Get Mystery Box with random crypto!

ባለፈው Taxi ውስጥ ' ያገር ካስማ ሴት ነኝ እኔ ' የሚለው ዘፈን ተከፍቶ አንዱ ከኋላየ ላንቃው | ውብ ታሪኮች ®

ባለፈው Taxi ውስጥ " ያገር ካስማ ሴት ነኝ እኔ " የሚለው ዘፈን ተከፍቶ አንዱ ከኋላየ ላንቃው እስኪሰነጠቅ እየጮኸ አብሮ ይዘፍናል

ቱ!

ኸረ ዘንድሮ ወንዱን ምን ነካው ይሸማቀቃል ብየ ዞር ብየ አየሁት እሱ እቴ የዘሪቱን ፓርት እየጮኸ ጭራሹን አደባለቀዉ ወይ ዘንድሮ አልኩ

የድሮ ወንድ በ3 የዲሽቃ ጥይት እግሩን ተመቶ እና ጥይቱ እግሩ ውስጥ ቀርቶ ምንም አይመስለውም ቅዝቃዜ ሲሰማው ብቻ እግሩ ውስጥ ጥይት እንዳለ ያስታውሳል

ዘንድሮ የቡና ሰዓቴ ሳልጠጣ አለፈብኝ ብሎ አልጋ ላይ የሚወድቀው ብዙ ነው አረ ተዉ ግን ተዉ

ጭራሽ አንዱ እናና እናናየ አንቺ እናናየ እያለ እንባውን ሲያፈሰው አይቼ ይሄማ እርግማን ነው አልኩኝ። አቤት አለቃቀስ!

አብርሽ መላኩ | @WubTarikoch