Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ታሪኮች ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የሰርጥ አድራሻ: @wubtarikoch
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

ለውብና አጫጭር ታሪኮች እንዲሁም ወጎች ይቀላቀሉን!
#Like እንዲሁም #Forward ማድረግዎን አይርሱ!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-08-24 21:04:13 ፌስታል ብሎ ታክሲ ውሰጥ ቀውጦት
ተደናግጠው ሲሰጡት

የያዘውን ጫት ሁለት ቦታ ከፍሎ አስቀመጠበት።


@WubTarikoch
4.6K viewsABᴜᴊᴀ, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:41:41 ያዝልኝማ..!

የመሆን እንጂ የመባል ገመድ ላይ አትንጠልጠል። የመባሉ ያንተ እውነተኛ ገመድ ስላልሆነ መበጠሱ አይቀርም። የመሆኑ ገመድ ግን የግልህ ስለሆነ ከቆሸሸ ማጠብ፣ ካለቀ መቀየር፣ ያንተ ድርሻ ነው¡¡¡

#ሼር @WubTarikoch
5.2K viewsABᴜᴊᴀ, edited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 12:53:57 የሴት እንባ..!

አንዲት ቆንጆ ልጅ ለቅሶ ላይ ስታለቅስ አየኋት፡፡ እንባዋ ሲወርድ በያዘችው ሶፍት ስትጠርገው ሶፍቱ ቡና ዓይነት ቀለም ያዘ፡፡ ለካስ የተቀባቸው ሜካፕ እየለቀቀ ነበር።

ባሻዬ! ከዚህ በፊት የነገርኩህን ዛሬም እደግመዋለሁ፡፡ ወንድ ልጅ ሴትን ማስለቀስ የለበትም ። እንደ ሴት ልጅ እንባ ውድ ነገር የለም፡፡ ሴትን ካስለቀስካት ብዙ ወጪ ታስወጣሃለች፡፡ ይኸውልህ አንዲት ዘለላ እንባ ከሴቷ ዓይን ስትወርድ በመጀመሪያ ሎሪያል ከተባለው የዓይን ኩል ጋር ይቀላቀላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ Loreal Eye Liner ዋጋው 2100 ብር ነው፡፡ ከዚያም ዓይኗ ላይ ያለውን ሬቭሎን ማስካራ ያበላሸዋል። የአንድ ሬቭሎን ማስካራ ዋጋ 2300 ብር ነው፡፡

እንባዋ ከዓይኗ ወርዶ ጉንጫ ላይ ሲደርስ ፋውንዴሽኗን ያገኘዋል፡፡ የአንድ Lauder Foundation ዋጋ 2400 ብር ይገመታል። ከዚያም የተቀባችውን Zaron Blush ያበላሸዋል። የዚህም ዋጋ 2700 ብር ይሆናል። ከዚያም እንደ ፊቷ ከለር የምትቀባው ማክ ፓውደር በእንባዋ ምክንያት ቡኒ ቀለም I ሠርቶ በፊቷ ላይ ሲወርድ ይበላሻል። የአንዷ ብልቃጥ ማክ ዋጋ አሁን 5400 ብር ደርሷል።

በመጨረሻም እንባዋ ተንከባሎ ከንፈሮቿ ጋ ሲደርስ ከኤልዛ ሊፕስቲክና ከተደራቢው Avonlip Gloss ጋር ተቀላቅሎ ለሁለቱም የ 4400 ብር ኪሣራ ያስከትላል።

ባሻዬ! በድምሩ ተባበረኝ እባክህ፡፡ አንዷ ጠብታ የሴት እንባ በድምሩ 19300 ብር ያስወጣሃል።

ባሻዬ! እባክህ ሴትን ልጅ አታስለቅስ። እሷ ከምታለቅስ አንተ ብታለቅስ ይቀላል፡፡ ያንተ የቫዝሊን ዋጋ 13 ብር ከሃምሳ ሣንቲም ብቻ ነው።

ተስፋዬ ኃ.ማርያም | @WubTarikoch
6.7K viewsABᴜᴊᴀ, 09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 18:34:14 የዕለቱ ምርጥ..!

ስለ ገንዘብ - በድሃ ፊት አትናገር!
ስለ ጤንነትህ - ህመምተኛ ፊት አታውራ!
ስለ ጥንካሬህ - ደካሞች ፊት አትናገር!
ስለ ደስታህ - በተከፋ ሰው ፊር አታውራ!
ስለ ነጻነትህ - እስረኞች ፊት አትናገር!
ስለ ልጆችህ -መሃን ፊት አታውራ!
ስለ እናት እና አባትህ -ወላጅ አልባ ሰዎች ፊት አትናገር!

..ምክንያቱም ቁስሎቻቸውን ከበፊቱ በበለጠ እንዲቆስል እና እንዲደማ ምክንያት ትሆናለህና። ለምትሰጠው ነገር ሁሉ ትንሽ ፈገግ በል፣ ከልብህም ደስታን ጨምርበት፣ ለማንኛውም ሰው ጆሮ ስጥ፣ ግን ድምጽህን ቀንስ ሁሉንም ውደድ ጥቂቶቹን እመን፣ ማንንም ግን አትበድል። የውሸት ጓደኛ እና ጥላ አንድ ናቸው። ሁለቱም የሚቆዩት ጸሃይ እስክትጠልቅ ድረስ ብቻ ነው። መልካም ሰው ከሰው ልጅ የመንፈስ ምግብ ነው የማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑ የሚታወቀው ተፈትኖ ካለፈ ወይም ከወደቀ ብቻ ነው።

#ሼር @WubTarikoch
7.3K viewsAʙᴜDɪ, 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:55:28 ይህ በእንዲህ እያለ ..!
በእውቀቱ ስዩም


ስሚ! ሁሉ ነገር ዱሮ ቀረ ሲሉሽ ሀሰት እንዳይመስልሽ! የድሮ ጴንጤ የምር ጻድቅ ነበር፤ አይጠጣም፤ ከአፉም ክፉ አይወጣም፤ በእምነቱም ብዙ መከራ ይቀበል ነበር፤ ትዝ ይለኛል፤ ልጅ እግር እያለን እንቻለው ሰይፉ የተባለ የሰፈራችን ጴንጤ ነበር፤ እና አምልኮ ሲመለስ ስሚዛ ስር አድፍጠን እንጠብቅና እናበራየዋለን፤ እሚገርመኝ ነገር፤ እንቻለው ስንደበድበው በመመከት ፋንታ እጆቹን ደረቱ ላይ አመሳቅሎ ፥ አንጋጦ እያየ የሚወርደበትን በትር በጸጋ ይቀበላል፤ ከሰማይ ርዳታ እየጠበቀ መሆን አለበት፤ ርዳታው ሲዘገይ ፥ ጥፊውና ካልቾው ሲበረታ፤ እንቻለው ከድብደባ የተረፈውን ሰውነቱን ሸካክፎ በሩጫ ወደ ቤቱ ይሸመጥጣል፤” እህ! ሰማእትነትም ቢሆን ልክ አለው!” የሚል ይመስለኛል በልቡ ዛሬ ግራ ጉንጩን ብትመታው ቀኙን የሚያዞርልህ ወንጌላዊ ያለ አይመስለኝም፤ እንዲያውም ግራ ጉንጩ አጠገብ አያስደርስህም፤ ግራ ጉንጩ ላይ ከመድረስህ በፊት ቦዲጋርዶቹ እንደ ሸንኮራ ቀንጥሰው ለጠብታ አንቡላንስ ያስረክቡሀል::

ባህታዊ ራሱ ድሮ ቀረ! የድሮ ባህታዊ ፤ ዱር ጥሶ፤ ጤዛ ልሶ፤ ድንጋይ ተንተርሶ፤ የሌሊትን ግርማ ታግሶ ለህዝቡ ይጸልይ ነበር፤ የዛሬ ባህታዊ መሀል ከተማውን ጥሶ፥ ላፕቶፕ ተባጥሶ፤ የኔትወርክ መቆራረጥን ታግሶ ፥ ትንቢት ሰክሶ ፥ በዩቲብ ላይ ሲሸቅል ታገኘዋለህ፤

የእምነት አመል እንደየጊዜው ይለዋወጣል፤

በአለም ላይ ሁለት አይነት ሰዎች አሉ፤ ችግር የሚፈቱና ችግር የሚፈተፍቱ! ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር በያይነቱ ተትረፍርፏል! ችግሩን መፍታት ቀላል አይደለም፤ ለምሳሌ ሀኪም ለመሆን በትንሹ ሰባት አመት መማርና መመራመር ይጠይቃል፤ ባንጻሩ ሰው ባንድ ጀንበር ብቻ በሽታ ላይ ይወድቃል፤ የችግረኞች መብዛት እና የችግር ፈቺዎች ማነስ አንድ ነገር ፈጠረ፤ የችግር የመፈታት ቸሎታ ተላይ ተሰማይ ተሰጥቶናል እሚሉ አጭበርባሪዎች ከየቦታው እንዲፈለፈሉ ምክንያት ሆነ፤

ዛሬ፥ በሀይማኖት ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ስፍር ቁጥር የለውም፤ የሀይማኖት ከበርቴዎች ግብር አይከፍሉም፤ በአስራት ፥ በመባ በስጦታ የሚሰበስቡት በአካውንታቸው ስር ከመርመስምስ አልፎ ለልማት ሲውል አናይም፤ በበጎ ሰዎች አይን ሲገባ፥ ሀይማኖት ለበጎ አላማ መሳርያ ሊሆን ይችላል ብየ አስባለሁ፤ግን እየሆነ ያለው ሌላ ነው፤

የእምነት ሊቃውንት፥ በሰናይ ምግባር ላይ የተመሰረተ ስበከት ሲሰብኩ ከሰማችሁ ስንት ጊዜ ሆናችሁ? ዛሬ ዛሬ “ስብከት የተአምር ሰርከስ ከማሳየት እና ከማዝናናት አያልፍም! ይሄ ሁሉ , መስጊድ፤ ይሄ ሁሉ ቤተክስያን ባለበት አገር ፤ ግድያ፤ዝርፍያ፥ ቅጥፈት፥ዘረኛነት ደፈራ፥ አደንዛዥ እጽ፥ በዚህ መጠን መንሰራፋት ነበረበት? የሆነ አጀንዳ ሲመጣ ከየአቅጣጫው የሚጎረፈው የዘለፋ አይነት፥ እውነት በሀይማኖት ከታነጸ ማህበረሰብ የሚጠበቅ ነው? የሀይማኖት ሰዎች በቤትስራቸው ላይ እንደተኙበት አያሳይም?

ውሻ በቀደደው ልግባ ብየ ነው፤ አመሰግናለሁ።

@WubTarikoch
7.3K viewsABᴜᴊᴀ, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 16:32:56 How to calculate ..!

Normal person: 7+6=13

Me: if 7+7=14
& 6 is one less than 7,
then 7+6 must be 13


@WubTarikoch
6.6K viewsABᴜᴊᴀ, 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 14:36:41 ሰሞንኛ ..!
በእውቀቱ ስዩም

ትናንት ማታ በረንዳው ላይ ቁጭ ብለን ፥ ውስኪና የተልባ ጁስ እየጠጣን ስናወጋ ምኡዝ እንዲህ አለ፤ “ ከብዙ ሴቶች ጋራ መተኛት የብዙ ወንዶች ፍላጎት ነው ፤ ወንድ ልጅ ቢቻለው፥ ቢሰምርለት ቢቆምለት ከመላው ሄዋን ዘር ጋራ ቢዳመር አይጠላም፤ በሆርሞኑ በደሙ ያለ ነገር ነው፤ የባዮሎጂ ስሪቱ እንዲያ ነው ! ሼህ ቢሆን ቄስ ሳይንቲስት ሆነ ግምበኛ ለውጥ የለውም! ወንድ ልጅ ባንድ ሴት እሚወሰነው ሁለተኛ አማራጭ ሲያጣ ነው፤ በርግጥ ፍቅር የያያዘው ወንድ በፍቅረኛው ሊወሰን ይችላል! የፍቅርን ሀይል አልክድም”

ብዙ ሴቶችን መተኛት ለብዙዎቻችን የማይሰምር ህልም ነው፤ ስለዚህ የተሳካለትን ሰው እንቀናበታለን! እንጠምደዋለን! ባደባባይ ብናገኘው በግልምጫ እናፈርጠዋለን! በልባችንም እንዲህ እንብሰከሰካለን! እኔን የንጦጦ ብርድ ሲከካኝ እያደረ እሱ ምናባቱ ስለሆነ ነው እያማረጠ እሚበላው? ክርክሩ ላይ ድግምት አስሮ ካልሆነ በመልክ እንኳ እኔ እበልጠዋለሁ! እንዲያውም እኔ ሳልቦንሰው አልቀርም! ይሄ ሻኛ ፊት ! መፈጠሩን እንዲጠላ ካላደረሁት ወንድ አይደለሁም!

ሴቶች ፥ አተራማሽን ወንድ ሲገጥማቸው የወንዶችን ያክል አይጨክኑበትም፤ እንዲያውም በሴት አውል የሚሳቡና የሚጠመዱ ሴቶች አይጠፉም! ይሁን እንጂ ብዙ ሴት የሚያንባባ ወንድ ፥ ባብዛኛው ሴቶች ዘንድ እንደ ቁምነገር አይታይም! ልብን የሚያሳርፍ ባል ፤ መከታ የሚሆን አባት መሆን አይችልማ! ንብረቱን ትኩረቱን ጊዜውን የትም ስለሚበትን ለዘለቄታ ፤ ለህይወት አጋርነት | አይመርጡትም፤

ማህበረሰብ የቆመው የግለሰቡን እንደአሻው የመኖር ፍላጎት በመጨቆን መሆኑን አንርሳ! ከማህበረሰብ ተግባሮች አንዱ ፍትሀዊ የፍቅር ጉዋደኛ ክፍፍል ማድረግ ነው! አንድ ወንድ ብዙ ሴት ሰብስቦ ከያዘ፥ የሆነ ሰፈር ላይ ወንዶች በብህትውና መኖር ይገደዳሉ፤ ስለዚህ ብዙ ሴት የሚይዝ ወንድ የማህበረሰቡን ፍትሀዊ የሚስት ክፍፍል ያደናቅፋል ፤ ማህበረሰብ ሴት አውሉን በምድር በህግ ይቀጣዋል፤ በገሀነም እሳት ያስቦካዋል፤ ከዚያ በተረፈ በሀፍረት ያደባየዋል! በባህላችን ብዙ ሴት ጋ የሚሄድ ወንድ እንደ ሰው አይቆጠርም፤ ከአህያ ነው ምድቡ! “ አለሌ” የሚለውን ስም አስበኸዋል? አለሌ ማለት ከሴት አህያ አልፎ ሴት ፈረስ የሚሰርር አህያ ማለት ነው !

ስለዚህ በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ የተሳካላቸው መፍቅሬ -ሴት ወንዶች፥ ደስታቸውን ላለማጣት እና ደሞ በማህበረሰብ በትር ላለመቀጣት፥ በድብቅ በስውር በለሆሳስ ይራመዳሉ፤ በባህላችን ቅምጥ ፤ ውሽማ እና እቁባት አያያዝ ላይ የነበረው ምስጢራዊነት በሲአይኤ ውስጥ እንኳ አይገኝም፡፡ ንብረት ገላው የገጠመው መከራ ከዚህ አንጻር መታየት ያለበት ይመስለኛል! ማንም ስለንብረት ገላው ልጆችም ሆነ ስለ ልጆቹ እናት ደንታ ያለው አይመስለኝም! ስለራሱ ልጆች ደንታ ያለው አበሻ ምን ያህል ይሆናል? አጅሬ የተሸወደው ከብዙ ሴቶች ጋራ ይተኛ እንደነበር ባደባባይ ሲናዘዝ ነው ! እግዜር ይቅር ቢለው እኛ ይቅር አንለውም! ቦታ ብንቀይር ምን ይመስልሀል?”

“ ርእስም ብንቀይር ደስ ይለኛል”


@WubTarikoch
7.1K viewsAʙᴜDɪ, 11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 21:15:51 G(Old) jokes ..!

አንድ ልጅ ታክሲ እየጠበቀ ነበር:: እንደ ድንገት ታክሲው ከች ሲል ተወርውሮ ይገባና ከኃላ ወንበር መስኮቱን ከፍቶ ዱቅ እንዳለ በሜሴንጀር ሜሴጅ ይገባለታል ስልኩን አውጥቶ ሜሴጁን ሲከፍተው

ከፍቅረኛው(ሚስቱ) የተላከ ነበር።
"የኔ ፍቅር ዛሬ ካንተ ጋር ማደር ፈልጌ ነበር ሀሳብክን ብትነግረኝ ደስ ይለኛል"

ልጁ ጥርስ በጥርስ ሆኖ በሆዱ (ተገኝቶ ነው) እያለ መልሱን መጻፍ ጀመረ

የኔ ፍቅር በጣም ደስ ይለኛል የት እንገናኝ ብሎ እየጻፈ እያለ ከየት መጣ ሳይባል ሌባ ስልኩን ሞጭልፎት ይሮጣል። የዛኔ ልጁ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ ምን ቢል ጥሩ ነው..

በፈጠረክ send የሚለውን ብቻ ተጫንልኝ!!

@WubTarikoch
6.5K viewsABᴜᴊᴀ, edited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 19:44:10 ልጅቷን ለምን ሳምካት..?

በእድሜ የገፉ አባት ናቸዉ ከሁለት ወጣት ልጆቻቸዉ ጋር ሲኖሩችግር ይገጥማቸዋል :: ወንዱን ልጅ ስራ እንዲሰራ ይልኩታል ከመሔዱ በፊት ሊመክሩት ፈለጉና ''ልጄ ሆይ ስለ እህትህ ስትል አሏህን ፍራ አሉት:: አልገባዉም እህቱ አብራዉ አትሔድ ..ምን ለማለት ፈልገዉ እንደሆነ ሳይገባዉ ሳይጠይቅ ተሰናብቷቸዉ ሄደ:: ስራዉን ጨርሶ ሲመለስ አባት ልጄ ሆይ! ለምን ያቺን ልጅ ሳምካት አሉት ።

አባቴ አረ ማንንም አልሳምኩም አላቸዉ። ''በጭራሽ ስመሃታል!'' ብለዉ ሲያፋጥጡት አባቴ ማንም አላየንም ጨለማ ዉስጥ ነበርን ከአሏህ ዉጪ ማንም አልተመለከተንም ማን ነገረህ? ዋህይ(ራዕይ) ወረደልህ? እንዴት አወክ ብሎ ሲጠይቃቸዉ..

በሩን ከፍቼ ቤት ዉስጥ ቁጭ ብዬ ነበር ዉሀ ቅጂዉ ዉሀ ይዞ መጣ እህትህ ከፈተችለት ዉሃዉን ከገለበጠ በኃላ ሊወጣ ሲል እህትህን ግጥም አድርጎ ሳማት ያኔ አንተም የሰዉ እህት እንደሳምክ አወኩ ወደ ሌላ እንቅስቃሴ ብትገባ ዉሀ ቅጂዉም ወደሌላ እንቅስቃሴ ይገባ ነበር፡፡

በሰዉ እህት ሚቀልድ በእህቱ ይቀለዳል
• በሰዉ ልጅ ሚቀልድ በራሱ በልጁ ይቀለዳል
.በሰዉ ሚስት ሚቀልድ በራሱ ሚስቱ ይቀለዳል
« በሰዉ ልጅ በሰዉ ሚስት በሰዉ እህት ዝሙት የሚፈጽም እዳዉን በቤተሰቡ ይቀበላል፡፡ ዝሙት እዳ ነዉ ካበደርከዉ በቤተሠብህ ብድሩን ትቀበላለህ።

*ሁሉም ሰው የዘራውን ያጭዳል በራስህ ላይ (በቤተሰብህ) ላይ ሊደረግ የማትፈልገውን ነገር በሌሎች ላይ አታድርግ። በሌላ ሴት ላይ የምሰራዉ ስራ አንተ ሳታቅ በእህትህ ላይ እንደሚሰራ እወቅ የሌሎችን ሴቶች መብት ስትጠብቅ የአንተም እህት መብት ይጠበቃል፡፡

@WubTarikoch
9.2K viewsABᴜᴊᴀ, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 12:19:24 አብሮ አደግ ጓደኛዬ ከአንድ ወር በፊት ሊያገባ እንደሆነ እና እንዳጅበው ደውሎ ነገረኝ። በስራ ምክንያት የሰርጉ ቀን ወደሌላ ቦታ ተንቀሳቅሼ ሳልሄድ ቀረሁ፡፡ ከተመለስኩ በኋላ መንገድ ላይ ሳየው ሀፍረት እየተሰማኝ ባላየ ማለፍ ጀመርኩ።
በጣም ሲደጋገም የሆነ ስጦታ ገዝቼ ቤቱ መሄድ አንዳለብኝ ወሰንኩ።

ከመሄዴ በፊት ቤት መሆኑን ማረጋገጥ ስለነበረብኝ ደወልኩለት!

" ቤት ነህ እንዴ ሀቢቢ?" "አዎ ቤት ነኝ!" አለኝ
"ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ቤት እመጣለሁ ጠብቀኝ" አልኩት
"እሺ ግን በሰላም ነው?" አለኝ
"አዎ በሰላም ነው ለሰርግህ ስላልመጣሁ ዛሬ ካንተ ጋር ላሳልፍ ብዬ ነው"
"አሽሙር መሆኑ ነው? አለኝ
"ማለት አልገባኝም!" አልኩት
"ካንተ ግን ይሄን አልጠብቅም" ብሎ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋው!

ቆይቼ ከጓደኞቹ ሳጣራ ጀለስ ከሚስቱ ጋር ተፋቷል ;) Ebad


@WubTarikoch
9.2K viewsAʙᴜDɪ, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ