Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ታሪኮች ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የሰርጥ አድራሻ: @wubtarikoch
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

ለውብና አጫጭር ታሪኮች እንዲሁም ወጎች ይቀላቀሉን!
#Like እንዲሁም #Forward ማድረግዎን አይርሱ!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-10-26 16:28:29 ጥቁሩ አንበሳ..!

ሳዲዮ ማኔ፡ "ለሚትዝ ጋር ለመፈራረም እና ፈተናን ለመጋፈጥ ፈረንሳይ የደረስኩባትን የመጀመሪያ ቀን አስታውሳለሁ። ከደረስኩበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ልምምድ ማድረግ ነበረብኝ ነገር ግን አሰልጣኙ እስኪደውልልኝ ድረስ ቤት ውስጥ እንድቆይ ነገረኝ።"

    "እኔም ፈረንሳይ መሄዴን ለእናቴ ደውዬ መንገር ብፈልግም ስልኬ ላይ ምንም ብር አልነበረኝም። ታዲያ በማግስቱ ሜትዝ ላይ ከነበሩ አንዳንድ ጓደኞቼ ጋር ካርድ ለመግዛት ሄድኩና ደወልኩላት። ሰላም እማ፣ ፈረንሳይ ነው ያለሁትም አልኳት።"

እሷም፦ “ምንድን የትኛው ፈረንሳይ ነው ምትለኝ” አለችኝ።

እኔም፦ "አላመንሽኝም እንዴ እማ? ፈረንሳይ አውሮፓ ነዋ" አልኳት።

"አውሮፓ? ምን ማለትህ ነው? ሴኔጋል አይደል እንዴ የምትኖረው፤ የአጎትህ ቤት መሆን አለብህ" አለችኝ።

እኔም፦ "አዎ። አሁን ግን አውሮፓ ውስጥ ነው ያለሁት አልኳት።… ይህ ለሷ እብደት ነበር። በጣም ተገርማ በየቀኑ እየደወለች እውነት እንደሆነ ትጠይቀኛለች። ስጫወት እንድታየኝ ብዬ ቲቪ እንድታይ እስከነገርኳት ቀን ድረስ አላመነችኝም ነበር። እኔም በመጨረሻም ህልሜ እውን መሆኑን ተረዳሁ።"

ከምንም ነገር የሚመጣ ምንም ነገር የለም። ለህልሞችህ መፋለም አለብህ።


Inah Abubeker | @WubTarikoch
5.6K viewsAʙᴜDɪ, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 20:55:06 ''የተፈታች ሴት ምን አልባት እጅግ መልካምና ጥሩ ሚስት ሆና፣ በማይሆን ወንድ እጅ ወድቃ ይሆናልና አመለካከታችንን ልናስተካከል ይገባል''

@WubTarikoch
5.4K viewsAʙᴜDɪ, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 08:40:21 Business Opportunity ለሚፈልጉ ሰዎች ብቻ ድንቅ የBusiness እድል ይዘንላችሁ መተናል!

ስኬት በህብረት !

ስራ በመፈለግ ላይ ኖት?

ለውድ ቤተሰባችን ትልቅ እድል ይዘን መጥተናል። አብረን በመስራት አብረን እንደግ...

ዘላቂ እና ቋሚ ቢዝነስ

ስራ አሎት
ተጨማሪ ስራ ይፈልጋሉ
አዲስ ተመራቂ ኖት
ተማሪነሽ/ነህ

ሁሉንም ያከተተ የስራ እድል በኢትዮጵያ።
''ስኬት ዝግጅት እና ዕድል የሚገናኙበት ቦታ ነው''።

"አንዳንድ ነገሮች አንድ ጊዜ ብቻ ይከሰታሉ''።

#ለሁላችሁም የቀረበ ትልቅ እድል እንዳያመልጦ


ስለስራው ሙሉ መረጃ ለማግኘት


@focus012345
@Focus012345
5.6K viewsAʙᴜDɪ, 05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 07:57:14 . አምራች እና ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ፡፡
በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ፡፡ ነጋዴው ጠዋት ጠዋት 300 ግራም ዳቦ ሲልክለት ገበሬው ደግሞ ማታ ማታ 300 ግራም ቅቤ ሊልክለት ተስማሙ፡፡

በዚህ መልኩ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ነጋዴ የቅቤ መጠን እየቀነሰ መሄዱን አየ፡፡ በመጨረሻም ሚዛን ላይ ሲያስቀምጠው 150 ግራም ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህም በጣም አዘነ፤ ተበሳጨም፡፡ ገበሬውንም አስጠራው፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲያዳምጡት አድርጎ ‹ከተስማማነው ውጭ የቅቤውን መጠን ለምን ቀነስከው?› ሲል ጠየቀው፡፡

ገበሬውም ‹እኔ ፈጽሞ አልቀነስኩትም› ሲል በአግራሞት መለሰ፡፡ ነጋዴውም ቅቤውን በሚዛን ለክቶ አሳየው፡፡ 150 ግራም ነው፡፡ ገበሬውም አዘነ፡፡ ‹እኔ ቤት ውስጥ የ300 ግራም መለኪያ የለኝም፡፡ አንተ ጠዋት ዳቦውን ስትልክልኝ በእጅ ሚዛኑ አንደኛው ሰሐን ላይ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ቅቤውን በሌላኛው ሚዛን አስቀምጠዋለሁ፡፡ ልክ ከዳቦው ጋር እኩል ሲመዝኑ በዕቃ አዘጋጅቼ እልክልሃለሁ› አለው፡፡ ወዲያውም ጠዋት የላከለትን ዳቦ አውጥቶ ሚዛኑ ላይ አስቀመጠው፡፡ ዳቦው 150 ግራም ነበር የሚመዝነው፡፡
@WubTarikoch
6.0K views _U_K_I, edited  04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 18:23:11 Success is like being pregnant. Everybody says congratulation but nobody knows how many times yo got f*cked !

@WubTarikoch
5.8K viewsAʙᴜDɪ, 15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 20:05:12 መለስተኛ ሳክስ "እሱኮ አፉ ነው እንጂ ሚናገረው ሆዱ ባዶ ነው"

@WubTarikoch
6.6K viewsABᴜᴊᴀ, 17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 16:43:37 አንብቧትማ..!

ሁለት የሚዋደዱ ጓደሞች ቁጭ ብለው ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛዉ ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን አለው። ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው...

ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን ? ከዚያም የታመመ ሰው በሆስፒታል ውስጥ የሞተውን ሰው ሬሳ ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና አለ"።

ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም? ሕይወት ምንድን ነው ? ህይወትን በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:

*1. ሆስፒታል *2. እስር ቤት *3. መቃበር
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ። በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ። በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌለው ትገነዘባለህ።

የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው። ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን። ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን አልሀምዱ ሊላህ!!

@WubTarikoch
6.9K viewsABᴜᴊᴀ, 13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-21 20:27:59 ቆሎ ሲመጣ ኦንቾሎኒ ብቻ ከሚለቅም ሰው ጋር እንዴት ነው ምንግባባው!

@WubTarikoch
6.5K viewsAʙᴜDɪ, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-21 19:10:03 ባል እና ሚስት..!

1. ሮናልዶ በሚስቱ ጭቅጭቅ የተነሳ ወደ ድሮው መልኩ ተመልሷል። ሰሞኑን ጨዋታው ሳያልቅ ወደ ቤቱ መመለሱ የገረመው ጋዜጠኛ ጠየቀው፣
" ሮናልዶ! ጨዋታው ሳይጠናቀቅ ቀድመህ ወደ ቤትህ ለምን ሄድክ?"

"ሚስቴ ጆርጂና ደውላ 'ካልተጫወትክ ወንበር ላይ ተቀምጠህ ምን ትሠራለህ? በ10 ደቂቃ ውስጥ ካልመጣህ ቤቱን እቆልፈዋለሁ' ስላለችኝ ነው''

2. ባል ከሚስቱ ኋላ እየተራመደ ሲሄዱ የሚስቱን መቀመጫ አየና "አንቺ! ቂጥሽ አድጎ አድጎ አሮጌ የልብስ ማጠቢያ ማሽን መስሎ የለም እንዴ?" ሲላት በጣም ተናዳ መልስ ሳትሰጠው ዝም አለችው።

ማታ ወደ ቤት ሲመለሱ አማረውና ጠጋ ብሎ ሊያሻሻት ሲሞክር እንዲህ አለችው "ትንሽ ልብስ ለማጠብ ብዬ አሮጌውን የልብስ ማጠቢያ ማሽን አላስነሳውም። በእጅህ ለማጠብ ሞክር"

3. የ70 ዓመት ሃብታም ሽማግሌ ሚስቱን እንዲህ አላት "እኔ የምልሽ? ወጣት ሴቶችን ሳሳድድ የማትናደጂው ለምንድነው?" ሚስት መለሰችለት ".. ለምን እናደዳለሁ? ውሾች እንኳን የማይነዱትን መኪና እየሮጡ ያሳድዱ የለ!" ባሻዬ! ሴቶችን ሥርዓት የሚያሲዝልን የአገር መሪ ጠፋ ማለት ነው?

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch
6.5K viewsABᴜᴊᴀ, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 21:06:12 የሆኑ ባልና ሚስት ወደ አንድ እንስሳት ማቆያ ፓርክ በአጋጣሚ ይሄዳሉ እንዳጋጣሚ አንድ ዝንጀሮ አብራው ካለች ጓደኛው ጋር እየተጫወተ የነበረ ዝንጀሮ አገኙ ።

የሰውየው ሚስት እንዲህ አለች  “ምን አይነት ፍቅር  ነው ! እንዲህም አይነት አለ እንዴ ? አለች በመገረም! "

ከዚያም ወዲያው ዞዞር ማለት እንደጀመሩ  ሌላ አንድ ወንድና ሴት አንበሳ ጎን ለጎን ተለያይተው ተቀምጠው  አዩና........ ሚስትየዋ  “ፍቅር የሌለበት ምን አሳዛኝ ትዕይንት ነው አለች በማዘን "

ይህን የሰማው ባልተቤቷ እንዲህ አላት
“ያን ድንጋይ ወደ አንበሳይው ወርውሪና ተመልከቺ አላት ” እሷም ድንጋዩን አንበሳው ላይ ስትወረውር አንበሳው አንበሳይቱን ለመከላከል ሲጮኽ  አየች

ባልየውም ከዝንጀሮዋ ጋርም ድገሚው አላት እሷም ለአንበሳው እንዳደረገችው ድንጋዩን ወደ ዝንጀሮው ስትጥል ወንዱ ዝንጀሮ ዘሎ  ዛፍ ላይ  ወጣና ራሱን  ለማዳን ሴቷን ጥሎ ሄደ ።

ባሏም እንዲህ አላት “በምታይው ነገር አትታለይ ያየሺው ሁሉ ፍቅር አይምሰልሽ ፡፡ ብዙ ጊዜ ባዶ ልብን ለመደበቅ ሲባል የሚያታልል ገጽታ ወይም አስመሳይነት ይኖራል ፡፡
@WubTarikoch
6.9K views _U_K_I, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ