Get Mystery Box with random crypto!

ቀጣዩ የህወሃት ፊልም ርዕስ “የኬሚካል መሳሪያ ጥቃት”! *** ድርሰት- የህወሃት ማፊያ ቡድን ተ | Yalelet Wondye Gebeyehu

ቀጣዩ የህወሃት ፊልም ርዕስ “የኬሚካል መሳሪያ ጥቃት”!
***
ድርሰት- የህወሃት ማፊያ ቡድን
ተዋንያን- የህወሃት ማፊያ ቡድንና ንጹሃን ዜጎች
ዘውግ- የፈጠራ ተረት ተረት
ለእይታ የሚቀርበው- ለምዕራባውያን

ህወሃት የምእራባውያኑን ስስ ቦታዎች ጠንቅቆ ያውቃቸዋል።
ያኔ ከበርሃ አንከብክበው አዲስ አበባ እንዳደረሱት ዛሬም ያንኑ ስስ ቦታቸውን ለመነካካት እያሴረ ነው።
ደርሰንበታል!
ምእራባውያን ከአለም ውስብስብ ታሪክና ከፖለቲካ ቁማራቸው የተነሳ እነዚህ ቃላት ያስበረግጓቸዋል።
ጄኖሳይድ፣ የፆታ ጥቃት፤ ርሃብ፣ ኬሚካል መሳሪያ፣ ኒውክሌር
ከነዚህ ውስጥ እርግጠኛ ነኝ ሶስቱን ቃላት በተለይ ከህወሃት መሪዎችና ከደጋፊ መንጋዎቻቸው በየሰበቡ ሲጠሩ ሰምታችኋል።
ረሃብ፤ አስገድዶ መድፈርና በተለይ ጄኖሳይድ የሚሉትን ቃላት!
አሁን ደግሞ ኬሚካል መሳሪያ እንደ አዲስ ሙዚቃ ካፋቸው እየተደጋገመች ልትመጣ መሆኑን ደርሰንበታል! ይህ ሁሉ ያለምክንያት አይደለም። የራሳቸውን ዜጋ መርዘው ሲያበቁ መንግስት የኬሚካል ጥቃት ፈፀመብን ብለው ያጡትን የአለምን ትኩረት ለመሳብ ማቀዳቸውን ደርሰንበታል። ያለ አንዳች ሃፍረት ይህ 300 ሺህ በላይ የትግራይን ህዝብ አስጨርሶ እንደ ድል አድራጊ ፈርጥጦ ከተመለሰ የማፊያ ቡድን የሚጠበቅ ስራ ነው።
“ለምን ልጆቻችንን ወደ ጦርነት ትማግዳላችሁ” የሚለው የትግራይ ህዝብ ጫና ሲበዛባቸው፤ ተስፋ ያደረጉባቸው ምእራባውያንም ችላ ሲሏቸው የመጨረሻ የመጫወቻ ካርዳቸውን እየሳቡ ይመስላል።
ህዝባቸውን ላሰቡት እኩይ አላማ ለማሰለፍ አንድ ጠላት መፍጠር አለባቸው፤ ይህ ምናባዊ ጠላት ደግሞ ያለ የሌለ ጥፋት ሰርቷል በሚል ሃጢያቱን ማብዛት አለባቸው።
የሃውዜኑን ታሪክ ማስታወስ እዚህ ላይ ተገቢ ነው። በወቅቱ እየሳሳ የነበረውን የህዝብ ድጋፋቸውን ለማሰባሰብ “ሴራ በቋት” የሆኑት የህወሃት መሪዎች በሃውዜን ሆን ብለው ንጹሃን በአየር ጥቃት እንዲመቱ ማድረጋቸውን ታሪክን ጠጋ ብሎ ያጠና ሰው በግልጽ መመልከት ይችላል።
በተመሳሳይ ይህንኑ ጊዜው ያለፈበትን ዘዴ ዘንድሮም ደግመውታል።
በሴራና በተንኮል የተካኑት የህወሃት መሪዎችና ተከታይ መንጋቸው ሰሜን እዝን ባጠቁ እለት የዛኑ ቀን ነው “ትግራይ ጄኖሳይድ” የሚለው የቁራ ድምጻቸው መሰማት የጀመረው።
ጥቃቱን ራሳቸው አቅደው፤ እስካፍንጫቸው ታጥቀውና ተዘጋጅተው ፈጽመው ሲያበቁ “ተጠቃን፤ አለቅን” ማለት የጀመሩት የዛኑ ቀን መሆኑን የትዊተር ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና መዝግቦ ይዞታል።
ጄኖሳይድ የሚለው ተረት በህወሃት ተደርሶ፤ በህወሃት ዳይሬክት፤ ተደርጎ ለአለም የቀረበ ምርጥ የህወሃት የፊልም ስራ ነው።
በገፍ ባዘጋጁት የመከላከያ ወታደር አልባሳት ጎረምሶቻቸውን እያለበሱ በገዛ ህዝባቸው ላይ ለፈጸሙት ጥፋት ዜጎቻችን ተደፈሩ ሲሉም ሰምተናል።
በገፍ የእርዳታ እህል እየገባ ጭራሽ ለዜጎች የእለት ጉርስ እንዲሆን ከሚገባ የእርዳታ እህልና ነዳጅ በጠራራ ጸሃይ እየዘረፉ በዛው አፋቸው ርሃብ የሚለውን ቃል የአፍ ሟሟሻ አድርገውት ቆይተዋል። ለነገሩ ዝርፊያ ብርቃቸው አይደል፤ የተካኑበት ነው፤ 27 አመት ኢትዮጵያን በዝብዘው ራቁት ያስቀሯት በዚሁ የዝርፊያ ስራቸው አይደለምን?
አሁን ደግሞ እስካሁን ያሰቡትን ያህል ትኩረትና ተፅእኖ ማግኘት ያለመቻላቸው ሲያንገበግባቸው ወደ ሌላኛው የጥፋት ዘዴ ተሸጋግረዋል።
የምዕራባውያን ቀላቢዎቻቸውን ትኩረት ይስብልናል ያሉትን በኬሚካል መሳሪያ ጥቃት ደረሰብን የሚል ከንቱ እሪታቸውን እንደለመዱት ለማሰማት ሴራ እየሸረቡ ነው።
በጦርነት የሞቱባቸውን ወታደሮች የሲቪል ልብስ አልብሰው ወንዝ ውስጥ እየጣሉ መንግስት ንጹሃንን አጠቃ ብለው ያሰሩት የሲኤንኤን ዶክመንተሪ ትዝ አላችሁ?
የሞቱ ወታደሮቻቸውን በጅምላ መቃብር ቀብረው ለምእራባውያን የሃሰት መወንጀያ ምክንያት ሲያደርጉትስ አልነበረም?
ምእራባውያን ጋላቢዎቻቸው ደግሞ ይህ የኬሚካል መሳሪያ ጉዳይ ኢራቅንና ሶሪያን እንዲሁም ሌሎች ሃገራትን ያፈረሱበት ምክንያት ነውና ህወሃትም ፍርፋሪ የሚወረውሩለትን ምእራባውያንን ትኩረት ለመሳብ፤ “ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦልም ቢሆን እንወርዳለን” ያለውን ቃሉን ጠብቆ፤ የመጨረሻ ካርዱ የሆነችውን “በኬሚካል መሳሪያ ተጠቃሁ” ለቅሶን ሊጠቀምባት መሆኑን ደርሰንበታል።
ቀጣይ የህወሃት ፊልም ርዕስ ናት!
ነቅተንባችኋል!