Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ታሪኮች ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የሰርጥ አድራሻ: @wubtarikoch
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

ለውብና አጫጭር ታሪኮች እንዲሁም ወጎች ይቀላቀሉን!
#Like እንዲሁም #Forward ማድረግዎን አይርሱ!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-10-20 20:48:55 ሰዎች 666 ነው እስከሚሉህ ድረስ ወጥረህ ስራ !

@WubTarikoch
5.9K viewsAʙᴜDɪ, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 20:14:15 ጓደኛ ማለት...!

1. እንደፈለክ በነፃነት የምትሰድበው
2. በጣም ጨንቆህ ስታማክረው እሱ የሚቀልድብህ
3. በጣም አስከፍቶህ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ በድጋሜ የሚሰድብህ ??

እንደዚህ አይነት ጓደኛ ካለህ.. እድለኛ ነህ

@WubTarikoch
7.1K viewsABᴜᴊᴀ, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 20:27:14 Smart MOM..!

ከልጇ ትምህርት ቤት ስልክ ተደውሎ ልጅሽ እያስቸገረን ነው ይሏታል.. እኔ ቤት ውስጥ ሲያስቸግረኝ ደውዬላችሁ  አውቃለሁ ወይ ?

@WubTarikoch
1.9K viewsABᴜᴊᴀ, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 08:49:56 "የኔልሰን ማንዴላ ..

☞ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው ። ስሙም ፒተር ይባላል ።

አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት
ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ ። ዘረኛው ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና ወፍ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" አላቸው ፣
ብልሁ ማንዴላም " አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ
እሄዳለሁ" ብሏቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ። በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል።

አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ ....
►"ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ ብር በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ ጥበብ ቢኖር በቅድሚያ የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ጠየቀው ፣
►ማንዴላም "ገንዘቡን አወስደዋለሁ" ብሎ መለሰለት ።
►ፕሮፌሰሩም በግልምጫ " አንተ ሞኝ ነህ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ አወስድ ነበር" አለው፣
►ማንዴላ ፈገግ እያለ" ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው ።

በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል ። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ ፣ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ " ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ፃፍልኝ"
@WubTarikoch
1.3K views _U_K_I, edited  05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 10:10:52 Can't wait to go to አረብ ሀገር and change my fb name to ፍቅርተ ሀገሯን ናፍቂ ባል ፈላጊ ተፍለቅላቂ ከመቂ በገመድ ታነቂ


@WubTarikoch
1.3K viewsAʙᴜDɪ, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 19:23:52 #የሕይወትህን_መሪ_አሳልፈህ_አትስጥ!

አንድ አሜሪካዊ ሰው ለንደን ውስጥ ወደሚገኝ ሬስቶራንት ገባ፤ እንደገባም ጥግ ላይ አንድ ህንዳዊ ተቀምጦ አየ።

እናም ወደ ባልኮኒው አመራና የኪስ ቦርሳውን በእጁ እንደ ያዘ፣ እንዲህ ብሎ ጮኸ
"አስተናጋጅ! እዚህ ሬስቶራንት ውስጥ ላሉ ተመጋቢዎች በሙሉ ምግብ ጋብዤያቸዋለሁ፤ እዛ ጥግ ካለው ጠቋራ ህንድ በስተቀር!"

ሆኖም ከመናደድ ይልቅ ህንዳዊው ድምጹን ከፍ አድርጎ፣ አሜሪካዊውን እየተመለከተ"አመሰግናለሁ" አለው።
ይህም ሰውዬውን አስቆጣው።

እናም በድጋሜ አሜሪካዊው የኪስ ቦርሳውን አወጣና ጮኸ "አስተናጋጅ፤ አሁን ለሁሉም ጠርሙስ ወይን እና ተጨማሪ ምግብ ጋብዣለሁ፤ እዛ ጥግ ካለው ጠቋራ ህንድ በስተቀር!"

እናም አስተናጋጁ ከሰውዬው ገንዘቡን ተቀብሎ ምግብ እና ወይኑን ለተስተናጋጆቹ ማቅረብ ጀመረ። አሁንም ህንዳዊው አልተናደደም፤ በድጋሜ በፈገግታ ተሞልቶ "አመሰግናለሁ" አለ፡፡

ይህም ይበልጥ አሜሪካዊውን አበሳጨው፤ እናም ባልኮኒው ላይ እንደተደገፈ ወደፊት አዘንብሎ አስተናጋጁን ጠየቀው
"ያ ሕንዳዊ ሰው ምንድን ነው ችግሩ? ከእርሱ በቀር ለሁሉም ሰው ምግብ እና መጠጥ ገዛሁ፤ ነገር ግን ከመናደድ ይልቅ _ እየሳቀ 'አመሰግናለሁ' ይለኛል፤ እብድ ነው?"

አስተናጋጁም በአሜሪካዊው ንግግር እየሳቀ እንዲህ አለው "አይ እብድ አይደለም ፤ እሱ የዚህ ሬስቶራንት ባለቤት ነው"

@WubTarikoch
1.6K views _U_K_I, 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 18:21:41 ቻይና..!

ፌስቡክ ላይ 4 ቻይናውያን አውሮፕላን ውስጥ የአንዱን ኢትዮጵያዊ ሞባይል ሿሿ እንደሠሩትና ሲፈተሹ ዕቃው መገኘቱን አነበብኩ። እኛ አገር የሚመጡ ቻይናውያን ዕቃ ብቻ ሳይሆን ሰውን ከነነፍሱ ሿሿ ይሠራሉ።

አንዱ ቻይናዊ አንዷን ኢትዮጵያዊ ተዋወቃት። አንድ ቀን ቻይናው ልጅቷን ቤቱ ይወስዳትና ግንኙነት ማድረግ ይጀምራሉ። ከ10 ደቂቃ በኋላ ቻይናው ጨርሶ ተነስቶ ወደ መስኮቱ ይሄድና እጁን ዘርግቶ ከተንጠራራ በኋላ አልጋ ሥር ይገባል።

ቻይናው ወዲያው ከአልጋው ሥር ይወጣና አሁንም ከልጅቷ ጋር ይተኛና ሲጨርስ አሁንም ወደ መስኮቱ ሄዶ ከተንጠራራ በኋላ አልጋ ሥር ይገባል። ሰውዬው ወዲያው ከአልጋ ሥር እየወጣ ለ5 ተከታታይ ጊዜ እንዲሁ ያደርጋል። በዚህ ጉዳይ ልጅቷ ግራ ገብቷት ከአልጋው ላይ ወርዳ አልጋ ሥር ስትመለከት 5 ተመሳሳይ ቻይናውያን ራቁታቸውን አገኘቻቸው። ባሻዬ!1 ለ 5 አደረጃጀትን ወደ ኢትዮጵያ ያመጣችው ቻይና ነች።

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch
2.1K viewsABᴜᴊᴀ, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 18:39:18 "ምናለበት ብታስቀድመን! መኪና ይዘህ አይደል?" ይሉታል..  "እናንተን ለመቅደም መስሎኝ መኪና የገዛሁት!!

@WubTarikoch
2.1K viewsABᴜᴊᴀ, 15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 15:05:40 ህይወታችንና የገደል ማሚቶው...

አንድ ልጅ ከአባቱ ጋር ወደ አንድ ተራራ ላይ እየተንሸራሸሩ ነበር፡፡ ድንገት ልጁ አንሽራተተውና ሲወድቅ “እካካካካካ!” ብሎ ጮኸ፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ተራራውም “እካካካካካ!” ሲል ደገመለት፡፡ “ማነህ አንተ?” ሲል ጠየቀ ልጁ በጉጉት፡፡ “ማነህ አንተ?” አለው ተራራውም መልሶ፡፡ “አደንቅሃለሁ!” ሲል ጮኸ ልጁ፡፡ ተራራውም መልሶ “አደንቅሃለሁ” አለ፡፡ በመልሱ የተናደደው ልጅ “ፈሪ!” ብሎ አንባረቀ፡፡ ተራራውም “ፈሪ!” ብሎ ጮኸበት፡፡ .

ግራ የገባው ልጅ ወደ አባቱ ዘወር ብሎ “ምን እየተካሄደ ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ አባትየው ፈገግ ብሎ “ልጄ! አድምጥ” አለውና “አሸናፊ ነህ!” አለ ጮክ ብሎ፡፡ ከተራራው ውስጥ የሚሰማውም ድምጽ መልሶ “አሸናፊ ነህ!” አለ፡፡ ልጁ ምንም ነገር ባይገባውም በአድናቆት ተዋጠ፡፡ አባትየው እንዲህ ሲል ምሥጢሩን ገለፀለት፤ “ሰዎች የገደል ማሚቶ ይሉታል፤ እሱ ግን ሕይወት ነው። አንተ የምትናገረውን ወይም የምታደርገውን ነገር መልሶ ላንተው ይሰጥሃል። ሕይወታችን በቀጥታ የድርጊታችን ነፀብራቅ ነው፡፡

በዚህች ዓለም ላይ ሰዎች ብዙ ፍቅር እንዲሰጡህ ከፈለግህ የራስህን ልብ በሰዎቹ ፍቅር ሙላው። የሥራ ባልደረቦችህ በጥራት እንዲሰሩልህ ከፈለግህ አንተ በጥራት ስትሰራ ይዩህ፡ : ይህ እውነታ በሁሉም የሕይወት ገጽታዎች ውስጥ በማንኛውም ነገር ላይ ይሰራል። ሕይወት የሰጠሃትን ማንኛውንም ነገር መልሳ ትሰጥሃለች” አለው፡፡ ሕይወትህ አጋጣሚ ሳይሆን የራስህ ነፀብራቅ ነው!!

ዶ/ር አቡሽ አያሌው | @WubTarikoch
706 views _U_K_I, edited  12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 17:47:35 የብረት ሙታንታ..!

ድሮ ጥንት... ድሮ አረቦች ግመሎቻቸውን ይዘው ለንግድ ሲጓዙ ምናልባት ሚስቶቻቸው ከሌላ ወንድ ጋር ይማግጣሉ ብለው ስለሚያስቡ የብረት ሙታንታ አሠርተው ሚስቶቻቸው ላይ ያጠልቁባቸው ነበር። የብረት ሙታንታው ሽንት ለመሽናት ብቻ ትንሽዬ ክፍተት ይደረግበትና ይቆለፋል።

ባልዬው ክፉ ከሆነ  ደሞ በሽንት መሽኛው በኩል ባለው ስንጥቅ ቦታ በዚግ ዛግ ቅርጽ እንደ መጋዝ ሹል አድርጎ ከቆለፈው በኋላ ቁልፉን ይዞ ለብዙ ወራት ቆይቶ ሲመለስ ሚስቱን ከብረት ሙታንታው እሥር ቤት አውጥቶ በሽቶና በከርቤ እንድትታጠብ ይደረጋል። ከሁሉም የከፋ የሚሆነው ባልየው በሄደበት ከሞተ ወይም ቁልፉ ከጠፋበት ነው። በዚህን ጊዜ ሴትየዋን ቶሮኖ ቤት ማመላለስ የግድ ይሆናል።

ባሻዬ! ለኔ የትግራይ ህዝብ በዚህ የብረት ሙታንታ የተቆለፈበት ይመስለኛል። አብዮታዊ ዴሞክራሲ የተባለ የብረት ሙታንታ። መስመርና ኃይልና የተባለ የብረት ሙታንታ። የብረት ሙታንታው ያለው ቁልፍ አንድ ብቻ ሲሆን፣ መለስ ሲሞት ለእነ ደብረጺዮን አስረክቦ ሄደ።

የትግራይ ህዝብ በዚህ እሥር ቤት ነፃ የሚያወጣውን ቁልፍ ታግሎ ከነ ጌታቸው ረዳ ሊነጥቅ ይገባዋል። "እነ ጌቾ ሆይ! ለድርድር ወደ ደቡብ አፍሪካ ትሄዳላችሁ ተብሏል። እዚያ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅምና ቁልፉን ለትግራይ ህዝብ አስረክባችሁ ሂዱ!"

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch
873 viewsAʙᴜDɪ, 14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ