Get Mystery Box with random crypto!

ህይወታችንና የገደል ማሚቶው... አንድ ልጅ ከአባቱ ጋር ወደ አንድ ተራራ ላይ እየተንሸራሸሩ ነበ | ውብ ታሪኮች ®

ህይወታችንና የገደል ማሚቶው...

አንድ ልጅ ከአባቱ ጋር ወደ አንድ ተራራ ላይ እየተንሸራሸሩ ነበር፡፡ ድንገት ልጁ አንሽራተተውና ሲወድቅ “እካካካካካ!” ብሎ ጮኸ፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ተራራውም “እካካካካካ!” ሲል ደገመለት፡፡ “ማነህ አንተ?” ሲል ጠየቀ ልጁ በጉጉት፡፡ “ማነህ አንተ?” አለው ተራራውም መልሶ፡፡ “አደንቅሃለሁ!” ሲል ጮኸ ልጁ፡፡ ተራራውም መልሶ “አደንቅሃለሁ” አለ፡፡ በመልሱ የተናደደው ልጅ “ፈሪ!” ብሎ አንባረቀ፡፡ ተራራውም “ፈሪ!” ብሎ ጮኸበት፡፡ .

ግራ የገባው ልጅ ወደ አባቱ ዘወር ብሎ “ምን እየተካሄደ ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ አባትየው ፈገግ ብሎ “ልጄ! አድምጥ” አለውና “አሸናፊ ነህ!” አለ ጮክ ብሎ፡፡ ከተራራው ውስጥ የሚሰማውም ድምጽ መልሶ “አሸናፊ ነህ!” አለ፡፡ ልጁ ምንም ነገር ባይገባውም በአድናቆት ተዋጠ፡፡ አባትየው እንዲህ ሲል ምሥጢሩን ገለፀለት፤ “ሰዎች የገደል ማሚቶ ይሉታል፤ እሱ ግን ሕይወት ነው። አንተ የምትናገረውን ወይም የምታደርገውን ነገር መልሶ ላንተው ይሰጥሃል። ሕይወታችን በቀጥታ የድርጊታችን ነፀብራቅ ነው፡፡

በዚህች ዓለም ላይ ሰዎች ብዙ ፍቅር እንዲሰጡህ ከፈለግህ የራስህን ልብ በሰዎቹ ፍቅር ሙላው። የሥራ ባልደረቦችህ በጥራት እንዲሰሩልህ ከፈለግህ አንተ በጥራት ስትሰራ ይዩህ፡ : ይህ እውነታ በሁሉም የሕይወት ገጽታዎች ውስጥ በማንኛውም ነገር ላይ ይሰራል። ሕይወት የሰጠሃትን ማንኛውንም ነገር መልሳ ትሰጥሃለች” አለው፡፡ ሕይወትህ አጋጣሚ ሳይሆን የራስህ ነፀብራቅ ነው!!

ዶ/ር አቡሽ አያሌው | @WubTarikoch