Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት ወጣቶች በተጋበቡት ዕለት ምሽት ወደ ማረፊያቸው ገብተው ለመተኛት እየተዘጋጁ ነበር። ሙሽሪት | ውብ ታሪኮች ®

ሁለት ወጣቶች በተጋበቡት ዕለት ምሽት ወደ ማረፊያቸው ገብተው ለመተኛት እየተዘጋጁ ነበር። ሙሽሪት መታጠቢያ ክፍል ውስጥ እንዳለች

"እባክህ መብራቱን አጥፋው" አለች

"በቅድሚያ ከዚያ መውጣት አለብሽ። አሁን መብራቱን ባጠፋው በጨለማው ውስጥ ስትመጪ ልትወድቂ ትችያለሽ'' አለ።

"የምልህን ስማ! መብራቱን አጥፋው!"

"ችግሩ መብራቱን ማጥፋቱ አይደለም። እኔም ራሴ መብራቱ እስኪጠፋ ቸኩያለው ሃሳቤ ግን ላንቺ ነው"

"ለምን ቸኮልክ?!" ሙሽሪት ቱግ አለች።

"ዕውነቱን ለመናገር ከዚህ የተሻለ ወቅት አላገኝም። ግራ እግሬ አርቴፊሻል ነው።" አለ ሙሽራው።

"መብራቱን እንድታጠፋው የፈለኩት አርቴፊሻል ጡቶቼ እንዳይታዩብኝ ስለፈለኩ ነው። ደረቴ ባዶ ልሙጥ ነው"

"ወይ ፈጣሪዬ!... ምንጊዜም ከወርቅ የተሰራች አውሮፕላን ደረትሽ ላይ የምታደርጊው ለዚህ ነው ለካ?? ደህና ሜዳ ላይ አሳርፈቻታል። ሌላም ችግር ካለብሽ አሁኑኑ ብሰማው ይሻላል። ከዚህ በኋላ መደንገጥ አልፈልግም"

"እሺ እነግርሀለው....የግራ አይኔ አርቴፊሻል ነው"

"በቃ የኔም ጥርሶች በሙሉ አርቴፊሻል ናቸው" አለ ሙሽራው።

"እባክህ እኔም ፍንክች አልልም። የኔም ፀጉር አርቴፊሻል ነው። በራስ ቅሌ ላይ አንዲት ፀጉር የለችም። ያለው ዊግ ብቻ ነው"


@WubTarikoch