Get Mystery Box with random crypto!

በህጻናት ደም የሚራጨው የወንበዴው ቡድን ****** #ሼር ህዝባዊ ማዕበል አሰለፍኩ ሲል በተደጋ | Yalelet Wondye Gebeyehu

በህጻናት ደም የሚራጨው የወንበዴው ቡድን
******
#ሼር
ህዝባዊ ማዕበል አሰለፍኩ ሲል በተደጋጋሚ የሚደሰኩረው የህውሃት ሃይል የትኛው ህዝባዊ ሃይል ተሰለፈ ብለን አሰላለፉን ስናይ ህጻናት እና ወጣቶችን ከፊት አድርጎ ሰልፉ ሲጀምር እናያለን።

ህጻናት እና ወጣቶች ለምን ከፊት ብለን የጠየቅን እንደሆን ደግሞ ይህ አሸባሪ ቡድን ከፊት ወጣቱን ለነጠቃ እና ለዝርፊያ እንዲያመቸው በየደረሰበት ያገኘውን እየዘረፈ እና እያጠፋ ለመሄድ በማሰብ አንደኛው ሲሆን ይህም ውንብድና ፣ንጥቂያ እና ዝርፊያ የዘወትር ተግባሩ በመሆኑ ቅድሚያ ሰጦት ይንቀሳቀሳል ፤ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በሚያሳዝን መልኩ ከወጣቶቹ ጋር ህጻናትን ጨምሮ ከፊት የማሰለፉ ሚስጥር እናት ሰው እንዳያይባት ደብቃ ያሳደገችውን አንድ ፍሬ ልጇን የጥይት ማብረጃ ለማድረግ እና ለማስጨረስ ለሌላው ሰራዊቱ መንገድ ጠራጊ እንዲሆኑለት በማሰብ ነው።

ታድያ በግዳጅ ወጣቱን ካልተዋጋህ እንደሌላው ትግራዋይ እኩል የጥቅም ተካፋይ አትሆንም እያለ እያስፈራራ ህዝቡን አንቆ ህዝባዊ ማዕበል ይዞ የተነሳው ይህ ሃይል ብዙ መለወጥ መስራት የሚችሉ ገና መኖርን ያልጠገቡ የህይወት ትርጉም እንኳን በቅጡ ያልገባቸውን ሃገርን መለወጥ የሚችሉ ባለብዙ ተስፋወችን ህጻናትን እና ወጣቶችን እያስቀጠፈ አላማ የሌለው ሞትን እንዲሞቱ እያደረጋቸው ይገኛል ።

የህፃናት መብት ተሟጋች ነን የሚሉት ለዮክሬናዊያን ህፃናት ጥብቅና የቆሙት ምዕራባዊያን ምነው በግዳጅ ውጊያ ለገቡት የትግራይ ህፃናቶች ዝምታን መረጡ።

Amnesty International USA
The New York Times
Al Jazeera English
L'Ambassade des Etats Unis, Kinshasa
U.S. Embassy Addis Ababa
The Mehdi Hasan Show
BBC News Africa

የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
https://t.me/yaleletwondyegebeyehu