Get Mystery Box with random crypto!

በሻዬ..! የቴሌቪዥን መንፈሳዊ ፕሮግራም ላይ ከሌላ አገር የተኮረጀ ነገር አለ። 'እጃችሁን ቴሌቪ | ውብ ታሪኮች ®

በሻዬ..!

የቴሌቪዥን መንፈሳዊ ፕሮግራም ላይ ከሌላ አገር የተኮረጀ ነገር አለ። "እጃችሁን ቴሌቪዥን ላይ አድርጋችሁ ፀልዩ" የሚለው ልማድ አይመቸኝም፡፡

ባልና ሚስት መንፈሳዊ ፕሮግራም በቲቪ እየተከታተሉ ነው። ፓስተሩ "ፈውስ የምትፈልጉ የፕሮግራማችን ተከታታዮች ምዕመናን አንድ እጃችሁን ቴሌቪዥኑ ላይ፣ አንድ እጃችሁን ደሞ
የሚያማችሁ ቦታ ላይ አድርጋችሁ ከእኔ ጋር ፀልዩ" አለ።

ሚስትየው አንድ እጇን ቲቪው ላይ ሌላውን እጇን ልቧ ላይ አደረገች። ባልየውም አንድ እጁን ቲቪው ላይ፣ ሌላውን እጁን ደግሞ እንትኑ ላይ አድርጎ መፀለይ ጀመረ።

ይህንን ያየችው ሚስቱ እንዲህ አለችው "ውዴ!ፓስተሩ የሚፀልየው እኮ ህመምን ለመፈወስ እንጂ ሙታንን ለማስነሳት አይደለም"

ተስፋዬ ኀ.ማርያም | @WubTarikoch