Get Mystery Box with random crypto!

ጦርነቱን ለዘረፋና ለንግድ የሚጠቀሙበትን አካላት ህዝቡ ራሱ እየመነጠረ በአደባባይ እርምጃ መውሰድ | Yalelet Wondye Gebeyehu

ጦርነቱን ለዘረፋና ለንግድ የሚጠቀሙበትን አካላት ህዝቡ ራሱ እየመነጠረ በአደባባይ እርምጃ መውሰድ አለበት!

☞ በዛሬው እለት እንኳ ከወልዲያ ደሴ ለአንድ ሰው 2000 ብርና ከዚህም በላይ እያስከፈሉ ኪሳቸውን የሚያደልቡ ጅቦችን!

☞ ተሽከርካሪዎችን ለግዳጅ ተፈልጋችኃል ብለው በድርድር እስከ 10ሺህ ብር ተቀብለው የሚለቁ ትራፊኮችና የመንገድ ትራንስፖርት ሰራተኞችን

☞ ህብረተሰቡ የኑሮ ውድነትና ግሽበቱን መቋቋም ተስኖት እያጣጣረ ባለበት ሁኔታ ፥ ጦርነቱ መጀመሩ ከተነገረበት እለት ጀምሮ በአንድ ኩንታል እህል ላይ 500 ብርና በላይ እንዲሁም በሌሎች የፍጆታ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ ጭማሬ በማድረግ ላይ ያሉ ስግብግቦችን

☞ ነዳጅና ጥሬ ብርን ጨምሮ ፥ ለሽብር ቡድኑ በተለያዩ መንገዶች ተደራሽ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ የጠላት አጋር ነጋዴዎችን

☞ የጦርነቱን ግርግር እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የግለሰቦችንም ሆነ የመንግሥት ድርጅቶችን በቡድንም ሆነ በግል ለመዝረፍ የሚንቀሳቀሱ ሌቦችን

☞ በምድርም ሆነ በአየር የሽብር ቡድኑን አካላት ኬላዎችን አሳልፈውና ሀሰተኛ ሰነዶችን አዘጋጅተው የማዘዋወር ስራ የሚሠሩ የመንግስትም ሆነ ከማህበረሰቡ የወጡ አካላትን

☞ ለአንዳንድ ከድተው ወይም ጠፍተው የሚመጡ የሰራዊቱ አካላትን መሳሪያ በመግዛትና የሲቪል አልባሳትን በመስጠት ተባባከሪ የሚሆኑ ማናቸውም አካላትን …ወዘተ

የመሳሰሉትን ከጠላት ባልተናነሰ ሁኔታ ህዝቡን እያሰቃዩና ለጠላት እየተባበሩ ያሉ አካላትን ከመንግሥት የፀጥታ አካላት ጋር ጥብቅ ቁርኝት በመፍጠር በአደባባይ መቀጣጫ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ሊሆን ይገባል!