Get Mystery Box with random crypto!

Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ

የሰርጥ አድራሻ: @tjmma
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.14K
የሰርጥ መግለጫ

I didn't bit the land that feeds you!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-07-06 18:19:25 ከምኔው ከምኔው ነበር ያለው ዘፋኙ።
እኛ እንደ ጀግና አክብረን የተቀበልንህ ታግለህ ታታግለናለህ የጦር አመራር ልምድህን ታካፍለናለህ በሚል እንጅ ከመንግሥት ተልዕኮ ተቀብለህ ልዩ መሳሪያ ይዘህ በመምጣት ጥቃት ታስከፍትብናለህ ወንድሞቻችንንም ታስገድላለህ ታስጨርሰናለህ ብለን አልነበረም፤ እንዳስገደልከን የማንገድልህ ስም ስላለህ ነው ከዚህ በኋላ ከእኛ ፍቃድ ውጭ እንድትንቀሳቀስ አንፈቅድልህም ብለው ከሰሞኑ ጃውሳን ተቀላቀለ ተብሎ ሰበር ዜና የተሰራለትን ብ/ጀኔራል ከድንገተኛ የመከላከያ ኦፕሬሽን የተረፉ የጃውሳ አባላት እንዳሰሩት ተሰምቷል። ይገርማል።
እዚጋ ደግሞ ሌላ መጠፋፋት። ተጨማሪ ጥፋት።

አሁንም የተረፋችሁትም ሆነ ሌሎቻችሁ የሚጠቅማችሁ የሕይወት የመውጫ መንገድ በስሜት ፈረስ እየጋለባችሁ በእውር ድንብር የገባችሁበት የትጥቅ ትግል ሳይሆን የመንግሥት የሰላም ጥሪን መቀበል ወይም የሰላም ካውንስሉን የሰላም ጥሪን ተቀብሎ በድርድር በሰላም ወደወጣችሁበት ማህበረሰብ መቀላቀል ነው። ሌላው መንገድ ፈፅሞ ሊጠቅማችሁ የማይችል ሱሳይድ ነው። ጀሮ ያለው ይስማ!

ሰላም ለሐገራችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!
1.1K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-06 13:31:50 ዓለም ላይ እስካሁን በሕዕቡም ሆነ በአደባባይ ከተደረጉ የትጥቅ ትግሎች የጃውሳን ለየት የሚያደርገው የአባላቱ የትግል ስም ሻለቃ እንትና፣ ሜጄር ጀኔራል እንትና፣ ሌተናል ጀኔራል እንትና እንዲሁም ጀኔራል እንትና በሚል የከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ የሚጠራ መሆኑ፣ እንዲሁም ሊቆጣጠሩትና ሊያጠፉት በሚፈልጉት በአካባቢያቸው በሚገኘው ደንቆሮ ቦቅቧቃ ወላዋይ አቋም የለሽ ዳፍንታም አመራር የሚታገዝ የጥፋት ሃይል መሆኑ ነው።
1.1K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-06 13:03:59
የከፍታው ንጉስ!
1.1K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-05 18:01:26 በየሰፈሩ እየተሹለከለከ የራሱ ሰፈር ሰው ላይ መንገድ የሚዘጋው እገታ ግድያ የሚፈፅመውና በዝርፊያ ላይ የተሰማራው ጃውሳና የሚዲያ ክንፉ አንዱ ሌላኛውን የሚጠራው በከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ነው። ከጃውሳ መካከል ያለ ማዕረግ የሚጠራ የለም። ያለ ማዕረግ የሚጠራ ጃውሳ አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን የማዕረጉ መነሻ ሻለቃ መሆኑ ዓለም ላይ ካሉ አማፂያን ወታደራዊ ተቋማት ለየት ያደርገዋልና በአስደናቂነቱ እንዲመዘገብ ያደርገዋል።

ነገር ግን

ጃውሳ ነኝ ብሎ የሚሰማራ ማንም ዘራፊ ወንበዴ ወይም የተጠያቂነት ስጋት ያለበት ወንጀለኛ ሁሉ በቀጥታ የሻለቃነት ማዕረግ ወዲያው በተቀላቀለበት ቅፅበት በሚያገኝበትና ውሎ ሲያድር ደግሞ ብርጋዲየር ጀኔራል፣ ሜጀር ጀኔራል፣ሌተናል ጀኔራል፣ ጀኔራል እየተባለ በሚጠራበት ሁኔታ እንዴት እስካሁን ፊልድ ማርሻ በሚለው ማዕረግ የሚጠራ አንድስ የጃውሳ አባል ሳይኖር ይቀራል? Just Asking!
1.3K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-03 15:44:54 ለአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት 33 ቢሊየን ብር ወጭ ወጣበትን መባሉን ተከትሎ ሐብት ያላግባብ የባከነ አስመስለው የሐዘን ድንኳን በማስጣል ለማስለቀስ ከሚሞክሩት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ "የኮሪደር ልማቱ ሲጀመር አናስጀምርም፣ እየተሰራ አናሰራም ሲሉ የነበሩ፣ ስራው ሲያልቅ ደግሞ አቃቂር እያወጡ ለማጣጣል ጊዜያቸውን ሲያባክኑ የሚታዩ፥ የመልካም ነገር ሁሉ ተቃዋሚና የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞን ማየት የማይፈልጉ የሚመስሉ እንዲሁም የስራ ዝርዝሩን በማያውቁት ሁኔታ ወይም የኦዲት ውጤት በእጃቸው ሳይኖር ፍርድ ለመስጠት ብቻ የፈጠኑ ደፋሮች ናቸው የሚለውን ጉዳይ ወደጎን ላቆየውና ስለ 33 ቢሊየን ብር ግዙፍ ገንዘብ መሆን ለማሳየት ከ10 ዓመት አልፎም ከ20 ዓመት በፊት የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በጀት በማምጣት ለማነፃፀርና በእነዛ ፕሮጀክቶች በጀትም 33 ቢሊየን ብሩ አስልተው ብዙ ፕሮጀክቶች እንደሚወጣው አቋም መያዛቸውን ስመለከት ትርፉ መድረቅ ነው በሚል ነገሩን ተውኩት።

ሰላም ለሐገራችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!
1.6K views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-02 19:09:23
አዲስ አበባ እየተሰራ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ሽንቱን እንዲህን ለመሽናት ሞራል ያገኘውን እንዴት ነው?
1.8K views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-02 11:50:25 የቀጣዩ ቀዳሚ የሰበር ዜና ሸፋች ለመሆን ዶጭሌን ገ.ም.ጭ.ሌ ሊቀድመው ይችላል። ጫካ ካሉ 7ት አባላት ጋር ተቀላቅሎ ለመታገል አቋም የሚያሲዝ ድፍረት ጠፋ እንጅ ባሉበት ሆነው በሏቸው ከሚሉት ከእነ በላቸው መካከልም ቀዳሚ ሊኖር ይችላል።

ሕወሓት ኢህዴን/ብአዴንን የአካባቢ ሚሊሻ እንዲያዘጋጅ ወደመጨረሻ አካባቢ ፈቃድ ስትሰጥ የተቀላቀለና ጦርነትን መምራት ቀርቶ ውጊያ ያላየ የኮታ ጀኔራል ሁሉ ያ ወቅት የሚደገም መስሎት ለዛውም ከዘራ ተደግፎ ጫካ መግባቴ ይታወቅልኝ ማለቱ አስቂኝ ነው። ዛሬ ትናንት አይደለም!

በነገራችን ላይ
በአማራ ክልል በመንግሥትና በፓርቲ እንዲሁም በልማት ድርጅቶች ውስጥ ከሚገኙት የእነ ገዱ...የእነ ላ.. የእነ አደናግራቸው... የእነ አባ... የእነ X..ቡድን አባላት የሆኑ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መቃብር ጠባቂዎችን ሁኔታውን አይተን ስማቸውን በዝርዝር ልናወጣው እንችላለን። በያዙት የመንግሥት ኋላፊነት ሕዝቡ የሚገባውን አገልግሎት እንዳያገኝ በሕዝብና በመንግሥት መካከል ቅራኔ እንዲፈጠር፣ የመንግሥት የትኩረት ማዕከል ልማት እንዳይሆን የተጀመሩና አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች ዕቅድን የማደናቀፍ፣በመንግስት ደጋፊዎች ላይ ተፅዕኖ እያሳደሩ እውነቱ እንዲዛባና አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዲከፈል እያስፈራሩ ለመቀጠል የሚገፉበት ከሆነ አንድ ባንድ ሁሉንም በየደረጃው እንደ ብቅል እያወጣን ለማስጣት እንገደዳለን።

የውዳቂዎቹ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መቃብር ጠባቂ ተላላኪዎች መንፈስ ሌላ ተላላኪ ፈጥሮ የክልሉን ማህበረሰብ እረፍት ይነሳ ዘንድ የመደመር አቀንቃኞችን እንዳሻቸው ለማጥቃት ለማሸማቀቅ
ሞራል ኖሯቸው እንዲፈነጩባቸው አንፈቅድም!!!

ይኼው ነው!!

ሰላም ለሐገራችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!!
2.0K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-02 06:52:54 የሰበር ሰበር ዜና
በጣርማ በር አካባቢ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሌተናል ጀኔራል ፋኖ አርበኛ አውጋቸው ግሸር አቤ አካባቢ የሚገኙ ከ7 በላይ የሚሆኑ የፋኖ አባላትን በይፋ መቀላቀሉ ተረጋገጠ።

ሌተናሉ ፋኖው አርበኛው አውጋቸው የግሸር አቤ ፋኖዎችን መቀላቀሉን ተከትሎ ግን የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ። የአውጋቸውን የጣርማ በር የጦር አመራርነታቸውንና የቀደመ ታሪካቸውን በቅርበት ከእኛ በላይ የሚያውቅ የለም የሚሉ ሰዎች" አውጋቸው ትናንት በኮታ ዛሬ በቡታንታና በቡታ ጩኸት ስሙ ያለ ስራ በፌስቡክ የገነነ በተግባር የተነነ ሴራና ሸራን ለይቶ የማያውቅ በጠላት ወጥመድ እየገባ የሚመራውን ሰራዊት በማስጨረስ የሚስተካከለው የጦር መኮነን እንደሌለ በመጥቀስ በጣርማበሮቹ ላይ የደረሰው ዕጣፈንታ በግሸር አቤ እንዳይደገም እያሳሰቡ ነው።በአንፃሩ የሌተናል ፋኖ አርበኛ አውጋቸው ማዕረግ ሰጭዎች የሆኑት የቀድሞ አዛዦቹ ጭፍሮች ደግሞ አውጋቸው፥ በኮማንዶ ሥልጠና፣ በኢንዶክትሪኔሽን፣ በአደረጃጀት፣ በወታደራዊ ስምሪት፣ በሎጀስቲክስ፣...በቅኝት፣ በተልዕኮ፣ በግዳጅ አፈጻጸም፣ በወታደራዊ ግምገማ፣ በመልሶ ማደራጀት፣ በሽምቅ ውጊያ፣ በግንባር ፍልሚያ፣ በአንገት ቦታ ቁጥጥር፣ ገዥ መሬትን ቀድሞ በመያዝ፣ በምሽግ ሰበራ፣ ... ዓለም ላይ ሊስተካከለው የሚችል የጦር መኮንን አለመኖሩን በመጥቀስ አሁን በይፋ የተቀላቀላቸውን የግሸር አቤ ፋኖዎችን ተስፋ እንደሚያለመልም፣ 7ቱን ፋኖዎች በአጠረ ጊዜ አባዝቶም ይሁን አራብቶ ወደ 70ሺ እንደሚያሳድጋቸው፣ በሂደት ግሸር አቤ ሲጠባቸው ወደሌሎች አካባቢዎች እንደሚስፋፉ በልበ ሙሉነት እየተናገሩለት ነው። እየተመኙለት ብሎ መተርጎምም ይቻላል።
እኛ ግን እስኪ የሁሉንም መጨረሻ አብሮ ያሳየን በማለት ብቻ ለጊዜው ጉዳዩን ለማለፍ እንወዳለን።
1.8K views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-01 20:58:09 ሰበር ዜና

ቶማስ ጀጃው የሚኖረው ናዝሬት ነው እየተባለ ቢነገርም በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ መግባቱን የአይን እማኞች አረጋገጡ። ጠላት አይኑ እያየ ጀሮው እየሰማ አዲስ አበባ በሰላም መግባቱ ደስ ይላል። በቃ ምንም ማድረግ አይቻልም።
1.8K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-01 11:49:01
1.9K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-01 11:48:55 ከሰሞኑ የእነ ገዱ...የእነ ላ.. የእነ አደናግራቸው... የእነ አባ... የእነ X..የእነ ፍለጠው ቁረጠው...የእነ መናጆው ...ቡድን በአሜሪካ ባደረገው ስብሰባ

አንድ ሐሙስ የቀረው መንግሥት በእኛ ድክመት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ዳግም ሕይወት ዘርቶ ሐገሩን ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚቆጣጠርበትንና ሕዝባችንን ዳግም በባርነት ቀንበር የሚመራበት ዕድል ልንፈጥር አይገባም። የዶ/ር ዐብይ መንግሥት፣ መንግሥት እንዳይሆን ከወዲሁ ቀድመን መሥራት አለብን። አሁን ካለንበት ከፍ ወዳለ ደረጃ ማደግ ባንቻል እንኳን ያለንበትን ቁመና ለማስጠበቅ ሁላችንም ሳንሰለቻች አንዱ አንዱን ከመጥለፍ ወጥቶ የአሸናፊነት ተስፋ ሰንቆ በፅናት መታገል ይጠበቅበታል። የትግላችን ግብ ዳር አልደረሰም። በእኛ አለመግባባትና መከፋፈል ፋኖዎቻችንንም እየከፋፈለ ነው። ሙሉ ድጋፉን ሰጥቶን የነበረው ሕዝባችንም እየሸሸን ብቻ ሳይሆን እያዘነብንም ይገኛል።በተለይ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በግልጽ የሚታየው እንቅስቃሴ ለእኛ ጀርባ እየሰጠ ለመንግሥት ለዶ/ር ዐብይ ድጋፉን ሲሰጥ እየተመለከትን ነው።ይህ ችላ ሊባል የሚችል ጉዳይ አይደለም።ለምን ሆነ ብለን ግምገማ ካላደረግንና የማስተካከያ እርምጃ ካልወሰድን ውጤቱ ለሁላችንም አይጠቅምም። ትናንት ታግለን ለድል እናበቃሃለን ብለን ያስከተልነውና ያነገሰን ሕዝብ ይቅርና አብሮን ለትግል የተሰለፈው ጓዳችን በዚህ አያያዛችን አፈሙዙን ወደእኛ ላለማዞሩ ዋስትና የለንም። በሴራ ተከፋፍለን እርስ በርሳችን ወደመጠፋፋት መሽቀዳደም የለብንም።

ፖለቲካ የቡድን ስራ ነው። የተሻለ የተጫወተ ብዙ አድናቂዎችንና ደጋፊዎችን ከጎኑ ማሰለፉ የማይታበል ሐቅ ነው። ለአማራ ሕዝብ ስንል የግል ቁርሾ ልዩነት ከአማራ ሕዝብ ክብርና ጥቅም አይቀድምም፣ አይበልጥምምና ልዩነታችንን ወደጎን አድርገን እንደ ግል ከመታገል ወጥተን እንደ ቡድን ተናበን ልንታገል ይገባል።
የዶ/ር ዐብይ የብልፅግና መንግሥት በአማራ ክልል በሁለት እግሩ ከመቆሙ በፊት ሁሉም የአማራ ታጋይ የማደናቀፍ ሕዝብና መንግሥትን የመነጣጠል የሰላም ድርድሩ እንዳይሳካ የፈጠነ ስራ ላይ መሰማራት አለበት።

እየሆነ ባለው ተስፋ ሳንቆርጥ ከትግሉ ሜዳም ሳናፈገፍግ እንደቀደመው የተቀናጀና የተደራጀ የሞቀ ትግል በተለይ ደግሞ የሚዲያ ዘመቻውን በአዲስ መልክ መጀመር ይኖርብናል። የሚዲያ ዘመቻችን የትኩረት ማዕከልም ልብ የሚሰብሩ አሳዛኝ፣ አናዳጅ፣ መንግሥትን ከሕዝቡ ሊነጥሉ የሚችሉ የተቀነባበሩ ፕሮፖጋንዳዎች ላይ ያነጣጠሩ ሊሆን ይገባል። ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ትግበራ አንፃር በጠለምትና በራያ በኩል ሰዎች እንዳይረጋጉ እንዲፈናቀሉ በተፈናቀሉት ላይ ደግሞ ከስር ከስር ፕሮፖጋንዳውን እንስራበት። በሌሎች አካባቢዎችም መንግሥት በተመሳሳይ ተፈናቃዮችን ወደቦታቸው ለመመለስ እየሰራ ስለሆነ ተፈናቃዮች ባሉበት እንዲቀጥሉ ከካምፕ እንዳይወጡ ከወጡ ግን ወደ ጫካ እንዲገቡና ስልጠና እንዲወስዱ ለልዩ ልዩ ተልዕኮ ልንጠቀምባቸው ይገባል። ወደተፈናቀሉበት አካባቢ ተመልሰው የሚሰፍሩ ከሆነም በዛ መልሶ የማፈናቀል ጥቃት የማድረስ የቀደመው አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል። በደብረብርሃን በጎንደር በወሎ በመተከል ከተፈናቀሉ ተፈናቃዮች መካከልም የተጎሳቆሉ ፎቶዎችንና ምስሎችን ቦታው ድረስ በመሄድ በተከታታይ ወደሚዲያ ማምጣት፣ ባለን Death Squad በሀይማኖት ተቋማት በፖለቲካ በወታደራዊ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት ያላቸውን ለብልፅግና ድጋፍ የሚሰጡ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ሰዎች ላይ የተጠና ጥቃት በመፈፀም የጥቃቱን አድራሽ መንግሥት መሆኑን በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ቀድመን ሚዲያ ላይ ልንሰራበት ይገባል።መጨከን አለብን። ትግሉ መልፈስፈስን አዛኝነትን ሳይሆን ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ነው። የያዝነው ትግል ብዙ ወንድሞቻችንን የምናጣበትን የደም መስዋዕትነት የሚጠይቅና ጠላቶቻችን በሚጨክኑት ልክ ብቻ ሳይሆን ከእነሱ በተሻለ መጨከን አለብን።ፋኖ በለለባቸው ወይም በተዳከመባቸው አካባቢዎች ደግሞ ባልታወቁ ሃይሎቻችን የተመረጠ ጥቃትና እገታ በመፈፀም መንገድም በመዝጋት ማህበረሰቡ ይህን የሚያደርገው መንግሥት ባይሆን በቀላሉ መቆጣጠር ይችል ነበር እንዲል የማድረግ ስራችንን ማጠናከር ይገባናል።

በጥቅሉ የትናንትም ሆነ የዛሬ የእኛ ትልቁ አቅም ሚዲያ ነውና ከዚህ በፊት የነበረውን አንድነታችንን መልሰን በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ባልተቋረጠ ተመጋጋቢ የሚዲያ ዘመቻ መንግሥትን የማፍረክረክ ዘመቻችን ልናስቀጥል ይገባል።

ፎቶው፣ መጽሐፍ ወንድም በወንድሙ ላይ ይነሳል እንዲል ጃውሳ በጃውሳ ላይ የተነሳበት ነው።
2.0K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-07-01 07:51:35 የእነ ገዱ...የእነ ላ.. የእነ አደናግራቸው... የእነ አባ... የእነ X..የእነ ፍለጠው ቁረጠው...የእነ መናጆው ...ቡድን ሰሞኑን በአሜሪካ ሰብሰባ አድርጓል። በስብሰባው ግን ሊሰባሰቡ አልቻሉም። በስብሰባው ለጊዜው በምን ተስማምተው የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጡ የሚለውን ጉዳይ ወደበኋላ በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል። ያው የውዳቂ ስብስብ ቢሆኑም ምኞታቸውን ማወቁ ስለማይከፋ ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልል በመንግሥትና በፓርቲ እንዲሁም በልማት ድርጅቶች ውስጥ ተሰግስገው የውዳቂዎቹን የወደቀ አጀንዳ የሚያራግቡ ውዳቂዎችን ለማወቅና ለማጥራት የሚጠቅምም ስለሆነ ነው!

ሰላም ለሐገራችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!!
1.7K views04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-30 14:11:08
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ በወዳጅነት ጨዋታው ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት በግሩም ሁኔታ አስቆጥረዋል።
1.8K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-30 12:09:43
ዶ/ር ዐብይእያሟሟቁ ነው። ክረምቱን...
1.6K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ