Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር እባላለዉ ከእለታት አንድ ቀን በትዳሬ ተስፋ ቆርጨ ባሌን ለመግደል አስባለዉ ማታውን ሳሰላስል | ውብ ታሪኮች ®

ፍቅር እባላለዉ ከእለታት አንድ ቀን በትዳሬ ተስፋ ቆርጨ ባሌን ለመግደል አስባለዉ ማታውን ሳሰላስል አድርና ጧት ላይ እንዴት ማንም ሰው በማይጠራጠርና እኔንም ወንጀለኛ በማያስደርገን መልኩ መግደል እንደምችል ለመመካከር እናቴ ጋር እሄዳለሁ።

እናቴም ማንም በማይጠረጥረው መንገድ እንድትገይው እረዳሻለሁ። ግን አንቺም ማድረግ ያለብሽ ነገሮች አሉ።

☞1ኛ መጀመሪያ ከባልሽ ጋር መታረቅ አለብሽ። ምክንያቱም ከሞተ በኋላ በፊት ፀብ ካልነበረሽ ማንም አይጠረጥርሽም

☞2ኛ ራሰሽን መጠበቅና ለባልሽ ቆንጆ ሆነሽ መታየት አለብሽ፡፡

☞3ኛ ጥሩ እንክብካቤና አድናቆት ስጪው። ያሰብሽውን እንዳይጠረጥር ያደርገዋል።

☞4ኛ ትዕግስተኛ ሁኚ ፍቅር ሰጪው ቅናት ቀንሺ የሚናገረውን
ጆሮ ሰጥተሽ አዳምጪው።

እነዚህን ነገሮች ማድረግ ትችያለሽ ? ብላ ጠየቀችኝ። እኔም ምንም ችግር የለውም። እማ ብቻ እርሱን የምገድልበትን መንገድ ንገሪኝ። አልኳት፡፡ እንደዚያ ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እነግርሻለሁ። በደንብ አድምጪኝ። አለችኝ። እኔም በአትኩሮት መስማት ጀመርኩ።

   ይህንን መርዝ በምግቡ ውስጥ በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ጨምሪ ቀስ በቀስ እያዳከመው ይገድለዋል። አለችኝ። ከዛ መርዙን ይዠ
በደስታ ወደ ቤቴ ሄድኩ። በተነገረኝ መሰረትም ለባሌ መስጠት ጀመርኩ።

ከወር በኋላ እንደገና እያለቀስኩ ወደ እናቴ ሄድኩ።
እማ አሁን ባለቤቴን መግደል አልፈልግም።በጣም ተለውጧል።
እንደያውም ለርሱ ያለኝ ፍቅር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው። እባክሽ እማ መርዙ እንዳይገድለው ምን ላድርግ? ያለ እርሱ መኖር አልችልም አልኳት ስቅስቅ ብየ እያለቀስኩ።

እናቴም  አይዞሽ ልጄ አታልቅሺ የሰጠሁሽ መርዝ
አልነበረም።የደቀቀ ስኳር ነበር። በርግጥ መርዝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ። ያ ነበር ባለቤትሽን ቀስ በቀስ እየገደለው የነበረው አየሽ አይደል ፍቅርና እንክብካቤ ስትሰጪው እንዴት አይነት መልካም
ሰው እንደሆነ። ስለዚህ ከዚህ ተምረሽ ለባልሽ መልካም ሚስት ሁኚለት። ብላ ነገረችኝ።

@WubTarikoch