Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ታሪኮች ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የሰርጥ አድራሻ: @wubtarikoch
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

ለውብና አጫጭር ታሪኮች እንዲሁም ወጎች ይቀላቀሉን!
#Like እንዲሁም #Forward ማድረግዎን አይርሱ!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-09-03 10:14:48 አንዱ ወጣት ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ሥራ አጥቶ ቤት ተቀምጧል። እናቱ ደሞ ልጃቸው ተምሮ ሥራ አለማግኘቱ አሳዝኗቸዋል። አንድ ቀን እናት ምሥር እየለቀሙ ልጁ ምሳ ሊበላ ወደ ቤት ሲመጣ፣

"ልጄ ዛሬስ ሥራ አላገኘህም?"

"በእኔ ሞያ ሥራ አይገኝም"

"ለመሆኑ የተመረቅኸው በምን ሙያ ነበር?"

"ጂኦሎጂ ነው እማዬ"

"ምን ማለት ነው እሱ?"

"የአፈር ምርምር፣ ጠቃሚውን ማዕድን ከማይጠቅመው አፈርና ድንጋይ መለየት ማለት ነው"

"ጎሽ! ታዲያ እዚህ ምሥር ውስጥ ያለውን አፈርና ድንጋይ ልቀምልኛ! እኔም አይኔ እየደከመ መጥቷል"

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch
1.2K viewsAʙᴜDɪ, 07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:18:22 ታሪክን ወደ ሁዋላና ወደፊት ..!

ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት • wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው ራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድር ለማምለጥ አይመችም፤ ከዚያም አልፎ፤ በንቁና አስፈሪ ዘበኞች ይጠበቃል፤ በአክሱም ዘመን ደብረዳሞ የልኡላን ማጎርያ ሆኖ አገልግሏል፤ የሸዋ ነገስታት በተራቸው ሲገዙ፤ ለዚህ ተግባር የመረጡት ቦታ፥ ወሎ ዛሬ ግሼን ማርያም የምትገኝበትን አምባ ነበር፤ የጎንደር ነገስታት በበኩላቸው ዘመዶቻቸውን “ወህኒ” ወደ ተባለ ስፍራ ማጋዝ ጀመሩ፤ ወህኒቤት የሚለውን ቃል የወረስነው ከዚህ ስፍራ ነው ፤ ወህኒ በመሰረቱ የፖለቲካ እስር ቤት ሲሆን ፥የመጀመርያው የፖለቲካ ወንጀል ከንጉስ መወለድ ነበር፤

ንጉሱ ድንገት ወራሹን ሳያሳውቅ በጦር ሜዳ ይገደላል እንበል፥ አንዱ የቤተመንግስት መኮንን ብድግ ይልና አንዱን ልኡል ከማጎርያ ቤት አውርዶ ዙፋን ላይ ያወጣዋል፤ ሌላው የጦር አዝማች , ደግሞ የኔን ምርጫ ካላነገስኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ይነሳል፤ ባንጋሾች መካከል የሚደረገው ፉክክር መዲናይቱን ባንዴ ወደ ፍርስራሽ እና ያስከሬን ክምር ይቀይራታል::

የቀድሞ ሰዎች እንዲህ አይነቱን ብሄራዊ አደጋ ለመቀነስ የፈጠሩት “ዘዴ “ የንጉስን ሞት መሰወር ነበር ፤ የንጉስ ሞት ቀርቶ ህመሙ እንኳ ለህዘብ ይፋ አይደረግም፤ በዘመነ መሳፍነት ጊዜ ፥ የየጁው ራስ አሊ ሲሞት ፤ አንድ አሳባቂ ( የዘመኑ ፓፓራዚ) ወሬውን አሾለከው፤ ወድያው የረጋው አገር መላወስ ጀመረ፤ ጉዳዩ ያሳሰባት አንዲት አልቃሽ እንዲህ ብላ ገጠመች፥
“ እሻ እሻ ነው እንጂ የእስራኤልን ሞት እንዲያልቅሰው አሊን ለምን ቀበሩት ።

“ እሻ እሻ “ ማለት ዝም በሉ ጸጥ በሉ ማለት ነው ፤ በዘመኑ የንጉስ ወገን ነን የሚሉ ሰዎች ዘራቸውን ከሰለሞን ስለሚመዝዙ “ እስራኤል “ በሚል የወል ስም ይታወቃሉ፤ በግጥሙ መስመር ላይ ያለው ህብረቃል “ እንዲያልቅሰው “ የሚል ነው፤ ሰሙ “ እንዲህ አልቅሰው “ ሲሆን ወርቁ “ ሰው እንዲተላለቅ” የሚል ትርጉም አለው ፤
ባጭሩ አልቃሺቱ፥

• ህዘብ እንዳይተላለቅ የንጉስ ሞት ይደበቅ “ ማለት ነው የፈለገችው ፤
ከጥንት እስከዛሬ አገረ-መንግስታችን የሚቆመው ባንድ ሰው ትከሻ ላይ ነው ፤ መሪ ሲታመም አገር ይታመማል፤ መሪ ሲሞት አገር በጥቂቱ ይሞታል፤ ይህንን መለወጥ የሚቻለው እንዴት ነው? የማይሞቱ ተቋሞችን በመገንባት ፤ የማይታመሙ ህጎችን በመመስረት? ወይስ ሌላ መላ አለ?

Bewketu Seyoum | @WubTarikoch
1.8K viewsAʙᴜDɪ, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:15:28 የሰሜኑን ጦርነት በቅርብ ርቀት መከታተል የምትፈልጉ ነጭ ነጯን ብቻ የምንዘግብበት ከስር ይቀላቀሉን
1.3K viewsAʙᴜDɪ, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:31:43 ያንተ ጓደኛ ይሄ ነው..?

ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል። አለቃውም 'መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህምበማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡

ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል፤አለቃውም 'ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤' በማለት ይወቅሰዋል፡፡

ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር ። አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር ፣ አለቃውም 'ምን አለህ?' ሲለው ወታደሩም እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ'፡፡ * እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁሉም ሠው ሲሸሽህ እሱ ግን የሚፈልግህ ነው!

Jabir  |  @WubTarikoch
2.1K viewsABᴜᴊᴀ, 14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:34:59 ምርጥ ባል..!?

ባለቤቴ ሴቶች ትምህርት ቤት ታስተምር ነበር። በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት አደርሳት ነበር። ትምህርት ቤቱ በር ላይ ስደርስ ከመኪናው ወርጄ በሩን ከፍቼላት ትወርዳለች። ይህ ነገር ታዲያ ት/ቤቱ ውስጥ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

የስራ ባልደረቦቿ ውይ ታድለሽ  ምን አይነት ፍቅር ነው፣ ምን አይነት እድለኛ ነሽ። ምነው እንዳንቺ ባል ባሎቻችን ቢሆኑ እያሉ ይቀኑባት ነበር። ተማሪዎቹ ሳይቀር ታድላ ይሏታል። ነገር ግን የመኪናው በር ተበላሽቶ ከውጭ እንጂ ከውስጥ እንደማይከፈት ከኔ ውጪ ሚያውቅ ሰው አልነበረም!

ባጭሩ አሁን እኔ ከአንድ ትምህርት ቤት የሶስት ሚስቶች ባል ነኝ። በሩን እስካሁን አላሰራሁትም። ይህ በር ለእኔ የእድል በር ሆኖልኛል።

achacher | @WubTarikoch
1.6K viewsAʙᴜDɪ, 16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:34:26 So የሚያጋጥምህ combination እንደሚከተለው ነው..!

1) ቆንጆ ትሆንና ደነዝ ትሆናለች

2) አስተዋይ ትሆንና ግን በጣም ኮስታራ ትሆናለች

3) ፍቅር አሰጣጥ ትችልና ከጎን ደግሞ ሌላ ደዋይ አላት

4) ትጉ ሰራተኛ ትሆንና ላንተ ጊዜ የላትም

5) ሀላፊነት የሚሰማት ትሆንና ግን ምንም ፍቅር አሰጣጥ አትችልም

6) ገንዘብ ይኖራትና ስድ ትሆናለች

7) ጨዋ ትሆንና ችስታ ትሆናለች

Ab Bella |  @WubTarikoch
3.5K viewsABᴜᴊᴀ, 08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:24:36 በሻዬ..!

የቴሌቪዥን መንፈሳዊ ፕሮግራም ላይ ከሌላ አገር የተኮረጀ ነገር አለ። "እጃችሁን ቴሌቪዥን ላይ አድርጋችሁ ፀልዩ" የሚለው ልማድ አይመቸኝም፡፡

ባልና ሚስት መንፈሳዊ ፕሮግራም በቲቪ እየተከታተሉ ነው። ፓስተሩ "ፈውስ የምትፈልጉ የፕሮግራማችን ተከታታዮች ምዕመናን አንድ እጃችሁን ቴሌቪዥኑ ላይ፣ አንድ እጃችሁን ደሞ
የሚያማችሁ ቦታ ላይ አድርጋችሁ ከእኔ ጋር ፀልዩ" አለ።

ሚስትየው አንድ እጇን ቲቪው ላይ ሌላውን እጇን ልቧ ላይ አደረገች። ባልየውም አንድ እጁን ቲቪው ላይ፣ ሌላውን እጁን ደግሞ እንትኑ ላይ አድርጎ መፀለይ ጀመረ።

ይህንን ያየችው ሚስቱ እንዲህ አለችው "ውዴ!ፓስተሩ የሚፀልየው እኮ ህመምን ለመፈወስ እንጂ ሙታንን ለማስነሳት አይደለም"

ተስፋዬ ኀ.ማርያም | @WubTarikoch
358 viewsABᴜᴊᴀ, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:28:15 ሁለት ወጣቶች መጠጥ ቤት ተገናኙ።
ሁለቱም እንደተያዩ እንዲህ ተባባሉ፣

"አባቴ ዶክተር መሆኑን ታውቃለህ?"
"የኔም አባት ዶክተር ነው"
"ዕወነትህን ነው? እኔ ደግሞ ዕድሜዬ 31 ነው"
"ይገርማል! የኔም ዕድሜ 31 ነው"
"በጣም ይገርማል! የአባቴ ስም አሻግሬ ይባላል"
"ዋው! የኔም አባት ስም አሻግሬ ነው"

ይህንን ከተነጋገሩ በኋላ ተቃቅፈው መሳቅና ማልቀስ ጀመሩ።
መጠጥ ቤት ውስጥ የነበረ አንድ ሰው አስተናጋጁን ጠራና ጠየቀው፣

"ልጆቹ ማናቸው?"
"የዶክተር አሻግሬ መንታ ልጆች ናቸው"
"ታዲያ ተቃቅፈው የሚስቁትና የሚያለቅሱት ለምንድነው?”
"ተዋቸው ባክህ! ሁሌ ሲሰክሩ እንዲህ ያደርጋቸዋል"

ባሻዬ! ምን እንድልህ ትፈልጋለህ? ... ምንም አልልህም።
ሰው ግን በመጠጥ ብቻ አይሰክርም። በሌላም በሌላም!!

ተስፋዬ ኀ.ማርያም | @WubTarikoch
3.3K viewsABᴜᴊᴀ, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 16:48:57 ባለፈው Taxi ውስጥ " ያገር ካስማ ሴት ነኝ እኔ " የሚለው ዘፈን ተከፍቶ አንዱ ከኋላየ ላንቃው እስኪሰነጠቅ እየጮኸ አብሮ ይዘፍናል

ቱ!

ኸረ ዘንድሮ ወንዱን ምን ነካው ይሸማቀቃል ብየ ዞር ብየ አየሁት እሱ እቴ የዘሪቱን ፓርት እየጮኸ ጭራሹን አደባለቀዉ ወይ ዘንድሮ አልኩ

የድሮ ወንድ በ3 የዲሽቃ ጥይት እግሩን ተመቶ እና ጥይቱ እግሩ ውስጥ ቀርቶ ምንም አይመስለውም ቅዝቃዜ ሲሰማው ብቻ እግሩ ውስጥ ጥይት እንዳለ ያስታውሳል

ዘንድሮ የቡና ሰዓቴ ሳልጠጣ አለፈብኝ ብሎ አልጋ ላይ የሚወድቀው ብዙ ነው አረ ተዉ ግን ተዉ

ጭራሽ አንዱ እናና እናናየ አንቺ እናናየ እያለ እንባውን ሲያፈሰው አይቼ ይሄማ እርግማን ነው አልኩኝ። አቤት አለቃቀስ!

አብርሽ መላኩ | @WubTarikoch
4.0K viewsABᴜᴊᴀ, edited  13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:55:09 የሰረቅኩት..!

ከቤት በጠዋት ነበር የወጣሁት 2 ሰዓት ላይ ለህክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ እንዳላረፍድ በማሰብ ነበር በጠዋት የወጣሁት ከቀጠሮዬ ቦታ ከሰዓቱ ቀድሜ 1:40 ላይ ደረስኩ :: እዛው ቆይቼ በሰዓቴ ህክምናዬን ካከናወንኩ በኋላ በዚሁ ለምን መንጃ ፈቃድ አላድስም ብዬ ወደ መንገድ ትራንስፖርት አመራሁ እዛ እንደደረስኩ ወረፋ ስለነበረው ወረፋ እየጠበቅኩ ስልኬን ፍለጋ ወደኪሴ ስገባ ስልኬን አጣሁት ።

ስልክ ድንገት ከኪስ ሲጠፋ ስሜቱን ታውቁታላችሁ መቼም ። የት እንደጣልኩት ማሰብ ጀመርኩ ከሆስፒታሉ ስወጣ ሰዓት ለማየት ኬሴ ውስጥ እንዳወጣሁት አስታወስኩ ስለዚህ ታክሲ ውስጥ ሻሻ እንደሰሩኝ ገባኝ ። ቀድሞ አዕምሮዬ ላይ የመጣው እና የቆጨኝ ነገር ሃይደርን ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ማስታወሻ ይሆናሉ ብዬ በየቀኑ የማነሳው ፎቶዎች መጥፋት ነበር ። በጣም የምወዳቸው ፎቶዎች ነበሩ ።

ወረፋዬን ጠብቄ መንጃ ፈቃዴን አድሼ ከመንገድ ትራንስፖርት ወጣሁ :: የሚገርመው ነገር የተፈጠረው የዛኔ ነው የሆነ ህፃን ልጅ ስልኩን እና የሆነ ወረቀት ሰጠኝ ስልኩን ሳየው የራሴ ስልክ ነው ። ከዛ ወረቀቱን ስከፍተው ስልኩን ለመስረቅ የተገደድኩት ልጄ ስለታመመብኝ ለአስቸኳይ ህክምና እና ለወተት ብር ስላስፈለገኝ ነበር ግን Wallpaper ላይ ካደረከው የልጅህ ፎቶ ላይ የፃፍከውን ፅሁፍ ሳየው የሆነ ስሜት ፈጠረብኝ እና ስልኩን መመለስ እንዳለብኝ ተሰማኝ ልጅ) ስላለህ ትረዳኛለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ በጣም ይቅርታ ልታግዘኝ ከፈለክ ግን በዚህ ስልክ ቁጥር ታገኘኛለህ ተብሎ ቁጥሩ ተፅፎበታል ።

በጣም አሳዘነኝ ምን አልባት እኔ በሱ ቦታ ብሆን ልጄ ቢታመምብኝ ለልጄ ቅድሚያ በመስጠት ስልኩን ሁሉ የምመልስለት አይመስለኝም ነበር ። በተፃፈው ቁጥር ደወልኩለት አነሳው ሰላም ካልኩት በኋላ ባለስልኩ መሆኔን ነገሬው እጄ ላይ ብር የለም ወተት የምትፈልግ ከሆነ ግን እቤት አለ ልላክልህ አልኩት እሺ አለኝ ስልኩን እና ወረቀቱን የሰጠኝ ልጅ አብሮኝ እንዲሄድ ነገረው ወደ ቤት እየሄድን አብሮኝ ከነበረው ልጅ ጋር ብዙ ነገሮችን አወራን ልጁ የምሩንም እንደሆነ ተረዳሁ ።

አሳዘነኝ ብችል እና እጄ ላይ ገንዘብ ቢኖረኝ ልጁን ባሳከምኩለት ግን ብር አልነበረኝም ። ቤት | እንደደረስን ለሃይደር የገዛሁት ግን አሁን ሃይደር እዚህ ስለሌለ የተቀመጡ 3 የቆርቆሮ ወተቶች ነበሩ እነሱን አብሮኝ ለመጣው ልጅ ሰጠሁለት እና ሄደ ። ቆይቶም ወተቶቹ እንደደረሱት ለሰራው ነገር ይቅርታ ጠይቆ እንደሚያመሰግነኝም ነግሮኝ እኔም አይዞህ ይሻለዋል ብዬው ስልኩን ዘጋሁት ።

ከመስረቁ በላይ ለልጄ ፍቅር Wallpaper ላይ በፃፍኩት ፅሁፍ ሀሳቡን ቀይሮ ስልኩን መመለሱ አስገረመኝ የልጅን ፍቅር ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነው ። ማጣት ከምንም በላይ የሚያመው ለልጅህ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት አቅም ሲያንስ ነው :: ስትወልድ የምትኖረው ለልጅህ ነው ለራስህ ማሰብ ታቆማለህ አባትነት ስሜቱ ጥልቅ ነው ለልጅህ ስትል የማይሆን ነገር ውስጥም ትገባለህ። አላህዬ ልለምንህ ማንም አባት ለልጁ ሲል አይቸግረው!! ልጁንም አላህ አፊያ ያድርግለት

የሃይደር | @WubTarikoch
4.4K viewsAʙᴜDɪ, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ