Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ታሪኮች ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የሰርጥ አድራሻ: @wubtarikoch
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

ለውብና አጫጭር ታሪኮች እንዲሁም ወጎች ይቀላቀሉን!
#Like እንዲሁም #Forward ማድረግዎን አይርሱ!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-10-05 17:22:57 ቤተሰቦቻችን ሌባ ለመሸወድ የሳሎን መብራት አብርተው የሚወጧት ነገርስ ..

@WubTarikoch
1.0K viewsAʙᴜDɪ, 14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 18:56:40 Fun facts..;)

1. "እውነት ለመናገር" ተብሎ የሚጀምሩ ሃሳቦች ሁሉ እውነት አይደሉም
2. አብዛኛው ወንድ ልጅ ከእናቱ ቀድሞ መሞት ይፈልጋል
3. ኳስ የማያዩ ሰዎች ብዙ ግዜ ቀልድ አይገባቸውም
4. ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኛ ያልሆነ የለም
5. የፈረንጅ ዘፈን መስማት እርድና ነው ብሎ መስማት ፋርነት ነው,
6. instagram ይልቅ facebook የበለጠ ያዝናናል,
7. ራሱን የሚንከባከብ ወንድ ሴታ ሴት አያስብለውም
8. በባስ መሄድን መጥላት ጢባር አይደለም 
9. በድንገት ሃብታም የሆነን ሰው በጥንቆላ መጠርጠር ምቀኝነት አይደለም

Abu Dii | @WubTarikoch
1.5K viewsABᴜᴊᴀ, 15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 18:56:16 አሁን ላይ ስለ ሁለት ትልቅና የተለያየ ገፅታ ያላቸው ሰዎች አንድ ነገር ልበላችሁ
1ኛዉ  ወጣቱ(Fire age)
2ኛዉ  አባቶቻችን(Old Guys)

ወዳጆቼ ምን አስተዋልኩኝ መሰላቹ እኛ ወጣቶች እኛ አዋቂ ነን፣እኛ ያልነዉ ልክ ነዉ፣ዘመናዊነት ዉስጥ ነን ብለን ዘራፍ እንላለን። አባቶቻችን ደሞ እኔ የህይወት ልምድ አለኝ ብዙ አስተምራኛለች አሳይታኛለች፣ ብዙ ወድቀን ተነስተናል ይላሉ።

አዉ ልክ ናቸዉ ባይ ነኝ ብዙ ነገሮችን ከነሱ እንማራለን። ወጣት ሆኜ የሰራሁትን ስህተት አንተ አንተ ደግመህ እንድትሰራ አልፈልግም ይሉናል...!!
አኔ እንዲህ ብናደርግ እላለዉ እኛ ወጣቶች የአባቶቻችንን ምክር ተቀብለን በስነ ምግባር አድምጠናቸዉ፣ እኛም ደሞ በኛ ጊዜ ስለተቀየረዉ ነገር ያልነበረዉ አሁን ላይ እንደተሻሻለ በእርጋታ ብናስረዳቸዉ ይቀበሉናል ብዬ አስባለሁ!!

እና ደሞ እኛም እድሜያቸዉ ገፍቷል ብለን አንናቃቸዉ። እነሱም ወጣት ነዉ ገና ነዉ ብለዉ አያታልሉን... ሁለቱም ፍፁም የተለያዩ የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች መካከል ትልቅ መከባበርን፣ ፍቅርን እና ሰላምን ማስፈን ይቻላል።
 
ሙራድ ሙሀመድ | @WubTarikoch
1.6K viewsAʙᴜDɪ, 15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 13:11:03 የጠቢቡ ሰሎሞን ፍርድ

ሦስት ነጋዴዎች ድንገት አንድ ቀን በንጉሥ ሰሎሞን የዘውድ ችሎት ተገኙ፡፡ ሦስቱም ለብዙ ዘመን አብረው ለመነገድ ተማምለው፣ ግመል ጭነው፣ ገንዘብ ቋጥረው፣ ስንቅ አንጠልጥለው፣ ሀገር ጥለው የሄዱ ናቸው፡፡
‹ንጉሥ ሆይ› አለ አንዱ በዙፋኑ ፊት እጅ ነሥቶ፡፡ ‹እኛ አብረን ለመነገድ ተስማምተን መንገድ የጀመርን ጓደኛሞች ነን› አለ፡፡
ሁለተኛውም ነጋዴ ተቀብሎ ‹ቃላችንንም አክብረን ለንግድ ሩቅ ሀገር ስንጓዝ ድንገት የሰንበት በዓል ደረሰብን› ሲል ቀጠለ፡፡
ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ሰንበትን አክብረን ለመዋል ስለፈለግንም ድንኳን ከተከልንበት ቦታ ራቅ አድርገን ጉድጓድ ቆፍረን ገንዘባችንን በከረጢት ቀበርነው፡፡ ከመካከላችን ማናችንም ገንዘቡን ተደብቀን ላንወስድ መሐላ ፈጽመን ነበር፡፡ በማግሥቱ ግን ወደ ጉደጓዱ ሄደን ስንቆፍረው ገንዘባችንን አጣነው› አለና አስረዳ፡፡ የመጀመሪያው ነጋዴም አንገቱን ከነቀነቀ በኋላ ‹ንጉሥ ሆይ ጉድጓዱን ስንቆፍርም ሆነ ገንዘቡን ስንደብቅ ሌላ ሰው ያየን የለም፡፡ ከሰረቅነው እኛው ነን፡፡ ነገር ግን ማናችን እንደሰረቅን ልንተማመን አልቻልንም› አለ፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን በልቡ ‹መስረቅ የቻለ ሰው መዋሸትና መሐላን ማፍረስ አያቅተውም› ብሎ አሰበና ነገሩን ቀለል አድርጎ ‹ነገ ተመልሳችሁ ስትመጡ ማን እንደሰቀረው እነግራችኋለሁ› ሲል አሰናበታቸው፡፡
በማግሥቱ ሦስቱ ጓደኛሞች መጡ፡፡ ችሎቱም ተጀመረ፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን ‹የእናንተን ጉዳይ ከመመልከቴ በፊት ሦስታችሁም ጠቢባን መሆናችሁን ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ በመሆኑም በሚከተለው ታሪክ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንድትሰጡ እፈልጋለሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ከልጅነታቸው ጀምሮ አብረው እየተማሩና እየተጫወቱ አደጉ፡፡ ወደፊት ትልቅ ሰው ሲሆኑ ተጋብተው አብረው ለመኖር ቃል ተግባቡ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የኑሮ መሥመር አለያያቸውና በተለያዩ ቦታዎች መኖርና መሥራት ጀመሩ፡፡ በዚህ መካከልም ሴቷ ቃል ኪዳንዋን ረሳችውና ሌላ ባል አገባች፡፡ ጋብቻው በተፈጸመበት ቀን ማታ የገባቺው ቃል ኪዳን ትዝ አላት፡፡ ደነገጠች፡፡ ነገሩን ለባልዋ ነገረቺው፡፡ ባልዋም ለቃል ኪዳን ትልቅ ቦታ የነበረው ሰው ነበርና ‹በይ ተነሺ ቃል የገባሺለትን ሰው እንፈልገው፤ ስናገኘውም ቃል ኪዳኑን ማፍረሳችንን ነግረነው፣ የገንዘብ ካሣም ከፍለነው ይቅርታ ያድርግልን፡፡ ያለበለዚያ ትዳራችን ይበላሻል› አላት፡፡
ሁለቱ አዲስ ተጋቢዎች ልጁ ይገኝበታል ወደሚባለው ቦታ ሩቅ መንገድ ተጉዘው አገኙት፡፡ የሆኑትንም ነገር ሁሉ ገለጡለት፡፡ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው፣ ገንዘቡን እንዲቀበላቸው ለመኑት፡፡ ልጁ ቀና ሰው ስለነበር ይቅርታ አደረገላቸው፡፡ ‹ያልሠራሁበትን ገንዘብ አልቀበልም› ብሎ ገንዘቡን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ እነርሱም አመስግነውት ተመለሱ፡፡ ሲመለሱ በመንገድ ላይ አንድ ዘራፊ አጋጠማቸውና የያዙትን ገንዘብ ነጠቃቸው፡፡ ልጂቱም ገንዘቡ በምን ምክንያት እንደተያዘ ታሪኩን እያለቀሰች ለዘራፊው ነገረቺውና እንዲመልስላቸው ለመነቺው፡፡ ዘራፊውም በታሪኩ ተደንቆ የወሰደውን ገንዘብ መለሰላቸው፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን ይህን ታሪክ ከተረከ በኋላ ‹ከባልየው፣ ከሚስቱ፣ ከቀድሞ ወዳጇና ከዘራፊው የትኛው ሰው የበለጠ ምስጋና ይገባዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?› ሲል ጠየቃቸው፡፡
የመጀመሪያው ነጋዴም ‹ለእኔ የበለጠ ምስጋና የሚገባት ሴቲቱ ናት፡፡ ቃል ኪዳንዋን አስታውሳ ይቅርታ ለመጠየቅ መነሣቷ ያስመሰግናታል› ሲል ሐሳቡን ሰጠ፡፡
ሁለተኛው ነጋዴም ‹ለእኔ ግን የበለጠ ምስጋና የሚገባው ባልዋ ነው፡፡ ምክንያቱም ሚስቱ ቃል ኪዳንዋን ማፍረሷን ስትነግረው ቃልዋን ተቀብሎ፣ ቤት ንብረቱን ትቶ፣ ገንዘቡን ይዞ ወደ እጮኛዋ ዘንድ መሄዱና ይቅርታ መጠየቁ ያስመሰግነዋል› ሲል አስተያየቱን ሰጠ፡፡
ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ባልና ሚስቱ ያደረጉት ነገር የሚገርምና የሚያስመሰግን ነው፤ ነገር ግን የቀድሞ እጮኛዋ ሞኝ ሰው ነው፤ ገንዘቡን መቀበል ነበረበት› ሲል ሐሳቡን ለገሰ፡፡
ንጉሥ ሰሎሞንም ሐሳባቸውን ከሰማ በኋላ ሦስተኛውን ነጋዴ ‹ገንዘቡን የሰረቅከው አንተ ነህ› አለው፡፡ ሰውዬውም ደነገጠና ወደ ንጉሡ ተመለከተ፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም ‹ያልደከመበትን ገንዘብ የሚመኝ አእምሮ ባይኖርህ ኖሮ ያንን ልጅ ሞኝ አትለውም ነበር፡፡ አስተሳሰቡ ከሌለ ድርጊቱ አይመጣም፡፡ አንተ ውስጥ ተጣምሞ የበቀለ ነገር አለ፡፡ ሁለቱ ጓደኞችህ ታማኝነትን ዋጋ ሰጥተውታል፤ አንተ ግን ለታማኝነት ዋጋ አልሰጠኸውም፡፡ ስለዚህ ካንተ በቀር ይህን ሊያደርግ የሚችል ሰው የለም፡፡
የአንተን አእምሮ ሳየው የተሠራበትን ነገር አየሁት፡፡ አእምሮ ሲሰጠን ተሠርቶ አልተሰጠንም፡፡ እንዲሠራ ተሰጠን እንጂ፡፡ ሰው በርስቱ ላይ እንዴት ያለ ቤት እንደሚሠራ መወሰንና ቤቱን መገንባት የእርሱ ድርሻ ነው፡፡ የሚጠቀመው ዕቃ የሚገነባበትም መንገድ የቤቱን ጥንካሬ ይወስነዋል፡፡ አእምሮም እንዲሁ ነው፡፡ በሕግ፣ በምግባር፣ በትምህርት፣ በጥበብ፣ የተገነባ አእምሮ ያንተን ዓይነት አስተሳሰብ አይኖረውም፡፡ አሁን የሰጠኽው ሐሳብ ያሳለፍከውን ሕይወት፣ የተዘራብህን ዘርና የተሠራህበትን ነገር አሳይቶኛል፡፡ ወላጆችህን አየኋቸው፤ ጓደኞችህን አየኋቸው፣ መምህሮችህን አየኋቸው፡፡ እነዚህ ሁሉም ወይም ከእነዚህ አንዱ የዘራብህ ዘር ትክክል አይደለም፡፡ ምናልባትም ይህ ዘር ባንተ ላይ መዘራቱን አታውቀው ይሆናል፡፡ ግን ተዘርቶብሃል፡፡
‹አንድ ታሪክ ልንገራችሁ› አላቸው ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡ እንዲቀመጡ ተፈቀደላቸው፡፡ ሁሉም ሌባውን ያወቀበት መንገድ አስደንቋቸዋል፡፡ ምንጣፍ ላይ ቁጭ አሉ፡፡
አንድ ቀን አንድ ልጅ እኔ ዘንድ ለፍርድ ቀረበ፡፡ የመጣው አባቱን ገድሎ ነው፡፡ ታዳሚዎች ሁሉም ‹አባቱን የገደለ ፈጽሞ ይሙት ይላልና ይገደል› ብለው ወሰኑበት፡፡ እኔ ግን ይህንን ነገር ያደረገበትን ምክንያት ለመረዳት ስለፈለግኩ ጠየቅኩት፡፡ ነገሩም እንዲህ ነበር፡፡ አንድ አባት ልጁን ሁል ጊዜ አንድ ነገር ያስተምረዋል፡፡ ጓደኞቼ መቱኝ ሲለው ‹በላቸው› ይለዋል፡፡ ፍየሉ ወጋኝ ሲለው ‹በለው› ይለዋል፡፡ ዕንቅፋት መታኝ ሲለው ‹በለው› ይለዋል፡፡ የአባቱ መፍትሔ ሁልጊዜ ‹በለው› ብቻ ነበር፡፡ ልጁ በዚህ ትምህርት ነበር ያደገው፡፡ አደገ፡፡ ጎለመሰ፡፡ ፈረጠመ፡፡ ያገኘውን ሁሉ እየደበደበ፡፡
አንድ ቀን የአባቱን በጎች ወስዶ አባቱ ሳይፈቅድለት ሸጠና መጣ፡፡ አባቱ ለምን እንደሸጠ ሲጠይቀው ‹ገንዘብ ያስፈልገኛል› አለው፡፡ አባቱ ተናደደና በበጎች መጠበቂያ ጅራፍ መታው፡፡ ያን ጊዜ ልጁ ድንጋይ አንሥቶ እንደ ቃየል አባቱን አናቱን መትቶ ገደለው፡፡ ልጁን ለምን አባቱን እንደገደለ ስጠይቀው ‹አባቴ ያስቸገረኝን ሰው ሁሉ እንድመታ አስተምሮኛል፡፡ አባቴም ስላስቸገረኝ መታሁት፡፡ ለመሆኑ ከመምታት በቀር ምን ማድረግ እችል ነበር?› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ይህ ልጅ ሌላ ነገር አልተማረምና ያደረገው የተማረውን ነው፡፡ ሰው የትምህርቱ ውጤት ነውና› አለው፡፡ ሰውዬውም በነገሩ ተገርሞ ገንዘቡን መለሰ ይለናል ሚድራሽ የተባለው የአይሁድ የትውፊት መጽሐፍ፡፡
ይህንን ታሪክ ሳነብ ዛሬ በልጆቻችን ኅሊና እየገነባን ያለነው የዘረኛነትና የጠባብነት፣ የጽንፈኛነትና የአምባገነንነት ጡብ ይታወሰኛል፡፡ እያንዳንዳችን ለሌላው ብለን የምናስታጥቃቸው ነገር አፈሙዙ ወደራሳችን ሊዞረን እንደሚችል ያሰብንበት አልመሰለኝም፡፡ የተጣመመ ሐሳብ እያሰጠን፣ የተጣመመ ትውልድ አፍርተን የተስተካከለች ሀገር አንደመመኘታችን ያለ ሞኝነት ከወዴት ይገኛል?

ዳንኤል ክብረት | @WubTarikoch
816 views _U_K_I, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 19:00:11 እኔ ምለው ስልካቹ ቻርጅ እስኪያደርግ ድረስ ምንድነው ምታደርጉት ?

comment
1.6K viewsAʙᴜDɪ, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 16:20:19 አንዳንድ ዕውነታዎች.. ;)

1. ባለ ፀጋው ሔንሪ ፎርድ የጓደኛው የቶማስ ኤዲሰንን የመጨረሻ ትንፋሽ በጠርሙስ ውስጥ አስገብቶ ጠርሙሱን ዘግቶ አስቀምጦት ነበር።

2. አይሁዶች ሰው ከሞተ በኋላ ነፍሱ በሞተበት አካባቢ ለ4 ቀናት ትቆያለች ብለው ያምናሉ።

3. በዶክተሮች መጥፎ የእጅ ፅሁፍ የተነሳ በየዓመቱ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች ይሞታሉ።

4. የወንድ ልጅ ብልት መጠን የቀኝ እጁን አውራ ጣት ሁለት እጥፍ ይሆናል።

5. ሴት ልጅ ትናንት ማታ ቦርሳዋ ውስጥ ያስቀመጠችውን ዕቃ የት እንዳደረገችው ልትረሳው ትችላለች፣ አንተ ከ2 ዓመት በፊት ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ የተናገርከውን ነገር ግን አትረሳልህም።

6. አንዲት እርጉዝ ሴት ደጋግማ ምራቋን ከተፋች ሆዷ ውስጥ ያለው ህፃን ፈሱን እየፈሳ መሆኑን እወቅ።

ባሻዬ! ሴቶቹ ከላይ ያሉትን 6 ዕውነቶች አንብበው ጨርሰውታል። አንተ ግን ተራ ቁጥር 4 ላይ ቆመህ የቀኝ እጅ አውራ ጣትህን እያየህ ነው።

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch
2.1K viewsABᴜᴊᴀ, 13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 12:42:03 በእንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጎድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች በጣምም መጮህ ጀመረች ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለተ አልቻለም፡፡

አህያዋም ብዙ ያገለገለችና ያረጀች ስለሆነች እንዲሁም ሌሎች እንስሳትም ወደ ጉድጓዱ እንዳይገብበት በማሰብ ጉድጓዱ ውስጥ ሊቀብራት ወሰነ፡፡

ጎረቤቶቹንም አስተባብሮ ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ አህያዋ ይህን ስትመለከት እየቀበራት መሆኑነ ተረዳችና በሰቀቀን አለቀሰች፡፡ይሁን እንጂ አህያዋ አፈር ሲደፋባት አንድ ነገር ታደርግ ጀመር፡፡ አፈሩ በተደፋባት ቁጥር አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ጀመር፡፡በተደጋጋሚ ከሚደፋባት አፈር ላይ መቆምም ትጀምራለች፡፡

በሂደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች ከፍ እያለች በመጨረሻም ጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መውጣት ቻለች፡፡

በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት  የሞከሩት ሰዎች በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡ ሰው ያስባል ፈጣሪ ይፈፅማል!

@WubTarikoch
2.1K views _U_K_I, edited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 17:56:57 ባሻዬ!

ለ5ኛ ጊዜ ከቸርች ከተባረርኩ በኋላ በነጻ ዝውውር እንኳን የሚቀበለኝ ቸርች አጥቼ ነበር። ሰሞኑን ግን አንዱ ፓስተር ሊወስደኝ እያሽኮረመመኝ ነው። እስከዚያው ግን ለሁለት ሰዎች ምክር ያስተላለፍኩበትን ይህንን ጽሁፌን ልጋብዝህ።

1. አንድ የምናውቃት ሴት ለረጅም ጊዜ ባል ሳታገባ ቆየች። ይቺ ሴት በአንዱ ነብይ የውሸት ትንቢት ተጭበርብራ ዕድሜዋን እየቆጠረች ትገኛለች። ነብይ ነኝ ባዩ ከብዙ ዓመታት በፊት "አንቺ የምታገቢው ፓስተር መርዕድን (የሙሉ ወንጌል ፓስተር የነበረው) ነው ብሏት አንድም ቀን አይቷት የማያውቀውን ፓስተር መርዕድን ቁጭ ብላ ስትጠብቅ ፓስተር መርዕድ ሚስት አገባ።
በጣም የሚያሳዝነው ነገር ልጅቷ ፓስተር መርዕድ ሌላ ሚስት አግብቶም መጥቶ ያገባኛል ብላ አሁንም እየጠበቀች ነው።

አንቺ ሴት! መርዕድ የሚባል በስም ሞክሼ የሆነ ሰው መጥቶ ካላገባሽ በስተቀር ያኛውን መርዕድ በመጠበቅ ሳታገኚው ትሞታለሽ። ምክሬን ስሚ!

2. ባሻዬ! አንተ ደሞ "ሌሊቱን በከባድ ቅዠት አሳለፍኩ ፣ ክፉ መንፈስ አግኝቶኛል፣ ፓስተሬ ጋ ሄጄ እጁን ጭኖ ይፀልይልኝ" አትበለኝ። ሁሉም ቅዠት ከክፉ መንፈስ አይመጣም። እስቲ ብርድ ልብስህን አጥበህ ሞክረው። ያደፈ ብርድ ልብስ ሽታ ከባድ ቅዘት ያመጣል።

Tesfaye H.Mariam | @WubTarikoch
3.4K viewsABᴜᴊᴀ, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 21:47:57 "ውዴ ግን ትወደኛለህ?" አለችው ፊት ለፊቷ የተቀመጠውን ባሏን።
"ምን አይነት ጥያቄ ነው? ምስቴ አይደለሽ እንዴ ወድጄ ነው የምወድሽ?" ሲል መለሰላት የውስጡን ፍቅር በሚገልፅ እይታ እያስተዋላት።

"ምን ያህል ነው ምትወደኝ? እስኪ በቁጥር ግለፅልኝ!" አለችው።

"65%" ሲል መለሰላት። እጅጉን ተናደደች። ፊቷም ፍም መሰለ። እንዲህ ይመልስልኛል ብላ አልጠበቀችም ነበር።
"ፍቅሬን ለመግለፅ ቁጥሮች አቅም አይኖራቸውም!" ማለቱ እንኳን ቢቀር 100% አለማለቱ አንገበገባት።
"ምናልባት ከእኔ በላይ የሚወዳትን ሴት አግኝቶ ይሆን እንዴ?" ስትል ለመጀሪያ ጊዜ ባሏን በሌላ ሴት ጠረጠረችው።

"ለምን 65% ብቻ ሌላውን ለማን ሰጥተህ ነው?" ስትል ተቆጥታ ጠየቀችው Read more ...
1.1K views _U_K_I, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:16:00 አንድ ሰው በጣም የሚያፈቅራትን ፍቅረኛውን ይቀጥራታል ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ አንድ የተጠቀለለ ስጦታ ይሰጣታል ፍቅረኛውም ከፍታ ስታየው አሻንጉሊት ነው ወዲያውኑ አመናጭቃ ስጦታውን ትወረውረዋለች፡፡

እሱም በመናደድ ግን ረጋ ብሎ “ምነው ውዴ ለምን ወረወርሺው?”
ይላታል “ይህን የልጅ ስጦታህን አልወደድኩልህም!” ትለዋለች፡፡
ይናደድና አሻንጉሊቱን ከወደቀበት አንስቶ ጥሏት ይወጣል፡፡ በሚያስጠላና በሚገርም አጋጣሚ ጥሏት በወጣ ቅጽፈት አስፓልት ሲሻገር መኪና ገጭቶት ህይወቱ አለፈች የቀብሩም ቀን ልጅት አሻንጉሊቱን ይዛ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች፡፡

በለቅሶዋ ማሃልም ውድ ፍቅረኛዋን በአሻንጉሊቱ ምክንያት በማጣትዋ
በቁጭት አሻንጉሊቱን ጭምቅ ታደርገዋለች ወዲያውም ከሻንጉሊቱ “Will you marry me?” #ታገቢኛለሽ? የሚል ድምጽ አወጣ፡፡
ልጅቷ አልቻለችም መሬት ላይ ተዘረረች፡፡

ስትወድቅም ከአሻንጉሊቱ ኪስ ሁለት ቀለበቶች እና አንድ አጭር
ጽሑፍ ወደቀ ጽሑፉ እንዲህ ይላል. . . የኔ ፍቅር ለዘላለም ላልከዳሽ ልታመንልሽ በፍቅር ስም ቃል እገባልሻለሁ!!

@WubTarikoch
1.9K views _U_K_I, edited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ