Get Mystery Box with random crypto!

ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከጥምር ጦሩ ጎን በመቆም የሃገርን ሉዓላዊነትና ክብር መጠበቅ የሁሉም | Yalelet Wondye Gebeyehu

ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከጥምር ጦሩ ጎን በመቆም የሃገርን ሉዓላዊነትና ክብር መጠበቅ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው!

ሃገራችን ኢትዮጵያን ክብርና ታሪኳን ለማሳነስና ለማፍረስ በአሸባሪው ህውሃትና ግብረ አበሮቹ በአራቱም የሃገራችን ማዕዘን ጦርነት ከተከፈተብን ቆይቷል።

እንደ ሃገር በአንድነት ፀንተን፤ እንደ ሕዝብ በክብር በርትተን ለመኖር ብቸኛው መፍትሔ የጠላትን እቅድና ፍላጎት በስሜት ሳይሆን በስክነት አስቦ በአንድነት በመመከት ነው።

በጠላት አሉቧልታ መደናገርና መከፋፈል ሳያስፈልግ በአንድነት፣ በመተጋገዝ ለጋራ ሃገር በጋራ መቆም ወቅቱ የሚጠይቀው ታሪካዊና ሞራላዊ ኃላፊነት ነው።

በመሆኑም የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት እና የትኩረት ማዕከል የሆነች ኢትዮጵያን ትናንት በነበራት ከፍታ ልክ አይነኬ ሁና የገጠማትን አሁናዊ ፈተና በድል እንድትሻገር፣ በአሸባሪው ህውሓት የተቃጣብንን ወረራ በብቃት እየመከተ የሚገኘውን፣ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን ጋሻና ጦር ሆኖ መከታ የኾነንን የሃገር መከላከያ ሰራዊትና ጥምር ጦሩን መደገፍ ኃላፊነታችንን ከመወጣታችንም በላይ የግድ የሚለን ወቅት ላይ ነን።

ስለሆነም ላቡን እና ደሙን እያፈሰሰ፤ ለሀገር እና ለወገኑ በበጋ ፀሀይ፤ በክረምት ዝናብ እየተፈራረቀበት አቀበት ቁልቁለቱ ሳይበግረዉ ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቀ ዉድ ሕይወቱን አስይዞ የሀገር ሉአላዊነትን እየጠበቀ ለሚገኘው የኢትዮጵያዊ ጠባቂ ሰራዊታችን ድጋፍ ማድረግ እና ትክክለኛ ደጀን መሆን የዜግነት ትንሹ ግዴታ መሆኑን በዉል በመረዳት ከሰራዊታችን ጎን በፅናት መቆም ይገባናል።

ከሰራዊታችን ጎን ደጀን ሆኖ መቆም ያልቻለ ኢትዮጵያዊ አገራችንን ሊያፈርሱ ዘወትር ነጋ ጠባ ከሚታትሩ አገር አፍራሽ የጠላት ኃይሎች ጋር ተባባሪ ከመሆን ተለይቶ አይታይም።

"ለሃገር ክብር በትግል እናብር"