Get Mystery Box with random crypto!

የገልቱዎች የተንኮል ወጥመድ!!!! ****** አሸባሪው ሁሉም አይነት ተንኮል እጁ ላይ በረዶ ሆኖ | Yalelet Wondye Gebeyehu

የገልቱዎች የተንኮል ወጥመድ!!!!
******
አሸባሪው ሁሉም አይነት ተንኮል እጁ ላይ በረዶ ሆኖበታል። እስከ አሁን በጣም በርካታ የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳዎችን ቢጠቀምም ሁሉም አንድ እርምጃም ሊያራምዱት አልቻሉም። አሁን ደግሞ አዲስ የአልሞት ባይ ተጋዳይ የሞኝ ተንኮል ሸርቧል።

''መከላከያ የህዝብ አለኝታ ስለሆነ የትግራይ ህዝብ በእልልታና በደስታ በታላቅ አክብሮት እየተቀበለ እንዲያሳልፈው'' የሚል የጅላጅል ፕሮፓጋንዳ እያሰራጨ ነው። ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን የተሰጠውን ወታደራዊ የኦፕሬሽን ተልዕኮ የት፣ መቼና እንዴት እንደሚያከናውን ጠንቅቆ የሚያውቅና በከፍተኛ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ሥራውን የሚሰራ እንጂ ጁንታው በጣረ ሞት ውስጥ ሆኖ በነደፈው የሴራ ወጥመድ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ጀግናው መከላከያችን ሁሌም ባለ ድል ነው!