Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ታሪኮች ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubtarikoch — ውብ ታሪኮች ®
የሰርጥ አድራሻ: @wubtarikoch
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

ለውብና አጫጭር ታሪኮች እንዲሁም ወጎች ይቀላቀሉን!
#Like እንዲሁም #Forward ማድረግዎን አይርሱ!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-09-27 14:32:18 ሁለት ወጣቶች በተጋበቡት ዕለት ምሽት ወደ ማረፊያቸው ገብተው ለመተኛት እየተዘጋጁ ነበር። ሙሽሪት መታጠቢያ ክፍል ውስጥ እንዳለች

"እባክህ መብራቱን አጥፋው" አለች

"በቅድሚያ ከዚያ መውጣት አለብሽ። አሁን መብራቱን ባጠፋው በጨለማው ውስጥ ስትመጪ ልትወድቂ ትችያለሽ'' አለ።

"የምልህን ስማ! መብራቱን አጥፋው!"

"ችግሩ መብራቱን ማጥፋቱ አይደለም። እኔም ራሴ መብራቱ እስኪጠፋ ቸኩያለው ሃሳቤ ግን ላንቺ ነው"

"ለምን ቸኮልክ?!" ሙሽሪት ቱግ አለች።

"ዕውነቱን ለመናገር ከዚህ የተሻለ ወቅት አላገኝም። ግራ እግሬ አርቴፊሻል ነው።" አለ ሙሽራው።

"መብራቱን እንድታጠፋው የፈለኩት አርቴፊሻል ጡቶቼ እንዳይታዩብኝ ስለፈለኩ ነው። ደረቴ ባዶ ልሙጥ ነው"

"ወይ ፈጣሪዬ!... ምንጊዜም ከወርቅ የተሰራች አውሮፕላን ደረትሽ ላይ የምታደርጊው ለዚህ ነው ለካ?? ደህና ሜዳ ላይ አሳርፈቻታል። ሌላም ችግር ካለብሽ አሁኑኑ ብሰማው ይሻላል። ከዚህ በኋላ መደንገጥ አልፈልግም"

"እሺ እነግርሀለው....የግራ አይኔ አርቴፊሻል ነው"

"በቃ የኔም ጥርሶች በሙሉ አርቴፊሻል ናቸው" አለ ሙሽራው።

"እባክህ እኔም ፍንክች አልልም። የኔም ፀጉር አርቴፊሻል ነው። በራስ ቅሌ ላይ አንዲት ፀጉር የለችም። ያለው ዊግ ብቻ ነው"


@WubTarikoch
1.5K views _U_K_I, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 15:04:11 ኳስና ሴት..!

ስለኳስ የማታውቅ ሴት ጋር ሁነህ ጨዋታ ስታይ 

Her:"የትኞቹ ቡድኖች ናቸው የሚጫወቱት?"
Him: "ማን ሲቲ ከ ሊቨርፑል"
Her: "እኔ ሊቨርፑል እወዳለሁ"

Him: "አዎ ጥሩ ቡድን ነው"

Her: " ሮናልዶ እየተጫወተ ነው?"
Him:  "ለሁለቱም አይጫወትም"
Her: "እሺ......ውዴ ግን ያኛው ክሪስ ብራውን ነው?"
Him: "አይ......እሱማ ማኔ ነው"
Her: "አሺ.....ግን ይመሳሰላሉ.... ቢጫው ካርድ ለምንድነው?”
Him: "ማስጠንቀቂያ ነው ለተጫዋቹ"

* ከደቂቃዎች በኋላ ስተርሊንግ አስቆጠረ

Her: "ማኔ ነው አይደል ያስቆጠረው?"
Him: "አይደለም[እየተረጋጋ]...ስቴርሊንግ ነው ለማን ሲቲ"
Her: "እንደት? ሊቨርፑል እኮ ነበር ማስቆጠር የነበረበት"......"ቀዩ ካርድስ ለምንድነው?”

Him: " ተጫዋቹ በሰራው ጥፋት ከሜዳ እንዲወጣ ትዕዛዝ ነው"
Her:, "ታዲያ ካሁን አሰልጣኝ አይሆንም?" 
Him: "አአአአአአህ.... አይደለምምምም"
Her: "አሃሃ... ካርዶቹ ልክ እንደ ትራፊክ መብራት ቢጫ ለማስጠንቀቂያ እና ቀይ ለአደጋ ናቸው"

Him"ልክ ነው ውዴ"
Her: "አረንጓዴ ካርድስ?"
Him: "እንደዛ የሚባል ነገር የለም"
Her:  "ሊቨርፑል አለም ዋንጫ እንዲያሸንፍ እፈልጋለሁ"

after few minutes ..*

her: "ማነው ያ ቁጭ ያለው? ፓትሪክ ስትዋርትን የሚመስለው? "
Him : " ፔፕ ጋርዲዮላ የማን ሲቲ አሰልጣኝ ነው"
Her : "ለምን አይጫወትም?"

Share it for ur friends | @WubTarikoch
2.1K viewsABᴜᴊᴀ, 12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 17:14:14 ባሻዬ..!

ሁለት ነገሮች አስገርመውኛል፣
1. ወንዶች ብዙ መጠጥ ጠጥተው ከሰከሩ በኋላ፣
1.1 አላስፈላጊ ቃላትን ይናገራሉ፣
1.2 በጣም ስሜታዊ ይሆናሉ፣
1.3 መኪና በአግባቡ አያሽከረክሩም፣
1.4 ማሰብ ያቆማሉ፣
1.5 ያለ ምንም ምክንያት ከሰው ጋር ይጣላሉ።

ባሻዬ! እኔን የሚገርመኝ ታዲያ ሴቶች ሳይጠጡና ሳይሰክሩ ከላይ ያሉትን አምስቱን ማድረግ መቻላቸው ነው።

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch
949 viewsABᴜᴊᴀ, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 20:24:02 እኚህ እናት ለባንክ ቤት ሰራተኛዋ ካርዳቸውን ሰጥተው "አስር ዶላር ማውጣት እፈልጋለሁ" አሏት።ከመቶ ዶላር በታች የሚያወጡ ከሆነ እባክዎ ATM ይጠቀሙ አለቻቸው።ሴትየዋም "ለምን" ብለው ጠየቁ።የባንክ ሰራተኛዋም በስጨት ብላ ካርዱን እየመለሰች ይሄ የባንኩ ህግ ነው ይልቁን ቦታ ይልቀቁልኝ ከኋላ ያለውን ሰልፈኛ ላስተናግድበት አላቻቸው።

ሴትየዋም ለጥቂት ደቂቃ ዝም እንደማለት አሉና ካርዳቸውን ለባንኩ ሰራተኛ መለሰው "እንዲያውም የእናንተን ባንክ አልፈልገውም ገንዘቤን በሙሉ አውጣና ስጠኝ" አሏት።የባንኩ ሰራተኛም ሴትየዋ ባንክ ውስጥ ያላቸውን የገንዘብ ሙጠን ስታይ ደነገጠች።ጭንቅላቷን ነቅነቅ አድርጋ ከእክብሮት ጋር በአካውንትዎ $300,000 ዶላር ነው ያለው።ባንካችን ደግሞ በዚህ ሰአት ይሄን ያክል ገንዘብ የለውም ነገ ተመልሰው የሚመጡ ከሆነ ቀጠሮ ልያዝልዎት? አለቻቸው።

ሴትየዋም "እሺ አሁን ማውጣት የምችለው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን ስንት ነው" ብለው ጠየቁ።የባንኩም ሰራተኛ እስከ $3,000 ዶላር ብላ መለሰች።"እሺ እንደዛ ከሆነ $3,000 ዶላር ስጪኝ"አሉ።የባንኩ ሰራተኛም ፈገግ ብላ ገንዘቡን ሰጠቻቸው።

ሴትየዋም $10 ዶላር አውጥተው ከቦርሳቸው ከተቱና የተቀረውን $2990 ገንዘብ መልሰው ለሰራተኛዋ ሰጥተው የባንኩን ሰራተኛ ይሄንን መልሰሽ ከአካውንቴ ክተችልኝ አሉዋት።

The moral of this story is....

ዘላለም | @WubTarikoch
2.2K views _U_K_I, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 17:46:56 ፈገግ..!

ምክረ ረቡዕ (ረቡዕ እንደሚል ሰው ግን አሽቃባች አለን?)it's እሮብ

*ልክ ጠዋታ ላይ ቤተሰቦችሽ ቀስቅሰው እምቢ ስትይ ቁርስ በልተሽ ተመልሰሽ ተኚ ካሉሽ ከማደጎ ቤት ነው ያመጡሽ እህቴም

*አንተም ብትሆን ምግብ እየበላችሁ አንቆህ እህትህ ውሃ ከሰጠችህ የነርሱ ቤት ልጅ አደለህም ማለት ነው

* እግርሽን or ሆድሽን አሞሽ ለእናትሽ ስትነግሪያት ይሄ ስልክ ነዋ ከማለት ይልቅ እኔን ብላ የምትንከባከብሽ ከሆነ ከማደጎ ነው ያመጡሽ ማለት ነው

*ከአባትህ ጋር ቁጭ ብለህ ኢሳት እያየህ ስትቀይርበት ፀጉርህን አንጨባረህም ዝም ካለህ ያለምንም ስድብ ብር የሚሰጥህ ከሆነ ወንድሜ ወጥተህ ቤተሰቦችህን ፈልግ

* ከቤት ልትወጪ ብለሽ ዘንጠሽ ወንድምሽ Wow አምሮብሻል ካለሽ ምንም ጥያቄ የለውም ከትቦ ውስጥ ነው ያገኙሽ

Rihana | @WubTarikoch
2.5K viewsABᴜᴊᴀ, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 17:29:30 የኛ ጉዳይ..!

አሁን ላይ ታዳጊ ሴቶች ከቤተሰብ ትዕዛዝ ዉጭ መሆን፤ማፈንገጥ ይስተዋላል። ይህ የሆነበት ምክንያት እንደኔ የቤተሰብ ችግር ነዉ እላለሁ። መፍትሔዉም ያለዉ እዛዉ ነዉ ባይ ነኝ።

1ኛ፦ ልጆችን በዕምነት ስነ ምግባር ዉስጥ አንፀን ማሳደግ አለብን፤የጥበብ ሁሉ መጀመርያ ፈጣሪን መፍራት ነዉ

2ኛ፦ የጓደኛ ግፊት ነዉ ይህን ደግሞ ለመቀነስ እንዲህ ብናደርግስ አባት፣እናት እንዲሁም ታላላቅ እህት፣ወንድሞች በትርፍ ጊዜያቸዉ ወስደዉ የማዝናናት ነገሮች ቢለመዱስ፤አንዳንዴም ስጦታዎችን መስጠት።
      ይህን ካደረግን ነገሮች አዲስ አይሆንባቸዉም ከሌሎች ሰዎች ጋር ሄዶ የማየት ጉጉቱ ይቀንሳል፤በዚህ መልኩ ተታላይነትን መቀነስ ይቻላል ብዬ አስባለው።

3ኛ:- ግልፅነት ነዉ;ድርጊቶቻቸዉን በነፃነት እንዲነግሩን ገጠመኞቻቸዉንም እንዲያካፍሉን ፤ሲያጠፉም አስፈሪ ርምጃዎችን በመዉሰድ ፈንታ መምከር  መገሰፅ ግልፅ ሆነዉ እንዲያድጉ ይረዳል።

4ኛ:- የእናት ምክርና እንክብካቤ ለታዳጊ ሴቶች ወሳኙ ነገር ነዉ። እናት ልጆቿን ወደ ራሷ በመያዝና በማቅረብ ትክክለኛዉን ፍቅር ማሳየት ስለ ፍቅር ማስተማር ነዉ።

5ኛ:- ነፃነት መስጠት፣ከወንድ ልጅ አሳንሶ አለማየት፣ተፅዕኖን ከነሱ ላይ መቀነስ ነገሮችን ማድረግ እንደሚችሉ እኛም እንደምናምናቸዉ ማሳየት በራሳቸዉ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ።
                                      
ሙራድ ሙሐመድ | @WubTarikoch
2.5K viewsABᴜᴊᴀ, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 13:54:11 አደብ..!

እርጅና ከያዛቸው ሰዎች ጋ ስትገናኝ፦

አውቀውኛል…
እኔ ማን ነኝ?…
  የማን ልጅ ነኝ?…

እያልክ አታስጨንቃቸው። ማስታወስ ባለመቻላቸው ልባቸው እንዲሰበርና እንዲያዝኑ አታድርጋቸው። ሰላምታህን አቅርበህ፣ ስምህን ንገራቸውና በለሰለሰ አንደበት አናግራቸው።

| @WubTarikoch
3.6K viewsAʙᴜDɪ, 10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 12:08:10
በናንተው ውድ አባላቶቼ ትዕዛዝ መሰረት

ደብተር 900 በመግባቱ የተሰሩ ምርጥ MEMEኦችን ጋበዝኳችሁ!! ለጓደኞቻችሁ Forward በማድረግ በጋራ ይሳቁ !!

@WubTarikoch
4.3K viewsAʙᴜDɪ, 09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 20:32:10 ፈገግ የሚያስብል ነገር ልpost ብዬ.. አንዳንድ ሜምበሮች ስለሚቆጡ እየተውኩ ነው። ምን ይሻላል ወገን.. Maal Wayya??

Comment
4.4K viewsAʙᴜDɪ, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 07:25:58 ፍቅር እባላለዉ ከእለታት አንድ ቀን በትዳሬ ተስፋ ቆርጨ ባሌን ለመግደል አስባለዉ ማታውን ሳሰላስል አድርና ጧት ላይ እንዴት ማንም ሰው በማይጠራጠርና እኔንም ወንጀለኛ በማያስደርገን መልኩ መግደል እንደምችል ለመመካከር እናቴ ጋር እሄዳለሁ።

እናቴም ማንም በማይጠረጥረው መንገድ እንድትገይው እረዳሻለሁ። ግን አንቺም ማድረግ ያለብሽ ነገሮች አሉ።

☞1ኛ መጀመሪያ ከባልሽ ጋር መታረቅ አለብሽ። ምክንያቱም ከሞተ በኋላ በፊት ፀብ ካልነበረሽ ማንም አይጠረጥርሽም

☞2ኛ ራሰሽን መጠበቅና ለባልሽ ቆንጆ ሆነሽ መታየት አለብሽ፡፡

☞3ኛ ጥሩ እንክብካቤና አድናቆት ስጪው። ያሰብሽውን እንዳይጠረጥር ያደርገዋል።

☞4ኛ ትዕግስተኛ ሁኚ ፍቅር ሰጪው ቅናት ቀንሺ የሚናገረውን
ጆሮ ሰጥተሽ አዳምጪው።

እነዚህን ነገሮች ማድረግ ትችያለሽ ? ብላ ጠየቀችኝ። እኔም ምንም ችግር የለውም። እማ ብቻ እርሱን የምገድልበትን መንገድ ንገሪኝ። አልኳት፡፡ እንደዚያ ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እነግርሻለሁ። በደንብ አድምጪኝ። አለችኝ። እኔም በአትኩሮት መስማት ጀመርኩ።

   ይህንን መርዝ በምግቡ ውስጥ በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ጨምሪ ቀስ በቀስ እያዳከመው ይገድለዋል። አለችኝ። ከዛ መርዙን ይዠ
በደስታ ወደ ቤቴ ሄድኩ። በተነገረኝ መሰረትም ለባሌ መስጠት ጀመርኩ።

ከወር በኋላ እንደገና እያለቀስኩ ወደ እናቴ ሄድኩ።
እማ አሁን ባለቤቴን መግደል አልፈልግም።በጣም ተለውጧል።
እንደያውም ለርሱ ያለኝ ፍቅር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው። እባክሽ እማ መርዙ እንዳይገድለው ምን ላድርግ? ያለ እርሱ መኖር አልችልም አልኳት ስቅስቅ ብየ እያለቀስኩ።

እናቴም  አይዞሽ ልጄ አታልቅሺ የሰጠሁሽ መርዝ
አልነበረም።የደቀቀ ስኳር ነበር። በርግጥ መርዝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ። ያ ነበር ባለቤትሽን ቀስ በቀስ እየገደለው የነበረው አየሽ አይደል ፍቅርና እንክብካቤ ስትሰጪው እንዴት አይነት መልካም
ሰው እንደሆነ። ስለዚህ ከዚህ ተምረሽ ለባልሽ መልካም ሚስት ሁኚለት። ብላ ነገረችኝ።

@WubTarikoch
4.8K views _U_K_I, edited  04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ