቻናል አርማ yaleletwondyegebeyehu — Yalelet Wondye Gebeyehu Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yaleletwondyegebeyehu — Yalelet Wondye Gebeyehu
የሰርጥ አድራሻ: @yaleletwondyegebeyehu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.00K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-09-05 20:16:39
3.3K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 20:14:21 ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከጥምር ጦሩ ጎን በመቆም የሃገርን ሉዓላዊነትና ክብር መጠበቅ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው!

ሃገራችን ኢትዮጵያን ክብርና ታሪኳን ለማሳነስና ለማፍረስ በአሸባሪው ህውሃትና ግብረ አበሮቹ በአራቱም የሃገራችን ማዕዘን ጦርነት ከተከፈተብን ቆይቷል።

እንደ ሃገር በአንድነት ፀንተን፤ እንደ ሕዝብ በክብር በርትተን ለመኖር ብቸኛው መፍትሔ የጠላትን እቅድና ፍላጎት በስሜት ሳይሆን በስክነት አስቦ በአንድነት በመመከት ነው።

በጠላት አሉቧልታ መደናገርና መከፋፈል ሳያስፈልግ በአንድነት፣ በመተጋገዝ ለጋራ ሃገር በጋራ መቆም ወቅቱ የሚጠይቀው ታሪካዊና ሞራላዊ ኃላፊነት ነው።

በመሆኑም የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት እና የትኩረት ማዕከል የሆነች ኢትዮጵያን ትናንት በነበራት ከፍታ ልክ አይነኬ ሁና የገጠማትን አሁናዊ ፈተና በድል እንድትሻገር፣ በአሸባሪው ህውሓት የተቃጣብንን ወረራ በብቃት እየመከተ የሚገኘውን፣ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን ጋሻና ጦር ሆኖ መከታ የኾነንን የሃገር መከላከያ ሰራዊትና ጥምር ጦሩን መደገፍ ኃላፊነታችንን ከመወጣታችንም በላይ የግድ የሚለን ወቅት ላይ ነን።

ስለሆነም ላቡን እና ደሙን እያፈሰሰ፤ ለሀገር እና ለወገኑ በበጋ ፀሀይ፤ በክረምት ዝናብ እየተፈራረቀበት አቀበት ቁልቁለቱ ሳይበግረዉ ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቀ ዉድ ሕይወቱን አስይዞ የሀገር ሉአላዊነትን እየጠበቀ ለሚገኘው የኢትዮጵያዊ ጠባቂ ሰራዊታችን ድጋፍ ማድረግ እና ትክክለኛ ደጀን መሆን የዜግነት ትንሹ ግዴታ መሆኑን በዉል በመረዳት ከሰራዊታችን ጎን በፅናት መቆም ይገባናል።

ከሰራዊታችን ጎን ደጀን ሆኖ መቆም ያልቻለ ኢትዮጵያዊ አገራችንን ሊያፈርሱ ዘወትር ነጋ ጠባ ከሚታትሩ አገር አፍራሽ የጠላት ኃይሎች ጋር ተባባሪ ከመሆን ተለይቶ አይታይም።

"ለሃገር ክብር በትግል እናብር"
3.3K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 22:40:14 የገልቱዎች የተንኮል ወጥመድ!!!!
******
አሸባሪው ሁሉም አይነት ተንኮል እጁ ላይ በረዶ ሆኖበታል። እስከ አሁን በጣም በርካታ የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳዎችን ቢጠቀምም ሁሉም አንድ እርምጃም ሊያራምዱት አልቻሉም። አሁን ደግሞ አዲስ የአልሞት ባይ ተጋዳይ የሞኝ ተንኮል ሸርቧል።

''መከላከያ የህዝብ አለኝታ ስለሆነ የትግራይ ህዝብ በእልልታና በደስታ በታላቅ አክብሮት እየተቀበለ እንዲያሳልፈው'' የሚል የጅላጅል ፕሮፓጋንዳ እያሰራጨ ነው። ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን የተሰጠውን ወታደራዊ የኦፕሬሽን ተልዕኮ የት፣ መቼና እንዴት እንደሚያከናውን ጠንቅቆ የሚያውቅና በከፍተኛ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ሥራውን የሚሰራ እንጂ ጁንታው በጣረ ሞት ውስጥ ሆኖ በነደፈው የሴራ ወጥመድ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ጀግናው መከላከያችን ሁሌም ባለ ድል ነው!
2.1K views19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:50:46 የህወሓት ቀጣይ እስትራቴጅና የመጨረሻ ግብ ብሎ ካስቀመጣቸው ሚስጢራዊ ሰነዶች ውስጥ የተወሰኑትን እንድታውቁት እናጋራችሁ።

#አንደኛ ህወሓት ሰላም እንደማይፈልግና አማራን እንዴት እንደጥላት ፈርጆ ሲያበቃ አሁን ወዳጅ መስሎ ለመበተን እየሰራ እንዳለ፣

#ሁለተኛ በተጨባጭ መሳርያ የሚያቀርቡለት ሃይሎች(ሀገሮች) መኖራቸውን ማመኑን፣

#ሶስተኛ በሀገራችን የተለያዩ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ አማፂያንና ሽብርተኞችን እንዴት እንደሚደግፍ ያመነበትን፣

#አራተኛ የእርዳታ ድርጅቶችን እንዴት አግባብቶ የእርዳታ ቁሳቁስ እንዳይነፍጉት እያደረገ እንዳለና እንደሚያደርግ አስቀምጧል።

#አምስተኛ የትግራይ ወጣቶችን የማይቀርና የመጨረሻ ድል ነው እያለ እያምታታና እያታለለ ለጦርነት አሰልፎ እንደሚማግድ፣

የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ምንም ትርጉም ስለሌለው መንግስት ሰላም አይፈልጉም ብሎ እያሳጣን ብለው ከዚህ ወቀሳ ለማምለጥ ሲሆን ዋናው ግባቸው በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አኩራፊዎችን በማበራከት ኢትዮጵያን ማፍረስ እንጂ በድርድር ሰላም ይመጣል ብለው እንደማያምኑ ከተገለፁት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
2.1K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:33:06 ቀጣዩ የህወሃት ፊልም ርዕስ “የኬሚካል መሳሪያ ጥቃት”!
***
ድርሰት- የህወሃት ማፊያ ቡድን
ተዋንያን- የህወሃት ማፊያ ቡድንና ንጹሃን ዜጎች
ዘውግ- የፈጠራ ተረት ተረት
ለእይታ የሚቀርበው- ለምዕራባውያን

ህወሃት የምእራባውያኑን ስስ ቦታዎች ጠንቅቆ ያውቃቸዋል።
ያኔ ከበርሃ አንከብክበው አዲስ አበባ እንዳደረሱት ዛሬም ያንኑ ስስ ቦታቸውን ለመነካካት እያሴረ ነው።
ደርሰንበታል!
ምእራባውያን ከአለም ውስብስብ ታሪክና ከፖለቲካ ቁማራቸው የተነሳ እነዚህ ቃላት ያስበረግጓቸዋል።
ጄኖሳይድ፣ የፆታ ጥቃት፤ ርሃብ፣ ኬሚካል መሳሪያ፣ ኒውክሌር
ከነዚህ ውስጥ እርግጠኛ ነኝ ሶስቱን ቃላት በተለይ ከህወሃት መሪዎችና ከደጋፊ መንጋዎቻቸው በየሰበቡ ሲጠሩ ሰምታችኋል።
ረሃብ፤ አስገድዶ መድፈርና በተለይ ጄኖሳይድ የሚሉትን ቃላት!
አሁን ደግሞ ኬሚካል መሳሪያ እንደ አዲስ ሙዚቃ ካፋቸው እየተደጋገመች ልትመጣ መሆኑን ደርሰንበታል! ይህ ሁሉ ያለምክንያት አይደለም። የራሳቸውን ዜጋ መርዘው ሲያበቁ መንግስት የኬሚካል ጥቃት ፈፀመብን ብለው ያጡትን የአለምን ትኩረት ለመሳብ ማቀዳቸውን ደርሰንበታል። ያለ አንዳች ሃፍረት ይህ 300 ሺህ በላይ የትግራይን ህዝብ አስጨርሶ እንደ ድል አድራጊ ፈርጥጦ ከተመለሰ የማፊያ ቡድን የሚጠበቅ ስራ ነው።
“ለምን ልጆቻችንን ወደ ጦርነት ትማግዳላችሁ” የሚለው የትግራይ ህዝብ ጫና ሲበዛባቸው፤ ተስፋ ያደረጉባቸው ምእራባውያንም ችላ ሲሏቸው የመጨረሻ የመጫወቻ ካርዳቸውን እየሳቡ ይመስላል።
ህዝባቸውን ላሰቡት እኩይ አላማ ለማሰለፍ አንድ ጠላት መፍጠር አለባቸው፤ ይህ ምናባዊ ጠላት ደግሞ ያለ የሌለ ጥፋት ሰርቷል በሚል ሃጢያቱን ማብዛት አለባቸው።
የሃውዜኑን ታሪክ ማስታወስ እዚህ ላይ ተገቢ ነው። በወቅቱ እየሳሳ የነበረውን የህዝብ ድጋፋቸውን ለማሰባሰብ “ሴራ በቋት” የሆኑት የህወሃት መሪዎች በሃውዜን ሆን ብለው ንጹሃን በአየር ጥቃት እንዲመቱ ማድረጋቸውን ታሪክን ጠጋ ብሎ ያጠና ሰው በግልጽ መመልከት ይችላል።
በተመሳሳይ ይህንኑ ጊዜው ያለፈበትን ዘዴ ዘንድሮም ደግመውታል።
በሴራና በተንኮል የተካኑት የህወሃት መሪዎችና ተከታይ መንጋቸው ሰሜን እዝን ባጠቁ እለት የዛኑ ቀን ነው “ትግራይ ጄኖሳይድ” የሚለው የቁራ ድምጻቸው መሰማት የጀመረው።
ጥቃቱን ራሳቸው አቅደው፤ እስካፍንጫቸው ታጥቀውና ተዘጋጅተው ፈጽመው ሲያበቁ “ተጠቃን፤ አለቅን” ማለት የጀመሩት የዛኑ ቀን መሆኑን የትዊተር ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና መዝግቦ ይዞታል።
ጄኖሳይድ የሚለው ተረት በህወሃት ተደርሶ፤ በህወሃት ዳይሬክት፤ ተደርጎ ለአለም የቀረበ ምርጥ የህወሃት የፊልም ስራ ነው።
በገፍ ባዘጋጁት የመከላከያ ወታደር አልባሳት ጎረምሶቻቸውን እያለበሱ በገዛ ህዝባቸው ላይ ለፈጸሙት ጥፋት ዜጎቻችን ተደፈሩ ሲሉም ሰምተናል።
በገፍ የእርዳታ እህል እየገባ ጭራሽ ለዜጎች የእለት ጉርስ እንዲሆን ከሚገባ የእርዳታ እህልና ነዳጅ በጠራራ ጸሃይ እየዘረፉ በዛው አፋቸው ርሃብ የሚለውን ቃል የአፍ ሟሟሻ አድርገውት ቆይተዋል። ለነገሩ ዝርፊያ ብርቃቸው አይደል፤ የተካኑበት ነው፤ 27 አመት ኢትዮጵያን በዝብዘው ራቁት ያስቀሯት በዚሁ የዝርፊያ ስራቸው አይደለምን?
አሁን ደግሞ እስካሁን ያሰቡትን ያህል ትኩረትና ተፅእኖ ማግኘት ያለመቻላቸው ሲያንገበግባቸው ወደ ሌላኛው የጥፋት ዘዴ ተሸጋግረዋል።
የምዕራባውያን ቀላቢዎቻቸውን ትኩረት ይስብልናል ያሉትን በኬሚካል መሳሪያ ጥቃት ደረሰብን የሚል ከንቱ እሪታቸውን እንደለመዱት ለማሰማት ሴራ እየሸረቡ ነው።
በጦርነት የሞቱባቸውን ወታደሮች የሲቪል ልብስ አልብሰው ወንዝ ውስጥ እየጣሉ መንግስት ንጹሃንን አጠቃ ብለው ያሰሩት የሲኤንኤን ዶክመንተሪ ትዝ አላችሁ?
የሞቱ ወታደሮቻቸውን በጅምላ መቃብር ቀብረው ለምእራባውያን የሃሰት መወንጀያ ምክንያት ሲያደርጉትስ አልነበረም?
ምእራባውያን ጋላቢዎቻቸው ደግሞ ይህ የኬሚካል መሳሪያ ጉዳይ ኢራቅንና ሶሪያን እንዲሁም ሌሎች ሃገራትን ያፈረሱበት ምክንያት ነውና ህወሃትም ፍርፋሪ የሚወረውሩለትን ምእራባውያንን ትኩረት ለመሳብ፤ “ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦልም ቢሆን እንወርዳለን” ያለውን ቃሉን ጠብቆ፤ የመጨረሻ ካርዱ የሆነችውን “በኬሚካል መሳሪያ ተጠቃሁ” ለቅሶን ሊጠቀምባት መሆኑን ደርሰንበታል።
ቀጣይ የህወሃት ፊልም ርዕስ ናት!
ነቅተንባችኋል!
2.6K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:42:31
3.7K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:42:26 በህጻናት ደም የሚራጨው የወንበዴው ቡድን
******
#ሼር
ህዝባዊ ማዕበል አሰለፍኩ ሲል በተደጋጋሚ የሚደሰኩረው የህውሃት ሃይል የትኛው ህዝባዊ ሃይል ተሰለፈ ብለን አሰላለፉን ስናይ ህጻናት እና ወጣቶችን ከፊት አድርጎ ሰልፉ ሲጀምር እናያለን።

ህጻናት እና ወጣቶች ለምን ከፊት ብለን የጠየቅን እንደሆን ደግሞ ይህ አሸባሪ ቡድን ከፊት ወጣቱን ለነጠቃ እና ለዝርፊያ እንዲያመቸው በየደረሰበት ያገኘውን እየዘረፈ እና እያጠፋ ለመሄድ በማሰብ አንደኛው ሲሆን ይህም ውንብድና ፣ንጥቂያ እና ዝርፊያ የዘወትር ተግባሩ በመሆኑ ቅድሚያ ሰጦት ይንቀሳቀሳል ፤ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በሚያሳዝን መልኩ ከወጣቶቹ ጋር ህጻናትን ጨምሮ ከፊት የማሰለፉ ሚስጥር እናት ሰው እንዳያይባት ደብቃ ያሳደገችውን አንድ ፍሬ ልጇን የጥይት ማብረጃ ለማድረግ እና ለማስጨረስ ለሌላው ሰራዊቱ መንገድ ጠራጊ እንዲሆኑለት በማሰብ ነው።

ታድያ በግዳጅ ወጣቱን ካልተዋጋህ እንደሌላው ትግራዋይ እኩል የጥቅም ተካፋይ አትሆንም እያለ እያስፈራራ ህዝቡን አንቆ ህዝባዊ ማዕበል ይዞ የተነሳው ይህ ሃይል ብዙ መለወጥ መስራት የሚችሉ ገና መኖርን ያልጠገቡ የህይወት ትርጉም እንኳን በቅጡ ያልገባቸውን ሃገርን መለወጥ የሚችሉ ባለብዙ ተስፋወችን ህጻናትን እና ወጣቶችን እያስቀጠፈ አላማ የሌለው ሞትን እንዲሞቱ እያደረጋቸው ይገኛል ።

የህፃናት መብት ተሟጋች ነን የሚሉት ለዮክሬናዊያን ህፃናት ጥብቅና የቆሙት ምዕራባዊያን ምነው በግዳጅ ውጊያ ለገቡት የትግራይ ህፃናቶች ዝምታን መረጡ።

Amnesty International USA
The New York Times
Al Jazeera English
L'Ambassade des Etats Unis, Kinshasa
U.S. Embassy Addis Ababa
The Mehdi Hasan Show
BBC News Africa

የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
https://t.me/yaleletwondyegebeyehu
3.7K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 22:17:55 ዐቢይ ድንገት ተነስቶ ወደ አልጀሪያ የሄደው ለድርድር እንደሆነ አንዳንድ የደኅንነት ምንጮች እየጠቆሙ ነው፤ ቀደም ሲል የድርድር ኮሚቴ መቋቋሙን ጠሚውም እንደሌለበት ቢገልፅም ራሱ ሂዷል። ግን ለሕዝብ ግልፅ መደረግ የለበትም ወይ?
3.4K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:55:37 ጦርነቱን ለዘረፋና ለንግድ የሚጠቀሙበትን አካላት ህዝቡ ራሱ እየመነጠረ በአደባባይ እርምጃ መውሰድ አለበት!

☞ በዛሬው እለት እንኳ ከወልዲያ ደሴ ለአንድ ሰው 2000 ብርና ከዚህም በላይ እያስከፈሉ ኪሳቸውን የሚያደልቡ ጅቦችን!

☞ ተሽከርካሪዎችን ለግዳጅ ተፈልጋችኃል ብለው በድርድር እስከ 10ሺህ ብር ተቀብለው የሚለቁ ትራፊኮችና የመንገድ ትራንስፖርት ሰራተኞችን

☞ ህብረተሰቡ የኑሮ ውድነትና ግሽበቱን መቋቋም ተስኖት እያጣጣረ ባለበት ሁኔታ ፥ ጦርነቱ መጀመሩ ከተነገረበት እለት ጀምሮ በአንድ ኩንታል እህል ላይ 500 ብርና በላይ እንዲሁም በሌሎች የፍጆታ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ ጭማሬ በማድረግ ላይ ያሉ ስግብግቦችን

☞ ነዳጅና ጥሬ ብርን ጨምሮ ፥ ለሽብር ቡድኑ በተለያዩ መንገዶች ተደራሽ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ የጠላት አጋር ነጋዴዎችን

☞ የጦርነቱን ግርግር እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የግለሰቦችንም ሆነ የመንግሥት ድርጅቶችን በቡድንም ሆነ በግል ለመዝረፍ የሚንቀሳቀሱ ሌቦችን

☞ በምድርም ሆነ በአየር የሽብር ቡድኑን አካላት ኬላዎችን አሳልፈውና ሀሰተኛ ሰነዶችን አዘጋጅተው የማዘዋወር ስራ የሚሠሩ የመንግስትም ሆነ ከማህበረሰቡ የወጡ አካላትን

☞ ለአንዳንድ ከድተው ወይም ጠፍተው የሚመጡ የሰራዊቱ አካላትን መሳሪያ በመግዛትና የሲቪል አልባሳትን በመስጠት ተባባከሪ የሚሆኑ ማናቸውም አካላትን …ወዘተ

የመሳሰሉትን ከጠላት ባልተናነሰ ሁኔታ ህዝቡን እያሰቃዩና ለጠላት እየተባበሩ ያሉ አካላትን ከመንግሥት የፀጥታ አካላት ጋር ጥብቅ ቁርኝት በመፍጠር በአደባባይ መቀጣጫ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ሊሆን ይገባል!
4.2K views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:03:41 ያሳዝናል!
መንግስት ቆቦ ከተማን አስረክቦ መውጣቱን አምኗል!!

መንግስት ቆቦን ለመልቀቅ ያስቻለውን ምክንያት ሲገልጽ "የህዝብን ከፍተኛ እልቂት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል ቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚያስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ... " የሚል ነው::

ይኸው እንግዲህ "ስልታዊ ማፈግፈግ" ስሟን ቀይራ መጥታልች!!
2.6K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ