Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ጉዳይ..! አሁን ላይ ታዳጊ ሴቶች ከቤተሰብ ትዕዛዝ ዉጭ መሆን፤ማፈንገጥ ይስተዋላል። ይህ የ | ውብ ታሪኮች ®

የኛ ጉዳይ..!

አሁን ላይ ታዳጊ ሴቶች ከቤተሰብ ትዕዛዝ ዉጭ መሆን፤ማፈንገጥ ይስተዋላል። ይህ የሆነበት ምክንያት እንደኔ የቤተሰብ ችግር ነዉ እላለሁ። መፍትሔዉም ያለዉ እዛዉ ነዉ ባይ ነኝ።

1ኛ፦ ልጆችን በዕምነት ስነ ምግባር ዉስጥ አንፀን ማሳደግ አለብን፤የጥበብ ሁሉ መጀመርያ ፈጣሪን መፍራት ነዉ

2ኛ፦ የጓደኛ ግፊት ነዉ ይህን ደግሞ ለመቀነስ እንዲህ ብናደርግስ አባት፣እናት እንዲሁም ታላላቅ እህት፣ወንድሞች በትርፍ ጊዜያቸዉ ወስደዉ የማዝናናት ነገሮች ቢለመዱስ፤አንዳንዴም ስጦታዎችን መስጠት።
      ይህን ካደረግን ነገሮች አዲስ አይሆንባቸዉም ከሌሎች ሰዎች ጋር ሄዶ የማየት ጉጉቱ ይቀንሳል፤በዚህ መልኩ ተታላይነትን መቀነስ ይቻላል ብዬ አስባለው።

3ኛ:- ግልፅነት ነዉ;ድርጊቶቻቸዉን በነፃነት እንዲነግሩን ገጠመኞቻቸዉንም እንዲያካፍሉን ፤ሲያጠፉም አስፈሪ ርምጃዎችን በመዉሰድ ፈንታ መምከር  መገሰፅ ግልፅ ሆነዉ እንዲያድጉ ይረዳል።

4ኛ:- የእናት ምክርና እንክብካቤ ለታዳጊ ሴቶች ወሳኙ ነገር ነዉ። እናት ልጆቿን ወደ ራሷ በመያዝና በማቅረብ ትክክለኛዉን ፍቅር ማሳየት ስለ ፍቅር ማስተማር ነዉ።

5ኛ:- ነፃነት መስጠት፣ከወንድ ልጅ አሳንሶ አለማየት፣ተፅዕኖን ከነሱ ላይ መቀነስ ነገሮችን ማድረግ እንደሚችሉ እኛም እንደምናምናቸዉ ማሳየት በራሳቸዉ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ።
                                      
ሙራድ ሙሐመድ | @WubTarikoch