Get Mystery Box with random crypto!

እረፍት በዘዴ..! ሁለት የፋብሪካ ሰራተኞች እያወሩ ነው ። ሳራ: ዛሬ አለቃዬን በዚም በዛም | ውብ ታሪኮች ®

እረፍት በዘዴ..!

ሁለት የፋብሪካ ሰራተኞች እያወሩ ነው ።

ሳራ: ዛሬ አለቃዬን በዚም በዛም ብዬ ማስፈቀድ አለብኝ ።

አሊ : እንዴት አርገሽ?
ሳራ : ዝም ብለህ የማረገውን ተመልከት

ሳራ ኮርኒሱ ላይ ወጥታ ተንጠለጠለች ( ልክ እንደ አምፖል) በዚህ መሀል አለቃዋ ገባ ።
አለቃ: እንዴ!!! ምን እየሰራሽ ነው ሳራ ?

ሳራ : አምፖል ለመሆን እየሞከርኩ ነው ።

አለቃ : በይ በይ!!! ቀኑን ሙሉ ስትሰሪ በመዋልሽ አእምሮሽ ልክ አይመስለኝም ፤ የስራው ጫና ነው መሰለኝ ። ወደ ቤት ሄደሽ እረፍት አርጊ ሲላት.. አሊም ተከትሏት ወጣ

አለቃ: አንተ ደግሞ ወዴት ነህ?

አሊ : በጭለማ መስራት አልችልም! ብሎት ተያይዘው ወጡ ።

@WubTarikoch