Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ታሪኮች ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የሰርጥ አድራሻ: @wubtarikoch
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

ለውብና አጫጭር ታሪኮች እንዲሁም ወጎች ይቀላቀሉን!
#Like እንዲሁም #Forward ማድረግዎን አይርሱ!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-09-18 19:23:13 መጠንከር አለብህ ..!

ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ አንተ መክበድ አለብህ፤ ሰዎች ለምን አልተረዱኝም ብለህ አትዘን በተግባር ማን እንደሆንክ አሳያቸው! አለም ለጠንካሮች ታዳላለች፤ ሰዎችም ቢሆኑ ደካማ አይወዱም።

ከሁሉ በላይ ግን ለራስህ ስትል ቆራጥ መሆን አለብህ ምክንያቱም በምንም ነገር ውስጥ ብታልፍ የማይጥል ፈጣሪና ወድቆ የማይቀር ማንነት ስላለህ!

InspireEthiopia | @WubTarikoch
4.7K viewsAʙᴜDɪ, 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 12:18:20 ከንቱ ተስፋ..!

ቀዝቃዛ በሆነ ምሽት አንድ ቢሊየነር ከቤት ውጭ አንድ ድሃ ሽማግሌ  አገኘ። ‹በዚ ቅዝቃዜ ውጪ ላይ ኮት እንኳን አለበስክም አይበርድህም  እንዴ› ብሎ ጠየቀው። አዛውንቱም "ኮት የለኝም ነገር ግን ለምጄዋለሁ ሲል መለሰለት። ቢሊየነሩም "ቆይ ጠብቀኝ ወደ ቤቴ ሄጄ ኮት አመጣልሀለው" ብሎት ሄደ።

ድሃው ሰውም በጣም ተደስቶ እጠብቅሀለው አለው። ቢሊየነሩ ወደ ቤቱ ደረሰ ግን በስራ ተጠምዶ ስለ ምስኪኑ ሰው ረሳ። በማግስቱ ጠዋት ድነገት ምስኪኑን አዛውንት አስታወሰና ሊፈልገው ወጣ ነገር ግን  ምስኪኑን አዛውንት በቅዝቃዜው ሞቶ አገኘው።

ምስኪኑ አዛውንትም እንዲህ የሚል ደብዳቤ አስቀምጦለት ነበር  "ሞቅ ያለ ልብስ ሳላገኝ ቅዝቃዜውን ለመቋቋም የሚያስችል የአእምሮ ጥንካሬ ነበረኝ, ነገር ግን እንደምትረዳኝ ቃል ስትገባ, ቃልህ የአእምሮ ኃይሌን ገደለው!"

@WubTarikoch
5.7K views _U_K_I, edited  09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 22:03:05 #ተማሪ - teacher ጥያቄ መጠየቅ ይቻላል

#አስተማሪ - ይቻላል ጠይቀኝ

#ተማሪ - teacher ማር እግር አለው እንዴ

#አስተማሪ - የለውም ለምን ጠየከኝ

#ተማሪ - አይ አባዬኮ ማታ የኔ ማር እግርሽን ክፈች ሲል ሰምቼ ነው

@WubTarikoch
5.6K views _U_K_I, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 20:21:41 እረፍት በዘዴ..!

ሁለት የፋብሪካ ሰራተኞች እያወሩ ነው ።

ሳራ: ዛሬ አለቃዬን በዚም በዛም ብዬ ማስፈቀድ አለብኝ ።

አሊ : እንዴት አርገሽ?
ሳራ : ዝም ብለህ የማረገውን ተመልከት

ሳራ ኮርኒሱ ላይ ወጥታ ተንጠለጠለች ( ልክ እንደ አምፖል) በዚህ መሀል አለቃዋ ገባ ።
አለቃ: እንዴ!!! ምን እየሰራሽ ነው ሳራ ?

ሳራ : አምፖል ለመሆን እየሞከርኩ ነው ።

አለቃ : በይ በይ!!! ቀኑን ሙሉ ስትሰሪ በመዋልሽ አእምሮሽ ልክ አይመስለኝም ፤ የስራው ጫና ነው መሰለኝ ። ወደ ቤት ሄደሽ እረፍት አርጊ ሲላት.. አሊም ተከትሏት ወጣ

አለቃ: አንተ ደግሞ ወዴት ነህ?

አሊ : በጭለማ መስራት አልችልም! ብሎት ተያይዘው ወጡ ።

@WubTarikoch
5.7K viewsAʙᴜDɪ, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 16:40:15 «ቃም! አለበለዝያ እንቅልፍ ያስቸግርሃል!»

«ቢቀርብኝ ይሻላል!»

«ፈጣሪ የፈጠረውን እምቢ የምትል አንተ ማነህ?»

«ፈጣሪ ጫትን ቢፈጥርም ቃሙ ያለ ግን አይመስለኝም!»

«ታዲያ ቤት እንድንጠርግበት የተከለው ይመስልሃል?»

ከመፅሐፍት አምድ | @WubTarikoch
6.0K viewsABᴜᴊᴀ, 13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 12:40:17 አባት የሚጠባ ልጁን እንዲጠብቅለት ከውሻ ጋር ትቶ ወደ አደን ይሄዳል ከአደን ሲመለስ ውሻው በደም ተጨማልቆ በሩ ላይ አገኘው ውሻው የተጨማለቀበትን ደም ሲምለከት ልጁን በልቶ እንደሆነ ገመተ ልክ ሁላችንም እንደምንገምት በጣም ተናዶ ለአደን ይዞት የወጣውን መሳሪያ አቀባበለና ውሻውን የጥይት እሩምታ አወረደበት ።

የተረፈውን የልጁን አካል ለማየት ወደ ውስጥ እየሮጠ ገባ ነገር ግን ልጁ አንዳችም መጥፎ ነገር አላገኘውም ይልቁንስ ከፊቱ ለፊቱ በደም የተጨማለቀ ተኩላ ሞቶ ተመለከተ .. የእድሜ ልክ ፀፀት ። አይተህ አትፍረድ አዕምሮህንም ለፍርድ ሹመት ስጥ።


ከፌስቡክ መንደር | @WubTarikoch
5.8K views _U_K_I, edited  09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 17:37:51 አስገራሚ ዕውነቶች ስለ ሴቶች..!

1. ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በእንቅልፋቸው ይቃዣሉ (ወንዶች ተጠንቀቁ)

2. ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ብቻቸውን ሲሆኑ በፈሳቸው ይዝናናሉ ( ማነሽ! ቴፑን ክፈችው) |

3. አንዲት ሴት ከፈለገች 69 ጊዜ መውለድ ትችላለች (አርብቶ አደር) |

4. ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ብዙ የቀለም ዓይነቶችን መለየት ይችላሉ (ከጌታሁን ሄራሞ አይበልጡም)

5. ረጃጅም ሴቶች በካንሠር የመያዝ ዕድል አላቸው (ሚስቴ የለችበትም)

6. የሴቶች የልብ ምት ከወንዶች ይበልጣል (እንኳን አወቅን)

7. ሴቶች በቀን 20 ሺህ ቃላት ይናገራሉ። በዚህም ከወንዶች በ13 ሺህ ቃላት ይበልጣሉ (የኤሌክትሪክ የልብስ መስፊያ ሲንጀር)

8. በዓለም ያሉት የመጀመሪያ 20ዎቹ ሴት ሃብታሞች ሃብታቸውን ያገኙት ከባሎቻቸው ወይም ከአባቶቻቸው ወርሰው ነው (ምስኪን ወንዶች) |

9. ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ፈጥነው ይሰክራሉ። (አንዳንድ ቀዳዳ በርሜሎች ግን አሉ)

10. ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በአንድ ጊዜ ብዙ ሥራ ይሠራሉ (አልቻልናቸውም)

11. የሴት የአንጎል መጠን ከወንድ የአንጎል መጠን በ9% ያንሳል (ደጋግመን ስንናገር የሚሰማን ጠፋ እንጂ)

12. የሴቶች ዓይን በደቂቃ 19 ጊዜ ሲርገበገብ የወንዶች ግን 11 ጊዜ ይርገበገባል(ቀዥቃዦች)

13. ሴቶች ከወንዶች ይበልጥ የማሽተት ችሎታ አላቸው (ባሻዬ! ተጠንቀቅ ሃሳብህንም ቢሆን በማሽተት ያውቁታል)

14. አንዲት ሴት በህይወት ዘመኗ 1.8 ኪሎ ግራም ሊፕስቲክ ትውጣለች (ወንዶች ተጠንቀቁ)

15. ሴቶች በተፈጥሮአቸው ዝቅተኛ የሆነ ድምጽ የመስማት ፀጋ ስለተሰጣቸው ልጆቻቸው ሌላ ክፍል ተኝተው እንኳን ትንፋቸውን የማዳመጥ ችሎታ አላቸው (ክብር ለእናቶች። ባሻዬ! አንተ ግን እየተገላበጥክ አንኮራፋ)

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch
6.2K viewsAʙᴜDɪ, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 20:58:00 አንድ ሰው በእሱ ላይ ሁለት ነገሮች እስካልተሟሉ ድረስ ሙሉ (ብቁ) ሰው አይባልም።

1ኛው; በሰዎች እጅ ካለ ነገር የተብቃቃ (ጥቡቅ) እስከ ሚሆን እና

2ኛው; ከሰዎች በሚደርስበት ነገር ቸልተኛ (ባላየ የሚያልፍ) እስከ ሚሆን ነው።
  
አዩብ አል-ሰህቲያኒ | @WubTarikoch
6.1K viewsAʙᴜDɪ, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 17:01:55 አንድ ሆቴል ለጋ ጥብስ አዝዤ "ቀይ ስጋ ብቻ ይሁን... ጮማ እንዳይገባበት" ስለው .. "ይለቀም?" አለኝ...

"አይ መጀመሪያም እንዳይገባበት" ስለው .. "እንደዛ ማድረግ አልችልም ተቀላቅሎ ተመዝኖ ነው የሚመጣው አለኝ"... ከዛ ድጋሚ  "ይለቀም?" ብሎ ጠየቀኝ..

ከዛ እኔም ከጮማው ጋር ሊለጠፋ የሚችሉትን ቀያይ ስጋዎች አስቤ ... " አይ ተወው በቃ፣ እዚሁ እራሴ እለቅመዋለው" አልኩት!

Mahlet | @WubTarikoch
1.7K viewsAʙᴜDɪ, 14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 15:59:05 Maths ትምህርት እና square ደብተር ያላቸው ግንኙነት ሳይገባኝ ይሄው 2015 ሊመጣ ነው!

አመለወርቅ | @WubTarikoch
546 viewsABᴜᴊᴀ, 12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ