Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት ወጣቶች መጠጥ ቤት ተገናኙ። ሁለቱም እንደተያዩ እንዲህ ተባባሉ፣ 'አባቴ ዶክ | ውብ ታሪኮች ®

ሁለት ወጣቶች መጠጥ ቤት ተገናኙ።
ሁለቱም እንደተያዩ እንዲህ ተባባሉ፣

"አባቴ ዶክተር መሆኑን ታውቃለህ?"
"የኔም አባት ዶክተር ነው"
"ዕወነትህን ነው? እኔ ደግሞ ዕድሜዬ 31 ነው"
"ይገርማል! የኔም ዕድሜ 31 ነው"
"በጣም ይገርማል! የአባቴ ስም አሻግሬ ይባላል"
"ዋው! የኔም አባት ስም አሻግሬ ነው"

ይህንን ከተነጋገሩ በኋላ ተቃቅፈው መሳቅና ማልቀስ ጀመሩ።
መጠጥ ቤት ውስጥ የነበረ አንድ ሰው አስተናጋጁን ጠራና ጠየቀው፣

"ልጆቹ ማናቸው?"
"የዶክተር አሻግሬ መንታ ልጆች ናቸው"
"ታዲያ ተቃቅፈው የሚስቁትና የሚያለቅሱት ለምንድነው?”
"ተዋቸው ባክህ! ሁሌ ሲሰክሩ እንዲህ ያደርጋቸዋል"

ባሻዬ! ምን እንድልህ ትፈልጋለህ? ... ምንም አልልህም።
ሰው ግን በመጠጥ ብቻ አይሰክርም። በሌላም በሌላም!!

ተስፋዬ ኀ.ማርያም | @WubTarikoch