Get Mystery Box with random crypto!

የብረት ሙታንታ..! ድሮ ጥንት... ድሮ አረቦች ግመሎቻቸውን ይዘው ለንግድ ሲጓዙ ምናልባት ሚስቶ | ውብ ታሪኮች ®

የብረት ሙታንታ..!

ድሮ ጥንት... ድሮ አረቦች ግመሎቻቸውን ይዘው ለንግድ ሲጓዙ ምናልባት ሚስቶቻቸው ከሌላ ወንድ ጋር ይማግጣሉ ብለው ስለሚያስቡ የብረት ሙታንታ አሠርተው ሚስቶቻቸው ላይ ያጠልቁባቸው ነበር። የብረት ሙታንታው ሽንት ለመሽናት ብቻ ትንሽዬ ክፍተት ይደረግበትና ይቆለፋል።

ባልዬው ክፉ ከሆነ  ደሞ በሽንት መሽኛው በኩል ባለው ስንጥቅ ቦታ በዚግ ዛግ ቅርጽ እንደ መጋዝ ሹል አድርጎ ከቆለፈው በኋላ ቁልፉን ይዞ ለብዙ ወራት ቆይቶ ሲመለስ ሚስቱን ከብረት ሙታንታው እሥር ቤት አውጥቶ በሽቶና በከርቤ እንድትታጠብ ይደረጋል። ከሁሉም የከፋ የሚሆነው ባልየው በሄደበት ከሞተ ወይም ቁልፉ ከጠፋበት ነው። በዚህን ጊዜ ሴትየዋን ቶሮኖ ቤት ማመላለስ የግድ ይሆናል።

ባሻዬ! ለኔ የትግራይ ህዝብ በዚህ የብረት ሙታንታ የተቆለፈበት ይመስለኛል። አብዮታዊ ዴሞክራሲ የተባለ የብረት ሙታንታ። መስመርና ኃይልና የተባለ የብረት ሙታንታ። የብረት ሙታንታው ያለው ቁልፍ አንድ ብቻ ሲሆን፣ መለስ ሲሞት ለእነ ደብረጺዮን አስረክቦ ሄደ።

የትግራይ ህዝብ በዚህ እሥር ቤት ነፃ የሚያወጣውን ቁልፍ ታግሎ ከነ ጌታቸው ረዳ ሊነጥቅ ይገባዋል። "እነ ጌቾ ሆይ! ለድርድር ወደ ደቡብ አፍሪካ ትሄዳላችሁ ተብሏል። እዚያ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅምና ቁልፉን ለትግራይ ህዝብ አስረክባችሁ ሂዱ!"

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch