Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሰው በጣም የሚያፈቅራትን ፍቅረኛውን ይቀጥራታል ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ አንድ የተጠቀለለ ስጦ | ውብ ታሪኮች ®

አንድ ሰው በጣም የሚያፈቅራትን ፍቅረኛውን ይቀጥራታል ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ አንድ የተጠቀለለ ስጦታ ይሰጣታል ፍቅረኛውም ከፍታ ስታየው አሻንጉሊት ነው ወዲያውኑ አመናጭቃ ስጦታውን ትወረውረዋለች፡፡

እሱም በመናደድ ግን ረጋ ብሎ “ምነው ውዴ ለምን ወረወርሺው?”
ይላታል “ይህን የልጅ ስጦታህን አልወደድኩልህም!” ትለዋለች፡፡
ይናደድና አሻንጉሊቱን ከወደቀበት አንስቶ ጥሏት ይወጣል፡፡ በሚያስጠላና በሚገርም አጋጣሚ ጥሏት በወጣ ቅጽፈት አስፓልት ሲሻገር መኪና ገጭቶት ህይወቱ አለፈች የቀብሩም ቀን ልጅት አሻንጉሊቱን ይዛ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች፡፡

በለቅሶዋ ማሃልም ውድ ፍቅረኛዋን በአሻንጉሊቱ ምክንያት በማጣትዋ
በቁጭት አሻንጉሊቱን ጭምቅ ታደርገዋለች ወዲያውም ከሻንጉሊቱ “Will you marry me?” #ታገቢኛለሽ? የሚል ድምጽ አወጣ፡፡
ልጅቷ አልቻለችም መሬት ላይ ተዘረረች፡፡

ስትወድቅም ከአሻንጉሊቱ ኪስ ሁለት ቀለበቶች እና አንድ አጭር
ጽሑፍ ወደቀ ጽሑፉ እንዲህ ይላል. . . የኔ ፍቅር ለዘላለም ላልከዳሽ ልታመንልሽ በፍቅር ስም ቃል እገባልሻለሁ!!

@WubTarikoch